7 Aug 2026, 09:44 UTC164 views8 reactionsread 8 August 2026 ◈የወንጌል ለምምዳችን በተቃራኒው ሁኗል።
በስሁት ልምምድ እነዚህን አፍርተናል👇
◈1.)የእግዚአብሔርን ቃል እንደተራ ቃል መለማመድ፤
◈2.)ወንጌልን ሙያና መብያ መድረግ፤
◈3.)የማንኖረውን ቃል ለሌላው መስበክ፤
◈4.)ሳይታወቁ በማስመሰል ሲታወቁ በመቃረን መኖር፤
◈5.)ሞትንና ትንሣኤ ሙታንን፣ፍትሐ እግዚአብሔርን መርሳት፤
◈6.)እግዚአብሔር አጎታችን እስኪመስለን ድረስ መዳፈር፤
◈7.)አምላካዊ አደራን ከቁስ አደራ በታች አድርጎ ማየት፤
◈8.)ፌዝን ቧልትን እንደ ቁም ነገር ማዘውተር፤
◈9.)ሲጠቀለል፦ምረረ ገሀነመ እሳትን ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን መዘንጋት ይስተዋልብናል።
◈10.)መፍትሄው ከእነዚህ ጉዳዮች በተቃራኒ መኾን ነው።
➾ "ሰውነትን ለሥጋዊ …
❤6🔥2
Signed тнє 𝖘𝖊𝖈𝖗𝖊𝖙 𝖔𝖋 тαиα
7 Aug 2026, 04:36 UTC222 views4 reactionsread 8 August 2026 File
ከአባ ጊዮርጊስ ጋራ
ወደ እመቤታችን....! 🙏
ብንሄድ ያምርብናል!
https://t.me/Semarit888
❤4
Signed тнє 𝖘𝖊𝖈𝖗𝖊𝖙 𝖔𝖋 тαиα
6 Aug 2026, 14:37 UTC293 views6 reactionsread 8 August 2026 ወርኀ ነሐሴ
➾ ነሐሴ የሚለውን ቃል አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ላይ “ናሴ” ማለት መጨረሻ የመስከረም ዐሥራ ኹለተኛ በማለት ይፈቱታል፡፡
/አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝመበ ቃላት ገጽ ፮፻፴፯/
➾ ከሐምሌ ቅዱስ ቂርቆስ አንሥቶ እስከ ሐምሌ አጋማሽ ያለው ወቅት ነጎድጓድ በብዛት የሚሰማበት፣ መባርቅት የሚጮኹበት ወቅት ነው፤ በዚህ ወቅት በጸሎተ ቅዳሴው ከወንጌል በፊት የሚሰበኩት ምስባካት ጊዜውን የሚያወሱ የፈጣሪን ድንቅ ጥበብ የሚመሰክሩ ናቸው፤ ለአብነት ብንመለከት ‹‹ያዐርግ ደመናተ እምአጽናፈ ምድር፤ ወገብረ መብረቀ ለጊዜ ዝናም ዘያወጽኦሙ ለነፋሳት እመዛግብቲሆሙ ➛ ከምድር ዳር ደመናትን ያወጣል፤ በዝናም ጊዜ መብረቅን አደረገ፤ ነፋ…
❤5🥰1
Signed тнє 𝖘𝖊𝖈𝖗𝖊𝖙 𝖔𝖋 тαиα
6 Aug 2026, 14:06 UTC277 views5 reactionsread 8 August 2026 Photo
†ትእዛዘ አበው†
➾ “አንተ ሰው የበደለህን ይቅር ሳትል ወደ ጾም አትግባ፡፡ አንተን በበደለህ ሰው ላይ በቁጣ እያለህ የምትጾመው ጾም ከንቱ ነው ፤ እግዚአብሔርም አይቀበለውም፡፡
ጾምህን በፍቅርና እርሱን ተስፋ በማድረግ በእምነት ካላደረግኸው አንተን ፈጽሞ ሊረዳህ አይችልም፡፡ በጠብ ሆኖና በውስጡ ጠላትነትን አንግሦ የሚጾም ጸዋሚ እግዚአብሔርን ይጠላዋል ፤ ከመዳንም ፈጽሞ የራቀ ነው፡፡"
†ቅዱስ ኤፍሬም †
እግዚአብሔር እንደሕፃናቱ
ኀዳጌ-በቀል ወቂም
የኾነ ልብን ያድለን! 🙏🙏
እንኳንም አደረሳችሁ! 🙏
🙏4🥰1
