21 May 2026, 17:15 UTC49 views2 reactionsread 7 August 2026 👉ስኬት ማለት...
በአጠቃላይ አነጋገር ስኬት (Success) ማለት የታለመን ዓላማ ወይም ግብ ከዳር ማድረስ ማለት ነው። ይሁን እንጂ ስኬት ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ ትርጉም ሊኖረው ይችላል። ለንዳንዶች የገንዘብ ብልጽግና ሲሆን፣ ለሌሎች ደግሞ የአእምሮ ሰላም፣ ደስተኛ ቤተሰብ ወይም ለሌሎች ሰዎች ጠቃሚ መሆን ሊሆን ይችላል።
ስኬትን በሦስት ዋና ዋና መንገዶች ማየት ይቻላል፡-
#ውጫዊ ስኬት (Objective Success): ይህ እንደ ሀብት፣ ዝና፣ ማዕረግ እና ቁሳዊ ጥቅሞች ያሉ ሌሎች ሰዎች ሊያዩት የሚችሉት ስኬት ነው።
#ውስጣዊ ስኬት (Subjective Success): ይህ ደግሞ ግለሰቡ በራሱ የሚያገኘው እርካታ፣ የውስጥ ሰላም እና ከራሱ እሴቶች ጋር ተ…
❤2
Signed Teka#
18 May 2026, 15:22 UTC77 views2 reactionsread 7 August 2026 5 የመክሰር Risk የሌላቸው መካከለኛ የ Business አይነቶች።
1, የሬስቶራንት Business ፦ ስራውን በደንብ ካወቅክበት ትርፋማ ንግድ ነው። ግን ስራውን በደንብ ማወቅ አለብህ plus ደግሞ Strategic የሆነ ስፍራ ላይ ነው መክፈት ያለብህ። ጥራት እና Consistency ላይ ትኩረት ማድረግም አለብህ። ምግብ ቤትህ ቦታው ጥሩ ቢሆንም እንኳ የጣእም መዋዠቅ ካለው ደንበኛ ያሳጣሀል። እንዲሁም አሁን ባለው ሁኔታ የ Takeaway እና የ Delivery አገልግሎት ማካተት ጥሩ ገቢ አለው። የሬስቶራንት [ የምግብ ቤት ] ቢዝነስ በአለም ላይም ሆነ በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ሁልጊዜም ከሚንቀሳቀሱ እና ፈጣን የገንዘብ ዝውውር ካላቸው የንግድ ዘርፎች ቀዳሚ…
👍2
Signed Teka#
24 Feb 2026, 04:24 UTC112 views1 reactionsread 7 August 2026 "ይሁንታን የምትሻ ከሆነ እስረኛ ነህ!!"
ዮናታን በጋሻው
ዘመኑ ተለውጧል። ከእንግዲህ አንተን ለማሰር መንጋው ሰንሰለት አያስፈልገውም። አሁን ማሰሪያው ጭብጨባ ነው። ጠባቂዎች የሉም። ወህኒ ቤቶች የሉም። ዛቻዎች የሉም። የፈገግታዎች፣ ላይኮች፣ አድናቆቶችና እና ግብዣዎች ዓለም ውስጥ እነሱን ማጣት ብቻ በቂ ነው። ቁጥጥር ከእንግዲህ በፈቃድ እንጂ በኃይል አይተገበርም።
ከቀደሙት ትውልዶች በተሻለ ነጻ እንደሆንን እናስባለን፤ ምክንያቱም መናገር፣ መጻፍ እና ሃሳባችንን መግለጽ ስለምንችል። ግን ሃሳብህን የምትገልጸው ሁልጊዜ በድርድር ከሆነ ነጻ አይደለህም። እያንዳንዱ ሃሳብህ ከሌሎች ተቀባይነትን የሚጠብቅ ከሆነ ንግግርህ ወደ ትወና ይቀየራል። ትወና ደግሞ በፍጹም…
👍1
Signed Teka#
17 Feb 2026, 15:11 UTC108 views1 reactionsread 7 August 2026 ✳️ ካልሰራህ ትጨነቃለህ"
✳️ ይህ ቃል ቀላል ይመስላል፣ ግን በውስጡ ጥልቅ እውነት አለው፡፡ ሰው ሲቆይ አካሉ ብቻ ይቆያል፤ አእምሮው ግን አይቆይም፡፡ ሐሳቦች ይበዛሉ፣ “ምን እየሰራው ነው?" "ነገ ምን ይሆናል?'' “ለምን እኔ?'' ያሉ ጥያቄዎች
