7 Aug 2026, 08:12 UTC215 views8 reactionsread 10 August 2026 Photo
ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እንዲሁም ለገፃችን ቤተሰቦች በሙሉ በጉጉትና በናፍቆት ለሚጠበቀው ለፍልሰታ ጾም እንኳን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን አሜን!!! ♥•፨•
•፨•💚💛❤️ ፍልሰታ ❤️💛💚 •፨•
< ፍልሰታ > ፈለሰ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን የሚገልጸው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለቆ መሔድን ፣ መሰደድን ፣ መፍለስን ያመለክታል ። የእመቤታችን ሥጋ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መፍለስን በኃላም በገነት በዕፀ ሕይወት ስር ከነበረበት መነሳቱን ለማመልከት ይነገራል ። ይህም ጾመ ፍልሰታ በሌላ አጠራሩ ጾመ ማርያም በመባል ይታወቃል ። በዚህም ወቅት በብዛት የሚነገረው ቃለ እግዚአብሔር በአብዛኛው ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር …
❤8
29 Jul 2026, 12:29 UTC681 views14 reactionsread 10 August 2026 Photo
‹‹አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ፡፡
መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት።
ቀጥለውም በያዙት መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ፡፡ የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ከተቱት፡፡
ወዲያው ወታደሮቸ በሩምታ ተኩሰው ገደሏቸው፡፡
ይህ እንደሆነ አስገዳዩ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ።
ማታ ከአስገዳዩ ኮሎኔል ጋር ተገናኝተን ስንጫወት ‹‹በዚህ ቄስ መገደል እኮ ሕዝቡ ተደስቷል›› አለኝ፡፡
‹‹እንዴት?›› ብለው ‹‹አላየህም ሲያጨበጭብ?›› አለኝ፡፡ ‹‹ባታውቀው ነው እንጂ የሕዝቡ ባሕል ሲናደድም ያጨበጭባል›› አልኩት፡፡
‹‹እንዴት?›› ቢለኝ እጄን አጨብጭቤ አሳየሁት፡፡"…
😢11❤3
26 Jul 2026, 10:22 UTC762 views20 reactionsread 10 August 2026 Photo
8 ዓመት 😭
የዛሬ 8 ዓመት
* በዚች ቀን :-
* በዚች ስአት
በኢትዮጵያ ስአት አቆጣጣር ከጥዋቱ 2 ስአት:-
* July 26 ,2018
* ሐምሌ 19 ,2010
ነበር ::
በ53 ዓመቱ በመስቀል አደባባይ
የበረሀው ጀግና ኢንጂነር ስመኘው በሞት ያጣነው
ነብስህን ከደጋግ ጋር ያድርግልን
🙏🙏🙏
©gursha
ጥያቄ ካለዎት❓ 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia
😢9❤6😭3👍1🕊1
25 Jul 2026, 13:09 UTC738 views5 reactionsread 10 August 2026 የአለማችን ብቸኛ የኢትዮጵያ መንትያ ነገስታት
ከክርስቶስ ልደት 300 አመት ቦኃላ የኢትዮጵያ ንጉስ የሆነው
#አፄ_አልዓሜዳ እንደ አብርሀም እና ይስሀቅ ልጅ ሳያገኝ ለብዙ ጊዜ