Signed тнє 𝖘𝖊𝖈𝖗𝖊𝖙 𝖔𝖋 тαиα
4 Aug 2026, 04:59 UTC413 views8 reactionsread 8 August 2026 💥የተፈጥሮን ሕግ የለወጡ አምላካዊ ተአምራት🔥🔥🔥
─━━━━━⊱✿⊰━━━━━─
➾ መጽሐፍ ቅዱስ፦ ሰብአዊ አእምሮን ሊያስደንቁ የሚችሉ ፣ አልፎ ተርፎም ለማመን ሊከብዱ የሚችሉ ድንቅ ታሪኮችን የያዘ፤ የእግዚአብሔርን ሁሉን ቻይነት የሚመሰክር ቅዱስ መጽሐፍ ነው።
➾ እነዚህን ታሪኮች በሥጋዊ ዓይን ተመልክቶ በምክንያታዊነት ብቻ ለመመርመር ለሚሞክር ሰው ለማመን ሊከብዱ ይችላሉ፤ ነገር ግን በእምነት ዐይን ተመልክቶ የእግዚአብሔርን ሁሉን ቻይነት ለሚያምን ሰው ግን የፈጣሪን ሁሉን ቻይነት እና አምላካዊ ኃይል የሚያስረዱ ድንቅ ምስክሮች ናቸው።
✍️ለምሳሌ፦👇
💥 ኤልያስ በሰረገላ እሳት ተሳፍሮ ብሔረ ሕያዋን አርጓል። (2ኛ ነገሥ 2፥11)
💥 አህያ ጌታ…
❤7🔥1
Signed тнє 𝖘𝖊𝖈𝖗𝖊𝖙 𝖔𝖋 тαиα
2 Aug 2026, 13:12 UTC533 views6 reactionsread 8 August 2026 File
https://t.me/Semarit888
❤4🙏2
Signed тнє 𝖘𝖊𝖈𝖗𝖊𝖙 𝖔𝖋 тαиα
1 Aug 2026, 18:41 UTC576 views5 reactionsread 8 August 2026 ነገረ ሥሉስ ቅዱስ
➾ “አብ ፀሐይ ነው፤
➾ ወልድ ፀሐይ ነው፤
➾ መንፈስ ቅዱስም ፀሐይ ነው።
ከኹሉ በላይ የኾነ አንድ የእውነት ፀሐይ ነው።
➾ አብ እሳት ነው፤
➾ ወልድ እሳት ነው፤
➾ መንፈስ ቅዱስም እሳት ነው።
በልዕልና ያለ አንድ የሕይወት እሳት ነው።
➾ አብ ጎሕ(ጥባት፣ ብርሃን) ነው፤
➾ ወልድ ጎሕ(ጥባት፣ ብርሃን) ነው፤
➾ መንፈስ ቅዱስም ጎሕ(ጥባት፣ ብርሃን) ነው፤
በብርሃኑ ፀዳል ጨለማ የራቀበት አንድ የጥዋት ጎሕ ነው።
➾ አብ ጕንደ ወይንነው፤
➾ ወልድ ጕንደ ወይን ነው፤
➾ መንፈስ ቅዱስም ጕንደ ወይን ነው።
ዓለሙ ኹሉ የጣፈጠበት አንድ የሕይወት ወይን ነው።
➾ አብ ሐሊብ ነው፤
➾ ወልድ ሐሊብ ነው፤
➾ መንፈ…
🔥3❤2
Signed тнє 𝖘𝖊𝖈𝖗𝖊𝖙 𝖔𝖋 тαиα
1 Aug 2026, 09:33 UTC541 views5 reactionsread 8 August 2026 ጌታ ሆይ!🙏
➾ በኢትዮጵያ ላይ፡ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን፣ ምዕመናንን፣ ምልክቶችንና ትውፊቶችን "ማየት አንፈልግም" የሚሉ በዝተዋል እና ።
➾ አቤቱ በቸርነትህ፡ የጠሉትን እንዳያዩ፡ ዓይናቸውን አጥፍተህ ልባቸውን ታሳርፍላቸው ዘንድ እለምንሃለሁ።🙏🔥🤭
© Dr Meskerem Lechisa
https://t.me/Semarit888
🔥2😢2❤1
Signed тнє 𝖘𝖊𝖈𝖗𝖊𝖙 𝖔𝖋 тαиα
31 Jul 2026, 18:12 UTC420 views5 reactionsread 8 August 2026 Photo
🌹🌹🌹 ነገረ ማርያም 🌹🌹🌹
ድንግል ማርያም በሊቃውንት በሚከተሉት ተመስላለች።
፩. የማክሰኞ እርሻ (ዘፍ.1፥11)
፪. የአቤል ደግነት (ዘፍ.4፥4)
፫. የኖኅ መርከብ (ዘፍ.6፥4)
፬. ሰላማዊት ርግብ (ዘፍ.8፥11)
