6 Jan 2022, 04:21 UTC≈1,020 viewsread 9 August 2026 Photo
ልጅቷ የቤታቸው በር ይንኳኳና ስትከፍተው ፍቅረኛዋ ነው ፥😳😳ግን አባቷ በቅርብ እርቀት ስለነበሩ በስነ ስርአት ሰላም አላለችውም ወዲያውኑም ልጁ እንዳይቀባጥር በኮድ
# እሷ ፦ ሀይ ሰላም ነው አባቴ ቤት ነው የሚለውን የበውቀቱ ስዩም መፅሐፍን ልትወስድ መጥተህ ነው ?
# ልጁ ወዲያው ይነቃና እረ እኔስ የበአሉ ግርማን ታዲያ የት ልጠብቅሽ የሚለውን መፅሐፍ ልወስድ ነበር።
# እሷ ውይ እሱን መፅሐፍ እንኳን ቶሎ አላገኘውም ባይሆን የአዳም ረታን ከማንጎ ጥላ ስር "የሚለውን መፅሐፍ ልስጥህ
# ልጁ ጥሩ እዛው እንደደረስኩ እደውላለሁ የሚለውን መፅሐፍም እንዳትረሺው
# እሷ እረ ምንም ችግር የለም የይስማክ ወርቁን ቶሎ መጣለሁ የሚለውንም ይዤልህ መጣለሁ ።
…
Signed Yidnekachew Girma
2 Dec 2021, 04:06 UTC793 viewsread 9 August 2026 የዛሬው ሌሊት ስም
"አይጥ ስትጠግብ ስታበዛ ሩጫ
ሄዳ ታሸታለች የድመት አፍንጫ
ሲባል የነበረው እስከነ ተረቱ
ባንቺ ላይ ደረሰ በክልፍልፊቱ፤"
ተብሎ ይጠራል(ከ.ሚካኤል)
Signed Yidnekachew Girma
2 Dec 2021, 04:06 UTC759 viewsread 9 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed Yidnekachew Girma
1 Dec 2021, 17:30 UTC727 viewsread 9 August 2026 Photo
ተፃፈ በጌታቼው ረዳ!
//...........................//
ጋሸና ላይ ሆኖ ይታያል መቀሌ:
ተቀብሬ ቀረሁ አለመታደሌ::
ስዋልል ስፏልል
ስፎክር ከርሜ
ይሄው ቀረሁልሽ
መከነብኝ ህልሜ::
#ለአዲስ_አበባ_መሆኑ ነው
Signed Yidnekachew Girma
30 Nov 2021, 01:42 UTC648 viewsread 9 August 2026 ላጤ ተዋረደ ተናቀ ተረገጠ ተሽሟጠጠ ወገን 😥😥
ላጤ ትስእር✊!
እኚያ የትልቅ ፍንዳታ ተንከሲስ አከራዬ ገና በጠዋቱ እየጦለቡኝ ነው
"ዋትሳብ ተከራዬ..."
"ኧረ መአት ይሳቦት እቴ.."
"ምናልክ አንት ጢንዚዛ..."
"ኧረ ወደዛ ... ይልቅ የሽንት ቤት ቁልፍ..."
"ሊመጠጥ ነው ፖፖህ ላይ ተጠቀም..."
"ባለፈው ሳምንት አይደል እንዴ የተመጠጠው?.."
"የዝጋሉ ሽንትቤት ወርቅ መሰለህ እንዴ የሚቀበርበት!...ሞላ...በቃ ጥቅጥቅ ብሎ ሞላ ...ዩዝ ኤንድ ስሩአችሁን ተጠቀሙአ..." ኧረ እኚህ ሞት እምቢ አፈሉ!..
"ምንድነው እሱ ደሞ?"
"ፍሬሽ ላጤ ነሽ መሠለኝ....ፌስታልና ሀይላንድ አታርፍም?..."
"እ..."
"አጣድፎሻል መሠለኝ ደፈነብሽ...!"
"ኧ…
Signed Yidnekachew Girma
17 Nov 2021, 21:24 UTC633 viewsread 9 August 2026 የሪህ በሽታ ምልክት እና መፍትሄዎቹ
#Gout
ሪህ ምንድንነው?
