28 Oct 2023, 09:35 UTC≈5,480 viewsread 7 August 2026 ርዕስ ፦ ውዝግብ
ምን እየሰራሁ ነው _ የት ጋር ነው የቆምኩት
እያሉ ከራስ ጋር _ መሟገት ቀን ከሌት
ግራ ግብት ያለው _ ዥዋዥዌ ስሜት
ተሰምቷቹህ ያውቃል ...
እቅዳችሁ ሌላ _ የሚሆነው ሌላ
ጠበቀ ስትሉት _ መልሶ እሚላላ
በማድረግ በመተው _ መሀል መወዛገብ
መልስ አልባ ጥያቄን _ ቀን ከሌት መሰብሰብ
ዝም ብሎ መተኛት _ ሲነጋ መነሳት
ያለቅድ ተጉዞ _ ተመልሶ መምጣት
በውሸት ፈገግታ _ አስመስሎ መዋል
ምን አለበት እሱ _ እንደደላው መባል
ብዙ አይነት ሀሳቦች _ እያነሱ መጣል
የተደጋገመ አንድ _ አይነት ቀን መግፋት
ነገን አለመዋቅ ....
ለብዙ ነገሮች _ ደርሶ ትርጉም ማጣት
ተሰምቷቹህ ያውቃል ...
አስባ መጨነቅ - አፈግፍጎ መ…
Signed Nardos Tadele
25 Oct 2023, 22:37 UTC≈3,730 viewsread 7 August 2026 (ኦሪት ዘጸአት ምዕ. 15)
----------
3፤ እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው፥
18፤ እግዚአብሔር ለዘላለሙ እስከ ፍጻሜ ይነግሣል።
ርዕስ፦ ግን-ለምን...?
ትውልድ እመት ይበል
ይፋረደን እክል
ቀላያትም አንሻ___!
አይድረስ - ጠባሳ
አጋዥም - ዓይሻ
አይፈልግ - መካሻ
አልፎም - እጅ-መንሻ።
የትውልድ - እፎይታ
ከአመፅ - መለያ
የፃዲቃን መታያ
ሰላምን - መማሪያ
…
Signed Nardos Tadele
7 Jan 2023, 20:39 UTC≈2,810 viewsread 7 August 2026 ርዕስ ፦ ያንደበቴ መንሻ
ፍጥረት እልል ይበል ፤
ይሰማ እቢልታው ፣
አይሁድም ትመስክር ፤
በዜማ ታቅልጠው ፣
እስራኤል ታመስግን ፤
ወርዶል መስፍኗ ፣
አለም እልል ትበል ፤ ተወልዶል መድኗ ።
ትቢት ተፈጸመ ፤ ሰማያት ደመቁ ፣
ሰባሰገል ታዘው ፤ ለምስጋና በቁ ፣
ምድር ተጨነቀች ፤ አለቆች አመፁ ፣
ሊያፀድቀን ቢመጣ ፤ ሊያጠፉ ከገፁ ።
ስጋ ለብሶ መቶ ፤
በግርግም ተወልዶ ፣
ሊያስታርቀን ወዶ ፤
…
Signed Nardita
12 Nov 2022, 11:24 UTC≈3,140 viewsread 7 August 2026 ርዕስ፦ ቼ በለው !
የህይወት ጎዳና ገፁ ሲለወጥ ፣
በጭንቀት ታክቶ ጀርባው ሲመለጥ ፣
የእንቅፋት አፅሙ ቋጥኝ ሲገለጥ ፣
ሸክም ዘቦብህ ትብያው ሲላላጥ ፣
ሲሆን ድጥ በድጥ ፣
ሾህ ጭቃ ቅይጥ ፣
ልብህ አይደንግጥ ።
በምኞት ቅዥት በስጋት ርዶ ፣
አይፍረስ ግንቡ ወኔህ ተንዶ ፣
ከቆመው ቆመህ ከንፈር ከመምጠጥ ፣
በተስፋ ፈረስ በልጓም ሸምጥጥ ።
አያረጅ የለ አይለዋወጥ …
Signed Nardita
3 May 2022, 18:38 UTC≈2,870 viewsread 7 August 2026 ርዕስ ፦ በጊዜ ' ይሉንታ' ፤
ጊዜን ከሚያሳጥር ፤ ከርካሽ ትረካ ፣
መቋጫ ከሌለው ፤ ነብስን ሚያረካ...!
