6 Dec 2024, 12:04 UTC≈3,330 viewsread 26 September 2026 ስለ ውሃ ጥምቀት በሚገባ እንዳልተረዳን አስተውያለሁ ። እኔም የተማርኩት የውሃ ጥምቀት አፍአዊ ምስክርነት ብቻ በማድረግ ነው።ማለትም ለሰዎች ጌታን ተቀብለናል ለማለት በውሃ ጥምቀት እንደሚናሳይ እንደሚንመሰክር ብቻ ማሰባችን ስህተት ነው።
የውሃ ጥምቀት ልዩና ድንቅ የእግዚአብሔር መለኮታዊ አሰራር የሚፈጸምበት ነው። አዳማዊነት ተነቅሎ ፥ የክርስቶስ ማንነት የሚተከልበት ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ሳይለምን የሚያስታራቅ አስታራቂ ነው።pdf ገጽ 31 ይመልከቱ!
[የተጨመረ ነው በበፊቱ ጽሑፍ ላይ]
Signed Edilu
6 Dec 2024, 11:56 UTC≈3,130 viewsread 26 September 2026 1.ስለ ትምህርቴ ሥላሴ https://t.me/FistumTehadiso/799
2.ስለ ቅድሜ መከራ ንጥቀት https://t.me/FistumTehadiso/1259
3. ስለ መዳንና ቅድስና https://t.me/FistumTehadiso/1294
አንብቧት!
Signed Edilu
24 Aug 2024, 04:20 UTC≈3,110 viewsread 26 September 2026 Photo
🌱ትምህርቴ ሦስትነት በአንድነት፣
🌱የቤተክርስቲያን ቅድሜ መከራ ንጥቀት አስተምህሮ በቃለ እግዚአብሔር ስመዘን፣
🌱ኢየሱስ ክርስቶስ ሳይለምን የሚያስታርቅ አስታራቂ ፣
እስካሁን እነዚህን መጻሕፍትን [በpdf] አቅርቤያለሁ ፦ https://t.me/FistumTehadiso ። ስለዚህም ነገር እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ ። በትንሿ መክሊቴ ለማትረፍ ተጣጥርያለሁ። የነገውን ጌታ ያውቃል ።
Signed Edilu
23 Aug 2024, 06:52 UTC≈3,420 viewsread 26 September 2026 #መሰዊያ_ታቦት_አለን|| “መሠዊያ አለን፥ ከእርሱም ሊበሉ ድንኳኒቱን የሚያገለግሉ መብት የላቸውም።” ዕብ 13፥10
የብሉይ መቅደስ አገልግሎት ሙሉበሙሉ ዋናው አካሉ እስኪመጣ ድረስ የሚያገለግል ስለኾነ፣ ለሐዲስ አገልግሎት ስፍሯን ለቋል፤ አገልግሎቱን ጨርሷል ። ጌታችንም ሊቀ ካህናት እንደመኾኑ መጠን መሰዋዕቱን በምድር ባለችው መቅደስ [ድንኳን] አላቀረበም ። ራሱ በሠራት በሰማያዊት መቅደስ ስለኛ መስዋዕቱን አቅርቧል ። በዚህም የብሉይን አገልግሎት አስረጅቶ የሐዲስ ኪዳንን አገልግሎት በሰማይ #በይፋ አስ|ጀምሯል ። ዕብ 8፤9።
ጌታችን በሰማይ መቅደስ ባስጀመረው አገልግሎት ከቀደሙት በሚልቅና በሚሻል መልኩ ፣በአንድ ጊዜ ባቀረበው መስዋዕት ብቻ እስከዛሬ ያገ…
Signed Edilu
22 Aug 2024, 18:31 UTC≈1,830 viewsread 26 September 2026 በጣም ኮርቼባችኋለሁ። እናንተ የብዙዎች ተስፋ የሚታለመልሙ ብርቱዎች ናችሁ። ለብዙዎችም በረከቶች ናችሁ። የብዙዎች እንግልት ታስወግዳላችሁ ።የብዙዎችን ጉድለት ታሞላላችሁ፤ ትሸፍናላችሁ።
#እራሳችሁ በዚህ ልክ በመሥራታችሁ ተደነቅሁ ፤ የቤተክርስቲያን በረከት ናችሁ። እንግዲህ በርቱ፤አትታከቱ 👐
***
https://youtube.com/watch?v=s8aOzzREGoA&si=THaOdxU09GR69Kha&fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR2PfFGuapXG9VqtwMJBJMEHcSjy2UawULS-8wSMBZ6UTyZyZvUuZS7sr98_aem_mn21kIoV6s5ZR3AXSZNWuQ
Signed Edilu
14 Aug 2024, 19:31 UTC≈3,380 viewsread 26 September 2026 File
"የክርስቶስ ሥራ አለመረዳት በድንዛዜ እንዲኖርን ያደረገኝም ስለኾነ፣ ሌሎችን እንደኔ ለነበሩት ለማገዝ የአቅሜን ለማስረዳት ተጣጥሪያለሁ። ..