➡️ሪህ በመገጣጠሚያዎች ውስጥ በተከማቸ የዩሪክ አሲድ ክሪስታሎች የሚፈጠር የአርትራይተስ አይነት ነው። ይህም በአጥንት መገጣጠሚያዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ህመም የሚያስከትል የህመም ዓይነት ነው፡፡
ሪህ በአንድ ወይም በብዙ መገጣጠሚያዎች ላይ ህመም እና እብጠት ያስከትላል. በተለምዶ በትልቁ ጣት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ነገር ግን ጉልበት ቁርጭምጭሚት እግር እጅ የእጅ አንጓ እና ክንድ ጨምሮ በሌሎች መገጣጠሚያዎች ውስጥም ይገኛል.
ዩሪክ አሲድ በሰውነት ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኝ ንጥረ ቅመም ሲሆን ይህ ንጥረ ቅመም በሰውነት ውስጥ በተወሰነ መጠን መገኘት ያለበትና በሽንት በኩል የሚወገድ ነው፡፡ ሆኖም…
Signed Yidnekachew Girma
6 Nov 2021, 04:12 UTC599 viewsread 9 August 2026 ከማን በልጠህ ነው- ከማን ተሽለህ
ኢትዮጵያ ትውደም- ብለህ የመጣህ
አፋር፣ አማራው ኦሮሞ፣ ደቡብ
ከመጤፍ ቆጥረህ- የኢትዮጵያን ሕዝብ
ልታንበረክክ- ከያዝክ ግብግብ
ይሄን ጠጣና- አንተው አሸልብ፡፡
የእናት አገሬን- ክብሯን የነካ
አይድንምና-
በግብጽ ድጋፍ- በእነ አሜሪካ
እጣ ፈንታህን- ሞትህን እንካ፡፡
ባንዳ አስገብሮት- አገር ከሚናቅ
ባንተ ሕልፈት ላይ
AGOWA ከስሞ- ዓድዋ ይድመቅ፡፡
Signed Yidnekachew Girma
28 Oct 2021, 02:15 UTC599 viewsread 9 August 2026 #ናፈቀኝ_አሁንስ 🚶♂
የሰው ዋጋ ወርዶ፣ ኑሮ ሳይወደድ
በዘር በጎጥ ሀሳብ ፣ ማንም ሳይታረድ
የግፍ በደል ግንዱ ፣ከስሩ ተነቅሎ
የፍትህ ባንዲራ ፣ከፍ ብሎ ተሰቅሎ
ሀገሩን የሚሸጥ ፣ ለሆዱ የሚያድር
ጠላት ባንዳ ጠፍቶ፣ከእምዬ ምድር
ከተራ መግለጫ ፣ፖለቲካው አልፎ
ያጠላብን ሀዘን ፣ ፅልመቱ ተገፎ
ገደለው ሰቀለው ፣ ቆረጠው ፈለጠው
አንደዜ ተያዘ ፣ አንደዜ አመለጠው
ከሚል ሽብር ወሬ ፣ጆሯችን እርቆ
ትንሹም ትልቁም ፣ ያላሳብ ቦርቆ
ሀዘን ዋይታ እሪታ ፣ሳይሰማ መርዶ
ማንም ሳይሰቃይ፣ ከቀየው ተሰዶ
የሚስኪን ደም እንባ፣ በከንቱ ሳይፈስስ
መች ነው የምኖረው ናፈቀኝ አሁንስ
#ሼን ✍
Signed Yidnekachew Girma
28 Oct 2021, 02:13 UTC577 viewsread 9 August 2026 #እራሴን_ታዘብኩት 🤔
ሳቅና ደስታውን ከሰው በመጠበቅ
ከብሶት ጓዳው ውስጥ ተክዞ ሲደበቅ
ሲያጨበጭቡ ከፍ ሲተቹት ደግሞ ዝቅ
እያለ ከላይ ታች እንዲሁ ሲዋዥቅ
እራሴን ታዘብኩት ••••
ባለፈ ትናንቱ ዛሬው ላይ ሲበሳጭ
የዃሊት በማሰብ ከራሱ ጋር ሲጋጭ
መተው እየቻለ መወሰን ሲያቅተው
መሄድ እያለበት እዛው ቁሞ ሳየው
እራሴን ታዘብኩት ••••
ምንም ለማይፈይድ እርባና ቢስ ነገር
