24 Aug 2026, 17:42 UTC140 views9 reactionsread 24 August 2026 አላህ ሆይ!
የሰዎችን ስብራት በመጠገን ፣ የብዙዎችን ተስፋ በማደስ እና የፈዘዙ ፊቶች ላይ የደስታ ብርሃን በመርጨት ለሚተጉት ወገኖቻችን የቸርነትህን እና የጥበቃህን ሰፊ መጋረጃ ዘርጋላቸው። የሠሩት መልካም ሥራ በአንተ ዘንድ ተቀባይነት ያለው፣ የልባቸውን ንጽህና የሚያጎላ እና ያበረከቱትን በጎ አስተዋጽኦ በመልካም ምንዳ ካሳቸው።
አላህ ሆይ !
በዚህ ውክቢያና ዝብርቅርቅ በበዛበት ዓለም ውስጥ፣ በውስጣቸው ለተሸከሙት ጭንቀትና ፈተና ፈጣን እፎይታን ለግሳቸው። የተዘጋጉ የሕይወት በሮችን ሁሉ በችሮታህ ቁልፍ ክፈትላቸው። በሥራቸው፣ በኑሯቸው፣ በትዳራቸውና በእያንዳንዱ እርምጃቸው ላይ የማይነጥፍ በረካ አፍስስባቸው። ከክፉ ቀን፣ ከሰው ዓይንና ከድንገተኛ …
❤9
24 Aug 2026, 17:41 UTC146 views3 reactionsread 24 August 2026 Photo
እስካሁን በተደረገው ድጋፍ ወደ እህታችን ዘሀራ አብዱ ሰዒድ አካውንት አጠቃላይ 𝟒,𝟒𝟖𝟔,𝟎𝟎𝟎 (አራት ሚሊዬን አራት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺህ) ብር ገቢ ሆኗል።
ዛሬ ደግሞ በምርቃት ብቅ ብያለሁ። የመጀመሪያው አስተያየት መስጫ ሳጥኑ ላይ የተቀመጠውን ዱዓ ከልቡ አጣጥሞ «አሚን» ያለ፣ አቅሙ ከፈቀደ 𝟐𝟎𝟎 ብር በእህት ዘሀራ አካውንት ላይ ጣል እንዲያደርግ በአክብሮት እጠይቃለሁ።
𝐙𝐄𝐇𝐀𝐑𝐀 𝐀𝐁𝐃𝐔 𝐒𝐄𝐈𝐃
𝐂𝐁𝐄:- 𝟏𝟎𝟎𝟎𝟕𝟖𝟑𝟕𝟖𝟒𝟐𝟔𝟔)
𝐌𝐨𝐛𝐢𝐥𝐞:- +𝟐𝟓𝟏𝟗𝟖𝟖𝟑𝟏𝟔𝟎𝟓𝟕
https://t.me/abuafnanmoh
❤3
23 Aug 2026, 18:21 UTC510 views20 reactionsread 24 August 2026 Photo
ለእህታችን ለዘሀራ ዓብዱ ሰዒድ የጀመርነው የ𝟐𝟎𝟎 ብር ቻሌንጅ በውጤታማነት ቀጥሏል። እስካሁን በተደረገ የጋራ ርብርብና ህዝባዊ ትብብርም በእህታችን በዘሀራ አብዱ ሰዒድ የባንክ አካውንት ውስጥ የተሰበሰበው አጠቃላይ ገንዘብ 𝟒,𝟑𝟖𝟎,𝟏𝟏𝟕 (አራት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሰማኒያ ሺህ አንድ መቶ አስራ ሰባት) ብር ደርሷል።
እስኪ ዛሬ ደግሞ፦
🛑 እንደ ናርዶስ ሽታ የሚያውዱት ልጆቿ በእቅፏ ውስጥ እንዲገቡ የኛ የ 𝟐𝟎𝟎 ብር ድጋፍ ትልቅ ለውጥ መፍጠር ይችላልና ቻሌንጁን ተቀላቀሉ።
𝐙𝐄𝐇𝐀𝐑𝐀 𝐀𝐁𝐃𝐔 𝐒𝐄𝐈𝐃
𝐂𝐁𝐄:- 𝟏𝟎𝟎𝟎𝟕𝟖𝟑𝟕𝟖𝟒𝟐𝟔𝟔
𝐌𝐨𝐛𝐢𝐥𝐞:- +𝟐𝟓𝟏𝟗𝟖𝟖𝟑𝟏𝟔𝟎𝟓𝟕
https://t.me/abuafnanmoh
👍19❤1
23 Aug 2026, 10:32 UTC633 views23 reactionsread 24 August 2026 Video
ጥንቃቄ :- ቪዲዮው ስሜታዊ የሆኑ ትዕይንቶችን ይዟል 🛑
በህንድ ማሃራሽትራ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ኻፍዲያ ዱንጋር በተሰኘ ተራራ ጫፍ ላይ የተከሰተ አሳዛኝ እና አስደንጋጭ ዜና ነው።
