18 Jul 2026, 10:42 UTC36 views4 reactionsread 9 August 2026 "ለምንድነው ድንገት የተውከኝ አለቺኝ ?"
"እኔ'ንጃ ምን አልባት ፈርቼሽ ይሆናል"።
በአይኗ እየተቅለሰለሰች "ምኔ አስፈራህ ትባ'ላለች አሉህ ወይ "
ጥቁረቷ የዐይኗን ውበት ጨምሮታል ጥቁረቷ ጥርሷን ጥርሰ በረዶ ናት እንድትባል ያደረጋት ይመስለኛል።
ስታምር !
ትክ ብዬ እያየኋት
"የመወደድ ርኃብ ያለብሽ ይመስላል "አልኳት
ምን ማለት ነው ??
"የሚወደኝ አጥቼ ማለት ነው? " ሳቀች አሳሳቋ ፌዝ አዝሏል
አይምሰልሽ
የአንዳንድ ርሃብ ምንጭ እኮ የአቅርቦት እጥረት አይደለም የአስተዳደግ ጠባሳም ሊሆን ይችላል።
ቀጠሮ ኖርበት የክት ልብሱን አጥቦ ፀሃይን እንደሚጠብቅ ሰው ነው ቀልብሽ ቆሌሽ ሁሉ ነገርሽ መወደድሽን የሚጠብቀው ....
እመኚኝ ቲጂ
ማስከተል …
🔥3🙏1
19 Jun 2026, 15:53 UTC71 views2 reactionsread 9 August 2026 Photo
ስለ ሚካኤል” ብሎ የተማጸነ፣ የነፍሱን ቁልፍ ለሊቀ መላእክቱ አሳልፎ የሰጠ ሰው... በምድር ላይ ቢወድቅ እንኳ በሰማይ መቆሚያ አለው። እርሱ የወደቁትን የሚያነሳ፣ የዛሉትን የሚያበረታ፣ በምልጃው ጽናትም ሰውን ከሞት ወደ ሕይወት የሚያሻግር ታማኝ ባለአደራ ነው።
ቅዱስ ሚካኤል የምስኪናን ጋሻ፣ የፈራች ነፍስ ብቸኛ ዋስትና፣ በምልጃውና በጥበቃው ሰውን ከምድራዊ መከራ ወደ ሰማያዊ ሰላም የሚያሻግር የምሕረት መልአክ ነው። በእርሱ ጽኑ ቃል ኪዳን ነፍሳችን ሁልጊዜ በረከት ታግኝ ።አሜን !🙏
እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
❤1🙏1
14 Jun 2026, 12:57 UTC80 viewsread 9 August 2026 በአገራችን ፖለቲካ ውስጥ አንድን ችግር ለዘላለም ለማደብዘዝ ከተፈለገ ምርጡ ዘዴ ምንድነው? “አጥኚ ኮሚቴ” ማቋቋም!
ማንኛውም ችግር ሲፈጠር ወዲያው “ከፍተኛ ግብረ-ኃይል ተዋቅሮ ወደ ስራ ገብቷል” ይባላል። ኮሚቴው ያጠናል፣ ያጠናል... በመጨረሻም “ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ሌላ ንዑስ ኮሚቴ ማቋቋም ያስፈልጋል” 😢የሚል መግለጫ ያወጣል። በኮሚቴ መአት አገሪቱ ስትናወጥ፣ ችግሩ ራሱ ሰልችቶት በራሱ ጊዜ ይጠፋል።😔
1 Jun 2026, 08:58 UTC110 viewsread 9 August 2026 "…እነሆ፥ እንዳልነበረ ናችሁ፥ ሥራችሁም ከንቱ ነው፤ የሚመርጣችሁም አስጻያፊ ነው።" ኢሳ 41፥24
