28 Aug 2026, 10:14 UTC396 views14 reactionsread 28 August 2026 Photo
እምነት ተስፋ ላይ ያርፋል፤ ተስፋን ግን የተጠጋ አይደለም። አብርሃም ተስፋውን ሳይቀበል በፊት አመነ፤ ያንንም ታማኙ—በማንነቱና በምንነቱ— አምላክ ጽድቅ አድርጎ ቆጠረለት። ተስፋውን (ይስሐቅን) ተቀብሎ እያጣጣመው ሳለም፣ የተሰጠውንና እንደ ዐይኑ ብሌን የሆለትን ልጅ አቅርብ ተባለ። ለመውጣት፣ ለመቀበልም እንደ ታዘዘ ሁሉ፣ ለመስጠትም ታዘዘ። ማመን ለመቀበል ብቻ ሳይሆን ለመስጠትም እንደ ሆነ አጸና። አሁንም በድርጊቱ ጸደቀ። እግዚአብሔርን እንዳመኑ አፍ ተሞልቶ የሚነገርላቸው፣ በተግባራቸውም እምነታቸውን ፍጹም ያደረጉ ናቸው። እግዚአብሔርን እንዳመንን ሐሳባችን፣ ንግግራችን፣ ሥራችንም አንድ ሆነው ሊገልጡ ይገባል።
James 2:22
You see that his f…
❤14
27 Aug 2026, 04:08 UTC628 views23 reactionsread 28 August 2026 Photo
ጽድቅ እምነት ላይ ያርፋል፤ የእምነት መቀመጫውም ልብ ነው። ያመኑትን መናገርና መኖር ከዚይ የሚከተል ነው። እግዚአብሔር በክርስቶስ ያሰበውን ሐሳብ፣ የሠራውን ሥራና የሰጠውን ተስፋ ስናምን ጽድቃችን ይጸናል። የሚጸናውም በእርሱ ነው። እርሱ ያጸደቀውን ደግሞ የሚሽር ማንም የለም። ጳውሎስ እውነታውን በቅለቱ እንዲህ አስቀመጠው፤ "የምትጸድቀው በልብህ አምነህ ነው፤ የምትድነውም በአፍህ መስክረህ ነውና" (ሮሜ 10፥10 አመት)። ከልባቸው ያመኑ በንግግራቸው ክብደት ይታወቃሉ፤ ቃላቸው ያመኑበትን ተስፋ ስለሚይዝም ምስክርነታቸው ድነትን ያረጋግጣል።
Romans 10:10
For it is with your heart that you believe and are justified,…
❤23
26 Aug 2026, 04:17 UTC687 views28 reactionsread 28 August 2026 Photo
ቀድሞ የቀረበ ጥያቄ ቅድሚያ ተሰጥቶት ሊስተናገድ ይገባል። ጥያቄው ደግሞ እጅግ አንገብጋቢ—የሞትና የሕይወት ጕዳይ—ከሆነ ፋታ ሊሰጠው አይገባም። ኢያኢሮስ የተባለው የምኩራብ አለቃ "ትንሿ ልጄ በሞት አፋፍ ላይ ነችና. . .መጥተህ እጅህን ጫንባት" ብሎ ጌታን ለመነ። ጌታም ተስማምቶ ጕዞ ቀጥሎ እያለ፣ ሌላ ታማሚ (የከፋም ቢሆን ለሞት የሚያሰጋ አልነበረም) መንገድ ላይ አዘገየው። የሴትየዋ ጥያቄ ተመልሶ፣ ደሟ ቆሞ ምስክርነት ተሰምቶ ሲያልቅ፣ "ልጅህ ሞታለች" የሚል አስከፊ ዜና ለኢያኢሮስ መጣለት። ኢየሱስ እጅ ላይ ጥያቄው 'ሞተ'። 'ጌታ ፈጥኖ ቢሆን ኖሮ፣ ሳትሞት ይደርስ ነበር' የሚለው ሐሳብ አባቷን ጨምሮ የብዙዎችን አእምሮ ሳያልፍ አልቀረም። ጌታም ሰዎቹ ያ…
❤28
25 Aug 2026, 08:21 UTC753 views23 reactionsread 28 August 2026 Photo
