15 Jun 2026, 06:36 UTC271 views1 reactionsread 10 August 2026 Photo
ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ።
ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ በደረሰ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል።
አደጋው የደረሰው ከደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች መካከል በሚገኘው የሐረጎ መንገድ ላይ ነው።
ዛሬ ሰኔ 08/10/18ዓ.ም ማለዳ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የሕዝብ አውቶቡስ በተለምዶ ሐረጎ እየተባለ በሚጠራው መንገድ ላይ በደረሠበት አደጋ እስካሁን የ28 ሰው ሕይወት ሲያልፍ በርካቶች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባተቸዋል።
የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው በግምት100 ሜትር ጥልቀት ወዳለው ገደል ገብቶ ነው አደጋው የደረሠው። በሕይወት…
❤1
11 May 2026, 17:07 UTC461 viewsread 10 August 2026 Photo
የደሴ ሙዚየም የተዘረፉ ቅርሶችን ለመተካት በስጦታ ማሰባሰብ መቻሉ ተነገረ
የደሴ ሙዚየምን ተንቀሳቃሽ ቅርሶችን በአዲስ መልክ መመዝገብ ፣መለየት ፣ወደ ዘመናዊ ዳታ ቤዝ ሶፍትዌር የማስገባት የኮዲንግ ስራ ፣ የቦታ አቀማመጥ የማመቻቸት ፣ከቅርስ ባለአደራ ማህበር ጋር በመሆን ኤግዚቢሽን የማዘጋጀት እንዲሁም ሁሉንም ቅርሶች የመመዝገብ ስራ መሠራቱን የደሴ ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ስፖርት መምሪያ አስታውቋል ።
የመምሪያው ኃላፊ አቶ ሰኢድ አራጋው ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት የደሴ ሙዚየም የተዘረፉ ቅርሶችን ለመተካት የቅርስ መግዣ ገንዘብ ባለመኖሩ በስጦታ የማሰባሰብ ስራ ተሰርቷል ።
17 የስዕል ዉጤቶች ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማ…
19 Oct 2025, 17:10 UTC≈1,050 views6 reactionsread 10 August 2026 Photo
ታላቁ አባት ሐጂ ኡመር ኢድሪስ አረፉ
የቀድሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የክቡር ዶ/ር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ወደ አኼራ ሄደዋል።
ታላቁ የሃይማኖት አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ወደ ዛሬ ወደ አኼራ ሄደዋል።
ቴሌግራም ቻናል : t.me/Dessiecity
ፌስቡክ ፔጅ ➤ Fb.com/DesieTimes
😢5❤1
14 Oct 2025, 14:35 UTC912 views4 reactionsread 10 August 2026 የደሴ ከተማ አሰ/ር ፖሊስ መምሪያ የሌዛ ደሳለኝ ግድያ በተመለከተ ተከታዩን መረጃ ሰጥቷል።
ወጣት ሌዛ ደሳለኝ የተባለች የከተማችን ነዋሪ በቀን 28/01/18 ዓ,ም በደሴ ከተማ ቦርከና ቀበሌ ልዩ ስሙ ሀቢታት አካባቢ ባልታወቁ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ ተፈፅሞባት ህይወቷ ማለፉ ይታወቃል።
የተፈፀመው የወንጀል ድርጊትም ለፖሊስ መረጃው እንደደረሰው በፍጥነት በቦታው ደርሶ አስፈላጊውን ተግባር አከናውኗል።
የደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አማካኝነት የፍትህ አካላትን ያካተተ የምርመራ ቡድን በማዋቅር ምርመራው በታክቲክና በቴክኒክ ማስረጃዎችን በማጣራት ወንጀል ፈፃሚውን አካል በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰራ ሲሆን በቀጣይ የምርመራ ቡድኑ የደረ…
❤4
13 Oct 2025, 17:08 UTC629 viewsread 10 August 2026 #የተሳሳተ_መረጃ
ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ስሟ ሊዛ ደሳለ የተባለች ተማሪ ህይወቷ አልፎ እንደተገኘች እና የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ እንደሆነች እየተገለጸ ይገኛል።
ነገር ግን ሟቿ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ አለመሆኗን እያረጋገጥን የተማሪዋ ሞት አሳዛኝ ቢሆንም በተሳሳተ መረጃ የወሎ ዩኒቨርሲቲን ስም ለማጥፋት እና ኃላፊነት በጎደለው አኳኋን የተለያዩ ሚዲያወችን በመጠቀም የተቋሙን ስም ለማጠልሸት ሙከራ ያደረጋችሁ አካላት ላይ አስፈላጊውን የህግ አግባብ በመከተል ተጠያቂ የምናደርግ መሆኑን እናሳውቃለን።