31 May 2026, 10:05 UTC118 views4 reactionsread 9 August 2026 ከብልጽግና ኮሪደር ፕሮጀክት በተዓምር በተረፈች አንድት ካፌ ዮናስ ተቀምጦ ቡና እየጠጣ ነው… እቺው ካፌ የፈረንሳይ ለጋሲዮን ቁልቁለት ላይ የሚነፍሰውን የግንቦት ወር ውርጭ ተቋቁማ፣ የሰፈሩን የቀድሞ ትዝታ በነጠላ ጠቅልላ የያዘች ብቸኛ መጠለያ ሆናለች።(በትክክል ያለችበት ቦታ መናገር "ትፍረስ" ብሎ እንደመጠቆም ስለሆነ ትቼዋለሁ😌) ከመስኮቱ ባሻገር ግን የኮሪደሩ ቅባት ቀለም እና ድም ላይት አልቆ፣ አሁን ሌላ ትልቅ ድግስ ተተክቷል። በአዲሶቹ የኮንክሪት የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች ላይ የሰባተኛው ሃገራዊ ምርጫ ፖስተሮች በደመቁ ቀለማት ይንቦገቦጋሉ። ሜዳው ብቸኛ ተወዳዳሪ ለገጠመው አውራ ፓርቲ የተመቻቸ መሆኑንና ድምፅ ሳይሰበሰብ የድል መግለጫው መዘጋጀቱን የሰፈ…
😁3🤩1
24 May 2026, 09:49 UTC100 views1 reactionsread 9 August 2026 የሰማዩን ፀሐይና ጨረቃን አጥፍቶ፣ እንደ አዲስ እንደ ማብራት ያለ ውድ ሀብትና እውቀት የያዙ መስለው፣ ምስኪኑን ለሚያሸማቅቁ፤
በሆነ ሞያ “ኤክስፐርት ነን፣ እኛን ያህል የለም” ብለው ለሚንጠባረሩ፣ ግን አንድ ቀን እነሱም አንዳች የማይረዱ “ጀማሪ” እንደነበሩ ለዘነጉ፤
ዛሬ ከተማ ገብተው፣ ጫማ አድርገው... የትናንት ማንነታቸውን ባቆዩላቸው ገበሬ ባዶ እግር ቤተሰቦቻቸው ላይ ለሚንበላጠጡና ለሚንቁ፤
ጊዜ ዙፋን ላይ አስቀምጦ ነጭ ልብስ ስላላበሳቸው ብቻ፣ ጊዜ አዳፋ ልብስ ባረገፈባቸውና በቆሰሉት ላይ ለሚመፃደቁ፤
እጃቸው በሰለሉት እና አቅም ባጡት ፊት፣ ብርቱ መስለው ጡንቻቸውን ለሚወጥሩ፤
እግር በሌላቸው፣ መራመድ ባቃታቸው ሰዎች ፊት... ሆን ብለው ሩ…
❤1
17 May 2026, 16:59 UTC104 views6 reactionsread 9 August 2026 መጋቢት አጋማሽ ላይ የሚዘንበው ካፊያ የፒያሳውን አስፋልት በብርድ እየገረፈው ነው። እድሜ ጠገቡ ካፌ ውስጥ የቡና ማሽኑ ጩኸትና የደንበኞች ሹክሹክታ ቢሰማም፣ ከመስኮቱ ጥግ ያለው ጠረጴዛ ላይ ግን ጸጥታ ሰፍኗል።
ወጣቱ ዮናስ ከተቀመጠ ሁለት ሰዓት አልፎታል። ፊት ለፊቱ ባዶ ወንበር አለ፤ በጠረጴዛው ላይ ደግሞ ሁለት ስኒ ቡናዎች ይገኛሉ። የአንዱ እንፋሎት አልቆ የቀዘቀዘ ሲሆን፣ የዮናስ ስኒ ግን አሁንም በግማሹ እንደተሞላ ነው።
ዮናስ በየደቂቃው ወደ ካፌው በር ይመለከታል። በሩ በተከፈተ ቁጥር ነፍሱ ቀድማ ደጅ ትወጣለች። የገቡት ሰዎች እርሷ እንዳልሆኑ ሲረዳ ደግሞ፣ ትከሻው ዝልፍልፍ ብሎ ተመልሶ ወንበሩ ላይ ይለጠፋል።
አስተናጋጁ አረጋዊ፣ ጋሽ መላኩ ይ…
🔥4⚡1😢1
27 Apr 2026, 23:16 UTC127 views4 reactionsread 9 August 2026 አንድ አያት ለልጅ ልጁ እንዲህ አለው፦
"በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ሁልጊዜ የሚዋጉ ሁለት ተኩላዎች አሉ። አንደኛው ክፉ ነው፤ ቁጣን፣ ስንፍናን፣ ሱስንና ስድብን ይወክላል። ሁለተኛው ደግሞ መልካም ነው፤ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ ትጋትንና ክብርን ይወክላል።"
ልጁም ጠየቀ፦ "ታዲያ የትኛው ተኩላ ያሸንፋል?"
