29 Apr 2025, 20:14 UTC≈6,910 views74 reactionsread 8 August 2026 የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ 9 ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች
📖 “ያዕቆብን ወደድሁ ኤሳውን ግን ጠላሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።” ሮሜ 9፥13
የቀጠለ...👆👇👆👇
👉 የቃሉ ትርጓሜ ምንድነው ቢሉ አስቀድሞ እንደተናገረው “ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና አስቀድሞ የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው...” ሮሜ 8፥29-30 እንዲል የእግዚአብሔር ምርጫ ወሰን የለሽ በሆነው እውቀቱ ላይ የተመሰረተ ነው። እግዚአብሔር ያዕቆብን የወደደው የመረጠውና የጠራው ያዕቆብ ለእግዚአብሔር ፍቅር የሚቀበልና በጎ ምላሽ የሚሰጥ እንደሆነ አስቀድሞ ስላወቀ ነው። ኤሳውንም ጠላው …
❤45👍24👎5
Signed Yared G [ተክለ ማርያም]
29 Apr 2025, 20:12 UTC≈5,460 views19 reactionsread 8 August 2026 የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ 9 ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች
📖 “ያዕቆብን ወደድሁ ኤሳውን ግን ጠላሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።” ሮሜ 9፥13
👉 በሥጋ ከአብርሃም የተወለዱት [እስማኤልና የኬጡራ ልጆች] ሁሉ የአብርሃም ልጆች ተብለው እንዳልተጠሩ ይልቁኑ በተስፋው ቃል የተወለደው በይስሐቅ እንደተጠራ ከገለጸ በኋላ ከአንድ ማሕጸን ከተገኙት ያዕቆብና ኤሳው ምንም እንኳ የበኩር ሆኖ የተወለደው ኤሳው ቢሆንም የተመረጠው ታናሹ ያዕቆብ እንደሆነ ታላቁ ለታናሹ ይገዛል ተብሎ እንደተነገረ ይናገራል። 'ታላቅ' የተባሉ አይሁድ ናቸው። እግዚአብሔርን በማወቅ ከአሕዛብ ይቀድማሉና። አሕዛብ እርሱን [መሲሁን] በሃይማኖት ሲቀበሉት አይሁድ ግን ክደውታል። አሕዛ…
❤10👍9
Signed Yared G [ተክለ ማርያም]
14 Apr 2025, 15:54 UTC≈4,770 views21 reactionsread 8 August 2026 መርገመ በለስ
"...አዳም በገነት እርቃኑን ሆኖ በየትኛው ቅጠል ነበር እርቃኑን የሸፈነው? ይህች ቅጠል እንዴት እንደደረቀች አየህን?አዳም የሸፈነባት እርቃኑን የሸፈነባት አይደለችምን? ጌታ ኢየሱስ ወደ ለመለመችው የበለስ ዛፍ መጥቶ አዳም እርቃኑን የሸፈነባትን ቅጠል በቃሉ አደረቃት። አዳምን ድሃ ሆኖ ስላገኘው ንጹህ የሆነ የብርሃንንም ልብስ ሰጠው። ይሀውም ብርሃን ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ የተሰራ ነው። የተጠመቃችሁ ክርስቶስን ለብሳችኋልና። የበለሱን ቅጠል አድርቆ የነፍሱን ድህነት ሰጠው..." [ ድርሳነ ዮሐንስ አፈወርቅ - የሰኞ ጠዋት ግብረ ሕማማት ምንባብ]
❤19👏2
Signed Yared G [ተክለ ማርያም]
13 Apr 2025, 16:39 UTC≈4,420 views25 reactionsread 8 August 2026 እንደምን አመሻችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች?
በቀጣዩ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አይኖረንም።መልካም ሰሙነ ሕማማት ይሁንልን።
❤25
Signed Yared G [ተክለ ማርያም]
10 Apr 2025, 20:01 UTC≈4,590 views13 reactionsread 8 August 2026 የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ 9 ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች
📖 “ይህም፥ የተስፋ ቃል ልጆች ዘር ሆነው ይቆጠራሉ እንጂ እነዚህ የሥጋ ልጆች የሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም ማለት ነው።” ሮሜ 9፥8
👉 ቅዱስ ጳውሎስ ከእስራኤል የተወለዱ እስራኤላውያን አይደሉም በማለት በእግዚአብሔር ተስፋ የተነገረለትን መዳንና ጸጋ ለመቀበል በዘር ለአይሁድ ብቻ የተሰጠ ሳይሆን በመንፈሳዊ የሚደረግ [የሚተረጎም] እንደሆነ ይገልጻል። በሥጋ የአብርሃም ዘር ብቻ መሆን በቂ አይደለም በዘር አይሁድ ነገድ መሆን መዳንን ለማረጋገጥ በቂ እንዳልሆነ ይናገራል። ቅዱስ ጳውሎስ ይህን በአብርሃም ልጆች ይስሐቅና እስማኤል አድርጎ ይሞግታል። ይስሐቅና እስማኤል ሁለቱም የአ…
👍7❤6
Signed Yared G [ተክለ ማርያም]
8 Apr 2025, 19:20 UTC≈3,400 views9 reactionsread 8 August 2026 የቀጠለ...👆👇👆👇
👉 አይሁዳውያን በአባቶቻቸው በኩል ስለተቀበሉት ብዙ በረከቶችና ከእግዚአብሔርም ስለተሰጣቸው ተስፋ ራሳቸው የእግዚአብሔር ሕዝቦች እንደሆኑ ያምናሉ። እግዚአብሔር የሰጠውን ቃልኪዳን [ተስፋ] ለዘላለሙ የማይሻር ነውም ይላሉ። የተነገረው የእግዚአብሔር ቃልም (ቃልኪዳኑ)እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዘሩ የገባውን ቃልኪዳን ያመለክታል። “የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ።” ዘፍ. 12፥3 ፤
“አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ...” ዘጸ. 19፥5 የሚሉት ናቸው።
👉 ቅዱስ ጳውሎስም "የእግዚአብሔር ቃል …
❤8👍1
Signed Yared G [ተክለ ማርያም]
8 Apr 2025, 19:13 UTC≈2,970 views7 reactionsread 8 August 2026 የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ 9 ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች
📖“ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የተሻረ አይደለም። እነዚህ ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እስራኤል አይደሉምና፤ የአብርሃምም ዘር ስለሆኑ ሁላቸው ልጆች አይደሉም፥” ሮሜ 9፥6
👉 ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ.9:4-5 ላይ አይሁዳውያን ስለተሰጣቸው በረከቶች ይዘረዝራል። ክርስቶስን ባለመቀበላቸው የተወሰደባቸውን የአይሁድ ተመራጭነት ይናገራል። ለእስራኤል ሕዝብ ተመራጭነት ምልክት ናቸው ብለው ሐዋርያው ያቀረባቸው:-
1. እስራኤል መሆናቸውን- ይሀውም አባታቸው ያዕቆብ በህልሙ ሲታገል ከቆየ በኋላ ካልባረከኝ አልለቅቅህም በማለቱ እስራኤል የሚል ስም ሰጥቶ ባርኮታል:: ስለዚህ እስራኤል ለሚለው ቃ…
❤5👍2
Signed Yared G [ተክለ ማርያም]
5 Apr 2025, 19:06 UTC≈3,040 views18 reactionsread 8 August 2026 ከ 60 በላይ ጥያቄዎችና ማብራርያ ትምህርቶች የተካተቱበት የማርቆስ ወንጌል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን በዚህ ቻነል 130 ገጽ በሚሆን Pdf በመጽሐፍ መልክ ከለቀቅነው እንደ ቀልድ 5 ዓመት ሆነው። የማርቆስን ወንጌል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትን እንዴት አገኛችሁት?
❤18
Signed Yared G [ተክለ ማርያም]
3 Apr 2025, 20:59 UTC≈3,450 views9 reactionsread 8 August 2026 የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ 9 ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች
📖 “በሥጋ ዘመዶቼ ስለ ሆኑ ስለ ወንድሞቼ ከክርስቶስ ተለይቼ እኔ ራሴ የተረገምሁ እንድሆን እጸልይ ነበርና።” ሮሜ 9፥3
👉 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ብዙ ኅዘንና የማያቋርጥ ጭንቀት አለብኝ በማለት በሥጋ ወንድሞቹ ስለሚሆኑ አይሁድ አለማመን ያለውን የልቡና ኃዘን ይናገራል። አይሁድ ለእነርሱ ጠላትነት አለበት ብለው ይከስሱት ነበርና። በዚህም የተነሳ ኅዘንና ጭንቀት እንዳለበት ይናገራል። ይህም ንግግሩ እውነተኛ ስለመሆኑ ሦስት ምስክሮችን ያቀርባል። ክርስቶስ፣ መንፈስ ቅዱስና ሕሊናውን ምስክር አድርጎ ያቀርባል።
ቅዱስ ጳውሎስ እንደ አባቱ ነቢየ እግዚአብሔር ሙሴ ከራሱ ድኅነት የአይሁድ…
❤5👍4
Signed Yared G [ተክለ ማርያም]
3 Apr 2025, 19:44 UTC≈2,750 views3 reactionsread 8 August 2026 የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮሜ ሰዎች
ምዕራፍ 9
ቅዱስ ጳውሎስ በክርስቶስ መጽደቅ መዳን እንደሚገኝ በቀደሙት ምዕራፎች አብራርቶ ጽፏል። ጽድቅ በክርስቶስ የሚገኝ ከሆነ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ትቷቸዋል የሚል እንዳይኖር እግዚአብሔር ሕዝቡን የተወ እንዳልሆነ ከምዕራፍ 9-11 ባሉት ክፍሎች እያብራራ ይጽፋል::
ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ምዕራፉ
👉 አስቀድሞ የርሱ ወገን ስለሆኑት አይሁድ ያለውን ጭንቀት [ሮሜ.9:1-5]
👉 እውነተኛ የእግዚአብሔር ልጆች እነማን እንደሆኑ [ሮሜ.9:6-29]
-የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት የተስፋው ልጆች እንጂ በሥጋ የተወለዱት እንዳልሆኑ፤
- የእግዚአብሔር የምህረቱ ዕቃዎች እንደ…
❤3
Signed Yared G [ተክለ ማርያም]
1 Apr 2025, 20:17 UTC≈2,900 viewsread 8 August 2026 አንብባችሁ ጥያቄ የምትልኩበት የመወያያ Group link ነው 👇👇👇 https://t.me/+VrUcJE_9FV8xZDY0
Signed Yared G [ተክለ ማርያም]
1 Apr 2025, 16:57 UTC≈2,930 views7 reactionsread 8 August 2026 በቀጣይ ምዕራፍ ዘጠኝን እንጀምራለን። ምዕራፍ ዘጠኝን አንብቡና ስታነቡ ጥያቄ ያስነሳባችሁን ክፍል በመላክ ተሳተፉ።
❤7
Signed Yared G [ተክለ ማርያም]
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Orthodoxbiblestudy. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.