21 May 2026, 06:35 UTC88 views1 reactionsread 9 August 2026 Photo
ዐረገ በስብሀት
ሰላም ለዕርገትከ ዘኢይትረከብ መጠኑ
ወለንብረትከ ሰላም ለአቡከ ውስተ የማኑ
ኢየሱስ ክርስቶስ እለ ኪያከ ተአመኑ
ቅዱሳነ ዘእምኀቤከ ወንጹሐነ ይኩኑ
ጰራቅሊጦስሃ መንፈስከ ፈኑ።
ሰላም ለዕርገትከ በዘባነ መብረቅ ወነጎድጓድ፤
ከመ ትፈኑ መንፈሰከ በአምሳለ ነፋስ ወነድ፤
መድኃኔዓለም ክርስቶስ በመንግሥትከ ዋሕድ፤
ይቤሉከ ለለ ዕለቱ ሰማያውያን ነገድ፤
መንግሥቱ ዘለዓለም ወምኩናኑኒ ለትውልደ ትውልድ፡፡
እንኳን አደረሳችሁ
🕊1
10 Apr 2026, 11:59 UTC137 viewsread 9 August 2026 Photo
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የአርብ ጸሎት
ጌታዬ ሆይ! በቀራንዮ ኮረብታ ላይ የተፈጸመውን ያንን ታላቅ ምስጢር ሳስብ ነፍሴ በአድናቆት ትቀልጣለች። እነሆ፣ የሰማይና የምድር ጌታ በሁለት ወንበዴዎች መካከል እንደ አንዱ ወንበዴ ተቆጥሮ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ አያለሁ።
ጌታ ሆይ! ያንን የተቀደሰ ፊትህን እመለከታለሁ፤ መላእክት በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ ሊያዩት የማይደፍሩት ፊትህ፣ ዛሬ በኃጢአተኞች ምራቅ ተበላሽቷል። ፊቱ ላይ በሚወርደው ደም ውስጥ እያንዳንዱ ጠብታ ለእኔ የሚጮኽ የፍቅር ቃል አለው። ጌታ ሆይ! 'ለምን እንዲህ ሆንህ?' ብዬ ብጠይቅህ፣ መልስህ 'ስለ ወደድኩህ ነው' የሚል ብቻ ነው።
ያንን በመስቀል ላይ የነበረውን ጥማትህን አስባለሁ። አንተ እኮ ለ…
10 Apr 2026, 11:27 UTC89 views1 reactionsread 9 August 2026 Photo
...ዮሐንስን "የምወደው ልጄ ወዴት ነው ያለው ? እንዴት አድርጌ ነው ላየው የምችለው ?" አለችው ። ዮሐንስም " በተሰበሰበው ሰው መሐል አይንሽን ቀና አድርገሽ ወደ ምስራቅ ተመልከቺ ። በመስቀሉ ላይ ተሰቅሎ ታይዋለሽ ።" አላት ። አይኗንም ወደ ላይ አቅንታ በተመለከተች ጊዜ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ዐየችው። በሰውም መካከል እየሔደች ከአጠገቡ ደርሳ ቆመች ፤ በመከራም ሲሰቃይ አየችው ። ጌታም የእናቱን መከራና ኀዘን ባየ ጊዜ ወደ ዮሐንስ ተመልክቶ "ይኽች እናት ትኹንህ" አለው ። እርሷንም "ይኽ ልጅሽ ይኹንሽ" አላት ። ዮሐንስም "ወደ ቤታችን እንሒድ " ብሎ እመቤታችንን አስገደዳት ። እመቤታችንም "እባክኽ ተወኝ ለልጄ ላልቅስለት ብቻውን ነው …
❤1
30 Jul 2025, 11:20 UTC336 views0 reactionsread 9 August 2026 Photo
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
በዛሬው ዕለት (ሐምሌ 23) የታላቋ የሰማዕታት ሁሉ ልዕልት የቅድስት ማሪና ዘ አንጾኪያ በሰማዕትነት ያረፈችበት በዓል ነው።
እንኳን አደረሳችሁ
@StBarbaraStmarinaYouths
@MAHIBESTRBARBARAMARINA
14 Jul 2025, 06:18 UTC275 views1 reactionsread 9 August 2026 እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ እና ለቅዱሳን አበው አብርሃም አባ_ሲኖዳ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ሥሉስ ቅዱስ
በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው:: አብ :ወልድ : መንፈስ ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::
ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት "ቅድስት ሥላሴ" እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው…
❤1
5 Apr 2025, 06:17 UTC287 viewsread 9 August 2026 መዝሙረ ዳዊት ።
መዝሙር ፩ ።
የጻድቃንና የኃጥአንን ግብር የሚናገር ። ዳዊት በመዝሙር የተናገረው ይህ ነው ሃሌ ሉያ።
በክፉዎች ምክር ያልሄደ ምስጉን ነው ።
በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ ።
በዋዘኞችም መንበር ያልተቀመጠ ።
ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕግ ፈቃዱ የሆነለት ።
ሕጉንም በመዓልትም በሌሊትም የሚያነብ ።
እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች ።
በየጊዜዋ ፍሬዋን እንደምትሰጥ ።
ቅጠሏም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል ።
የጀመረውን የሚፈጽም ።
ኃጥአን ግን እንዲህ አይደሉም ።
ነገር ግን ነፋስ ከምድር ፊት እንደሚጠርገው
ትቢያ ናቸው እንጂ ።
ስለዚህ ክፉዎች ከፍርድ አያመልጡም ።
ኃጢአተኞችም በጻድቃን ምክር አይሄዱም ።
እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገ…
5 Apr 2025, 06:09 UTC189 views1 reactionsread 9 August 2026 "ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የውስጤን የሚረዳልኝ እንዳንተ ያለ ማንንም አላገኝም፤ ከአንተ ጋር ስሆን ብቻ ደህንነት ስለሚሰማኝ ለአንተ ለአምላኬ ልቤን ከፍቼ ምስጢሬን አዋይሃለሁ። ቃልህን የምሰማ ነገር ግን የማላስተውል ደካማ ነኝና፣ ናፍቆቴን ቢገልፅልኝ እንባዬን በፊትህ አፈሰዋለሁ።ልቤን ከሚያጸናውና በሃይሉ ከሚደግፈኝ ጋር እንደሆንኩ አውቃለሁና ከአንተ ጋር ብቻ ስሆን ብቸኝነት አይሰማኝም። ያለ አንተ ግን ባዶነቴና ብቸኝነቴ ያስጨንቀኛል። ከእኔ ጋር የሆንክ አማኑኤል አምላኬ ሆይ ነፍሴ ከአለምና በአለም ካሉት ከቁሳዊ ነገሮች ይልቅ የአንተን ሁሉን ቻይነት ትናፍቃለች። ውስጤ የማትወሰን አንተን ተጠምቷል። ከአንተም በቀር ይህን የሚረዳኝልኝ ከቶ የለም።"…
❤1
5 Apr 2025, 06:08 UTC146 views1 reactionsread 9 August 2026 Photo
"ሁሉን የያዘውን ያዙት ሁሉን የሚገዛውን አሰሩት የህያው የአምላክን ልጅ አሰሩት በቁጣ ጎተቱት በፍቅር ተከተላቸው በሚሽልተው ፊት እንደማይናገር እንደየዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፡፡ ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት ፡ ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት በመኳንንት በሚፈርደው በርሱ ፈረዱበት፡፡ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የእሾህ ዘውድ አቀዳጁት ለኪሩቤል የግርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፡፡ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሽፍነው ከፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባርያ እጁን አፅንቶ ፊቱን መታው፡፡ የመላእክት ሰራዊት በፍፁም መደንገጥ ለሚሰግዱ እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡
ይህ…
🙏1
3 Apr 2025, 06:30 UTC143 viewsread 9 August 2026 የሚያስፈልገን..ከ...ምንፈልገው
