19 Aug 2020, 08:09 UTC≈2,670 viewsread 8 August 2026 ፀሐይ ከመሬት 149,598,023 ኪ.ሜ ትርቃለች። (ይህ አሐዝ ሲጠጋጋ መቶ ሃምሣ ሚልየን ኪ.ሜ ይሆናል።)
እጅግ በጣም ፈጣን እና ዘመናዊ መንኮራኩር ያለማቋረጥ በከፍተኛ ፍጥነት ቢጓዝ ከፀሐይ ቀጥሎ ያለችው ኮከብ ጋ ለመድረስ 70 ሺህ ዓመታት ይፈጅበታል!
የፀኃይ ክብደት የመሬትን 333,000 እጥፍ ነው። ይህም በቁጥር ሲገለፅ 1.99×10^27 ቶን ይሆናል።
ፀኃይ ብርሃንዋን የምትሰጠው በሴኮንድ 4 ሚልየን ቶን ሃይድሮጅን አቶሞችን በማቃጠል ወይንም በመጠቀም ነው።
ፀኃይ ያላትን ሃይድሮጅን ወደ ብርሃን ጉልበት የምትለውጥበት ሂደት በዓመት 360,000,000 ቶን ክብደት ትቀንሳለች። በዚህም ስሌት መሠረት ከ5000 ሚልየን ዓመት በኋላ ፀሐይ ትጠፋለች ወይ…
Signed ✿₮ēĐ✿
17 Aug 2020, 08:05 UTC≈1,480 viewsread 8 August 2026 ለመሬት ቅርብ የሆነችዋ ኮከብ ፀሐይ ስትሆን የምትገኝበት ጋላክሲ ስያሜ ሚልክ ዌይ ወይም ፍኖተ ሀሊብ ይባላል። ፍኖተ ሀሊብ በሁለንተናው ዓለም ካሉት 10 ቢልየን ጋላክሲዎች አንዱ ሲሆን ከፀሐይ 400,000,000,000 (አራት መቶ ቢልየን) እጥፍ የሙቀት ጉልበት ያመነጫል። የጎን ስፋቱ በጠቅላላው (71 ኳድሪሊየን) 71,000,000,000,000,000 ኪ.ሜ,ነው!
በባዶ አይናችን ልናየው የምንችለው ቅርቡ የሕዋ አካል ሜሲየር 31 የተባለው እና በአንድሮሜዳ የጋላክሲ ስብስብ ውስጥ የሚገኘው ግዙፍ የከዋክብት ክምችት ነው። ከመሬት 2.3 ሚልየን የብርሃን ዓመት ወይንም 2.18 × 10^19 ኪ.ሜ ይርቃል!!! በአንድ ቅጽበት ወደ ሰማያዊው አካል ቀና ብለን የምንመ…
Signed ✿₮ēĐ✿
16 Aug 2020, 09:42 UTC≈1,140 viewsread 8 August 2026 የሰው ልጆች በደረሱበት ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ምጥቀት የተፈጠረው እጅግ በጣም ረቂቅ እና ግዙፍ ቴሌስኮፕ ሁብል ቴሌስኮፕ ይባላል። በዚህ ሁብል ቴሌስኮፕ አጋዥነት 175 ቢልየን ጋላክሲዎችን ለማየት ተችሏል!!! ወደፊት የሚሰሩት ቴሌስኮፖች ደግሞ ከዚህም የበለጠ ተዓምር ያሳዩናል ተብሎ ይጠበቃል።
የሁለንተናው ዓለም ትልቁ ጋላክሲ በቪርጎ የጋላክሲ ስብስብ ውስጥ የሚገኘው ኤቤል 2029(Abell 2029) የተባለው ጋላክሲ ሲሆን ከእኛ ጋላክሲ 10 ሴክስቲሊየን (10,000,000,000,000,000,000,000) ኪ.ሜ ይርቃል!
