2 Apr 2026, 19:36 UTC112 views3 reactionsread 8 August 2026 #የአእምሮ_ስፋትና_የውይይት_እርከኖች !
1. ደካማ ሰዎች ስለ ሰዎች ያወራሉ
ይህ የታችኛው የውይይት ደረጃ ነው። ደካማ የተባሉት በአካል ሳይሆን በሃሳብና በብስለት ደረጃቸው ነው። እነዚህ ሰዎች ጊዜያቸውን የሚያጠፉት የሌሎችን ስህተት በመፈለግ፣ ሰዎችን በመተቸት፣ በሃሜትና በሰው የግል ሕይወት ውስጥ ጣልቃ በመግባት ነው። ራሳቸውን ለማሻሻል ከመጣር ይልቅ ሌሎችን ዝቅ በማድረግ የረኩ ይመስላቸዋል። ውይይታቸው በምቀኝነት፣ በወሬና በከንቱ ትችት የተሞላ በመሆኑ ለራሳቸውም ሆነ ለህብረተሰቡ የሚጨምሩት እሴት የለም።
2. መካከለኛ ሰዎች ስለ ሁነቶች (ክስተቶች) ያወራሉ!
መካከለኛ የሚባሉት ሰዎች ትኩረታቸው በወቅታዊ ድርጊቶችና ክስተቶች ላይ ነው። ስለ ስፖርት ው…
❤3
2 Apr 2026, 19:36 UTC107 viewsread 8 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
2 Mar 2026, 06:51 UTC243 views3 reactionsread 8 August 2026 " #ተኩላ_በምክር_በግ _አይሆንም"
✔️ተኩላና በግ በባሕርያቸው ፍጹም ተቃራኒ ናቸው። ተኩላ አዳኝ፣ ጨካኝና በነጣቂነት የሚኖር እንስሳ ሲሆን፤ በግ ደግሞ የዋህ፣ ታዛዥና የማይጎዳ እንስሳ ነው። ይህ አባባል የሚያስተምረን፣ አንድ ሰው በውስጡ የያዘው መሠረታዊ ባህሪ በምክር ወይም በንግግር ብቻ በቀላሉ እንደማይለወጥ ነው። ምክር ውጫዊ ግብዓት ሲሆን፣ ተፈጥሮ ግን ውስጣዊ ማንነት ነው። ስለዚህ የሰው ልጅ በውስጡ የደበቀው ክፉ ማንነት ካለ፣ በቃላት ጋጋታ ብቻ ተፈጥሮውን ሊገታው እንደማይችል ያስገነዝበናል።
✔️ብዙዎቻችን "ሁሉንም ሰው በመምከርና በፍቅር መለወጥ ይቻላል" ብለን እናምናለን። ይህ በጎ ሃሳብ ቢሆንም፣ አባባሉ ግን እውነታውን እንድንጋፈጥ ያስገድደና…
👍3
2 Mar 2026, 06:51 UTC126 viewsread 8 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Channel name was changed to «Nablis_ናብሊስ»
1 Mar 2026, 06:38 UTC147 views3 reactionsread 8 August 2026 Photo
አዋዋልህ ሕይወትህን ይወስናል!!
