27 Jun 2026, 11:02 UTC381 views11 reactionsread 6 August 2026 ዋ ኪሳራ
.
የምድር ፀሐይ ስታዘቀዝቅ፣ የሕይወትም መጋረጃ ሊዘጋ ሲል...ሰብአ-ነፍስ ወደ ኋላ ዞራ ትመለከታለች። የኖረችበትን ዘመን፣ የደከመችበትን ሩጫ፣ የከፈለችበትን መስዋዕትነት ሁሉ በአእምሮዋ መዝገብ ላይ ታገላብጣለች። ያኔ...በዚያ ብርሃንና ጨለማ በሚጋጩበት የመጨረሻ ሰዓት...አንድ አስደንጋጭ እውነት ፊቷ ላይ ይደቀናል። እነሆ ያ ሰማያዊ ድምፅ በነፍስያ ጓዳ ውስጥ ማስተጋባት ይጀምራል፦ «በሥራዎቻቸው በጣም ከሳሪዎቹን እንንገራችሁን?»
ይህ ጥያቄ ተራ ጥያቄ አይደለም። የሰውን ልጅ ከኖረበት የቅዠት እንቅልፍ የሚቀሰቅስ፣ ልብን የሚያናውጥ መለኮታዊ ጥሪ ነው! ከሳሪ ሲባል... ንብረቱን ያጣ ነጋዴ፣ ወይም ስሙ የጠፋ ባለጸጋ አይደለም። እርሱማ ዱንያ ላይ…
❤8💔3
29 May 2026, 18:24 UTC630 views9 reactionsread 6 August 2026 ሲመሽ...ሰው ሁሉ “መልካም ህልም” ይመኝልሃል። ከንፈሮች በለመዱት ቃል፣ ምላሶች በለመዱት ዜማ የሌሊቱን ግርዶ ሊያቆዝሙት ይሞክራሉ። ነገር ግን ማንም ቆም ብሎ አይጠይቅም፤ ምናለ... ምናለ ጥሩ የሆነ “እውን” ቢመኙልን? ምናለ ንጋታችንን የሚያበራ፣ የሚጨበጠውንና የሚኖረዉን ህይወት የሚባርክ ቅን ልቦና ቢኖራቸው?
እውነታችን በህመም ተሞልቶ፣ ቀናችን በለቅሶና በውጣ ውረድ ታሽቶ፣ የህልማችን ማማርና በሌሊት የምንቀዝፈው የቅንጦት መርከብ ምን ይጠቅማል? በቁማችን የምንቃጠልበት እቶን እያለ፣ በህልማችን የገነትን ወንዞች ብንሻገር ምን ትርጉም አለው? አይናችንን ስንገልጥ የሚጠብቀን ምሬትና ስብራት እየታወቀን፣ አይናችን ሲከደን የሚፈጠረው የሰከንዶች ማታለያ ምን…
❤8💔1
26 May 2026, 07:45 UTC640 views12 reactionsread 6 August 2026 የአረፋ ቀን...የሰማይ ደጆች ወለል ብለው ተከፍተው፣ የሰው ልጅ ስብራት ሁሉ የሚጠገንበት የዕንባና የምሕረት ቀን። ይህ ቀን ሲመጣ፣ የቆሰሉ ነብሶች ተስፋን ሰንቀው ወደ ፊት ይራመዳሉ፤ ምክንያቱም ዛሬ በምድር ላይ ካሉ ዕለታት ሁሉ በበለጠ ፈጣሪ ለሰው ልጅ ልመና በጣም ቅርብ የሚሆንበት ልዩ ዕለት ነውና።
የአረፋ ቀን...አረፋ ተራራ ላይ ቆመህ ወደዚያ ታላቅ ስብስብ ስትመለከት፣ ዓይንህ ሳይሆን ልብህ ነው የሚያለቅሰው። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ታያለህ...ሁሉም ነጭ ለብሰዋል፣ ሁሉም የዚህን ዓለም የውሸት ክብርና ኩራት አውልቀው ጥለዋል። ሀብታም የለም፣ ደሃ የለም፣ የተናቀ የለም፣ የተከበረ የለም፤ ሁሉም እኩል ሆኖል፣ አቧራ የለበሰ ፊቱንና የተሰበረ ልቡን…
❤11❤🔥1
25 May 2026, 18:49 UTC548 views17 reactionsread 6 August 2026 ቀኑ መሽቶ ሌቱ ተጋምሷል...ክፍሉ ውስጥ የነገሠው ጸጥታ ከባድ ነበር። መስኮቱ ላይ የተሰቀሉት መጋረጃዎች በለስላሳው የሌሊት ነፋስ እየተወዛወዙ ወደ ውስጥ የሚገባውን የጨረቃ ብርሃን ያስጨፍሩታል። እርሱ ግን አልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጦ፣ እጆቹን እርስ በእርስ አጣብቆ ወደ መሬት ያያል። የልቡ ትርታ በዝምታው ውስጥ ጎልቶ ይሰማል። በትከሻው ላይ ያረፈው የሕመም ሸክም አጉብጦታል።
ቀና ብሎ ከፊቱ ወደተቀመጠው መስታወት ተመለከተ። በዕድሜና በሃሳብ የዛሉ ዓይኖቹን አየና በረጅሙ ተነፈሰ።
