30 May 2026, 14:48 UTC301 views6 reactionsread 7 August 2026 📃ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
••●◉ ✞ ◉●••
የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ❓ ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን❓ ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ❓ አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን❓ እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ። ማቴ 5፡42-48፡፡
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊…
❤4🙏2
Signed Wondie
22 Jun 2025, 09:33 UTC≈1,500 views7 reactionsread 7 August 2026 🔔እነሆ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም ከዚያ አለ ቢሏችሁ አትመኑ🙅ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ እነሆ አስቀድሜ ነገርኳችሁ።በማቴ 24፥24
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🔊ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ🙅።ማር 13፥15
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📢ወንድሞች ሆይ ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ።ዕብ 3፥12
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙏እንደተማራችሁት በሃይማኖት ጽኑ፣ ልዩ ልዩ ዓይነት በሆኑ እንግዳ ትምህርት አትወሰዱ፣ በዐመጸኖች ስህተት ተስባችሁ ከራሳችሁ …
❤3🔥2🥰2
Signed Yene💖፫💖
20 Jun 2025, 17:23 UTC996 views4 reactionsread 7 August 2026 💁♂ቅዱስ ሚካኤል በመጽሐፍ ቅዱስ📖
••●◉ ✞ ◉●••
📃እንዲህም ሆነ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፡፡ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፡፡ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን ❓አለው፡፡ እርሱም አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ አለ፡፡ ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ፡፡ ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድን ነው ❓አለው፡፡ የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን አንተ የቆምህበት ሥፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን በፊቱ አውልቅ አለው፡፡ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ ይላል (ኢያሱ 5÷13-15)፡፡ ይህን ጥቅስ ልብ ብለን ብና…
🙏2❤1🥰1
Signed Yene💖፫💖
14 Jun 2025, 16:27 UTC754 views3 reactionsread 7 August 2026 💁♂አላመሰግንም ከየት የመጣ ነው ❓
••●◉ ✞ ◉●••
💁♂ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ሞላባት አሰምታም እንዲህ አለች አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው የጌታዬ እናት ወደኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆናል❓ የሰላምታሽ ድምጽ ወደኔ በመጣ ጊዜ ጽንሱ በማህጸኔ ዘሏልና ሉቃ ፩፥፳፰-፵፫
