24 Jan 2026, 10:51 UTC285 viewsread 6 August 2026 Photo
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ደብዳቤ ላከ
ጥር 16/2018 (አሐዱ ራድዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፊታችን የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. በመላ ሀገሪቱ የሚጀመረውን የመራጮች ምዝገባ ተከትሎ፣ በትግራይ ክልል የሚገኙ የምርጫ ጣቢያ ጽሕፈት ቤቶች እስከ ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዝግጁ እንዲሆኑና ሪፖርት እንዲደረግለት የሚጠይቅ ደብዳቤ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጽፏል።
ቦርዱ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ በላከው ደብዳቤ፣ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደውን 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ለማከናወን የጊዜ ሰሌዳ ማሻሻያ ማድረጉንና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጿል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሌ በ…
Signed እፀ-ሳቤቅ✉ ፩፱፰፯
23 Jan 2026, 07:37 UTC231 viewsread 6 August 2026 Photo
“ ቶተንሀም ውስጥ እርግማን ያለ ይመስለኛል “ ቶማስ ፍራንክ
የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ ቡድናቸው ውስጥ በርካታ ጉዳት መመዝገቡ እንዳበሳጫቸው ገልጸዋል።
አሰልጣኙ በንግግራቸውም በጉዳት ምክንያት ክለቡ ውስጥ እርግማን እንዳለ እንደሚሰማቸው ተናግረዋል።
በተጨዋቾቹ ላይ እየተፈጠረ ያለው ጉዳት “ እርግማን ወይም እንደዛ ነገር ይመስላል ነገርግን ጉዳት የእግርኳስ አካል ነው “ ብለዋል።
ቶተንሀሞች ሌላኛውን ተጨዋች ሉካስ ቤርግቫል በጉዳት ምክንያት ለረጅም ጊዜ አጥተዋል።
ክለቡ በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው የመጨረሻ አምስት ጨዋታዎች በጉዳት አንድ ተጨዋች ማጣቱ ይታወሳል።
ቶተንሀም በአሁኑ ሰዓት ኩዱስ ፤ ሪቻርልሰን ፤ ቤርግቫል…
Signed እፀ-ሳቤቅ✉ ፩፱፰፯
23 Jan 2026, 07:36 UTC170 viewsread 6 August 2026 Photo
🔵ከአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር የቦርድ አባላት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ
አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ከተመሰረተችበት ባለፉት 8 ዓመታት ጀምሮ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ በዜናና ወቅታዊ እንዲሁም በመዝናኛ ዝግጅቶች መረጃዎችን በቴሌቪዥን እና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቿ ስታደርስ ቆይታለች፡፡
ይሁን እንጂ አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ስራዋን ለመቀጠል አቅም ስለሌላት በቴሌቪዥንም ሆነ በየትኛውም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቿ ከዛሬ ታህሳስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በይፋ ስርጭት ማቆሟን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ስለሆነም ከተጠቀሰው ጊዜ ጀምሮ የአሻም ሚዲያ መታወቂያ በመያዝ ወይም የሚዲያዋ…
Signed እፀ-ሳቤቅ✉ ፩፱፰፯
23 Jan 2026, 07:34 UTC131 viewsread 6 August 2026 Photo
የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) አመራሮችና አባላት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።
ጥር 14/2018 (አሐዱ ራድዮ) የሰላም ስምምነት ተፈራርመው ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ የተመለሱት የአፋሕድ አመራሮችና አባላት፣ በዛሬው ዕለት በመዲናዋ የተከናወኑና እየተከናወኑ የሚገኙ አበይት የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በጉብኝታቸውም የዓድዋ ድል መታሰቢያን፣ በከተማዋ የተከናወነውን የኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችንና ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል። ይህ ጉብኝት የተከናወነው በአማራ ክልል መንግሥትና በድርጅቱ መካከል የተደረሰውን ዘላቂ የሰላም ስምምነት ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት በትላንትናው ዕለት መፈረ…
Signed እፀ-ሳቤቅ✉ ፩፱፰፯
22 Jan 2026, 23:59 UTC117 viewsread 6 August 2026 Photo
#NewsAlert : በጋምቤላ ከተማ ከነገ ጀምሮ ሞተር ሳይክል ማሽከርከር ተከለከለ።
ባለፈው ወር ህይወትን የቀጠፈ የሰላም መደፍረስ የገጠመው የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር በከተማው ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔውችን ማሳለፉን አሳውቋል።
በዚህም ፦
- ማንኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ሞተር ሳይክሎች ከነገ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማሽከርከር በጥብቅ ተከልክሏል።
- በከተማው የሚገኙ ባጃጆች አገልግሎት መስጠት የሚችሉት ከጥዋቱ 1 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።
- በከተማው የሚገኙ ሆቴሎችና ግሮሰሪዎች አገልግሎት መስጠት የሚችሉት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ ብቻ እንዲሆን ተወስኗል።
…
Signed Inside Ads
22 Jan 2026, 23:46 UTC105 viewsread 6 August 2026 Photo
❤️ እኔ እጋብዛለሁ የTelegram ቻናል ባለቤቶችን ወደ Inside Ads፡ ለእድገትና ለተመጪ ገቢ ብልህ መሳሪያ!