"ችግር የለውም..." አለው ለራሱ፣ ድምፁ ከክፍሉ ግድግዳዎች ጋር ተጋጭቶ ሲመለስ። "ልክ እኛ አላፊ ጠፊ እንደሆንነው ሁሉ... ህመሞቻችንም ያልፋሉ፣ ይጠፋሉ።"
ይህችን ቃል ሲናገራ…
❤17
23 May 2026, 06:52 UTC601 views14 reactionsread 6 August 2026 አዎ... ጩኸታችን በረደ፣ እምባችንም ደረቀ፤ ሰዎች ሲያዩን "ዳኑ" አሉ። እኛም መኖራችንን ለመቀጠል ስንል ብቻ "ድነናል" ብለን ራሳችንን ዋሸን። ነገር ግን ይሄ መዳን አይደለም፤ ህመሙ ጉሮሯችንን አንቆ እንዳይገድለን በረዶ እንደማልበስ ማለት ነው። "ቁስላችን ዳነ..." ስንል ደሙ መፍሰሱን አቆመ እንጂ፣ በውስጣችን የተሰበረው ማንነታችን ሰንጣቂው ህመም አልቀነሰም። የትላንቱ ትኩሳት ቢያልፍም፣ በነፍሳችን ውስጥ የቀረው ቅዝቃዜ ግን የማይወጣ ሆነ።
"...ጠባሳው ግን አልጠፋም" ይልቁኑ በየቀኑ ጎልቶ እየታየን የሚያነድ፣ የሚቀጠቅጥ ትውስታ ሆነ። ጠባሳችን የትላንት የዋህነታችን መቃብር ላይ የቆመ ሀውልት ነው። ስንቱን አምነን ስንቱ እንደከዳን፣ ህይወታችንን …
❤11❤🔥3
13 Aug 2025, 12:58 UTC≈2,870 views3 reactionsread 6 August 2026 Photo
የሁሉንም ሀገራት ትኬትዎን ከአማና ትራቭል ይቁረጡ
በመረጡት ቀን እና ሰዓት የአየር ትኬትዎን ማግኘት ይችላሉ...እንዲሁም የፍላይ ዱባይ ትኬቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ከእኛ ጋር ያገኛሉ
.
ለበለጠ መረጃ፦
0914199123
0914604581
አድራሻ፦ አዲስ አበባ-ፒያሳ-ሴካ የንግድ ማዕከል 7ኛ ፎቅ
.
Travel Without limits
.
AMANAH TOUR & TRAVEL AGENT
❤3
7 Sept 2024, 22:15 UTC≈2,960 views19 reactionsread 6 August 2026 ....አንድ የጌታሽ ዱንያ ላይ፣ ሁለቴ መጣን እንል ዘንድ ለትዝታ....
.
.
"ስካር
ከምሽቱ 6:07
<ኧረ ልጅቷ ዛሬ በጤናዋም አይደለች! ምን ነክቷት ነው።> ቅድም ጀምራ የምትስቀውን እንስት ግራ በመጋባት ውስጥ ያይዋታል። ስተፈልግ ደሞ እየሳቀች ታለቅሳለች። በአፏ አንድ ነገርን ከመደጋገም ውጭ ለሚጠይቋት ጥያቄ ምንም መልስ አልሰጥ ብላቸዋለች። <ሰክራ ነው> ብለው ጥለዋት ሄዱ። ከማንም በፊት ለድሮ ሚስጥረኛዋ ጨረቃ መናገር ነበረባትና እነሱ ከመሄዳቸው ወደ ሚስጥረኛዋ እየተመከተች መናገር ጀመረች።
< ሰማሻቸው ጨረቃዬ! ሰከረች አሉኮ ሃሃሃሃ ለነገሩ ምን ይበሉ እኔን ያሰከረኝ ነገር መች ገብቷቸው። ልክ ናቸዋ ሰክሪያለሁኮ፣ ግን ጠጥቼ አይደለም የሰከርኩት…
❤14🥰3👍2
2 Sept 2024, 22:33 UTC≈2,500 views21 reactionsread 6 August 2026 እየደከምክ ግን ላለመውደቅ በመፍጨርጨር ውስጥ ሳለህ የማይደርስልህ፣ የማያስተውልህ ወዳጅ የወደቅክ ቀን ሊያስተዛዝንህ ብቅ ይላል። የመውደቅ እንጂ ይዞ የመቆየት ህመም የሚያም አይመስለው ይሁን አሊያ ስትወርድ አንድኛውን አላቅስሐለሁ ብሎ ይሁን ብለህ ጠርጥር። እንጂ መውረድህ እፎይታ ሰጥቶት ከንፈር ይመጥልኛል ስትል አትጠርጥር።
አውቃለሁ እያነባህ የደስታ የሚመስላቸው ሰዎች እንዳሉ፤ እየታገልክ ቀና ያልከውን ከኩራት የሚመድቡት እንዳሉ ይገባኛል። ያለፍከው መከራ ልብህን እንደወንፊት አሳስቶ ቶሎ እንደሚከፋህም።
ግን....