ፈጣሪውን ሲማፀን ቆይቶ ታህሳስ 29 312 ዓ/ም መንትያ ልጆችን ወልዶ
ቀዳማዊውን ኢዛና ተከታዩን ሳይዛና ሲል ሰየማቸው።
ኢዛናና ሳይዛና በቤተመንግስት ስርዓተ ኦሪትን፣ ስርዓተ ክህነትን፣
የአይሁድ ስርአትን፣ ስርዓተ መንግስትን፣ የፈረስ ጉጉስን፣ የውሀ ዋናን፣
የጦር ፍልሚያን በሚገባ እየተማሩ አደጉ። ከ12 አመት ቦኃላም አባታቸው
አፄ አልዓሜዳ ወይም በንግስና ስሙ ሠይፈ አይዕርድ ህይወቱ ሲያልፍ
እድሜአቸው ሀገር ለመምራት ባለመድረሱ እናታቸው ንግስት ሶፍያ ወይም
አህይዋ በሞግዚትነት …
❤5
23 Jul 2026, 18:12 UTC662 views11 reactionsread 10 August 2026 Photo
መልካም ልደት
"የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ"
የቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ መልዕክት በመጨረሻው ሰዓት
(የአፍሪካ አባት ) ጃንሆይ
‹‹ያነበባችሁትን ሰምተናል ፣ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት ስንሆን
ስም ብቻ አይደለም፡፡ ቢሆንም በየጊዜው የሚለዋወጠው ነገር
ደግሞ ላገር የሚጠቅም ነገር እስካለበት … የኢትዮጵያን ታሪክ
ጠብቃችሁ ማልማት ከቻላችሁ የእኛ ታሪክ እዚህ ላይ ያበቃል።
ካልቻላችሁ የእናንተ ታሪክ ያበቃና የእኛ ይቀጥላል ፣
አገራችንንና ሕዝባችንን በምንችለው አገልግለናል ፣ የኢትዮጵያ
ሕዝብ እድል የእኛን መወገድ የሚጠይቅ ከሆነ ስራችንን
አቁመን ማንኛውንም ነገር ለመቀበል ዝግጁ ነን። ‹አሁን ተራው
የእኛ ነው› ካላችሁ ኢትዮጵያን ጠብቁ›› ጃንሆይ
መስከረም 2…
❤11
23 Jul 2026, 07:56 UTC608 views3 reactionsread 10 August 2026 Photo
"ይህንን የምታዩት በዩናይትድ ስቴትስ ዋና ከተማ ዋሺንግተን ዲሲ ለአፍሪካ አሜሪካውያን መታሠቢያ በተሰራ ሙዚዬም ውስጥ ነው።
አማርኛ ቋንቋችን ከሌሎች ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች ጋር በዓለም ዓቀፍ ተቋማት ውስጥ እንዲህ ዕውቅና አግኝቷል።"
©️መሥፍን
ጥያቄ ካለዎት❓ 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia
👏2❤1
22 Jul 2026, 10:00 UTC654 views4 reactionsread 10 August 2026 🇪🇹 ከኢትዮጵያ ጥበባት
🍀ከላይ የምትመለከቷት እጽ ቀጠጥና/ እፀ ደብተራ/የአህያ ጀሮ / እፀ እስራኤል ትባላለች።🍀
ለዛሬው ከብዙ የሕክምና ፈውሶቿ ጥቂቱን እንመልከት።
1⃣ኛ በተለያየ ምክንያት እግሩ ላበጠ ሰው አባቶቻችን ደብተራዎችና መሪጌታዎች ከላይ ያለችውን ቀጠጥና የተባለችውን እጽዋት ለመድሃኒትነት ይጠቀሙባታል።
🌿የቀጠጥናናን ቅጠል በእሳት ሞቅ እያደረጉ ያበጠው ቦታ ላይ መተኮስ ነው።
...እብጠቱ ይቀንሳል።
2⃣ኛ በተጨማሪም ቁስል አልድን ሲልና መግሉን ለማድረቅም ይህችን ብዙ ሥራዎችን ያላትን እጽ ይጠቀማሉ።
የቀጠጥናን ቅጠል አልሞ ደቁሶ ቁስሉ ላይ መነስነስ ነው።
3⃣ኛ እንስሳቶችን አውሬ እንዳይበላቸው ..."መስተኀድር" ይባላል።
ይህንን…
❤4
18 Jul 2026, 18:58 UTC931 views7 reactionsread 10 August 2026 🇪🇹 ኢትዮጵ/ኢትኤል
ኢትዮጵያ መጠሪያዋን ከየት አገኘች?
