1 Feb 2024, 20:57 UTC≈1,130 views10 reactionsread 8 August 2026 Photo
የፌደራል መንግስት ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ጥፋተኛ ናቸው ባለቸው ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ‼️
የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ በሰሜኑ ጦርነት ተጠያቂ መሆን ያለባቸውን አካላትን ተጠያቂ ማድረጉን ገልጿል።
በፕሪቶሪያው ስምምነቱ መሠረት በህወሓት በኩል ሲዋጉ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ህይወታቸው መመለስ እንደሚገባቸው አስታውቋል፡፡
የፌደራል መንግስት ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኃላ ለትግራይ ክልል ለትምህርት ለጤና፣ ለመንገድ ለዘላቂ ግቦች ማከናወኛን ጨምሮ ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚሆን በአጠቃለይ 37 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን በመግለጫው አስታውቋል።
https://t.me/FDREservice
👍7❤3
30 Dec 2023, 10:46 UTC≈1,220 views4 reactionsread 8 August 2026 መንግሥት ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በሁሉም ክልሎች ነፍጥ ላነገቡ ኃይሎች የሰላም በር መከፈቱ በበርካታ አካባቢዎች ሰላም እንዲፈጠርና ሕዝቡ ፊቱን ወደ ልማት እንዲያዞር ማድረጉን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ገለጹ።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ ያጋጠመውን ድርቅ በተመለከተ ከሰሞኑ የሰጠው መግለጫ ፈፅሞ የተሳሳተ መሆኑንም ገልፀዋል።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
ከሰላምና ደኅንነት አኳያ በየጊዜው የሚነሱና ያልተረጋጋ ድባብ ለመፍጠር የሚደረጉ ሙከራዎች ለሀገረ- መንግሥት ግንባታ ሂደት ተግዳሮቶች ሆነው መቀጠላቸውን አንስተዋል።
መን…
👍4
30 Dec 2023, 10:32 UTC497 views2 reactionsread 8 August 2026 Photo
መንግሥት የሠላም በሮችን አሁንም ክፍት እንዳደረገ ይገኛል‼️
🗣ዶ/ር ለገሰ ቱሉ
በአማራ ክልል መንግሥት በወሰዳቸው እርምጃዎች በአሁኑ ወቅት በክልሉ አንጻራዊ ሠላም ማረጋገጥ መቻሉን የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ።
በክልሉ የክልሉን ሕልውና ለመጠበቅ ሲባል አዲስ አመራር መመደቡን እና አዲስ አሰራር መዘርጋቱንም የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ተናግረዋል።
በክልሉ የሠላም ጥሪ በማወጅ ሠላምን ለማስጠበቅ መንግሥት በሰራው ስራ በርካታ መሳሪያ የታጠቁ የሽብር ቡድሩ አባላት ጥሪውን ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ስልጠና መግባታቸውንም ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።
መንግሥት የሠላም በሮችን አሁንም ክፍት እንዳደረገ ይገኛል ያሉት ሚኒስትሩ…
👍2
10 Dec 2023, 05:38 UTC532 views3 reactionsread 8 August 2026 በኅብረት የጠነከረች፣ በብዝኃነት የተዋበች ኅብረብሔራዊት ሀገር - ኢትዮጵያ!
*******
የዘንድሮው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን “ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ18ኛ ጊዜ ተከብሯል፡፡
መላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
ኢትዮጵያችን መልከ ብዙ ናት፡፡ ሀገራችን ብዝኃነት ያደመቃት፤ ኅብረት ያጠነከራት ኅብረብሔራዊት ሀገር ናት፡፡ ብዝኃነታችን መገለጫችን፤ አንድነታችንም የጥንካሬያችን ምንጭ ነው፡፡ በየዘመኑ ያጋጠሙንን ሀገራዊ ፈተናዎችን በአንድነት ቆማን መሻገር መቻላችን አንድነታችን የጥንካሬያችን መንጭ ስለመሆኑ በቂ ማስረጃ ነው፡፡ ይህ…
👍3
4 Nov 2023, 09:36 UTC615 views4 reactionsread 8 August 2026 ጥቅምት 24፤ መቼም የትም አይደገምም! - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሀገሩ ክብር የሚከፍለው መስዋዕትነት በተግባር ከታየባቸው ቀናት መካከል ጥቅምት 24፣ 2013 ዓ.ም አንዱ ነው፡፡ በዕለቱ በመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ የደረሰው ጥቃት በሀገራችን ታሪክ ጥቍር ጠባሳ አሳርፎ ያለፈ ክስተት ነው፡፡ ይህ በሠራዊቱ አባላት ላይ የተፈጸመዉ ጥቃት መቼም ቢኾን፣ በየትኛውም ቦታ ሊደገም የማይገባውና ታሪክ የማይረሳዉ አስከፊ ድርጊት ነው፡፡
በሠራዊታችን ላይ የተፈጸመዉ ጥቃት ሀገራችንን ከፍተኛ ዋጋ ያስከፈለ፣ ወደ አውዳሚ ጦርነት ጎትቶ ያስገባንና ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ያደረሰ በመኾኑ ሊረሳ የማይችልና ሊደገም የማይገባ…
👍3❤1
4 Nov 2023, 09:36 UTC399 viewsread 8 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
26 Oct 2023, 06:56 UTC508 views2 reactionsread 8 August 2026 ኢትዮጵያ ፈተናን ወደ ድል የሚቀይር የአሸናፊ ሠራዊት ባለቤት ናት! ፡- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
*****
መላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለ116ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን አደረሳችሁ!