አዋዋልህ የህይወትህ መገለጫ ነው፡፡ አንዲቷን ቀን የምታሳልፍበት መንገድ የዘመናት ሕይወትህን ይወስናል፡፡ ዛሬ የምትሠራው ነገር የወደፊት ሕይወትህን ይፈጥራል፡፡ የምትናገራቸው ቃላት፣ የምታፈልቀው ሐሳብ፣ የምትመገበው ምግብ እንዲሁም የምትወስዳቸው እርምጃዎች እጣ ፈንታህን ይወስናሉ፣ ማንነትህንና ሕይወትህን ይቀርፃሉ፡፡ ትናንሽ ውሳኔዎች በጊዜ ሂደት ግዙፍ ውጤት ያስከትላሉ። ‹‹ትርጉም አልባ» እለት የሚባል ነገር የለም፡፡
እያንዳንዳችን ለታላቅነት የሚያበቃ ጥሪ አለን፡፡ እያንዳንዳችን በውስጣችን ታላቅ ኃይል አለ፡፡ እያንዳንዳችን በዙሪያችን በሚገኙ ሰዎች፣ ሁናቴዎችና ነገሮች ላይ ተጽእኖ ማድረግ እንችላለን። በውስጣችን የሚገ…
👍2🔥1
19 Feb 2026, 19:26 UTC652 views4 reactionsread 8 August 2026 Photo
➨ ናርሲሲዝም (Narcissism)
ከቀላል ራስን
መውደድ ባለፈ፣ ጥልቅ የሆነ የስነ-ልቦና
መዛባት (Narcissistic Personality Disorder - NPD) ሊሆን ይችላል። እነዚህ ሰዎች በአብዛኛው የራሳቸውን አስፈላጊነት አጋንነው የሚያዩ፣ የሌሎችን ትኩረት አጥብቀው የሚፈልጉ እና ለሌሎች ሰዎች ስሜት ደንታ የሌላቸው ናቸው።
ናርሲሲስቶችን ለመለየትና ለመረዳት የሚረዱ ዋና ዋና ምልክቶች እነሆ፦
1. የናርሲሲዝም ዋና ዋና መገለጫዎች
➨ የበላይነት ስሜት (Grandiosity): ራሳቸውን ከማንም በላይ አዋቂ፣ ቆንጆ ወይም ስኬታማ አድርገው ያስባሉ። ያለ ምንም ተጨባጭ ምክንያት "ልዩ ክብር ይገባኛል" ብለው ያምናሉ።
➨ የአድናቆት ጥማት: ሁልጊዜ…
👍4
19 Nov 2025, 10:38 UTC795 views7 reactionsread 8 August 2026 #ሁሉም ለበጎ ነው
አንድ ፈረስ ብቻ ያለው አንድ ገበሬ ነበር።ከእለታት አንድ ቀን ፈረሱ ለግሞ ከቤቱ ያመልጣል....
ጎረቤቶቹም እቤት መጥተው
"ፈረስህ መጥፋቱን እና ማዘንህን ሰማን ልናፅናናህ መተን ነው"አሉት።
ገበሬውም" አላዘንኩም ለበጎ ነው አላቸው..."
ከጥቂት ቀን በኋላ ፈረሱ ከጠፋበት ቦታ ብዙ ፈረሶችን አስከትሎ ወደ ገበሬው ይመለሳል።ጎረቤቶቹም ወደ ቤቱ መጥተው"እንኳን ደስ አለህ ፈረስህ ብዙ ፈረሶችን ይዞልህ በመምጣቱ እንደተደሰትክ ሰምተን መጣን"አሉት።እሱም"ብዙም አልተደሰትኩም ለበጎ ነው!" አላቸው
ከጥቂት ጊዜ በኋላም ወጣቱ የገበሬው ልጅ አዳዲሶቹን ፈረሶች ሲያሰለጥን ወድቆ እግሩ ይሰበራል።ጎረቤቶቹ አሁንም መጥተው.."የልጅህን እግር መሰበር…
👍5❤2
22 Sept 2025, 22:04 UTC294 viewsread 8 August 2026 Photo
ከእለታት አንድ ቀን ሙላ ናስሩዲን በሰፈሩ ከሚገኝ ሱቅ በመሄድ ባለሱቁን ፦ " ቆዳ ይኖርሃል?" ሲል ጠየቀው
ባለሱቁም ፦ "አለኝ" አለ
ናስሩዲንም ፦ "ሚስማርስ አለህ?"ሲል ጠየቀ
ባለሱቁም ፦" አዎ አለኝ "ሲል ድጋሜ መለሰ
ናስሩዲንም አሁንም ጠየቀ ፦"ክርስ አለህ?"አለው
ባለሱቁም ፦"ክር አለኝ" አለ
ናስሩዲን ፦"መርፌስ አለህ?" ሲል ጠየቀ
"አዎ አለኝ " አለ ባለሱቁ
ናስሩዲን አንዲህ ሲል ተናገረ ፦ " ታድያ ጫማ እየሠፋህ ለምን አትሸጥም?" በማለት እየሳቀ ጥሎት ሄደ ።