' ትብያንም 'ያዘለ ፤ የሞላ መከራ ፣
በመንታ ያስነባል ፤ የኋሊት መራራ።
ክብሩ ከሌለበት ፤ ከጎደለ ህይወት ፣
በታወረ ብሌን ፤ ከሚመስል ገነት ፣
ካሮጊታት ረመጥ ፤ ከሚያስዋዥቅ ተረት ፣
በጊዜ ይሉንታ ፤ ከሚያስተኛ ብክነት ፣
እየሱስ ከሌለበት ፤ ካልጎላበት ስብከት ።
እራስህን ጠብቅ ፤ ንቃ …
Signed Nardita
Channel name was changed to «ገጣሚ ናርዶስ ታደለ✍✍»
12 Mar 2022, 09:42 UTC≈2,880 viewsread 7 August 2026 ርዕስ ፦ አይደለም እድል ፤
ከታዘለ ተስፋ ፤ የታመቀ ጩኸት ፣
በለጋነት እድሜ ፤ ባላበበ ጡዘት ፣
ተወላግዶ ፕላን ፤ በህይወት አቀበት ፣
በግዴለሽ መረን ፤ ሲፈለፈል ውርደት ።
አሻቅባ ብርሀን ፤ በጨቅላነት ሳስታ ፣
በእቅፏ አሩራ ፤ ጡቶቿንም ግታ ፣
አሳድጋ አድርሳ ፤ ስትናፍቅም ጓግታ፣
ለወግ ልታበቃ ፤ ፍሬዋን አጉልታ ፣
ስጠብቅ በደስታ ፤ ከተሰማ ዋይታ፣
ስታነባ ማየት ፤ ደረቷንም ደቅታ ፣
በመንታ ያስነባል....!
ልብን ይፈትናል ...😭😭...
ወጣ…
Signed Nardita
21 Sept 2021, 06:18 UTC≈1,960 viewsread 7 August 2026 👉👉#አይዞሽ_እራሴ 💪
ባንቺ ብቻ አይደለም •••••
የሂዎትን ጉዞ ፤ የመኖርን መንገድ፣
ማን ቀጥብሎ ሄደ ፤ ማን ሳይወላገድ ?
ማንስ ነው የኖረው ፤ ሁሌም እንደሳቀ፣
ለአፋታም ሳይከፋው ፤ ሰርክ እንደቦረቀ ?
ማንስ ይሆን ከቶ ፤ በእንባ ምንጭ ያራሰ፣
ሀዘን ሳይዳስሰው ፤ ብሶት ሳይጎበኜው፣
በ አልጋ ባልጋ ድሎት ዛሬን የደረሰ....?
ማ•••••••••ን•••••••••ም 🤷♂
እየሽ አይደል እኔ 🤔
ይብዛም ይነስ እንጂ!
•
•
በመኖር እንቅፋት ፤ ሁሉም ተደናቅፏል?
የግዜን አቀበት ፤ በማቃ…
Signed Nardita
4 Sept 2021, 08:54 UTC≈2,200 viewsread 7 August 2026 🙈🙈🙊🙊
ርዕስ ፦ ኩርፍያዬ
ያ' ንደበቴ ድምፅ ጠፍቶ፣
ከፈሬም ባያወራ፣
ብትሸሸግ ምላሴ፣
ጥርሴ ነጩ - ባያበራ፣
የተደበቀው - ቅሬታዬ፣
አፌን - ሞልቶ ቢያስጨንቀኝ፣
ዝምታዬ - ወፈረና፣
ሣልናገር - አጋለጠኝ።
በጋጣሚ ፦ ናርዶስ
Signed Nardita
25 Aug 2021, 12:37 UTC≈3,220 viewsread 7 August 2026 💀💀 ርዕስ ፦ ቆሞያለ ' በድኑ፤
°°°°°°°°°^°°°°°°°
ያዘገመ እርምጃ፣
ቢፈጥንም በግምጃ፣
' ተሳ - ስቦ ' ፤ መድረስ፣
መች ይቻልህና፣
መንገድ እንዳይጠፋ፣
' መሪ '- ትገዛና፣
ተጉዘህ......ተጉዘህ፣
ራዕይ - ከሌለበት፣
ዕግርማ - ጎሞ ነው፣
ነጂው - የሞተበት፣
ሂሊናው - መግሎበት፣
መልስ…
Signed Nardita
12 Aug 2021, 06:54 UTC≈2,250 viewsread 7 August 2026 📩📩 ደብዳቤ፧
:
፧
ርዕስ ፦ ለ...ማእዘኑ ጌታ፤
ጎደፈ እኮ ስሜ፣
ላሸቀ እድሜ ፣
ቆሸሸ እኮ ልቤ፣
ታመመብኝ ህልሜ።
አንተን አበጅቼ ፤ የፅላቴን ጌታ፣
ሀይማኖት በሚሉት ፤ ትረካ ስጋታ፣
በእልፍ ሎሌዎች ፤ በጋጋታ ተርታ ፣
መህልቄ ለቆብኝ ፤ ባከኩኝ በይታ።
ጌታ ተዛብቶብኝ ፤ ጌታዬን ሳበጀው፣
…
Signed Nardita
Channel photo updated
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Nardi333. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.