በዛሬው ዕለት 116ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን በሀገርአቀፍ ደረጃ እየተከበረ ነው፡፡ ጥቅምት 15 ቀን 1900 ዓ/ም በኢትዮጵያ ታሪክ ልዩ ስፍራ አለው፡፡ ዕለቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተቋማዊ መልክ ተላብሶ በሚኒስቴር ደረጃ የተመሰረተበት ቀን ነው፡፡ ኢትዮጵያ 116 ዓመታትን ያስቆጠረ፤ በትውልድ ቅብብሎሽ ፀንቶ የቆየና ሀገርን ያፀና የመከላከያ ተቋም ባለቤት መሆኗ ዛሬ ላይ ለጠንካራ ተቋማት ግንባታ ትልማችን እንደ ወረት የሚወሰድ በጎ የታሪካችን አካል በመሆኑ እ…
👍2
26 Oct 2023, 06:54 UTC392 viewsread 8 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
11 Jun 2023, 06:10 UTC≈1,850 views3 reactionsread 8 August 2026 “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ፈተናዎችን በመቋቋም አዎንታዊ እድገት ማስመዝገቡን ቀጥሏል”-ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሁሉንም ዓይነት ጫናዎች በመቋቋም አዎንታዊ ዕድገት ማስመዝገብ መቀጠሉንና ኢኮኖሚውን ከዳግም ስብራት ወደ ላቀ የእድገት ምህዋርነት በመቀየር በ2023 ዓ.ም ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት 156 ነጥብ 08 ቢሊዮን ዶላር እንደሚጠበቅ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡ግጭት የዜጎችን ደህንነት አደጋ ላይ እንዳይጥል ከሂሳብ ማወራረድ የጥላቻ መንፈስ ለመውጣት አቅጣጫ ተቀምጦ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ…
👍3
11 Jun 2023, 06:02 UTC820 views0 reactionsread 8 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
6 Jun 2023, 10:32 UTC≈1,220 viewsread 8 August 2026 Photo
ሂዩማን ራይትስ ዎች ላወጣው ሪፖርት ከኢፌዴሪ መንግስት የተሰጠ ምላሽ
https://t.me/FDREservice
15 May 2023, 04:09 UTC644 views4 reactionsread 8 August 2026 በወቅታዊ ጉዳዮች የተሰጠ መግለጫ
ሀገራችን ኢትዮጵያ በለውጥ ሂደት ውስጥ ከገባች አምስት አመታት ተቆጥረዋል። በዚህ የለውጥ ዓመታት ይሆናሉ ተብሎ ያልታሰቡ በርካታ ድሎች ተመዝበዋል። በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካ ዘርፎች አገራችንን ወደፊት ሊያስፈነጥሩ የሚችሉ በአለት ላይ የተገነቡ መሰረቶች ተጥሏል። ሆኖም ግን የተገኙ ስኬቶች አልጋ በአልጋ በሆነ ሁኔታ ውስጥ አልተመዘገቡም። ይልቁንም በበርካታ ፈተናዎችን በመሻገር የተገኙ ውጤቶች ናቸው።
ለውጡ ገና ከመነሻው እንዲጨናገፍ መጠነ ሰፊ ሴራዎች ተሸርበው፣ ለውጡን ለማጠልሸትና የለውጥ አመራሩን ተስፋ ለማስቆረጥ ጥቃቶች ተሰንዝሯል፤ የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ተከፍቷል። የብርቅዬ አመራሮች እና ዜጎች ህይወት ተቀጥፏ…
👍2🎉1🕊1
Showing the 12 most recent of 13 posts we hold for @FDREservice. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.