በዚህ ጽሑፍ ... ስለተቀበልነው ሕይወት እንደሚገባን በኃላፊነት መመላለስ እንደሚገባንና ከኃላፊነት የጎደለውን በማድረግ ከሕይወት መጉደል እንዳይመጣ ግንዛቤ ለመስጠት ጥረት ተደርጓል ። በክርስቶስ ለመኖር እግዚአብሔር ያደረገልንን የሰጠውን ስጦታ ለማስረዳት ብሎም #ስለ_ቅዱስ_ቁርባን ብዥታን የሚያጠራ ቀጥተኛ ትምህርት ለማቅረብ ተሞክሯል ።" [ኢየሱስ ክርስቶስ ሳይለምን የሚያስታርቅ አስታራቂ፤ ከመጽሐፉ መግቢያው የተወሰደ!]
Signed Edilu
13 Aug 2024, 13:49 UTC≈3,140 viewsread 26 September 2026 በትዕግሥት እንዲታነቡ በታላቅ ትህትና እጠይቃችኋለሁ። አንዳንድ ብዥታዎችን ለማጥራት ስለ ቅዱስ ቁርባን [ ] በቀጣይ አቀርባለሁ..
""በጌታ እራት ጊዜ መለኮታዊ አሠራር [መለኮታዊ ንክኪ] እንዳለው እንወቅ። የጌታ እራት እንደ ተዝካር ያለ መታሰቢያ አይደለም ። ቅዱስ ቁርባን ሰማያዊ መንፈሳዊ መብል ነው። በምንበላው እንጀራና በምንጠጣው ጽዋ የወልድ መለኮት ያርፍበታል፤ ለሰውነታችንም የሚያስፈልገውን ኹሉ ይሰጣል ።"
...
Signed Edilu
10 Aug 2024, 17:26 UTC≈3,000 viewsread 26 September 2026 ከማቴዎስ ወንጌል ጥናቴ [33]
“ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?” ማቴዎስ 6፥25፣26-34 ።
በዚህ ክፍል ላይ ጌታችን በተራራው ለተሰበሰቡት ሕዝብ፣ የሚበልጠውን ነገር እንዲያውቁ ትምህርትን ይሰጣል ። ደግሞም ስለ ፍላጎታችንም እዚሁ የሚቀረን ነገር ለማግኘት እንዳይኾን ያስገነዝበናል ። የሰማዩ ወፎች ለነገ መብል በመሰብሰብ በመጠመድ ባይጨነቁም እንኳ እንደሚመግባቸው እና የሚጠፋውን የሜዳ አበባ ከንጉሥ በላይ እንደሚያለብስ፣ እኛን ይልቁንም ከእነዚህ ፍጥረታት ለሚንሻል፣ የሚበልጠውን ነገር አብልጦ ልያደርግ' እንደሚችል ያስረዳል ። ይገር…
Signed Edilu
9 Aug 2024, 12:56 UTC≈2,900 viewsread 26 September 2026 Photo
የተከዳው አገልጋይ ሊቀ ካህናት!
