14 May 2026, 06:06 UTC547 views5 reactionsread 7 August 2026 “ያየን የለም እንጂ ያላየነው የለም”
(በእውቀቱ ስዩም)
ልጅ እያለን አንድ በሰፈራችን የታወቀ፥ ገዜ የተባለ ተወዛዋዥ ነበር፤ የሆነ ጊዜ ላይ የመቶ ሀያ ፕሮግራም አዘጋጆች ደብረማርቆስ መጥተው፥ ስለ ክልላችን የኪነጥበብ እንቅስቃሴ የሚዘግብ ፕሮግራም ሰሩ፤ በዚያ ፕሮግራም ውስጥ ። ገዜ ለአምስት ሰከንድ አካባቢ ወዝወዝ ሲል ይታያል ፤ ብልጭ ብሎ ይጠፋል ብንለው ይሻላል፤
ይቺም ዝና ሆና ፥ ገዜ ሊጠቀምባት ፈለገ፤ በማግስቱ፥ የከተማችን አንደኛ ቆንጆ ከገበያ ስትመለስ አስቁሞ ሊጀነጅናት ሞከረ፤ ፊትም ጀርባም ነሳችው፤
“አላወቅሽኝም ?”
“አላወቅሁህም” አለች ልጂቱ፤
ገዜ ቀብረር እያለ እንዲህ አለ፤
“ በሰፈራችሁ ቴሌቪዠን የለም መሰል “…
❤3👍2
12 May 2026, 15:10 UTC476 viewsread 7 August 2026 https://t.me/perspective_in_poetry
12 May 2026, 12:08 UTC483 viewsread 7 August 2026 Forwarded from @perspective_in_poetryFile
File, posted without a caption
12 Apr 2026, 10:48 UTC856 views10 reactionsread 7 August 2026 በጆሮው ከሰካው ኤርፎን ከሚመጣው ሙዚቃ ጋር እኩል ለመሄድ ሲል ድምፁን ከፍ አርጎ እየዘፈነ እንደሆነ ያወቀው አጠገቡ የተቀመጠችው ልጅ ዞር ብላ ስታየው ነው። ባደረገው ነገር አፍሮ የሚሰማውን ሙዚቃ ድምጽ ቀነሰና እይታውን ወደመስኮቱ መለሰ። ከመገናኛ የአውቶብስ ተራ ታክሲን ይዞ ገና መንገድ ከመጀመሩ ነው ዝናቡ መጣል የጀመረው። ውጭ ያለው ዝናብ ባልደረስኩ ፤ መንገድ ተዘጋግቶ እዚሁ በሆንኩ አሰኘው። ደግሞ ሲወጣ አየሩ ጥሩ ስለነበረ ያደረገው ጉርድ ሸሚዝ ነው። እንኳን ከታክሲ ወርዶ እንዲሁም ብርዱ እያንዘፈዘፈው ነው። ስልኩ ላይ ይሰማ የነበረውን ሙዚቃ ሲያቆም ታክሲ ውስጥ የተከፈተው ሬዲዮ ከዝናቡ ጋር እየታገለ ሲመጣ ተሰማው...
።።።።።።።።።።።።።።።።።…
❤9🕊1
9 Apr 2026, 13:44 UTC741 viewsread 7 August 2026 "ይቅርታ...!
ብዙ አለመውደዴ እና አለመብሰሌ ነው እንደዛ እየፈለግሽኝ ሳልጠነቀቅልሽ፥ ስሜትሽን ሳላስታምመው ችላ ያልኩሽ" አልኳት።
"ጥሩ ልጅ እንደሆንሽ ግዜ አሳይቶኛል፣ መልካም ልጅ እንደሆንሽ የሆንሽልኝ ነገሮች በግዜ ብዛት የበለጠ ተገልጦልኛል " አልኳት።
ትንሽ በስሱ ፈገግ ብላ...
" እንኳን ተውከኝ..! ብዙ ቀን አግኝቼ እንኳን ተውከኝ ማለት ፈልጌ ነበር ... መበሻሸቅ ይመስልብኛል ብዬ ነው የተውኩት።"
"ስለተውከኝ ... ስለገፋኸኝ ...ከመጤፍ ስላልቆጠርከኝ ... ስንት ቀን እያሰብኩ ሃሴት ተሰምቶኝ ያውቃል።
ያሁኑን ባሌን በየት በኩል አገኘው ነበር? አንተ ባትገፋኝ፤ ብዬ መሰለኝ። መገፋትን ማጣጣሜ ይሆናል ፍቅር በዚህ መጠን እንዲገ…
9 Apr 2026, 13:34 UTC665 views6 reactionsread 7 August 2026 ዐይኔ አረዘረዘ ፤
ልቤም ተሰበረ ፤
አንጀቴም ሆድ ባሰው ፤
ገና ሳይወለድ እንዴት ያረጃል ሰው !?
By Tewodros kassa
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
📝#share📖
@Esubealem
@Esubealem
❤6
9 Apr 2026, 13:34 UTC652 viewsread 7 August 2026 እባክህ
--------------------------------------
እባክህ አምላኬ?. . .