ማመን ማወቅና መደገፍ ነው። እግዚአብሔር ምጡቅና ትልቅ ቢሆንም ማንነቱ በሥራው ውስጥ የሚታወቅ፣ ባሕርይውም በአደራረጉ የተገለጠ ነው። "ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የማይታየው የእግዚአብሔር ባሕርይ፣ ይኸውም ዘላለማዊ ኀይሉና መለኮትነቱ፣ ከፍጥረቱ በግልጽ ይታያል" ተብሏል (ሮሜ 1፥20)። እምነትን የሚፈታተኑ አያሌ ነገሮች ሊኖሩ ቢችሉም፣ ለሚሰሙና ለሚያስተውሉ፣ በመንገዳቸውም እርሱን ለሚሉ ግን ብዙ ማስተዋልና ዕፎይታ አለ። ዘማሪው እንዲህ አለ፤ "መንገድህን ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤ በእርሱ ታመን፤ እርሱም ያከናውንልሃል" (መዝ 37፥5)። ጌታ አምላክ ሰዎች ይታመኑበትና መንገዳቸው ይቀና ዘንድ ቀርቧል፣ ብርሃኑንም አብርቷል። በሁሉ ዘንድ የተገለጠውንና ፍጥረቱን የ…
❤23
24 Aug 2026, 06:50 UTC798 views19 reactionsread 28 August 2026 Photo
እምነት የኑሮ ክፍል ነው፤ በየዕለቱ የምንለማመደው ክስተት ነው። የምንቀበለውንና የምንገዛውን ሁሉ አምነን ነው የምንወስደው፣ የምንጠቀመውም። እምነት ደግሞ ማረፊያ አለው፣ ብርታቱም በተስፋ ሰጪው ላየ ይወሰናል። እርሱም ለመታመን ምሉዕ፣ ቃሉን ለመፈጸም ታላቅ፣ ሁሉን ለማድረግ ደግሞ ብርቱ ነው። ስለ ተገለጠልን እናምነዋለን፤ እያመንነው ስንሄድም ይበልጥ እናውቀዋለን፤ እያወቅነው ስንመጣም እምነታችን እየጨመረ ይሄዳል። የእመነት አባት ለሆነው አብርሃም እንዲህ አለው፤ "አብራም እግዚአብሔርን አመነ፤ እርሱም ጽድቅ አድርጎ ቈጠረለት" (ዘፍ 15፥6)። አንድ ነገር ብቻ ነው የሚጠበቅብን፤ ያም ማመን። እግዚአብሔርን ያመኑም ጽድቁን ይካፈላሉ።
Genesis 15:6
Ab…
❤19
23 Aug 2026, 04:09 UTC865 views25 reactionsread 28 August 2026 Photo
ጌታ መሥዋዕት የሆነላቸውና ሌላ "ከተማ" ያዘጋጀላቸው ሕዝቦች የተደረገላቸውን የሚያስቡና የሚዘክሩ ናቸው። ስለ ተደረገላቸውም ነገር ሁሉ አምላካቸውን ያመሰግናሉ። የዕብራውያን ጸሐፊም ይህንኑ ያሳስበናል፤ "ስለዚህ ዘወትር የምስጋናን መሥዋዕት ይኸውም ለስሙ የሚመስክሩ የከንፈሮችን ፍሬ በኢየሱስ አማካይነት ለእግዚአብሔር እናቅርብ" (13፥15 አመት) በማለት። የተደረገልን ነገር እጅግ ክቡርና ታላቅ ከመሆኑ የተነሣ ሁልጊዜ የምናስበው፣ እግዚአብሔርንም የምናመሰግንበት ነው። "የዘወትር" ምስጋናም፣ ከንፈሮቻችን የሚያመነጩት የውለታና የአድናቆት ፍሬዎች ናቸው። የሚያመሰግኑ አንደበቶችም በአድናቆት የተሞሉ ስለሆኑ ለምሬት ቦታ የላቸውም።
Hebrews 13:15
Throu…
❤25
22 Aug 2026, 04:02 UTC885 views24 reactionsread 28 August 2026 Photo
#ArtSaturdays