መልካም - ቀን 🌻
አዳዲስ ሰዎችን ወደዚህ ቻናል በመጋበዝ ቻናሉ ተቀላቀሉ አሪፍ ትምህርት ታገኝበታላችሁ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Nablis_Fews
22 Sept 2025, 06:47 UTC380 views0 reactionsread 8 August 2026 Photo
ሙላ ናስሩዲን ፍቅር ያዘው።ጨርቅ የሚያስጥል ፍቅር።እናም በፍቅር ያሳበደችውን ሴት ለማግባት ወሰነ።ለእናቱ ነገራቸው። እናት ግን የወደድካት ሴት እምነት ስለሌላት ከሷ ጋር መጋባት አትችልም አሉት።
"ምን ይሻላል ሁለታችንም እኮ እንዋደዳለን" አለ ናስሩዲን።
"ከወደደችህ የምትላትን ትቀበላለች፤ስለ እምነት በደንብ አስረዳት፤አማኝ ትሆናለች" አሉ እናት።ሙላ በዚህ ተስማምቶ ወደ ፍቅረኛው ቤት ሄደ። ሰበካት ስለ ፈጣሪም ነገራት።ስለ እምነት አስረዳት።
፡
ከቀናት በኋላ ናስሩዲን እያለቃቀሰ እናቱ ወዳሉበት ማድቤት ገባ።ክንዳቸውን ተደግፎ እየየውን አስነካው
፡
"ምን ሆንክ ልጄ እቅዳችን አልሰራም?" እናት ጠየቁ።
"መስራት እንኳን ሰርቷል፤ ስለ እምነት ሰበኳት አመነች…
17 Sept 2025, 06:20 UTC949 views1 reactionsread 8 August 2026 🌴ለህሊናህ!
👉ወዳጄ! በሰው ልጅ አፈጣጠር ላይ ትልቁ የማይዳሰስ እና ዋጋ የሚሰጠው አካል ህሊና ነው። የህሊና ወቀሳ ከሰዎች ወቀሳ በእጅጉ ይለያል። ሰው ሲወቅስህ ለጊዜው ነው፤ ህሊናህ ግን እረፍት አይሰጥህም በተኛህና በነቃህ ቁጥር ተከታትሎ ይወጋሃል። #ለህሊናህ_መኖር ስትጀምር የዓለምን ሀብት ሁሉ በእጆችህ እንደጨበጥክ ማሰብ ትጀምራለህ።
👉ለህሊናህ መኖር ስትጀምር የአንተ ምርጥ ጠላቶች ውሽት፣ ክፋት... ይሆናሉ። በሰዎች ልቦና ውስጥ ለመቀመጥ ማስመሰል በበዛበት ሳቅና ውሸት በሞላበት መውደድ ውስጥ መመላስ ሳይሆን መፍትሔው #በጎ_ህሊና_መያዝ ብቻ ነው። ህሊና በሰዎች መቸገር እና መውደቅ ውስጥ ተባባሪ እንድትሆን አይሻም። ለህሊናህ መገዛት ስትጀምር ከሚያ…
👏1
17 Sept 2025, 06:15 UTC175 viewsread 8 August 2026 ውብ ቀን እንዲሆንልን!
ፈጣሪ አዲስን ቀን ውብ አድጎና ያስለመደንን የጸሃይ ብርሃን፣ እስትንፋስና የሚያስብ አእምሮ ሲሰጠን የቀረው ስራ የእኛ ነው፡፡ ይህ ስራ ግማሹ ውሳኔያችን፣ ግማሹ ደግሞ ጥንካሬያችን ነው!
የዛሬዋ ቀን ውብ እንድትሆን ውሳኔን ይጠይቃል፡፡ ይህ ውሳኔ፣ ለአናሳ ነገር አለመደላደልን፣ በጎ በጎውን ማሰብን፣ ያለፈውንና ፈጽሞ የማይመለሰውን መርሳትን፣ በእቅድ መኖርንና የመሳሰሉት ያካትታል፡፡
የዛሬዋ ቀን ውብ እንድትሆን ጥንካሬንም ይጠይቃል፡፡ ይህ ጥንካሬ፣ ምንም ነገር ብናደርግ መለወጥና ማስወገድ የማንችላቸውን ነገሮች ተቋቁሞ ማለፍን፣ መውጣትና መስራትን፣ በተከፈተልን መስክ ንቁ ተሳትፎ ማድረግንና የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡
የቀናችሁን ው…
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Nablis_Fews. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.