1 Aug 2026, 21:27 UTC≈8,380 views9 reactionsread 7 August 2026 Photo
በከፍተኛ ደህንነቱ የሚታወቀው የ Coldcard ሃርድዌር የኪስ ቦርሳ (Wallet) 88 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ቢትኮይን ሀክ በመደረግ ተዘረፈ...
በምስሉ ላይ ምትመለከቱት ቢትኮይንን በጥንቃቄ እና ከኢንተርኔት ነጥሎ (Air-gapped) ለመያዝ የሚያገለግሉ ታዋቂ የኮልድካርድ ምርቶች ናቸው።
ኮልድካርድ (Coldcard): ዲጂታል ገንዘብን (በተለይም ቢትኮይን) ከኢንተርኔት ነጥለው በአስተማማኝ ሁኔታ በቁስ አካል (Hardware) ተይዞ እንዲቆይ የሚያደርግ መሣሪያ (Wallet) ነው።
@Tech_433et @Tech_433et
❤9
31 Jul 2026, 14:57 UTC≈1,260 views8 reactionsread 7 August 2026 Photo
ጉግል በክሮም ላይ ለተገኙ 370 የደህንነት ክፍተቶች ማስተካከያ አወጣ
የጉግል ክሮም የደህንነት ቡድን በማሰሻው (Browser) ላይ ለተገኙ 370 የደህንነት ክፍተቶች የሶፍትዌር ማስተካከያ (Security Patches) አውጥቷል፤ ከእነዚህም ውስጥ 7ቱ እጅግ አሳሳቢ (Critical) የሚባሉ ናቸው።
ይህ የደህንነት ማስተካከያ እ.ኤ.አ ሐምሌ 29 የተለቀቀ ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች የክሮም ቨርዥን 151 (Version 151) ለዊንዶውስ እና ማክ (151.0.7922.71/.72) እንዲሁም ለሊኑክስ (151.0.7922.71) በአፋጣኝ ማዘመን (Update) ይኖርባቸዋል።
ከ7ቱ አሳሳቢ ክፍተቶች መካከል በCompositing, Views, Skia እና Ozone የሲስተም …
❤5👍3
29 Jul 2026, 15:23 UTC≈1,500 views9 reactionsread 7 August 2026 Photo
አፕል (Apple) በ iOS ላይ 87 እንዲሁም በ macOS Tahoe ላይ 155 የደህንነት ክፍተቶችን ማስተካከሉን ገለጸ
አፕል በቅርብ ጊዜ በኦፕሬቲንግ ሲስተሞቹ (Operating Systems) ላይ የተገኙ በርካታ የደህንነት ክፍተቶችን የሚያስተካክሉ ማሻሻያዎችን (Patches) መልቀቁን አስታውቋል።
ኩባንያው አዲሱን የ iOS 26.6 እና iPadOS 26.6 ዝመናዎችን ሲለቅ 87 የሚሆኑ የደህንነት ክፍተቶችን የዘጋ ሲሆን፤ እነዚህ ክፍተቶች የሳይበር ጥቃት አድራሾች ሚስጥራዊ የሆኑ የተጠቃሚ መረጃዎችን እንዲያገኙ፣ የአገልግሎት መንፈግ (DoS) እንዲፈጥሩ፣ ያልተፈቀዱ የኮድ ትዕዛዞችን እንዲያስፈጽሙ፣ ፋይሎችን እንዲያጠፉ፣ የደህንነት ስርዓትን ጥሰው እንዲገቡ…
👍5❤4
3 Jul 2026, 09:44 UTC≈2,250 views7 reactionsread 7 August 2026 Photo
ቻትቦት እንደ ቴራፒስት እንደሚያገለግል ያውቃሉ?
ሰዎች የአዕምሮ ጤናቸውን ለማሻሻልና ራሳቸውን ለመገምገም በሰው ሐኪሞች ብቻ ሳይሆን በሰው ሠራሽ አስተውሎት መሣሪያዎችም እየተጠቀሙ ነው።
ለ13 ዓመታት የጻፋቸውን የግል ማስታወሻዎችና መልዕክቶች ወደ ኤ.አይ ቻትቦት ያስገባ አንድ የ30 ዓመት ዕድሜ ያለው የሶፍትዌር መሐንዲስ በሕይወቱ ውስጥ በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ችግሮችን እንዲለይለት ጠይቆ ነበር። ማሽኑ የሰጠው ምላሽ ግን ቀጥተኛ ነበር። ለ13 ዓመታት ስለ ተመሳሳይ ችግሮች ሲጽፍ ቢቆይም እነሱን ለመፍታት ተግባራዊ እርምጃ አለመውሰዱን አሳውቆታል። ግለሰቡ ከዚህ በፊት የሥነ ልቦና ሕክምና ሲከታተል ቢቆይም ኤ.አይ በሰው ዓይን በቀላሉ ሊታዩ የማይችሉ የሕይወት …
👍6❤1
30 Jun 2026, 20:49 UTC≈2,510 views15 reactionsread 7 August 2026 Photo
አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት!