የማለዳ የነፍስ ስንቃችን
◆ በአንድ ወቅት አንድ መነኩሴ የወይራ ዘይት ዛፍ ተከለና ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል መጸለይ ጀመረ ፤ "ጌታ ሆይ ለዛፌ ይጠቅም ዘንድ ዝናብን አዝንብልኝ" አለ።
እግዚአብሔርምጸሎቱን ተቀብሎ ዝናቡን አዘነበለት ፤ ዛፉም ውኃን በጣም ጠግቦ አፈሩ ረሰረሰ። ለዛፉ ይጠቅም ዘንድ ግን ከመጠን በላይ የረሰረሰው አፈር መድረቅ ያስፈልገው ነበር። ስለሆነም መነኩሴው ወደ እግዚአብሔር ጸለየ "ጌታ ሆይ ብዙ ፀሐይ በዛፉ ላይ እንድታወጣ እለምንሃለሁ" አለ።
እግዚአብሔርምበለመነው መሠረት ፀሐይ አወጣለት ፤ ዛፉም አደገለት። መነኩሴው ልመናውን ቀጠለ "ጌታ ሆይ የዛፉ ሥር እና ቅርንጫፍ ይጠነክር ዘንድ ጥቂት ውርጭ…
3 Apr 2025, 06:15 UTC132 viewsread 9 August 2026 “ጨለማን ያሳደደው ብርሃን ዓለምን ሁሉ ያበራው ፋና የማይነዋወጥ መሰረትና የማይፈርስ ግንብ የማይሰበር መርከብና የማይሰረቅ ማህደር የለዘበ ቀንበርና የቀለለ ሽክም እርሱ ለአባቱ ሃይል ጥበቡም የሚሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
“ለሁሉ ያስባል ሁሉንም፡፡ ያጠግባል ለዕውራን ያዩ ዘንድ ብርሃንን ይሰጣቸዋል፡፡ የተዘጉ መስኮቶችን ይከፍታል ህሙማንን ይሰማቸዋል፡፡ የተደፈነችውን ጆሮ እንድትሰማ ያደርጋል፡፡ ከሰውነት የለምፅን ልብሶች ገፍፎ የስጋን መጎናፀፊያ ያለብሳል፡፡ የደረቀውን የእጅ ክንድ ያቀናል፣ የአንካሳውን እግር እንዲሄድ ያደርጋል ነፍስን ወደ ሕዋስዋ ይመልሳታል መንፈስንም በማደሪያዋ ያኖራታል፡፡ አለቆች ባሏቸው አጋንንት የእርያን መንጋ ያሰጥማል ከደከመችው…
31 Mar 2025, 15:58 UTC148 views1 reactionsread 9 August 2026 ተግባራዊ ክርስትና
አባ መቃሪዮስ በአንድ ወቅት ስለራሱ እንዲህ ሲል ተናግሯል “ወጣት በነበርኩበት ጊዜ በግብፅ በአንዲት መንደር በትንሽ ጎጆ እኖር ነበር በአንድ ወቅት የመንደሩ ነዋሪ እኔን ለቤተክርስቲያን ሹመት አጩኝ እኔ ግን ይህን ክብር ሽሽቼ ወደሌላ መንደር ሄድኩኝ፡፡ ከዚያም ትጉህ አገልጋይ የሆነ ረዳት አብሮኝ መኖር ጀመረ እኔ የምሰራቸውን የእጅ ስራወች እርሱ በመሽጥ ያገለግለኝ ነበር፤ በዚህ ወቅት በምኖርበት መንደር ያለች አንዲት ድንግል በድካም ዝላ ከጋብቻ ውጭ ዝሙት ትሰራና ታረግዛለች ቤተሰቦቿ ከማን እንዳረገዘች እንድትናገር ወጥረው ሲይዟት “ከመናኙ” ነው በማለት ተናገረች፤ የመንደሩም ሰው ተሰብስቦ ወደ እኔ መጣ ወደ መንደሩም እየጎተቱ ይዘውኝ …
🙏1
18 Mar 2025, 06:52 UTC223 views1 reactionsread 9 August 2026 * የሚገርመው በዚህች ምድር ላይ ለራሱ ብሎ የሚኖር አንድም ነገር የለም፤
* ወንዝ የራሱን ዉሃ አይጠጣም፣
* ባህር የራሱን ዓሳ አይበላም፣
* አትክልት የራሱን ፍሬ አይመገብም፣
* ፀሐይ የራሷን ሙቀት አትሞቅም፣
* ጨረቃ ለራሷ ብላ አትደምቅም፣
* አበባ ለራሱ ሲል አትፈካም፣
* ፍየል በግቷ የያዘችዉን ወተት አትጠጣም፣
- ነገሮች አንዱ ለሌላኛው እገዛ ነው የተፈጠሩት፣
- አንዱ ሌላው የጎደለዉን ለመሙላት ነው የተገኙት፣
- እኛም አንዳችን ለሌላኛችን እንኑር፣
- አንበላላ፣ አንጠፋፋ፣ እንተጋገዝ፣
* ሀሳብ የገባዉን - አዳምጠው፣
* ያማከረህን - መላ ስጠው፣
* ይቅርታ የጠየቀህን - እለፈው፣
* ቸገረኝ ያለህን - እርዳው፣
በዙርያችን ያለ ነገሮች…
🕊1
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @StBarbaraStmarinaYouths. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.