በከንቱ ሲደክም ቆጥሮ እንደ ቁምነገር
የሂዎት ገፁ ላይ አንዳች ሳይጨምር
አመት እያሰላ ልደቱን ሲጨፍር
እራሴን ታዘብኩት ••••
መጥቀም እየቻለ ለመጉዳት ሲዳዳ
በማስታረቅ መድረክ ለፀብ ሲሰናዳ
ከእግር እስከራሱ በጥፋት ተሞልቶ
ሌላው ላይ ሲፈርድ የራሱን ዘንግቶ
እራሴን ታዘብኩ…
Signed Yidnekachew Girma
11 Oct 2021, 03:24 UTC526 viewsread 9 August 2026 "A little about Gyni"
የአራተኛ አመት ተማሪዎች እያለን ለመጀመሪያ ጊዜ በምጥ ላይ ያለች እናት ስመለከት የተሰማኝን ስሜት ሁሌም አስታውሰዋለው፡፡ በሕክምናው ቋንቋ second stage (ህፃኑ ከእናቱ ማህፀን የሚወጣበት) የሚባለው የምጥ ደረጃ ላይ የነበረች እናት ነበረች፡፡
በፍፁም የማላውቀው ሕመም ቢሆንም እስከ አጥንቶቼ ድረስ ዘልቆ ተሰምቶኛል፡፡ ከአመታት በፊት በእናቶቻችን ላይ የፈጠርነው ሕመም ተሰምቶን ይሁን ነግ በኔ ብለን እንጃ እኔና አብረውኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዩ ሴት ጓደኞቼ እንዳለቀስን አስታውሳለው፡፡ የእናቶቻችን ጉዳት ለይቅርታም ለምስጋናም የማይመጥን ነው፡፡
የዛን ዕለት ማታ ይህቺን ስንኝ ለእናቴ ቋጠርኩ፡፡
እንደ ዘበት ኖሬ …
Signed Yidnekachew Girma
10 Oct 2021, 03:57 UTC440 viewsread 9 August 2026 Photo
"እግረኛ ነው ድሀ" ማለትሽን ሰምቼ፣
ይቻትልሽ አቶዝ እንዳቅሜ ገዝቼ፤
የሰው ልክ ይከብዳል አይሆን በግምት፣
ነይ እስቲ ልለካሽ? ነድቼው ልሙት!!!
Signed Yidnekachew Girma
8 Oct 2021, 17:40 UTC445 viewsread 9 August 2026 Photo
✍ #ራስ ምታት ያስቸግሮታል? እነዚህን ምግቦች ቢሞክሩስ?
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥
⏩ #የአበባ ጎመን፦ የነርቭ ስርዓትን ፣ ጡንቻንና ደም ግፊትን በማስተካከል የራስ ምታትን ይቀንሳል
⏩ #ወተት፣ ስኳር ድንች፦ በቫይታሚን ቢ2 ይዘታቸዉ የነርቭ እና ቀይ የደም ሴሎችን እድገትና በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራሉ
⏩ #ገብስ ፦ በቫይታሚን ቢ6 ይዘቱ ሄሞግሎቢንን (የሰዉነት ኦክስጂን ተሸካሚ ንጥረ ነገር) በመገንባት የነርቭ ስርዓት እንዲገነባ እና በሽታ ለመከላከል ያግዛል
⏩ #የዶሮ ስጋ፦ በያዘዉ ቪታሚን ቢ3 የደም ዝዉዉርን በማፋጠን የደም ቧንቧን ክፍት ያደርጋል፣ በወር አበባ ጊዜ ለሚከሰት ራስ ምታት፣ ለድብርት እንዲሁ…
Signed Yidnekachew Girma
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @EthioBooksStore. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.