በመፅሃፍ ቅዱስ ላይ እንደተጠቀሰው ሊቀ ካህኑብ መልከፄዴቅ ሶስት ወንድ ልጆች ነበሩት ከነኛ ልጆች አንዱ ደግሞ ኢትኤል ነበር ኢትኤል በመንፈስ ተመርቶ ካለበት ከሳሌም እስራኤል ወደ ጣና ላይ እንዲሰፍር ታዘዘ። ኢትኤል ጣና ሲደርስ ስሙን ቀይሮ ኢትዮጵ እንዲባል ሆነ። ኢትዮጵ ማለት ፦ ኢት - ስጦታ ማለት ሲሆን ዮጵ ደግሞ ቢጫ ወርቅ ማለት ነው። ኢትዮጵ የቢጫ ወርቅ ስጦታ! ኢትኤል ማለት ደግሞ የእግዚአብሄር ስጦታ ማለት ነው። የሃገራችን መጠሪያ የመጣው ከንጉስ ኢትዮጵ በኃላ ነበር በኢትዮጵ ኢትዮጵያ ተባለች።
ሃገራችን ኢትዮጵያ የሚለውን ስያሜ ከማግኘቷ በፊት እንቆጳግዮን ተብላ ትጠራ ነበር። በነገደ …
❤6🔥1
18 Jul 2026, 08:32 UTC809 views7 reactionsread 10 August 2026 🔘ከአክሱም ሀውልት ጀርባ ያለው መለኮታዊ ኃይል|ስለአክሱም ሀውልት ያልሰማናቸው አስደናቂ ምስጥሮች
✍🏾ተፃፈ በገብረ መድኅን
ተራሮች እየፈለፈለች ዓለቶችን እየወቀረች የማይፈነቀል የክርስትና ጥልቅ እምነቷን በጠንካራው ዓለትና በተራሮች ሆድ ውስጥ የመሠረተችው ታላቋ ኢትዮጵያ ሀገራችን በሌሎች የዓለማችን ክፍሎች የማይገኙ በብዛታቸውም ሆነ በአስተናነፃቸው የሚያስደንቁ በታላቅ ጥበብና ትጋት የታነፁ አብያተ ክርስትያናትና ሀውልቶች ባለቤት ናት።ከነዚህ የጥበቦቿ ማሳያ ከሆኑ አብያተ ክርስቲያናትና ሀውልቶች መካከል በቀዳሚነት ደረጃ የሚነሳው ከዛሬ 1700 አመታት እንደታነፀ የሚነገርለት በአክሱም ከተማ የሚገኘው የአክሱም ሀውልት ነው።
ዓለም በድንጋይ ዘመን አስተሳሰ…
❤7
16 Jul 2026, 20:10 UTC764 views9 reactionsread 10 August 2026 👉 የኢትዮጵያ ስርኦ መንግስታት (ከአዳም እስከ አሁን)
2⃣ ክፍል 2
7) የሸዋ ስርኦ መንግስት (1245 - 1555 ዓ.ም)
የሸዋ ስርኦ መንግስት ከ አፄ ይኩኑ አምላክ ጀምሮ 26 ነገስታት እየከታተሉ ያአስተዳደሩበት ዘመን ነው። በዚህ ስርኦ መንግስት ዘመን የኢትዮጵያ የመንግስት መቀመጫና መዲና ረጅም ዓመታት ከነበረበት ከሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ወደ መሀከለኛው የሀገሪቱ ክፍል የተሸጋገረበት ነው። ባለፉት ስርኦ መንግስታት ዘመን ግዮን ፣ ዋይዝ ፣ መንፊስ ፣ ቴብ ፣ ናፖታ ፣ መረዌ ፣ የሃ ፣ አክሱም ፣ ላስታ ወዘተ… የመንግስታት መቀመጫ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ከ1245 ዓ.ም ጀምሮ ግን የመንግስት መቀመጫ ወደ ሸዋ የተዘዋወረበት ጊዜ ነበር። በተለይ አንኮበር…
❤9
15 Jul 2026, 21:10 UTC755 views5 reactionsread 10 August 2026 Photo
የንጉሡ መልዕክት
❤5
14 Jul 2026, 07:08 UTC784 views12 reactionsread 10 August 2026 Photo
ሐምሌ 7 ልደት 🎂🎁🎉🎊💐🍾🎈
WOW HAPPY HAPPY BIRTHDAY 🎂🎁🎉🎊🎈
እንኳን ተወለድክ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
መወለድህ ለእኛ ኢትዮጵያን 💚💛❤️ ለምንወድ ህዝቦች ትርጉሙ ብዙ ነው: ኢትዮጵያ ስትል አብረን ኢትዮጵያ እንላለን::
ቴዲ ስላንተ ምን ተነግሮ ምን ይተዋል የተሰጠኽን ፀጋ ይዘኽ በአግባቡ በመጠቀም ለእኛ ለኢትዮጵያዊያኖች የፍቅር የሰላም የአንድነት ድምፅ ከመሆን ባለፈ... ለሰው ልጆች ሕይወት ሰላም እና ፍቅርን በመስበክ ስላሳየኸን የፍቅር የሰላም የመቻቻል የአንድነት መንገዶች ክብር ይገባሀል::
ቀርቦ አንተነትህን ለተረዳ በጥልቀት ላወቁህ ሰዎች ለሰው ልጆች ያለኸ አመለካከት ከፈጣሪ የሚሰጥ ፀጋ እንጂ እ…
❤10👍2
Showing the 12 most recent of 19 posts we hold for @Historical_Ethiopia. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.