ጌታችንን በሰማይ ባለች በእጅ ባልተሠራች፣ ራሱ በተከላት በመንፈሳዊት መቅደስ "የሚያገለግል ሊቀ ካህናት ነው፣ ስለእኛ የቆመ የተቀመጠ የኛ ወክል ነው" ስንል ከክብሩ ዝቅ አድርጋችኋል፣ እርሱ ለመፍረድ የተቀመጠ እንጂ የሚያገለግል ሊቀ ካህናት አይደለም ይላሉ። በእርግጥም ጌታችን በመስቀል ላይ አንዴ ባቀረበው መስዋዕት፣ማንም ስለራሱ የቀረበ መስዋዕት አድርጎ ብቀበል በእምነት ፈውስን የሚሰጥ እንደኾነ እንጂ ልመና በእርሱ ዘንድ አኹን የለም። አብ በእርሱ በኩል የሚመጡትን ኹሉ፣ ስለከፈለው ዋጋ በቂነት ቅቡልነት ስለሰጠው እንዲያው ይምራል። በክርስቶስ ያለቀው ሥራ "ስለነ ነው" በማለት በማመን ብቻ ለተቀበለው ሰው የክርስቶስ ሥራ …
Signed Edilu
9 Aug 2024, 07:05 UTC≈2,360 viewsread 26 September 2026 ድካም
በጌታ ለኾነ አማኝ ሥጋው ከኃጢአት በሂደት እየነፃ ይሄዳል ። ሥጋ ለጽድቅ ሕያው በመኾን በአማኙ ሕይወት መንፈሳዊነት እንዲገለጥ ያደርጋል ። በዚህ ሂደት ላይ አማኝ በአንድም በተለያየ ሁኔታዎች በተለያየ ጊዜያት፣ የሌለ የሚመስለው ሥጋዊ ባሕርይ ስገለጥ ድካም ይባላል ። የአማኙ ሥጋዊነት የተገለጠበት ኹኔታ ድካሙን ጉድለቱን ስያሳይ፤ ስህተት ልባልም ይችላል ። ይኽንንም ጉድለት ካጋጠመው ነገር በመረዳት፣ ያለበትን መንፈሳዊ ሁኔታ[ደረጃ] በማስተዋል የሚያስፈልገውን ጸጋ በመለመን ነፃ መኾን ይቻላል። በሕይወት እስካለን ድረስ ድካም አለ። ለዚህም ነው ፍጹም የኾነውን ነገር ለመልበስ የሚንቃትተው። ሥጋችን ኹሌም በባሕሪው ፍጹም ስላይደለ ። የማንም ።
ይኹን …
Signed Edilu
8 Aug 2024, 16:37 UTC≈1,980 viewsread 26 September 2026 Video
"ጠበል ፈለቀ" በማለት በውሸት አጥማቂ ነኝ በማለት የሚሠሩት መኖራቸውን እኚህ አባት ይገልፃሉ ። ልክ ጴንጤዎች ጋ ባለራዕይ ነቢይ ሐዋርያ በማለት ኑሮ ስከብዳቸው የራሳቸውን አጥቢያዎችን የሚከፍቱ ግለሰቦች እንዳሉ።
ሃሰተኞች እንደ እምነታቸው ደካማ ጎን መሥራታቸው ይደንቃል ። መጠንቀቁ መመርመሩ አይከፋም!
Signed Edilu
7 Aug 2024, 01:03 UTC≈2,100 viewsread 26 September 2026 Photo
በስምንት መቶ ሜትር የብር መዳሊያ ለኢትዮጵያ ያስገኘችው ጀግናው አትሌት አነጋጋሪ ኾናለች። ኢየሱስ በተሰደበበት ኢየሱስ ጌታ ነው ማለቷ፣ በኢየሱስ መሰደብ ያዘኑትን አስደስቶአቸዋል። በሌላ በኲል ደግሞ ከለመዱት [ስዕለ አድኖ] ውጪ የኾነውን ስላሳየች አብዘኛውን የተዋሕዶ አማኞችን አላስደሰታቸውም ። ኢየሱስ ጌታ ነው ማለቷ ግን እንዲህ ምቾት መንሳቱ ይደንቃል ። ኾኖም አትሌቷ ከዚህ በፊት በሱራፌል ደምሴ "እግርሽ መለኮት ተቀላቅሎበታል ወርቅ፣ ዋንጫ ታመጭያለሽ" በማለት ዘይት በማፍሰሱና አትሌቷም ኢየሱስ ጌታ ነው የሚለውን የተመለከቱት አማኞች ከደስታቸው ባሻገር ማዘናቸው አልቀረም ።
*በዚህ ውድድር ላይ ኾነ በስፖርት ባጠቃላይ ማንም ሰው በትጋቱ ልክ ዋጋውን …
Signed Edilu
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @FistumTehadiso. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.