••●◉ ✞ ◉●••
🙌ልብ በሉ ሰላምታዋ መንፈስ ቅዱስን የሚሞላ ሴት እንዴት የተመረጠች ናት❓በመንፈስ ቅዱስ የተሞላች አረጋዊት ሴት አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የምትባል ሴት እንዴት አይነት መመረጥ ነው በኤልሳቤጥ ብቻ አይደለም መልአኩ ቅዱ…
❤3
Signed Yene💖፫💖
28 May 2025, 13:35 UTC757 viewsread 7 August 2026 Photo
💁♂️ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ስውሯ ማርያም🔊
የጉዞዉ ዋና መርሀ ግብር
👉ዝማሬ
👉ትምህርተ ወንጌል
👉ጉብኝት
👉የገዳሙን በረከት መቀበል
🗓የጉዞዉ ቀን ሰኔ 29 /2017
#የጉዞዉ ዋጋ 800 ብር
📍መነሻ ቦታ : ቃሊቲ፣ሜክሲኮ እና መገናኛ ጠዋት 12፡00 ሰዓት ላይ
በጉዞው ፓኬጆች
ትራንስፖርት 🚌
ምሳ 🥪
የጉብኝት ፓኬጅ🤼
የታሸገ ውሀ🥤
🎫 ትኬት የሚገኝበት 👇
☎️+251 91 020 6544
Signed Yene💖፫💖
18 Apr 2025, 17:30 UTC938 viewsread 7 August 2026 Photo
📖ስለ ዓለም መበዥት ልጇ የተሰቀለባት የመጀመሪያም የመጨረሻም እናት
••●◉ ✞ ◉●••
✍ከሄሮድስ የሞት አዋጅ ታስጥለው ዘንድ ዓመታትን ስለእሱ ስትል ወደ በረሃ ተሰዳለች።ወንበዴዎች እንዳይነጥቋት፤ ዘራፊዎች እንዳይወስዱባት እልፍ ቀናትን በሰቀቀን አሳልፋለች።30 ዓመታትን ክርስቶስ የሚለውን ስም ከእርሷ ውጪ ማንም አያውቅም።ልጇ ታምራትን ሳያደርግ፤ሙት ሳያነሳ፤ሽባ ሳይተረትር ሰማያዊ መናን እና ፅዋን ከሰማይ አውርዶ ሳይመግብ በልቧ ያነገሰችው ውድ ልጇና ጌታዋ ነው።ዓለምን በመዳፏ የያዘውን ልጇን በጀርባዋ ተሽክማ ይዛ የተሰደደቸውን፤ ከበረሃ ወንበዴ በሰቀቀን የጠበቀችውን ልጇን ጲላጦስ በበርባን ምትክ ሞት ፈረደበት።በስስት የምትመለከ…
Signed Yene💖፫💖
21 Jul 2024, 13:20 UTC≈1,520 viewsread 7 August 2026 ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
https://www.tiktok.com/@wondie12/video/7394058131342445830?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7386261005708314117
✝️✨✝️✨✝️✨✝️✨✝️✨✝️✨
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን 🙏
✝️✨✝️✨✝️✨✝️✨✝️✨✝️✨
══════◄✣••✥••✣►══════
🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @efr21 📖 @Geb19 ⛪️
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19 ⛪️
💒 @efr…
Signed Yene💖፫💖
14 Jul 2024, 08:10 UTC≈1,530 views0 reactionsread 7 August 2026 🔊ምስጢረ ሥላሴ በብሉይ ኪዳን📖
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙏እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር፡ እግዚአብሔርም አለ፡- ሰውን በመልካችን እንደምሳሌአችን እንፍጠር ዘፍ 1፥26 እዚህ ላይ እግዚአብሔርም አለ ሲል አንድነቱ፣ እንፍጠር ሲል ከአንድ በላይ መሆኑን ግሱ /ቃሉ/ ያመለክታል፡፡በዚህ ንባብ እግዚአብሔር የሚለው ሥመ አምላክ ከአንድ በላይ የሆኑ አካላትን የሚመለከት መሆኑን ከተረዳን ስለ ሥላሴ ኃልወት በሌሎች የቅዱሳት መጻሕፍት ከተጻፉት ምንባባት ጋር በማገናዘብ ይህ ጥቅስ ፍጹም አንድነቱንና ልዩ ሦስትነቱን እንደሚመሰክር በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡ በዚህ አንቀጽ እንፍጠር በመልካችን እንደምሳሌያችን የሚለው ንግግር የሦስት ተነጋጋሪዎች ነው እን…