https://t.me/InsideAds_bot/open?startapp=r_321122018
Signed Inside Ads
22 Jan 2026, 19:17 UTC113 viewsread 6 August 2026 Photo
" ሴት እህቶችን ወደ መዝናኛ ቦታዎች በመውሰድና በሚጠጡት መጠጥ ውስጥ አደንዛዥ ዕጽ በመጨመር፤ ያልተገባ ድርጊት እንዲፈጽሙ በማድረግና በተንቀሳቃሽ ምስል በመቅረጽ በማኅበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ ነበር " - ፖሊስ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የቲክቶክ ፕላትፎርምን በመጠቀም ከባህልና ወግ ያፈነገጡ ተግባራትን ሲፈፅም የነበረ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳወቀ።
ፖሊስ ንጉሰ ዳዊት ወይም በቲክታክ ስሙ ግብዳው የተባለን ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ገልጿል።
ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ድርጊት ውስጥ ገብተው የተገኙ ግለሰቦች ላይ ህጋዊ ርምጃ በወሠደበት ወቅት ይኸው ተጠርጣሪ ለረዥም ጊዜያት ከአዲስ አበባ በመውጣት ቢሾፍቱ አ…
Signed እፀ-ሳቤቅ✉ ፩፱፰፯
22 Jan 2026, 19:09 UTC100 views1 reactionsread 6 August 2026 የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ካውንስል አባላትና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች ሚኒስቴሩ እያስገነባው የሚገኘውን የክህሎት ፓርከ ጎበኙ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በጉብኝቱ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት የክህሎት ፓርኩ አዳዲስ ሃሳብን ከማመንጨት ለገበያ አስከማቅረብ ድረስ ያሉ የክህሎት ልማት ሂደቶች በስፋት የሚተገበሩበት፣ አህጉርና ዓለም አቀፍ የክህሎት ኮንፍረንሶችና ውድድሮች የሚካሄዱበት ደረጃውን የጠበቀ ማዕከል እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡
የክህሎት ፓርኩ አዳዲስ አዳጊ የክህሎት ልማቶችን ጨምሮ ዘመኑን የዋጁ አዳዲስ አገልግሎቶችን ሁሉ እንዲያካትት ለማድረግ በየጊዜው የማሻሻያ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ የገለፁት ክብርት ሚኒስት…
👍1
Signed እፀ-ሳቤቅ✉ ፩፱፰፯
21 Jan 2026, 16:31 UTC106 viewsread 6 August 2026 ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ተሸጠ!
ከአዲስአበባ ቀደምት ዘመናዊ ሆቴሎች መካከል አንዱ የሆነው ዋቢ ሸበሌ በዛሬው እለት
ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ተሽጧል ።
ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድና የዋቢ ሸበሌ ሆቴል አክሲዮን ማህበር የቦርድ ፀሀፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን ተፈራርመዋል።
አቶ ጀማል አሕመድ የሆቴሉን አገልግሎት በዘርፉ አለም በደረሰበት ደረጃ በማዘመን ለእንግዶች ምቹና ጥራቱን የጠበቀ የማረፊያ ቦታ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የዋቤ ሸበሌ ሆቴል የቦርድ ፀሀፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን የሆቴሉን ታሪክ ጠብቆ በማዘመን ለትዉልድ ለማሻገር በመስማማቱ ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።…
Signed እፀ-ሳቤቅ✉ ፩፱፰፯
21 Jan 2026, 12:55 UTC97 viewsread 6 August 2026 Photo
#EthPL 🇪🇹
በ ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ወልዋሎ ዓ.ዩ ከሸገር ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 አጠናቀዋል።
ሄኖክ አዱኛ ሸገር ከተማን መሪ ያደረገች ግብ ቢያስቆጥርም ኮንኮኒ ሀፊዝ ወልዋሎን አቻ አድርጓል።
በጨዋታው የወልዋሎ ዓ.ዩ ተጨዋች ሰመረ ሀፍታይ የሸገር ከተማው አቤኔዜር ሕዝቅኤል ላይ በሰራው ጥፋት ቀይ ካርድ ተመልክቷል።
በሌላ በኩል የሸገር ከተማው ቡልቻ ሹራ የወልዋሎው ተጨዋች ኪም ላም ላይ በሰራው ጥፋት ቀይ ካርድ ተመዞበታል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
16 ሸገር ከተማ :- 16 ነጥብ
19 ወልዋሎ ዓ.ዩ :- 13 ነጥብ
Signed እፀ-ሳቤቅ✉ ፩፱፰፯
21 Jan 2026, 07:39 UTC88 viewsread 6 August 2026 Photo
በኦሮሚያ ክልል የመንግሥትና የፓርቲ ግምገማ በአዳማ ከተማ ተጀመረ
ጥር 13/2028 በኦሮሚያ ክልል የ2018 በጀት ዓመት የሁለተኛ ሩብ ዓመት የመንግሥትና የፓርቲ ሥራ አፈጻጸም ግምገማ በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።
በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራው ይህ መድረክ፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችንና የፓርቲ አመራሮች ተሳትፈውበታል። የግምገማው ዋነኛ ትኩረት ባለፉት 6 ወራት የታዩ ስኬቶችን ማጠናከርና ክፍተቶችን በመለየት ለቀጣይ የሥራ ዘመን ዝግጁነትን መፍጠር እንደሆነ ተገልጿል።
ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በመድረኩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ በክልሉ የተመዘገቡ ስኬቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ድክመቶች…
Signed እፀ-ሳቤቅ✉ ፩፱፰፯
19 Jan 2026, 16:58 UTC95 viewsread 6 August 2026 Photo
ማንችስተር ሲቲ እንግሊዛዊውን ተከላካይ ማርክ ጉሂ ከክሪስታል ፓላስ ማስፈረሙን በይፋ አስታውቋል።
ማንችስተር ሲቲ ለተጨዋቹ ዝውውር 20 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ አውጥተዋል።
Signed እፀ-ሳቤቅ✉ ፩፱፰፯
Showing the 12 most recent of 16 posts we hold for @Daguzena. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.