የሰው ልጅ በማንኛውም ሁኔታ በተለይ ደግሞ ተፈጥሯዊ ባልሆነ መንገድ ህይወቱን ሲያጣ ያሳዝናል። በመሆኑም ለሟች ቤተሰቦችና ጓደኞች መጽናናትን እንመኛለን።
ቴሌግራ…
12 Oct 2025, 13:23 UTC643 views4 reactionsread 10 August 2026 Photo
በትራፊክ አደጋ የሰው ህይወት አለፈ።
የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ኡመር መሀመድ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት በዛሬው እለት በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጨፋ ሮቢት ከተማ ልዩ ስሙ ጃራ ድልድይ አከባቢ የትራፋሪክ አደጋ መድረሱን ተናግረዋል ።
በዚህም ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት 73290 የሆነ ታታ አውቶቡስ እና ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት 41157 ተሳቢ መኪና ተጋጭተው በደረሰ የትራፊክ አደጋ መረጃው እስከ ተጠናከረበት ሰአት 10 ስዎች ህይወት ማለፉና 8 ስዎች ደግሞ ከባድ ገዳት እንደረሰባቸው የተጠቀሰ ሲሆን ከአደጋው ከባድነት አንጻር ቁጥሮቹ ሊጨምሩ እንደሚች…
❤4
28 Sept 2025, 06:06 UTC693 views1 reactionsread 10 August 2026 Photo
ደሴ ከተማ ምርጥ ወጣት እግርኳስ ተጨዋቿን አጣች።
በመሃል ሜዳ ተክኒሺያንነቱ የሚታወቀው ወጣቱ ተስፋየ ደሳለኝ (ቻቻ) አርፏል
ለደሴ ከተማና ለሌሎች ክለቦች እግርኳስ ክለቦች መጨዋት የቻለው ወንድሜ ወጣቱ ተስፋየ ደሳለኝ (ቻቻ) ባደረበት ህመም በቦሩ ሆስፒታል ጽኑ ህሙማን ክፍል ሲረዳ ቆይቱ ከዚህ አለም ድካም አርፏል።
ነብስ ይማር!!
ለቤተሰቦቹ ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለስፖርት ቤተሰቡ በሙሉ መጽናናትን ተመኘን
ቴሌግራም ቻናል : t.me/Dessiecity
ፌስቡክ ፔጅ ➤ Fb.com/DesieTimes
❤1
16 Sept 2025, 18:09 UTC750 views1 reactionsread 10 August 2026 Photo
የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ሐራ ገበያ የባቡር መስመርን ለማጠናቀቅ ከፍተኛ የመንግስት ቁርጠኝነት መኖሩን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
የኮርፖሬሽኑ የህግ አገልግሎት ሃላፊ አቶ ካሳሁን ሙላቱ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገልፁት ኮርፖሬሽኑ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማጠናከር ከኮይፓ ኢጣሊያ ጋር ማዕቀፋዊ ስምምነት አድርጓል።
ስምምነቱ አዳዲስ የባቡር መስመሮችን መዘርጋትን እንዲሁም እየተገነቡ ያሉ የባቡር መስመሮችን በፍጥነት አጠናቆ ወደ ስራ ማስገባትን የሚያካትት ነው ብለዋል።
ከዛም ባለፈ በጋራ ድርጅቶችን ማቋቋም እንዲሁም ትላልቅ ዎርክ ሾፖሽን ማሻሻል ጨምሮ በርካታ ስትራቴጂካዊ ስራዎች የሚሰሩበር የጋራ ስምምነት መሆኑን ገልፀዋል።
ስምምነቱ በተ…
❤1
15 Sept 2025, 13:31 UTC624 views2 reactionsread 10 August 2026 ይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ካስፈተናቸው 52 ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ ውጤት ማምጣታቸው ተገለፀ።
ከነዚህ ውስጥ 21ተማሪ ከ500በላይ ውጤት ያመጡ ሲሆን ቀሪዎቹ ከ408አስከ 499ድረስ ውጤት ያመጡ መሆኑን የትምህርት ቤቱ ምክትል ርእሰ መምህር አቶ ፍቅር በላይ ገልጸዋል።
እንኳን ደስ አላችሁ
ቴሌግራም ቻናል : t.me/Dessiecity
ፌስቡክ ፔጅ ➤ Fb.com/DesieTimes
👏2
15 Sept 2025, 13:31 UTC582 viewsread 10 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
15 Sept 2025, 13:31 UTC561 viewsread 10 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
15 Sept 2025, 13:31 UTC416 viewsread 10 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @DessieCity. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.