Signed Yene💖፫💖
19 Aug 2023, 17:30 UTC≈1,880 views2 reactionsread 7 August 2026 ✍️ደብረታቦር
══════◄✣••✥••✣►══════
ደብረታቦር ማለት በወይራ የተከበበ ተራራ ማለት ። ደብረታቦር ከጌታ ከዘጠኙ በዓላት አንዱ ነው። ወእምድኅረ ስሱ መዋዕል ነሥኦሙ እግዚእ ኢየሱስ ለጴጥሮስ ወለ ያዕቆብ ወለዮሐንስ እኍሁ ወአዕረጎሙ ደብረ ነዋኃ እንተ ባሕቲቶሙ ማቴ 17:-1 ከስድስተኛው ቀን በኃላ ወደ ጴጥሮስ፣ዮሐንስ፣ያዕቆብን ወደ ተራራ አወጣቸው ማለት በፍልጵስዩስ ከተማ የሰውን ልጅ ሰው ማን ይልዋል ብሎ ጠይቋቸው ዮሐንስ ነው የሚሉህ አሉዉ ኤልያስ ነው የሚሉህ አሉዉ እናተስ ማን ነው ትሉኛላችሁ ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ የእግዚአብሔር አብ የባህይሪ ልጅ ነህ ቢለው በአንተ ቃል መሰረትነት ቅድስት ቤተ-ክርስቲያንን አንፃታለው።የሲኦል ደጆችም …
👍2
Signed ወ ҉ን ҉ደ ҉ ሰ ҉ ን ҉ 💖፫💖
16 Apr 2023, 04:25 UTC≈2,140 views3 reactionsread 7 August 2026 📖በትንሣኤሁ ቅድስት አግብኦ ለብእሲ ዳግመ ውስተ ገነት/ልዩ በሆነች መነሳቱ ሰውን እንደገና ወደ ገነትአገባው::ቅ/ ኤፍሬም
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ይግብሩ በዓለ ሰማያት ይግብሩ በዓለ ደመናት ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሃጺባ በደመ ክርስቶስ።ቅ/ያሬድ
••●◉ ✞ ◉●••
📖ሞቱን በሚመስል ሞት ከርሱ ጋር ከተባበርን ትንሳኤዉን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፡፡ ሮሜ 6፥5
••●◉ ✞ ◉●••
🙏በዓሉ የሰላም የደስታ የፍቅር የመተሳሰብ ይሁንልን ፡፡እግዚአብሔር በህመም የአልጋ ቁራኛ የሆኑትን ምህረትን ይላክላቸው፡፡የጎደለንን እግዚአብሔር ይሙላልን።እንደ ሰደድ እሳት በ…
👍3
Signed ወ ҉ን ҉ደ ҉ ሰ ҉ ን ҉ 💖፫💖
11 Feb 2023, 17:01 UTC≈2,500 views6 reactionsread 7 August 2026 🙏በመንፈስ ቅዱስ የሚመራውን የቅዱስ ሲኖዶስን ትዕዛዝ አከብራለሁ ::
••●◉ ✞ ◉●••
💁♂ነገር ግን መንግስት የገባውን ቃል እና የወሰነውን ዉሳኔ የማይፈጽም ከሆነ መንፈሳዊ ተጋድሏችን የሚቀጥል ይሆናል🙅♂
••●◉ ✞ ◉●••
✍️አንድ_መንበር
✍️አንድ_ፓትርያርክ!
ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት ።
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን ❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪…
👍6
Signed ወ ҉ን ҉ደ ҉ ሰ ҉ ን ҉ 💖፫💖
9 Feb 2023, 10:30 UTC≈2,330 views6 reactionsread 7 August 2026 ማቅ የለበሰች ከተማ
••●◉ ✞ ◉●••
ከተማው እጅግ ያስጨንቃል! ሆድ ያባባል! ያዘነ ከተማ እንዴት ያለ እንደሆነ በአይናችን አይተናል። እንደዚህ ያለው ነገርስ በየትኛው ዘመን በየትስ ሀገር ተከናውኖ ይሆን? ከሌላ ፕላኔት የመጡ ባእዳን እንግዳ ፍጡራን የሆንን እስኪመል ድረስ ግራ ያጋባል! ሁሉም በጸጥታ ይተማል ! ሾፌሮች፣ ረዳቾች ፣ የታክሲ ተራ አስከባሪዎች፣ የካፌ አስተናጋጅዎች ፣ የመንግሥት ሰተኞች ሁሉም ጥቁር ለብሰዋል ፤ በእጦቱ ምክንያት ጥቁር ልብስ የሌለው ፊቱ ጠቁሮ የአንገት መስቀሉን አውጥቶ ይጓዛል ፣ ጥቁር ልብስ የሌላቸው እህቶችና እናቶች ደግሞ ጥቁር ሻሽ ጣል አድርገዋል።
••●◉ ✞ ◉●••…
😢4👍2
Signed ወ ҉ን ҉ደ ҉ ሰ ҉ ን ҉ 💖፫💖
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Geb19. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.