✳️ ይዞውህ ይጓዛሉ፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች መልስ ሳይኖራቸው ሲቀሩ ጭንቀት ይወልዳሉ፣ ልብን ያደክማሉ፣ ተስፋን ያጠፋሉ፡፡ ሰው ስራ ካልኖረው ዋጋውን ይጠይቃል፡፡ ራሱን ከሌሎች ጋር ያነጻጽራል፣ “እነሱ ተማሩ፣ እነሱ ኣሳኩ፣ እኔ ግን ለምን ቆሜያለው?'' ይላል፡፡ ከዚያ በኋላ ቀን ተቀን መኖር ይከብዳል፤ ጊዜ እንደ ጠላት ይመስላል፡፡ እርምጃ ከሌለ ሕይወት እንደ ተዘጋ መንገድ ይሆናል፡፡
✳️ ነገር ግን ስራ ሲገ…
👏1
Signed Teka#
10 Nov 2025, 10:15 UTC155 views0 reactionsread 7 August 2026 የህይወት ፍልስፍና / በወጣትነት ጊዜያችን ስለ ወደፊቱ ብዙም ሳናስብ የተለያዩ ውሳኔዎችን እናደርጋለን። አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ውሳኔዎች በመካከለኛ ዕድሜያችን ላይ ክፉኛ ዋጋ ያስከፍሉናል። አንድ ሰው ሲያረጅ ሊጸጸትባቸው ከሚችላቸው ነገሮች መካከል ጥቂቶቹ እነዚህ ናቸው፦
1. የተሳሳተ ሰውን ማግባት
በወጣትነት ጊዜ፣ የማግባት ዝንባሌያችሁን መርምሩ። እኩዮቻችሁን ለመፎካከር፣ ለማህበራዊ ክብር ወይም በጫና ምክንያት አታግቡ። ለፍቅርና ለጓደኝነት ብላችሁ አግቡ፣ ትክክለኛውን ሰው አግቡ፣ የልብ ጓደኛችሁን አግቡ። ምክንያቱም የተሳሳተውን ሰው ወይም በተሳሳተ ምክንያት ካገባችሁ፣ ቀሪውን ህይወታችሁን ከዛ ሰው ጋር መጋፈጥ ይኖርባችኋል። በሁለታችሁ መካከል ነገሮች ሊከ…
Signed Teka#
1 Nov 2025, 15:52 UTC114 viewsread 7 August 2026 ለጠላቶችህ በደንብ ትኩረት ስጥ ፥ ምክንያቱም ስህተቶችህን ቀድመው የሚያገኙት እነሱ ናቸውና ።
፦Antisthen
Signed Teka#
7 Oct 2025, 13:38 UTC169 viewsread 7 August 2026 ወርቃማ ምክሮች
① የምታምነውን ሰው ለይተህ እወቅ፤ ጨውና ስኳር ቢመሳሰሉም ተልዕኳቸው ግን የተለያየ ነው።
② ፍቅር አንድ ሰው የህይወት እጣ ፈንታውን ከመከተል በፍጹም አያግደውም።
③ አንድን ነገር አጥብቀህ ስትፈልገው፣ መላው ዓለም አንተ ያንን ነገር እንድታሳካው ይተባበርሃል (ጽኑ ሁን)።
④ ድልድዮችን አታቃጥል፤ ያንኑ ወንዝ ምን ያህል ጊዜ መሻገር እንዳለብህ ስታውቅ ትገረማለህ።
⑤ ሥራቸው ምንም ያህል ቀላል ቢመስልም፣ ሰርቶ ለሚኖር ሰው ሁሉ ክብር ስጥ (ለሥራ ክብር አለውና)።
⑥ ትምህርት አስፈላጊ ነው፣ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ የግድ አይደለም (ህይወት እራሷ ትምህርት ልትሆን ትችላለች)።
⑦ ደስታህ የግል ጉዳይህ ነው (በቅናት ጠብቀው)።
…
Signed Teka#
28 Sept 2025, 11:05 UTC136 views1 reactionsread 7 August 2026 የታማኝነት ፈተና
① በሆቴል ውስጥ ከሚጠጡት ሻይ ላይ ቤትዎ ከሚያደርጉት የበለጠ ስኳር የሚጨምሩ ከሆነ፣ የሙስና ዝንባሌ አለብዎት!