፭. ቀስተ ደመና (ዘፍ.9፥8-15)
፮. ዕፀ ሳቤቅ (ዘፍ.22፥9-13)
፯. የያዕቆብ መሰላል (ዘፍ.28፥10-20)
፰. ዕፀ ጳጦስ (ዘፀ.3፥1-6)
፱. ታቦተ ሙሴ (ዘፀ.25፥10-22)
፲. በትረ አሮን (ዘኍ.17፥8-11)
፲፩. የጌዴዎን ጸምር (መሳ.5፥36-40)
፲፪. የኤልያስ ደመና (1ኛ ነገ.18፥41)
፲፫. የኤልያስ መሶበ ወርቅ (1ኛ ነገ.19፥1-8)
፲፬. የኤልሳዕ…
❤5
Signed тнє 𝖘𝖊𝖈𝖗𝖊𝖙 𝖔𝖋 тαиα
31 Jul 2026, 18:12 UTC522 views6 reactionsread 8 August 2026 Photo
፴፫. ገነት ዕፁት አዘቅት ኅትምት (መሓ.4፥12)
፴፬. በሰማይ የታየች ዙፋን (ሕዝ.1፥26)
፴፭. ዐፅቀ አቤሜሌክ (ባሮ.3፥1)
፴፮. ደብተራ ኦሪት (ዘፀ.30፥26)
፴፯. መቅደሰ ሰሎሞን (1ኛ ዜና 22፥19)
፴፰. ቅድስተ ቅዱሳን (ዘፀ.30፥10)
፴፱. ዳንኤል የነበረባት ጉድጓድ (ዳን.14፥38)
፵. የሕይወት ዛፍ (ዘፍ.2፥9)
፵፩. በወርቅ የተለበጠች ማዕጠንት (ዘፀ.40፥5)
፵፪. መሶበ ወርቅ (ዕብ.9፥4)
፵፫. ጽላት ዘሙሴ (ዘፀ.24፥12)
፵፬. ሀገረ እግዚአብሔር (መዝ.45፥4)
፵፭. የዳዊት መሰንቆ (1ኛ ሳሙ.16፥23)
፵፮. ጸናጽል ዘውስተ ልብሱ ለአሮን (ዘፀ.39፥26)
፵…
❤3🙏3
Signed тнє 𝖘𝖊𝖈𝖗𝖊𝖙 𝖔𝖋 тαиα
31 Jul 2026, 07:29 UTC523 views6 reactionsread 8 August 2026 Photo
እመቦ ዘወድቀ በኃጢአት ኢይርሳእ።
➾ በኃጢአት የተሰነካከለ ሰው ቢኖር ኀጢአቱን አይዘንጋ!
እስመ ዘኢይትረሳእ፡፡
➾ ኀጢአቱን የማይዘነጋ ሰው በክብር ቀን አይረሳምና፤ ለክብር ይበቃል!🥰 ሲል ነው።
➾ ኀጢአተን የሚዘነጋ ሰው ግን ይትረሳእ ይላል፤ በክብር ቀን ይረሳል፤ ለክብር አይበቃም!😭 ሲል ነው።
አንድም፦ 👇
➾ ኀጢአቱን የማይዘነጋ ሰው በገሃገመ-እሳት ውስጥ አይረሳም።🥰 ኀጢአቱን የሚዘነጋ ሰው ግን ይትረሳእ! ይላል፤ በእሳተ ገሃነም ውስጥ ይረሳል። 🔥😭
/አባ ሕርቆስ በቅዳሴ ማርያም/
https://t.me/Semarit888
❤6
Signed тнє 𝖘𝖊𝖈𝖗𝖊𝖙 𝖔𝖋 тαиα
30 Jul 2026, 02:34 UTC586 views10 reactionsread 8 August 2026 Photo
ክርስትና ተረት አይደለም! 🔥
➾ "ክርስቲያን መኾንህን በቃላትህ ብቻ ሳይኾን በኑሮህና በባሕርይህ አስመስክር። ሰዎች የአንተን ደግነት፣ ትሕትናና ፍቅር ሲያዩ አንተን ሳይኾን በውስጥህ ያለውን ክርስቶስን ያመሰግናሉ።🙏🔥
➾ ያንተ ሕይወት ሰዎች የሚያነቡት ሕያው መጽሐፍ ነውና ገጾቹ በቅድስና የተሞሉ ይኹኑ።"
/ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ /
በረከቱ ትደረግልን!
https://t.me/Semarit888
❤10
Signed тнє 𝖘𝖊𝖈𝖗𝖊𝖙 𝖔𝖋 тαиα
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Semarit888. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.