ክርስቶስ ጌታ ሁለመናውን ለአምላኩና ለአባቱ አቅርቧል። ሰውነትን የተላበሰው (የጨመረው) ማንነቱ ለተልዕኮው አስፈላጊ ነበር፤ ፈቃዱን ሳይሆን የአባቱን ፈቃድ አድርጎ የመጨረሻውን ጽዋ ጠጣ። መጽሐፍም፣ “መልካም መዐዛ ያለው መባና መሥዋዕት” አድርጎ ራሱን አቀረበ ያለው ለዚህ ነው። እግዚአብሔር ክቡር የሆነውን የልጁን መሥዋዕት ሲቀበል፣ በእርሱ በኩል የሚቀርቡትን ሁሉ እንዲሁ ተቀብሏል።
Ephesians 5:2
and walk in the way of love, just as Christ loved us and gave himself up for us as a fragrant offering and sacrifice to God.
@ethbiblica
Telegra…
❤24
21 Aug 2026, 04:00 UTC≈1,160 views20 reactionsread 28 August 2026 Photo
ከከንፈሮች ምስጋና በላይ የሚቀርብ መሥዋት አለ። ያም የሰው ሁለንተና ነው። ጳውሎስ፣ "እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ" (ሮሜ 12፥1) አለ። እግዚአብሔር ድምፃችንን ብቻ ሳይሆን ሐሳባችንንም ይከታተላል፤ ድርጊታችንም እንዲሁ በእርሱ ዘንድ ይታያል። መሥዋዕት አድርገን የምናቀርበው ሰውነታችንም ይህን ሁሉ የሚጨምር ነው። ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ነገር ሁሉ ከሰጪው በላይ ተቀባዩን—ጌታን—ማገናዘብ፣ በተቻለ መጠንም መመጠን ይኖርበታል። "ቅዱስ"፣ "ደስ የሚያሰኝ" እና "ሕያው" መሥዋዕት መሆን የሚቻለውም፣ መሥዋዕት በሆነልን፣ ባነጻን፣ በቀደሰንና …
❤20
20 Aug 2026, 07:39 UTC≈1,100 views24 reactionsread 28 August 2026 Photo
ለዮናስ ምድር—መሬት—መሸሺያው፣ ባሕር መጣያው፣ የባሕሩ ጥልቅ ደግሞ (በጸጸት) መመለሺያው ሆነ። ከእግዚአብሔር ጽድቅና ፍትሕ 'በላይ' ሆኖ፣ 'እንዴት ለነነዌና አሦር ምሕረት ይገባል?' በማለት ቢሸሽም፣ የማይደበቁት (ሊሰወሩበት የማይቻለው) አምላክ አገኘው፤ ሊመልሰውም ስለ ወደደ በዓሣ አስይዞ ወደ ልቦናው እንዲመለስ አደረገው። በዚያም ድንቅ ጸሎት ጸለየ፤ "እኔ ግን በምስጋና መዝሙር፣ መሥዋዕት እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እሰጣለሁ፤ ድነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው” (2፥9)። በከባድ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ምስጋና ማቅረብ ከባድ ሊሆን ይችላል፤ በዓሣ ሆድ ለሞት ቅርብ ሆኖና መቼ አየር እንደሚቋርጥ በማይታወቅበት ሁኔታ እግዚአብሔርን ማመስገን፣ በርግጥም ምስጋና መሠ…
❤24
19 Aug 2026, 08:07 UTC≈1,050 views18 reactionsread 28 August 2026 Photo