የዚህ ጋላክሲ የጎን ስፋት ብቻ 53 ክዊንቲሊየን (53,000,000,000,000,000,000) ኪ.ሜ ሲሆን እንደ ፀሐይ የገዘፉ 2 ትሪሊየን…
Signed ✿₮ēĐ✿
12 Aug 2020, 08:13 UTC≈1,040 viewsread 8 August 2026 ከእነዚህም የግዙፎች ሁሉ ግዙፍ ከሚባሉት የክዋክብት ግድግዳ ወዲያ መጠኑ በአዕምሮ ሊገመት የማይችል ሕልቆ መሣፍርት የሌለው ወይም ጠረፉ በሰው አዕምሮ የማይቀመር ድንበር የለሽ ዓለም ይገኛል።
ጋላክሲ የክዋክብት ክምችት ሲሆን በአንድ ጋላክሲ ውስጥ 100,000 ክዋክብቶች ይገኛሉ። እያንዳንዱ ኮከብ ደግሞ ከፀሐይ የበለጠ ክብደት እና ስፋት አለው!!!
በአንድ ጋላክሲ ውስጥ ብቻ ስንመለከት ብርሃን ከአንድ የጋላክሲ ጫፍ እስከ ወደ ዚያው ጋላክሲ ጫፍ ለመጓዝ 100,000 ዓመታት ይፈጅበታል። ይህም ማለት 36,500,000 ቀናት ማለት ነው!!!
በሁለንተናው ዓለም(Universe) 10 ቢልየን ጋላክሲዎች አሉ። በዚህ ስሌት በሁለንተናው ዓለም የመጀመሪያው ክፍል ውስ…
Signed ✿₮ēĐ✿
11 Aug 2020, 14:35 UTC931 viewsread 8 August 2026 በሳይንሳዊው ግምት የዓለም ዕድሜ ከ11-17 ጂጋ ዓመት ሲሆን 1 ጂጋ ዓመት 1,000 ሚልየን ዓመታት ነው። ስለዚህ የዓለም ሳይንሳዊ ዕድሜ በትንሹ ከ11,000 ሚልየን እስከ 17,000 ሚልየን ዓመታት ይሆናል ተብሎ ይገመታል።
የሁለንናው ዓለም(Universe) የመጀመሪያው ድንበር ወይም ትልቁ ግድግዳ (The great wall) የሚባለው እና የሕዋውን አካል እንደ እንቁላል ቅርፊት ሸፍኖ የያዘው ታላቁ የሕዋ ግድግዳ በ1989 ዓ.ም "ማርግሬት ጌሪ" እና " ጆን ሁነችራ" በተባሉ ሁለት አሜሪካዊ የስነ-ፈለክ ጠበብቶች ተገኝቷል። ይህ የዓለም ግድግዳ ተብሎ ለጊዜው የተሰየመው የጋላክሲዎች ክምችት ግዝፈቱ ፍፁም አስፈሪ ሲሆን አኃዙም እንደሚከተለው ነው።
➧አግድም …
Signed ✿₮ēĐ✿
7 Aug 2020, 05:48 UTC943 viewsread 8 August 2026 ለሰባ ዓመታት የኖረ ሰው ከእድሜው ሶስት ዓመት የሚሆነውን ጊዜ የሚያሳልፈው በመፀዳጃ ቤት ውስጥ ነው።
ከሁለት ዓመት በታችየሆኑ ሕፃናት አብዛኛውን የእንቅልፍ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት ህልም በማየት ነው።
በማንኛውም ሰዓት 0.7 ፐርሰንት የዓለም ሕዘብ ከመለስተኛ እስከ ከፍተኛ የመጠጥ ስካር ውስጥ ይገኛል። ይህም ወደ 46 ሚልየን ይጠጋል። ይህም ማለት በማንኛውም ሰዓት 46 ሚልየን ሰው በስካር ስሜት ውስጥ ነው!