አያቱም መለሰ፦ "የምትመግበው ተኩላ ያሸንፋል!"
❤3🙏1
17 Apr 2026, 07:10 UTC148 views4 reactionsread 9 August 2026 Photo
አዲስ አበባ አዶ ሸገሩ ፤
እንኳን ሸገሩ፤
የሁሉ አይደል ወይ ሞላው ሀገሩ።
በፍቅር ጠርተው ከዳር እስከዳር ፣
መሃል ገቡና አቆሙን ከዳር ።
ባቆዩት ሀገር ጀግኖች በአንድነት፣
በአርበኝነት ፣
እንዴት ይገፋ ኢትዮጵያዊነት ።
The Legend Tedi🙏🙏
❤2👍1🔥1
12 Apr 2026, 12:46 UTC641 views4 reactionsread 9 August 2026 እነሆ ትንሣኤ!
መስቀሉ ላይ ያበቃ፣ መቃብር ውስጥ የተዘጋ የመሰለውን የሰውን ልጅ የሽንፈት ታሪክ፣ አንድ የማይታይ መለኮታዊ እጅ ገልጦ አዲስ የብርሃን ምዕራፍ ጀመረበት። የዚያ ድንጋያማ መቃብር ጸጥታ የሞት ማረጋገጫ አልነበረም፤ ይልቁንም የዓለሙ ሁሉ ትልቁ ተዓምር የተቀመረበት የሕይወት ማህፀን እንጂ። አዎ፣ ዓለም "አበቃለት" ብሎ ድንጋይ ባንከባለለበት ሥፍራ፣ ሰማይ "እነሆ ጀመረ" ብሎ ማኅተሙን ፈታው!
በሕይወታችን ስንቱን የ"ስቅለት" አርብ አሳልፈናል? ስንቱ ንጹሕ ተስፋችን ተገርፎ፣ ስንቱ የነገ ሕልማችን ተሰቅሎ፣ ስንቱ ደካማ ማንነታችን በሽንፈት መቃብር ውስጥ ተዘግቶ ያውቃል? ሰዎች "ከእንግዲህ አይነሳም" ብለው ከላያችን ላይ ከባድ የትዝብት ድን…
❤2🔥2
12 Apr 2026, 11:17 UTC118 viewsread 9 August 2026 የሆነ ሰፈር በጣም ታዋቂ ስትሆን ዐለም ላይ ሁሉ ታዋቂ የሆንክ ከመሰለህ የባከንክ ትሆናለህ:: ምክንያቱም መደበኛ ሥራህና ዓላማህ ታዋቂነትህን ማስጠበቅ ይሆንብሃል:: አይወድቁ አወዳደቅ ትወድቃለህ:: አንተ ውኃ ወይም ፀሓይ ወይም ሰማይ አይደለህም:: የኛዋ ፀሓይም የማትታወቅበት ጋላክሲዎች አሉ:: በመንደርህ ታወቅህ ማለት ሁሉም ያውቅሃል ማለት ስላልሆነ ዝም ብለህ አትፈ^ንዳ:: በተለይ ትልቅ ቦታ ለመድረስ Low profile ሆነህ ተንቀሳቀስ:: በትንሽ ነገር ዝነኛ ከሆንክ ብዙ ነገር ያሳጣሃል:: ሳትደርስ መድረስ ትክክለኛ መድረሻህን ይነጥቅሃል:: ልክ ሰዎች ጎበዝ ማለት ከጀመሩ ቆም ብለህ አስብ:: መጥፊያህ ነው:: ቆንጆ ሴቶችን ከሙያም ከመውለድም የሚያርቃቸ…
25 Mar 2026, 03:50 UTC132 viewsread 9 August 2026 https://t.me/psychological_inventory_bot?start=_tgr_CHeBX-gyYzg0
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Ybie_BeyondView. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.