በእጅ ስልካችን ረቂቅ እና ያልተፈቀዱ ግብይቶችን የሚፈፅሙ እና በስፋት እየተሰራጩ የሚገኙ ጎጂ መተግበሪያዎችን ስለማሳወቅ
****
ጥቃት አድራሾች የጥቃት ዘዴያቸውን በመቀያየርና ጎጂ መተግበሪያዎችን በማበለፀግ ወይም በመጠቀም ከሞባይል ላይ የግል መረጃ ስርቆትን ጨምሮ ያልተፈቀዱ የገንዘብ ዝውውሮችን ይፈፅማሉ።
የሚከተሉት እጅግ ውስብስብ፣ ረቂቅ እና አደገኛ የሆኑ ጎጂ መተግበሪያዎችም በስፋት እየተሰራጩ እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል።
1. ትረስት መተግበሪያ (Trust.Apk)
ትረስት የተሰኘው ጎጂ መተግበሪያ https://trust--application በሚል ማስፈንጠሪያ (ሊንክ) እየተሰራጨ የሚገኝ ሲሆን፣ ይህን ጎጂ መተግበሪ…
❤15
29 Jun 2026, 17:54 UTC≈2,150 views7 reactionsread 7 August 2026 Photo
የኢራን የሳይበር ጥቃት በሦስት እጥፍ መጨመሩን እስራኤል አሳወቀች
እስራኤል የኢራን የሳይበር ጥቃቶች በሦስት እጥፍ መጨመራቸውን ገለጸች፡፡ በኢራን እና በእስራኤል መካከል ያለው ወታደራዊ ውጥረት መባባሱን ተከትሎ፣ ከኢራን የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመራቸውን የእስራኤል ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣን አስታወቁ፡፡
የእስራኤል ብሔራዊ የሳይበር ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር ዮሲ ካራዲ ለጀርመኑ ዲ ዌልት ጋዜጣ እንደገለጹት፣ እ.ኤ.አ. በሰኔ 2025 ተመዝግቦ የነበረው 1 ሺህ 6 መቶ የጥቃት ሙከራ በሰኔ 2026 ወደ 4 ሺህ 8 መቶ አሻቅቧል ሲሉም አብራርተዋል፡፡
ባለሥልጣኑ እንደገለጹት፣ በጦር ግንባር የተኩስ አቁም ስምምነቶች ሊኖሩ ቢችሉም፣…
❤4👍3
10 Jun 2026, 06:48 UTC≈2,880 views4 reactionsread 7 August 2026 Video
ሩዋንዳ ብሔራዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ኤጀንሲ አቋቋመች
🇷🇼 አገሪቱ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ልማት እና አጠቃቀምን የሚመራላት ብሔራዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ኤጀንሲ ማቋቋሚያን አፅድቃለች።
ውሳኔው ሰኔ 1 ቀን በፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ በተመራው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ፀድቋል።
አዲሱ ኤጀንሲ የሩዋንዳውን የዲጂታል ኢኮኖሚ እና ብሔራዊ ልማትን ለመደገፍ ፈጠራን፣ ኢንቨስትመንትን እና የሰው ሠራሽ አስተውሎት አጠቃቀምን ያፋጥናል ተብሎ ይጠበቃል።
👆 የሩዋንዳ የሰው ሠራሽ አስተውሎት የኃይል ማዕከል የመሆን ትልም በተመለከተ የበለጠ ለማወቅ ቪዲዮውን ይመለከቱ፡፡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
@Tech_433et @Tech_433et
❤4
3 Jun 2026, 16:05 UTC≈3,290 views12 reactionsread 7 August 2026 Photo
ጎግል በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለሚፈጸሙ የማጭበርበሪያ ጥሪዎች አዲስ የመከላከያ ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ
ጎግል በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በመጠቀም የሰዎችን ድምጽ በመኮረጅ እና ስልክ ቁጥርን በመቀየር የሚፈጸሙ የማጭበርበር ጥሪዎችን ለመከላከል የሚያስችል አዲስ የደህንነት አማራጭ አስተዋውቋል።
"Fake call detection" (የሐሰተኛ ጥሪ ማወቂያ) የተሰኘው ይህ ቴክኖሎጂ፣ ጥሪዎች እውነተኛ መሆናቸውን በቅጽበት የሚያረጋግጥ ስርዓት አለው።
"Phone by Google" መተግበሪያን በሚጠቀሙ ተጠቃሚዎች መካከል በሚደረጉ ጥሪዎች ላይ፣ ስልኮቹ በራስ-ሰር (automatically) የተመሰጠረ የማረጋገጫ ምልክት እንደሚለዋወጡ ተገልጿል።
ጥሪው አጠራጣሪ…
❤12