@Kewket_Mahider
Signed ✿₮ēĐ✿
2 Aug 2020, 10:46 UTC915 viewsread 8 August 2026 በ1951 ዓ.ም በአሜሪካ ችካጎ ከተማ ውስጥ ጊርቱድ ሌቫንዶንስኪ የተባለች አንዲት ሴት ለማህፀን ካንሰር የ96 ሰዓት ወይም የ4 ቀናት ተከታታይ ቀዶ ሕክምና ተደርጎላታል።
@Kewket_Mahider
Signed ✿₮ēĐ✿
2 Aug 2020, 10:46 UTC939 viewsread 8 August 2026 ከአንድ መቶ የዓለም ሕዝብ ትክክለኛ ናሙና ውስጥ ሀምሳ ሰባቱ እስያዊ፣ ሀያ አንዱ አውሮፓዊ፣ አስራ አራቱ አሜሪካዊ፣ ስምንቱ ደግሞ አፍሪካዊ ነው።
@Kewket_Mahider
Signed ✿₮ēĐ✿
31 Jul 2020, 17:39 UTC823 viewsread 8 August 2026 በአሁኑ ወቅት እድሜያቸው ከ112 ዓመት በላይ የሆኑትና በሕይወት የማገኙት 15 ሰዎች ሲሆኑ ከእነዚህ መሐል 2 ወንዶች እና 13 ሴቶች ናቸው።
ከአስራ ሶስቱ ውስጥ ሰባቱ አሜሪካዊያን ሲሆኑ ሁሉቱ ደግሞ ጃፓናውያን ናቸው። የተቀሩት እያንዳንዳቸው ጣልያን፣ ፖርቹጋል፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ኢኳዶር፣ ፖርቶሪኮ ዜግነት ያላቸው ናቸው።
@Kewket_Mahider
Signed ✿₮ēĐ✿
31 Jul 2020, 17:39 UTC905 viewsread 8 August 2026 ኤላን ኤስፖዛቶ የተባለች አሜሪካዊት በ1941 ዓ.ም የትርፍ አንጀት ቀዶ ሕክምና ሲደረግላት እድሜዋ 6 ዓመት ነበር። ይህች ልጅ ይህ ቀዶ ሕክምና ከተደረገላት በኋላ ግን በፍፁም ከሰመመኑ መንቃት አልቻለችም። የስድስት ዓመቷ ልጅ እድሜዋ 44 ዓመት ሞልቶ ከዚህ አለም በሞት እስክትለይ ድረስ ለ37 ዓመት ከ111 ቀናት አዕምሮዋን በመሳት እድሜ ዘመንዋን በኮማ ውስጥ አሳልፋለች።
@Kewket_Mahider
Signed ✿₮ēĐ✿
30 Jul 2020, 09:22 UTC816 viewsread 8 August 2026 በ1997 ዓ.ም ዶ/ር እንድርያስ ዛኪስ የተባሉ አሜሪካዊ ሐኪም በፍሎሪዳ ግዛት ጃክስን ሆስፒታል ውስጥ ለአንዲት የ10 ወር ጣልያናዊት ልጅ ባደረጉት 16 ሰዓት የፈጀ ቀዶ ሕክምና ከሌላ ሰዎች የተለገሳትን 7 ዋና ዋና የሰውነት ክፍሎች ማለትም ጉበት፣ ጣፊያ፣ ጨጓራ፣ ትንሹ አንጀት፣ ትልቁ አንጀት፣ የቀኝ ኩላሊት እና የግራ ኩላሊት በአንድ ጊዜ ተክለውላታል።
@Kewket_Mahider
Signed ✿₮ēĐ✿
30 Jul 2020, 09:22 UTC881 viewsread 8 August 2026 በዓለማችን ታሪክ የሰው ልጆችን የእድሜ ጣራ ሪከርድ የሰበረችው ጂየን ሊውስ ካልሜንት የተባለች ፈረንሳዊ ናት። በ1875 ተወልዳ በኦገስት 4/1997 ከዚህ አለም በዘላለማዊ እረፍት ስትሰናበት እድሜዋ 122 ዓመት ከ164 ቀናት ነበረ። ካልሜንት ከ19 መቶ ክፍለ ዘመን ጀምራ ሙሉውን ሀያኛውን ክፍለ ዘመን ኖራበት 21ኛውን መቶ ክፍለ ዘመን ለማየት የቀራት ሁለት ዓመት ተኩል ብቻ ነበር።
@Kewket_Mahider
Signed ✿₮ēĐ✿
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Kewket_Mahider. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.