14 Jan 2025, 15:14 UTC≈1,600 views15 reactionsread 8 August 2026 Photo
ፎቶ ፦ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የእድሳት ሥራ ተጠናቆ በቅዱስ ፓትርያርኩ እየተመረቀ ነው።
የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የእድሳት ሥራ ተጠናቆ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ተመርቆ ታቦተ ሕጉ ጥንታዊነቱን ጠብቆ ወደ ታደሰው ካቴድራል በመግባት ላይ ይገኛል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎችና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የየክፍል ኃላፊዎች ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ ምዕመናንና ምዕመናት ተገኝተዋል።
መረጃው የቤተክርስቲያኒቱ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።
@S…
❤10👍4👏1
12 Jan 2025, 04:48 UTC≈1,300 views3 reactionsread 8 August 2026 Photo
ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ‼️
በዛሬው ዕለት 03/05/2017 ዓ.ም ከደቂቃዎች በፊት 12:19 ደቂቃ ላይ በአዋሽ ፈንታሌ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 5.2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ‼️
ንዝረቱ በአዋሽ፣በአዲስ አበባ እንዲሁም በደብረብርሃን ከፍተኛ እንደነበር ቤተሰቦች ጠቁመዋል።
=======================
@SEBER_ZENA_ET
@SEBER_ZENA_ET
❤3
8 Jan 2025, 08:18 UTC≈1,130 views2 reactionsread 8 August 2026 Photo
ነዳጅ 100 ብር ገባ‼️
በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ‼️
ሚኒስቴሩ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ከዛሬ ታኅሣሥ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው ሆኖ ተወስኗል።
1 አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር፣
2 አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር፣
3 አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር፣
4 አንድ ሊትር የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር፣
5 አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር እንዲሁም
6 አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር ሆኖ እንዲሸጥ ሚኒስቴሩ ወስኗል።
===========…
❤2
6 Jan 2025, 06:19 UTC888 views2 reactionsread 8 August 2026 Photo
#AtoBulchaDemeksa
ጉምቱው ፖለቲከኛ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ስም የነበራቸው ጉምቱው ፖለቲከኛ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
" አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን እገልጻለሁ " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " በሚችሉት ሁሉ ሀገራቸውንና አፍሪካን ያገለገሉ፣ በአቋማቸው ጽኑ፣ ሕዝቦችን ለማቀራረብ የተጉ፣ እውነት ነው ብለው ያመኑትን የትምና መቼም የሚናገሩ ነበሩ " ብለዋቸዋል።
" እንዲህ ዓይነት ብርቱ ሽማግሌዎችን ማጣት ጉዳቱ ለሀገር ነው። ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይቀበላት " ሲ…
❤1😭1
6 Jan 2025, 05:41 UTC727 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
Update‼️
ተደብቀው የነበሩት ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ተያዙ‼️
የአፋር ክልል ንግድ ቢሮ እና የክልሉ ጸጥታ አካላት ባደረጉት ርብርብ ነዳጅ ጭነው በየቦታው ተደብቀው የነበሩ ቦቴዎች ከተደበቁበት እንዲወጡ መደረጉ ተገለጸ፡፡
አዲስ አበባን ጨምሮ ለተለያዩ ክልሎች የሚጓጓዝን ነዳጅ ይዘው በአፋር ክልል ሰርዶ አድማስ በሚባል ቦታ በየጥሻው የተደበቁ ቦቴዎች በፀጥታ አካላት አሰሳ መያዛቸውን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
በአሁኑ ሠዓትም የክልሉ ንግድ ቢሮ ለተሽከርካሪዎቹ እጀባ እንዲሰጥ በማድረግ ወደ የመዳረሻቸው እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓል መባሉን የባለስልጣኑ መረጃ አመላክቷል፡፡
“በወሩ መጨረሻ የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ይሠራል” በሚል ያልተጨበጠ ተስፋ ነዳ…
❤1