② በህዝብ መጸዳጃ ቤት ውስጥ ቤትዎ ከሚጠቀሙት በላይ ሶፍት የሚጠቀሙ ከሆነ፣ ዕድሉን ካገኙ ሌባ ሊሆኑ ይችላሉ።
③ ሌላ ሰው ስለሚከፍል ብቻ ለሁሉም ይበቃ እንደሆነ ከግምት ሳያስገቡ ከምትጨርሱት በላይ ምግብ የምታስቀድሙ ከሆነ፣ ስግብግብ ነዎት። ዕድሉን ካገኙም ይሰርቃሉ።
④ ሰልፍ የመሰበር ልማድ ካለዎት፣ ከፍተኛ ስልጣን ቢሰጥዎት ቢሮዎን ያለአግባብ የመጠቀም ዝንባሌ አለብዎት።
⑤ የአንድን ሰው የመጀመሪያ ስም ከማወቅ ይልቅ የቤተሰብ ስሙን ለማወቅ የበለጠ የሚጨነቁ ከሆነ፣ የጎሰኝነት ዝንባሌ አለብዎት። ይባስ ብሎ አንድ ሰ…
❤1
Signed Teka#
10 Sept 2025, 12:37 UTC185 views1 reactionsread 7 August 2026 1. የሌሎችን ምስጢር የሚነግሩህን ሰዎች አትመን፣ ምክንያቱም የአንተንም ይነግሩበሀል።
2. ደስተኛ ስትሆን ቃል አትግባ ፣ ምክንያቱም ስሜቶች ይጠፋሉና።
3. በተናደድክ ጊዜ ውሳኔ አትወስን፣ምክንያቱም በአመክንዮ ማሰብ አትችልምና።
4. ችላ የሚሉህን አታሳድድ ምክንያቱም ዋጋህን ታጣለህና።
5. ሳታስብ አትናገር ፣ ምክንያቱም ቃላት ወደ ኋላ መመለስ አይቻልም።
6. በአንድ ሰው ህይወት ላይ አትቅና ፣ ምክንያቱም ትግላቸውን ስለማታውቅ።
7. ያለፈውን ነገር ከመጠን በላይ አታስብ ፣ ምክንያቱም አይለወጥምና ።
8. ከትንሽ ለመጀመር አትፍራ፣ ምክንያቱም ትልልቅ ነገሮች ጊዜ ይወስዳሉ።
9. በሌሎች ላይ ፈጥነህ አትፍረድ፤ ምክንያቱም ዕውነት የመሰለን ቶሎ ግልፅ ላይሆ…
👍1
Signed Teka#
2 Sept 2025, 10:09 UTC121 viewsread 7 August 2026 ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ከተሰማህ ይህንን አንብብ፤
1. ይህ አንድ ምዕራፍ ነው፡፡
አስቸጋሪ ጊዜያት የአንድ ምዕራፍ አካል ናቸው፡፡ ለዘላለም አይቆዩም፡፡ ሕይወት የደስታና የሐዘን ዑደት ነው፡፡
ይህም ያልፋል የሚለውን አስታውስ፡፡ አሁን በማዕበል ውስጥ ነህ፣ ነገር ግን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ሰማዩ ይጠራል፡፡ ታገስ፡፡
2. ከምታስበው በላይ ጠንካራ ነህ።
የብቃትህን መጠን በፍጹም አትገምትም፡፡
• መጥፎ ቀናትህን 100% ተቋቁመሃል፡፡
• በውስጥህ ተደብቆ የሚገኝ ጥንካሬ አለህ፡፡
• ችሎታህ ከማንኛውም ችግር ይበልጣል፡፡
ከምታስበው በላይ ጠንካራ እና ብቃት ያለው መሆንህን አስታውስ፡፡
3. ትናንሽ እርምጃዎች ይቆጠራሉ፡፡
እድገት ሁልጊዜ ትልቅ ዝላ…
Signed Teka#
19 Aug 2025, 05:53 UTC126 views2 reactionsread 7 August 2026 ማይክል ጆርዳን & ስኬት
ሰዎች እኔ በተፈጥሮ ችሎታ እንደተወለድሁ ይመስላቸዋል…
ነገር ግን ስንት ጊዜ እንደወደቅኩ አያውቁም።
በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የቡድን የስም ዝርዝር በተለጠፈ ሰዓት ስሜ አለመጻፉን ባየሁ ጊዜ ዓለም ተደፍታብኝ ነበረች በክፍሌ ውስጥ ዘግቼ፣ በዝምታ አምርሬ አለቀስሁ።
በኮሌጅ ውስጥ በቂ አቅም ጉልበትና ችሎታ የለህም ተብዬ ተነገርኝ። በNBA ውስጥ በተደጋጋሚ ተሰልፎ ጨዋታ እድል አጣሁ፣ ማድረግ ነበረብኝ የማልቻለው ግድግዳ ነበር፣ በዝምታም ክብደቱን ተሸከመሁ። ከ9,000 በላይ ኢላማቸው ያልጠበቁ ውርወራዎችን ሆኖው ከሸፉብኝ፣ 26 ጊዜ የጨዋታውን ድል የሚያመጣ ውርወራ በእጄ ነበር… ነገር ግን አልተሳካልኝም እና አልቻልኩም።…
❤2
Signed Teka#
22 Jul 2025, 10:23 UTC153 viewsread 7 August 2026 "ለሰዎች የምትሰጠው ምንም ነገር ባይኖርህ..
ሞቅ ያለ ፈገግታ እና መልካም ቃልን ስጣቸው.. ፍቅርን ስጣቸው.. መልካምነትን ስጣቸው.. የማበረታቻ ቃልን ስጣቸው.. ልብህን ስጣቸው"
ሰዎችን በማሳዘን ፈንታ ሁሌም ይህንን ብናደርግ ኢየሱስ በእኛ እንዳለ ያኔ ይታወቃል..
🙏
#አቡነ_ሽኖዳ
Signed Teka#
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @T2T4T5. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.