መታገልህን የሚረዳ፣ በቁም ውስጥህ እየተበላ እንደሆነ የሚያየው አሏህ አይበቃህም? ሊፈርድብህ ሳይሆን ሊሰማህ የተዘጋጀው አሏህ፤ ብስራቱን ሊሰ…
🥰18🙏2👍1
11 Aug 2024, 09:01 UTC≈2,630 views24 reactionsread 6 August 2026 ማናችን እንሆን...ከወንጀል የጠራነው በየትኛው መንገድ ይሆን መልካም ሰሪ ብቻ የሆነው በይፋም ሆነ በድብቅ ስንት ወንጀሎችን እንሰራለን...ነገር ግን የኛ ሩህሩና አዛኝ የሆነው አላህ ወደ እሱ በቀረብን ቁጥር ሁሉንም ወንጀላችንን ይምረናል እንደ ሰው ድጋሚ ሳያነሳ ወንጀላችንን ሁሉንም በምህረቱ ያልፍልናል ታዲያ ይሄን የመሰለ ጌታችንን ማመፅ እንዴት ቀላል ሆነ...?
.
.
@Re_Ya_zan
👍11❤10😭3
28 Jul 2024, 16:37 UTC≈4,000 views27 reactionsread 6 August 2026 እድሜ
ልጅነት የተለየ አለም አለው። ደስታ፣ ጨዋታ፣ መቦረቅ፣ መደባደብ… ከኛ ከትልቆቹ አለም እጅግ ይለያል። በጣም ጣፋጭ የማይገኝ የሚናፍቅ ጊዜ ነው "ኧረ ልጆች ልጆች እንጫወት በጣም፣ ከእንግዲህ ልጅነት ተመልሶ አይመጣም…" እያልን ትርጉሙን ሳናውቀው እየዘመርን ቦረቅንበት። ትልቅ መሆን እንደተመኘን ነፃነት ያለው እየመሰለን እየጓጓንለትም አደግን። ነገር ግን ስናድግ ትልቅነት እንዳሰብነው የሚናፈቅ አለም ሁኖ አላገኘነውም። ልጅ ሁነን እጃችን ላይ ትንሽ ነገር ከቧጨረን ሳምንቱን እንደ ህመምተኛ እጄን ነካብኝ፣ አያስበላኝም፣ አያስተኛኝም ብለን እንዳልቀበጥን ሁሉ፣ አሁን መች እንደቆሰለ ራሱ የማናውቀው ብዙ ቁስል ሰውነታችንን ሞልቶታል። መች እንደቆረጥነው ሳና…
❤21👍3👏3
27 Jul 2024, 09:11 UTC≈2,290 views25 reactionsread 6 August 2026 በምድር ላይ ባለህ ቆይታም ከመልካሞች ጋር ተወዳጅ...እነርሱ ከመካከላቸዉ በጠፋህ ጊዜ ፈላጊዎችህ ናቸዉ፣ መንገድ ስተህ ባዩህ ጊዜም ይመልሱሃል፣ በተዘናጋህ ጊዜ ያነቁሃል፣ በራቅካቸዉ ልክም ይናፍቃሉ፣ ከጌታቸዉ ጋር በተንሾካሾኩም ቁጥር ስምህን አይረሱም...🤍
@Re_Ya_zan
❤25
10 Jun 2024, 07:24 UTC≈2,870 views14 reactionsread 6 August 2026 መንገዶች በመድረሻቸው ይለካሉ.... መድረሻህ የሚገባው ከሆነ መንገድህ ሩቅ አይደለም፣ ደስ የሚል ተሞክሮ ነው.... አድካሚ አይደለም እውቀት ያጀበው እድገት ነው። መድረሻህ ተራ ከሆነ መንገድህ ቅርብ ቢሆንም ብክነት ነው.... ልፋትህ ቀላል ቢሆንም ባዶ ነው። ለዛም ይመስለኛል ለአኼራ ስንኖር ነገ እንደምንሞት፣ ለ ዱንያ ስንሰራ ገና ጊዜ እንዳለን መኖርን የተመከርነው። ብቻ...... ጀነት ለመግባት የሚበቃ ስንቅን ለመሸከፍ የዱንያ ቆይታችን በመርዘሙ አድክሞ አያውቅም.... ከደከመን ከመድረሻው ነው።
@Re_Ya_zan
❤12👍2
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Re_ya_zan. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.