30 May 2026, 09:15 UTC≈18,500 views25 reactionsread 7 August 2026 Photo
🚨🇨🇳 ቻይናውያን ሳይንቲስቶች ‘ጅምላ ጨራሽ’ የድሮን መንጋ ስልተ ቀመር ይፋ አደረጉ
አዲሱ አልጎሪዝም ባለ ቋሚ ክንፍ የድሮን ስብስቦች ሰፊ የጦር ሜዳዎችን በራሳቸው በመፈተሽ እያንዳንዱን ጠላት ሙሉ በሙሉ እንዲያጠፉ ያስችላቸዋል ሲሉ የቻይና መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
🔸 የውሳኔ አሰጣጥ ፍጥነቱ 6.6 ሚሊሰከንድ ነው።
🔸 ዘመናዊው ድር-መረብ ወዳጅ፣ ጠላት እና መልክዓ ምድርን እንደ የባሕሪያቸው በተለያዩ ነጥቦች የሚለይ “ሄትሮጅኒየስ ግራፍ” በመጠቀም ግራ መጋባትን ያስቀራል።
🔸 እያንዳንዳቸው የድሮን ግንኙነት መስመሮች በሚቋረጡበት ጊዜ ጠላቶች ለመጨረሻ ጊዜ የታዩበትን ቦታ የሚያስታውስ ልዩ ሞጁል አለው።
🔸 መፈለግ ወይም ማጥቃት እንዳለበት ከመረጠ በ…
😨13❤9🔥2😱1
16 May 2026, 10:58 UTC≈24,900 views23 reactionsread 7 August 2026 Photo
የአሜሪካ የነዳጅ ማደያዎች በኢራን ሃከሮች የሳይበር ጥቃት ተሰነዘረባቸው
በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች የነዳጅ መጠን መቆጣጠሪያ ስርዓቶች ላይ ለተሰነዘሩት ተከታታይ የሳይበር ጥቃቶች ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው ሃከሮች ሳይሆኑ አይቀሩም ሲል CNN የሀገሪቱን ባለስልጣናት ጠቅሶ ዘግቧል።
ሃከሮቹ ጥቃቱን የፈጸሙት ያለ ምንም የይለፍ ቃል በቀጥታ ከኢንተርኔት ጋር የተገናኙ አውቶማቲክ የነዳጅ ታንከር መቆጣጠሪያዎችን በመጠቀም ነው። በዚህም ጥቃት በማደያዎቹ ስክሪን ላይ የሚታየውን የነዳጅ መጠን ንባብ ማዛባት የቻሉ ሲሆን፣ በትክክለኛው ታንከሮቹ ውስጥ ባለው የነዳጅ መጠን ላይም የተወሰነ ጉዳት አድርሰዋል።
@Tech_433et @Tec…
❤10😱8👏4⚡1
13 May 2026, 16:56 UTC≈3,580 views12 reactionsread 7 August 2026 Photo
ማይክሮሶፍት በግንቦት ወር የደህንነት ማሻሻያ ለ120 የደህንነት ክፍተቶች መጠገኛ ለቀቀ
ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ማይክሮሶፍት በየወሩ በቋሚነት የማዘመኛ መጠገኛዎችን (Patch Tuesday) የሚለቅ ሲሆን፣ ይህ የደህንነት ማዘመኛ በሶፍትዌሮቹ ላይ በየጊዜው የሚገኙ አዳዲስ የደህንነት ክፍተቶችን ለመድፈን፣ የሲስተም ስህተቶችን (Bugs) ለማስተካከል እና ተጠቃሚዎችን ከዘመናዊ የሳይበር ጥቃቶች ለመጠበቅ በማሰብ ነው።
ይህን ተከትሎም በግንቦት ወር (ሜይ 2026) ማይክሮሶፍት ለ120 የሳይበር ጥቃት አጋላጭ ክፍተቶች የሚሆን መጠገኛ ማውጣቱን አስታውቋል። ኩባንያው ካቀረባቸው መፍትሄዎች መካከል 17ቱ "እጅግ አደገኛ" (Critical) በሚል ደረጃ ለተመደቡ ክ…
❤10👍1😎1
7 May 2026, 18:56 UTC≈24,500 views14 reactionsread 7 August 2026 Photo
ኦፕን ኤ.አይ GPT-5.5 Instant የተሰኘ አዲስ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴል ይፋ አደረገ፡፡
ኦፕን ኤ.አይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረውን GPT-5.5 Instant የተሰኘ አዲስ ሞዴል አስተዋውቋል። ይህ አዲስ ሞዴል ቀደም ሲል የነበረውን GPT-5.3 Instantን ሙሉ በሙሉ የሚተካ ሲሆን በተለይም እንደ ሕግ፣ ህክምና እና ፋይናንስ ባሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሹ ዘርፎች ላይ የሚታየውን ያልተረጋገጠ መረጃ የመፍጠር ወይም የ"Hallucination" ችግር በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀርፍ ነው።
አዲሱ ሞዴል የቀድሞውን ፈጣን ምላሽ የመስጠት ብቃት እንደጠበቀ የሚቆይ ከመሆኑም በላይ በሶፍትዌር ማበልፀግ እና በእውቀት ላይ በተመሰረቱ …
❤14
Showing the 12 most recent of 17 posts we hold for @Tech_433et. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.