ታሪኩ የተጀመረው ዕድሜው 18 ዓመት በሆነ ወጣት ዙሪያ ነው። ወጣቱ ውድ ስልክ እንዲገዙለት ወላጆቹን በመጠየቁና ለመግዛት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት ከቤተሰቦቹ ጋር አለመግባባት ይፈጠራል። በዚህ የተነሳ ራሱን ለማጥፋት በማሰብ ከተራራው ጫፍ ላይ ቆመ።
ወላጅ አባቱ «አይፎን 15 Pro እገዛልሃለሁ» እያለ ተማጸነው። በአቅራቢያው የነበሩትም ሰዎች ከገደሉ አፋፍ እንዲመለስ ለመኑት። የመረጠው ውሳኔ የሁሉ ነገር መፍትሄ እንደማይሆን፣ ራስን ማጥፋት የትኛውንም ችግር ሊፈታ እን…
😭16❤7
22 Aug 2026, 17:52 UTC704 views25 reactionsread 24 August 2026 Photo
ለእህታችን ለዘሀራ ዓብዱ ሰዒድ የጀመርነው የ𝟐𝟎𝟎 ብር ቻሌንጅ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል። የእናንተ የማይበገር ሰብአዊነትና የደግነት እጅ ተደምሮ በእህታችን በዘሀራ አካውንት ውስጥ የተሰበሰበው አጠቃላይ ገንዘብ አሁን ላይ 𝟒,𝟐𝟑𝟓,𝟏𝟎𝟑 (አራት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ አንድ መቶ ሶስት) ብር መድረሱን በታላቅ ደስታ እናበስራለን።
አሁን ብዙ መንገድ ተሻግረናል። ይህቺ ወጣት እናት ልጆቿን በናፍቆት የምታቅፍበትንና እንባዋ የሚታበስበትን ጊዜ እውን ለማድረግ የቀረን ቀሪ ርቀት እጅግ ጥቂት ነው። ከግባችን ደርሰን ለልጆቿ እንድትበቃ ጥረት ማድረጋችንን እንቀጥል።
እስኪ ዛሬ ደግሞ፦
🛑 የሰው አፍ ሊያወጣው፣ የሰው ልብ ሊሸከመው የማይችል ከባድ …
❤17👍6💔2
22 Aug 2026, 12:00 UTC687 views6 reactionsread 24 August 2026 Video
ይህ እጅግ በጣም አስደናቂ ተአምር ነው 🤔🤔🤔
https://t.me/abuafnanmoh
👍4🤔2
21 Aug 2026, 17:32 UTC910 views37 reactionsread 24 August 2026 Photo
ለእህታችን ለዘሀራ ዓብዱ ሰዒድ የጀመርነው የ𝟐𝟎𝟎 ብር ቻሌንጅ አበረታችና ተስፋ ሰጪ በሆነ መልኩ እየተጓዘ ይገኛል። እስካሁን ባለው ሂደትም፣ በእናንተ ሰብአዊነት እና ትብብር በእህታችን በዘሀራ አካውንት ውስጥ አጠቃላይ 𝟑,𝟎𝟕𝟎,𝟎𝟎𝟎 (ሶስት ሚሊዮን ሰባ ሺህ) ብር ገቢ መሆን ችሏል።
ከፈጣሪ ቀጥሎ ህልውናዋንና ተስፋዋን በእናንተ ላይ ያንጠለጠለችው ይህቺ የ𝟐𝟐 ዓመት ወጣት እናት፣ ከምትወዳቸው እና እንደ ዓይን ብሌኗ ከምትሳሳላቸው ንጹሃን ልጆቿ ጋር በጤና እና በሰላም የምትቀላቀልበትን ቀን በጉጉት ትጠብቃለች። ለዚህም መልካም ዓላማ እስካሁን ያደረጋችሁት ሁለንተናዊ ድጋፍ የላቀ ነው። አሁንም ቢሆን የቻላችሁትን ያህል በመርዳት የዚህ በጎ ተግባር አካል እንድ…
❤26👍8💔2😱1
19 Aug 2026, 18:20 UTC≈1,030 views27 reactionsread 24 August 2026 Video