6 Jan 2025, 05:40 UTC635 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
ነዳጅ‼️
ከጅቡቲ ነዳጅ ጭነው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሰበብ እየፈጠሩ በርካታ ቦቲዎች መቆማቸውን ጥቆማ ደርሶኛል። ለአብነት ያለ በቂ ምክንያት ጭፍራ ላይ በርካታ ቦቲዎች ቆመዋል። ነዳጅ ጭነው በየመንገዱ የቆሙ በርካታ ናቸው ብለዋል። ለዚህ መነሻው ደግሞ ከመጪው ወር ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ ላይ ማሻሻያ ይደረጋል በሚል ነው ብለዋል።
አንድ ቤተሰብ ከሰመራ ከተማ የላከልን👇
"እኔ ያለሁት ሰመራ ከተማ ነው በነዳጅ ምክንያት ብዙ መኪኖች በየሄድኩባቸው ከተሞች ብዙ መኪኖች እንደቆም አይቻለሁ ፣ሰመራ ሎጌያ፣ሚሌ ላይ ታች ሚሌ ፣ድቸቱ-----ሰማራ ባለው ነዳጅ ማደያ በሙሉ ነዳጅ የለም በጣም ትንሽና ለአደጋ ግዜ በሚመስል መልኩ ሰመራ ኤርታእሌ ነዳጅ ማደያ ማታ ላይ ሲሰጥ…
👍1
3 Jan 2025, 07:38 UTC637 views2 reactionsread 8 August 2026 አዲሱ መመሪያ ወደ ተግባር ሊገባ ነው
የትራንስፖርት ዘርፍ ችግሮችን ይቀርፋል የተባለው መተግበሪያ
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በከተማዋ የተሽከርካሪዎችን ሰሌዳ መፍታትና የአሽከርካሪዎችን መንጃ ፈቃድ መቀማት የሚያስቀር አሰራር ሊተግበር መሆኑን አስታውቋል፡፡
ተቋሙ ከጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በመዲናዋ ተግባራዊ ይደረጋል ያለው አዲስ አሰራር የትራፊክ ቁጥጥርን የሚያዘምንና ዜጎች የትራፊክ ቅጣት ለመክፈል የሚያጠፉትን ጊዜና የሰው ኃይል ብክነት የሚያስቀር ነው ተብሏል፡፡
ለዚሁ አገልግሎት የበለፀገው መተግበሪያ በየዓመቱ በአዲስ አበባ ከተማ እስከ 400 ሰዎች ህይወት እያጠፋ ያለውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስና የሚስተዋለውን ከፍተኛ የትራፊ…
❤1👍1
30 Dec 2024, 17:53 UTC947 viewsread 8 August 2026 Photo
#እንድታውቁት‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት ኤጀንሲው የመጨረሻ ያለውንና 8ኛውን የመሬት ይዞታ የማረጋገጥና የእወጃ መርሐግብር በ6 ክፍለ ከተሞች ከታህሳስ 10/04/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት ወራት ውስጥ እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወሳል።
ለመሆኑ የይዞታ ይረጋገጥልኝ ጥያቄ በሚቀርብበት ወቅት የሚያስፈልጉ መረጃዎች ምንድን ናቸው?
- የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣
- ማንነትን የሚገልጽ የታደሰ መታዎቂያ፣ መንጃ ፈቃድ፣
- ፓስፖርት ወይም ፋይዳ መታወቂያ፣
- ግብር የተከፈለበት ደረሰኝ፣
- ይዞታው በሊዝ የተገኘ ከሆነ የሊዝ ውል፣
- የፍርድ ቤት ውሳኔ ካለ…
30 Dec 2024, 06:54 UTC669 views2 reactionsread 8 August 2026 Photo
አሳዛኝ ዜና‼️
ዛሬ 20/04/2017 ዓ.ም በሲዳማ ክልል በቦና ዙሪያ ወረዳ በጋላና ወንዝ ድልድይ ላይ በደረሰው አደጋ ቁጥራቸው በውል ባይታወቅም ከ60+ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል‼️
አደጋ የተከሰተው አንድ አይሱዙ መኪና ከ60+ የሠርግ አጃቢዎች አሳፍሮ ወደ ዳዬ በንሳ መሥመር እየተጓዘ እያለ በጋላና ድልድይ ተምዘግዝጎ ወደ ወንዙ በመግባቱ እንደሆነ የዓይን እማኞች ገልፀዋል። በጋላና ድልድይ ተመሳሳይ የትራፊክ አደጋ ሲደርስ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ይህ እጅግ የከፋ አደጋ ነው ብለዋል።
የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል ገልፀው ከውሃው ውስጥ የአስኬረን ፍለጋው መቀጠሉን ምንጮች ገልፀዋል። ከ60 በላይ ሰዎች ሞተዋል ብለዋል።
ነፍስ ይማር፣መፅናናትን ይስጥ…
❤1😱1
29 Dec 2024, 10:51 UTC612 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
ኢትዮጵያ ሳትካተት ቀረች‼️
ኢትዮጵያ በሶማሊያ በሚሰማራዉ በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ ሳትካተት ቀረች‼️
በጸጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ ዉስጥ ለመካተት ያነሳችውን የተሳትፎ ጥያቄ ሶማልያ ሳትቀበለዉ ቀርታለች።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ (AUSSOM) ለማቋቋም ትናንት አርብ ዕለት በውሳኔ ሃሳብ አጽድቋል።
15 አባላት ያሉት ምክር ቤት በእንግሊዝ መሪነት የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ በ14 ድምጽ ሲያፀድቅ አሜሪካ የድምፅ ተአቅቦ አድርጋለች።
አምባሳደሩ ኢትዮጵያ የሚጠበቅባትን ለመወጣት ዝግጁ ናት ሲሉ…
❤1
Showing the 10 most recent of 10 posts we hold for @SEBER_ZENA_ET. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.