የአሳፍ መዝሙር (50) "ኅያሉ እግዚአብሔር" ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ የሚናገር፣ በምድር ያለውን ሁሉ የሚያውቅና የሚገዛ እንደ ሆነ ይናገራል። የሰዎች ልጆች መሥዋዕት ቢያቀርቡለት እንኳን፣ ከእርሱ የተቀበሉትን እንጂ ራሳቸው አመንጭተው (ዐዲስ ነገር ፈጥረው) ምንም ሊያደርጉ እንደማይችሉ ይብራራል። ትልቁ መሥዋዕትም ምስጋና እንደ ሆነ ይጠቀሳል፤ "የምስጋናን መሥዋዕት የሚሠዋ ያከብረኛል፤ መንገዱንም ቀና ለሚያደርግ፣ የእግዚአብሔርን ማዳን አሳየዋለሁ" (ቍ 23)። ምስጋና በቀላሉ ከተዘጋጀ 'መሥዋዕት' አይሆንም፤ ሰዎች ለምሕረት፣ በጎነት፣ ቸርነት፣ ተአምር ውለታዎች ለጌታ ምስጋና ያቀርባሉ፤ ማንነቱን እያሰቡና ገዢነቱን እየተረዱ፣ ሌላ ነገር ሳይቆጥሩ አምላክን ማድ…
❤18
18 Aug 2026, 04:17 UTC≈1,190 views25 reactionsread 28 August 2026 Photo
ትእዛዝ ከጥረት በላይ ነው፤ በደንብ ሳይሰሙ ለድርጊት መንደርደር ድካም፣ ብልሽት ወይም መልሶ ሥራ ነው። ለእስራኤል የመጀመሪያው ንጉሥ (ሳኦል)፣ ድርጊት ከእግዚአብሔር ፈቃድበላይ ሆኖ ነበር። እግዚአብሔር አማሌቃውያንንና የእነርሱ የሆነውን "አጥፋ" ብሎት ነበር። እርሱ ግን፣ "መልካም የሆነውን ሁሉ" አስቀረ፤ የሰባውንም ከብት እየነዳ ተመለሰ። ያደረገው ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስንፍናና በደል ሆኖ ተገኘ፤ በሳሙኤልም ፊት ጎድሎ ተገኘ። በጆሮ የሰማውን ትእዛዝ ሙሉ ለሙሉ እንደ መፈጸም፣ ዐይኖቹ ተስበው—በሠቡ በሬዎችና በጎች—ትእዛዙን 'አሻሻለው'። ሳሙኤልም፣ "መታዘዝ ከመሥዋዕት፣ ማዳመጥም ከአውራ በግ ሥብ ይበልጣል" (15፥22) አለው። በእግዚአብሔር ዘን…
❤25
17 Aug 2026, 04:04 UTC≈1,060 views20 reactionsread 28 August 2026 Photo
እግዚአብሔርን እንደ ሰጪ ያመኑ፣ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ አይቸገሩም። አብርሃም የቃል ኪዳኑን ልጅ ለመቀበል 99 ዓመት ኖረ፤ ወይም ቃል ከተገባለት ጊዜ ጀምሮ 25 ዓመታትን ጠበቀ። ውድና ብርቅ ልጁን ለአምላኩ እንዲሠዋ ሲጠየቅም 'እሺ' አለ፤ ታዘዘ። እግዚአብሔር መውሰድ የሚችለውን እንደሚጠይቅ ተረድቷል። ጠያቂውንም እንደ ሰጪ እንጂ ነጣቂ አልቆጠረም። ስለዚህም ለመሠዋት ወደ ኮረብታው ወጣ፤ ልጁን አሠረ፤ ቢላም አነሣ። ያን ጊዜም፣ ለመሠዋት መወሰኑ በሥራው ተረጋገጠ። ፍቅሩና መሳሳቱ ለአምላኩ ትእዛዝ ታዘዘ። አምላክም የበግ እንጂ የሰው ደም እንደማይሻ አረጋገጠ።
Genesis 22-2
Then God said, 'Take your son, your only s…
❤20
Showing the 12 most recent of 42 posts we hold for @DailyInjeraOfficial. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.