የመጣ የሄደው፣
ከሚበጠብጠኝ
እኔ የምገዛት፣
ሐገር ሰርተህ ስጠኝ።
By Behaylu Mulgeta
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
📝#share📖
@Esubealem
@Esubealem
8 Dec 2025, 05:48 UTC≈1,430 views17 reactionsread 7 August 2026 ቅንድቧን እንደ ሴት ፥ ኩል አልተኳለችው
ፀጉሯ ቢንጨባረር ፥ ጉዳዬ አላለችው
ከንፈሯን በቀለም ፥ አልለቀለቀችው
እንደነገሩ ነው ፥ ልቤን የረታችው ።
እንደ ነገሩ ናት
ካፈር የተሰራች ፥ አመለ ውሃ ናት
እንደ ነገሩ ናት
ባያምር ባይደምቅ ፥ ልብሷና ቀሚሷ
እግረመንገዷን ነው ፥ የምታምረው እሷ
እንደ ነገሩ ናት
በደበዘዘ መልክ ግልገል ፀሐይ አዳይ
ያለ ጋሻና ጦር በዝምታ ገዳይ
እንደ ነገሩ ናት
በጭብጨባ ብዛት የማትደናበር
በተቺ ዘለፋ የማትሰባበር
እንደ ነገሩ ናት
የገዛ ክንፎቿን አጣጥፋ የምትበር ።
By Habtamu Hadera
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
📝#share📖
@Esubealem
@Esubealem
❤14👍2🔥1
29 Sept 2025, 19:58 UTC≈1,630 views11 reactionsread 7 August 2026 አበባና ንብ
.
ንብ ነኝ ላበባዬ በማለዳ ንቁ
በጥኡም ማ'ዛዋ የምሳብ ከሩቁ
ወደሷ ለመጓዝ ልከንፍ የምቸኩል
ስዞራት የምውል ባለችበት በኩል።
.
አበባ ናት እሷም ለኔ የታመነች
ካለችበት ሳቴድ ትጠብቀኛለች
ከውብ ተፈጥሮዋ ማር እንዳሰናዳ
ትፈቅድልኛለች እኔነቴን ዎዳ።
.
የወለላን ጣዕም እቀስማለሁ ከሷ
ጥበቤ በጇነው በጄላይነው ነብሷ።
.
ከእግዜር ተጣምረናል አንዳችን ካንዳችን
ፈዋሽ መድሀኒት ጣፋጭ ነው ፍቅራችን።
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
📝#share📖
@Esubealem
@Esubealem
👍6❤4🔥1
27 Sept 2025, 11:28 UTC≈1,590 views18 reactionsread 7 August 2026 ከሌሊቱ ስድስት ሰአት ከምናምን የፃፍሁልሽ ግጥም
አንች የኔ ኮከብ አንች የእኔ ጨረቃ
ሌሊት ስድስት ሰአት ከ45 ደቂቃ
ድንገት ገድ ቀንቶኝ ከእንቅልፌ ስነቃ
ከበ'ሬ ደጃፍ ላይ ሰማሁኝ ሙዚቃ
ምን ይላል መሰለሽ
"መሄዱንስ ሂጂ አልከለክልሽም
በሴቱም ሴት አለ እናቴ አይደለሽም
እህቴ አይደለሽም"
ይህ ገራሚ ሀሳብ ይህ ጥዑም ሙዚቃ
በደረቀው ሌሊት
ቤቴን እና ልቤን ደጋግሞ ሲደቃ
ላዜምልሽ ሳስብ
ድምፅህ
ውሻንም አይጠራ ብለሽኛል ለካ
ያኔ
ቃልሽን ባከብርም ከቤቴ ሳትወጭ
ዛሬ አብረሽኝ የለሽ
ይኧው አዜምሁልሽ ምናባሽ ታመጭ
መሄዱንስ ሂጂ አልከለክልሽም
በሴቱም ሴት አለ እናቴ አይደለሽም
…
👏12❤6
28 May 2025, 18:33 UTC≈1,960 views9 reactionsread 7 August 2026 ደሃ የሆንህ እንደሁ...
ደሃ የሆንህ እንደሁ... ሲኦልህ ናት ምድር
ውልደትህ፣ ዕድገትህ... ኑሮህም አያምር !!!
...
ደሃ የሆንህ እንደሁ...
ከአፈር ቤት ተወልድህ - በአፈር ትድሃለህ
የአፈር ሲሳይ ርቆህ...
ከአፈር ከቆሻሻ - ምግብ ትለቅማለህ
በእንጀራ ሳይሆን - በረኃብ ታድጋለህ !
.
(በደሃ ሀገር ውስጥ - በውል ላስተዋለ
ምግብ ተከልክሎ - በረኃብ የሚያድግ አለ)
.
ልብስህም አፈር ነው - ቆሻሻ ያልፀዳ
ኑሮህ የሰቀቀን - የሰቆቃ፣ የዕዳ....
.
ዳኛው ቢፈርድ ባንተ - ስለማትሰጥ ጉቦ
መንግሥት ቢቀጣ አንተን - ያለ ፍርድ ያለ አግቦ
ግብር ቢጣል በአንተ - ያለህን ለመውሰድ
ምትገፋው አንተ - ከሀገር እንድትሄድ
የምትሞተው አንተ - በስደትህ …
❤8👍1
28 May 2025, 12:33 UTC≈1,570 views7 reactionsread 7 August 2026 የጥቁር ህዝብ ድል
የጥቁር ህዝብ እድል
የጥቁር ሰው ገድል
አንተ ላይ እንዲፃፍ ፣ ፈጥሮህ ለተአምራት
ጠርቼህ
ጠርቼህ
እንደገና ሚያምረኝ ፣ ደጋግሞ አንተን መጥራት!
ሚኒሊክ!!!
(በላይ በቀለ ወያ)
📝#share📖
@Esubealem
@Esubealem
💯4❤2👏1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Esubealem. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.