ዛሬ ለእህታችን ዘሃራ ዓብዱ ሰዒድ የ200 ብር ቻሌንጅ እንጀምራለን። አቅማችን የፈቀደውን ያህል በማዋጣት እና ይህን ቪዲዮ ሼር (Share) እና ሪፖስት (Repost) በማድረግ ለብዙዎች ተደራሽ እንዲሆን የበኩላችሁን አስተዋጽዖ እንድታበረክቱ በአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን።
እህታችን ዘሀራ አብዱን ለመደገፍ ከዚህ በታች በቀረበውና በስሟ በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር
ገቢ ማድረግ ትችላላችሁ
ZEHARA ABDU SEID
CBE 1000783784266
Mobile +251988316057
https://t.me/abuafnanmoh
❤14😭8💔4👍1
12 Aug 2026, 20:07 UTC≈1,760 views42 reactionsread 24 August 2026 Photo
ሁሌም የምታሳዩት በቃላት ለመግለጽ የሚከብድ ደግነትና ፍቅር ነው። ይኸው በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ በእህታችን ዘሀራ አብዱ አካውንት ውስጥ 1,320,000 (አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሃያ ሺህ) ብር ገቢ ሆኗል።
ይህ ህዝብ የኑሮ ውድነት እያጎሳቆለው እንኳን «ከእኔ ይልቅ ለወገኔ» ብሎ የእዝነት እጆቹን መዝርጋቱን ብዙ ጊዜ አስመስክሯል።
እባካችሁ ... «እኔ የምሰጣት ትንሽ ናት» አትበሉ። የእያንዳንዳችን 100 እና 200 ብር ተደምራ ነው ይህን ተአምር የሰራችው። የውኃ ጠብታዎች ቋጥኝን የሚበሱት በኃይል ሳይሆን በማያቋርጥ ጽናትና ተደጋጋሚነት ነው። የማያቋርጥ ጥረትና እልህ ደግሞ ከትልቅ ጉልበት ይልቅ ትልቅ ውጤት ማምጣቱ አይቀሬ ነው።
የቀረውንም በጋራ …
❤32👍10
10 Aug 2026, 18:32 UTC≈1,780 views42 reactionsread 24 August 2026 Video
እስኪ እነዚህን ለዓይን የሚያሳሱ ህጻናት ተመልከቷቸው፤ የራሳችሁን ልጆች አስቧቸው። ስቃያቸውን በእነሱ ጫማ ሆናችሁ ተረዱት። እናታቸው እንዲህ አልጋ ላይ ወድቃ የምትሞትበትን ቀን እንዲጠብቁ ብቻቸውን አንተዋቸው። የልጆቹን እንባ አብሰን እናታቸውን ለማትረፍ በጋራ እንረባረብ።
ZEHARA ABDU SEID
CBE 1000783784266
Mobile +251988316057
💔32😭5❤3🤔2
7 Aug 2026, 18:49 UTC≈1,670 views9 reactionsread 24 August 2026 ይህን ቤተሰብ አስታወሳችሁት ?
👇👇👇
https://www.facebook.com/share/p/1898HGbowW/
❤9
3 Aug 2026, 19:21 UTC≈2,110 views10 reactionsread 24 August 2026 ለሐያት ነስሩ የተደረገው ድጋፍ ውጤቱ ይህን ይመስላል።
👇👇👇
https://www.facebook.com/share/p/1BoXU8aY6V/
❤10
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @abuafnanmoh. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.