13 Jun 2022, 08:55 UTC≈131,000 views2,105 reactionsread 3 September 2026 📌ማሳወቂያ
ይህ የቴሌግራም ገፅ ለብዙሀን ተደራሽ መሆን ስላልቻለ 20ሺ አባላት እስኪደርስ ድረስ መረጃዎች እንደማንለቅ ልናሳውቅ እኖዳለን። ስለሆነም የቢቢሲ አማርኛ ዜናዎችን በእየለቱ ለማግኘት እስከዛው እነዚህን አማራጮች እንዲጠቀሙ በአክብሮት እንጠይቃለን።
ድረ-ገፅ:- https://www.bbc.com/amharic
የፌስቡክ አድራሻ:- https://m.facebook.com/BBCnewsAmharic/
@BBC_Amharic_News1
👍1,200❤288👎209😁113🔥80🎉55😢55🤩54
13 Jun 2022, 07:50 UTC≈109,000 views262 reactionsread 3 September 2026 የአሜሪካ ፖለቲከኞች የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ላይ ከስምምነት ደረሱ
በአሜሪካ የጦር መሳሪያ ቁጥጥርን በተመለከተ ልዩነት ያላቸው ሪፐብሊካን እና ዲሞክራቶች በአዲሱ መመሪያ ላይ ከስምምነት መደረሳቸው ተገለጸ። ሆኖም የምክረ ሃሳባቸው ሂደት የሚጠበቅበትን ያህል አልተጓዘም ተብሏል።
ፍሎሪዳ ውስጥ በአንድ ትምህር ቤት ላይ ከተከፈተ ተኩስ የተረፉት ዴቪድ ሆግ “ምንም እንኳን ይህ ስምምነት ትንሽ ቢሆነም ጠቃሚ እርምጃ ነው” ብለዋል።
ሌላዋ የቀድሞ ሕግ አውጪ እና እንደ አውሮፓውያኑ በ2011 በአሪዞና ግዛት ውስጥ ከተፈጸመ ጥቃት ጉዳት ደርሶባቸው የተረፉት ጋብሬል ጊፎርድስ ስምምነቱን “ጠቃሚ እርምጃ ነው” ብለውታል።
ተቀናቃኞቹ ከስምምነት የደረሱበት አዲሱ እቅድ የ…
👍179❤52😱11👎8🔥7🤩4🎉1
13 Jun 2022, 07:49 UTC≈79,000 views145 reactionsread 3 September 2026 አብዛኞቹ አፍሪካውያን ወጣቶች ከአህጉሪቱ መሰደድ እንደሚፈልጉ ጥናት አመለከተ
አብዛኞቹ አፍሪካውያን ወጣቶች በአገራቸውና በአህጉሪቱ ላይ ብሩህ ተስፋ እንደማይታያቸው አንድ ጥናት አመለከተ።
በጥናቱ ውስጥ ከተካቱት አፍሪካውያን ወጣቶች መካከል ሁለት ሦስተኛው ስለ እራሳቸው የወደፊት ተስፋ አውንታዊ ምልከታ ቢኖራቸውም፣ አገራቸውና አህጉራቸው አፍሪካ እየሄዱበት ባለው አቅጣጫ ላይ ተስፋ ሰጪ ነገር እንደማያዩ ተናግረዋል።
‘አፍሪካን ዩዝ ሰርቬይ’ በተባለው በዚህ ጥናት ውስጥ ከ15 የአፍሪካ አገራት የተወጣጡ ከ4,000 በላይ ወጣቶች ከአጥኚዎቹ ጋር የፊት ለፊት ቃለ ምልልስ አድርገው ነው፤ ስለአገራቸውና አህጉራቸው ያለቸውን አመለካከት ለአጥኚዎች የገለጹት።
ht…
👍104❤27👎5🔥5😁4
13 Jun 2022, 07:47 UTC≈62,900 views87 reactionsread 3 September 2026 ታዋቂው የትግርኛ ድምፃዊ ዳዊት ነጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
ታዋቂው ድምጻዊ ዳዊት ነጋ ትናንት እሁድ ሰኔ 5 ቀን 2014 ዓ.ም. አመሻሹ ላይ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የቅርብ ወዳጆቹና ዘመዶቹ ለቢቢሲ ገለጹ።
ዳዊት ነጋ ባደረበት ድንገተኛ ህመም ዓርብ ዕለት አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው አዲስ ህይወት ሆስፒታል መግባቱን ተናግረዋል።
ባለፈው ሳምንት ሰኞ ዕለት በጉንፋን መልክ የጀመረ ህመሙ ከተባባሰ በኋላ ዓርብ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ እስከ ቅዳሜ ድረስ ህክምና ሲደረግለት ቆይቷል።
ትናንት እሁድ ከሰዓት በኋላ ህመሙ ሲጸናበት ወደ ጽኑ ህሙማን ክትትል ክፍል መግባቱን እና ማታ 1፡00 ሰዓት አካባቢ ህይወቱ ማለፉን ጓደኞቹ እና ዘመዶቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል።…
👍52❤30👎3🎉2
13 Jun 2022, 06:51 UTC≈46,800 views62 reactionsread 3 September 2026 ለዩክሬን ሲዋጋ የነበረው የቀድሞ የብሪታኒያ ወታደር ተገደለ
የቀድሞው የእንግሊዝ ጦር አባል የነበረው ግለሰብ ዩክሬን ውስጥ መገደሉን ቤተሰቦቹ አሳወቁ።
ጆርዳን ጋትሊ ከብሪታኒያ ጦር በመውጣት ባለፈው መጋቢት ነበር በሩሲያ ከተወረረችው ዩክሬን ጎን ለመሰለፍ ወደ ጦር አውድማ ያቀናው።
የወታደሩ አባት ልጄ "ጀግና" ነው ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ፅፈዋል።
በምሥስራቃዊቷ የሰቨሮዶኔስክ ከተማ ውስጥ በነበረው ጦርነት ነው የተገደለው።
ከተማዋ ባለፉት ጥቂት ቀናት ከበድ ያለ ጦርነት እያስተናገደች ትገኛለች።
የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር "ዩክሬን ውስጥ የተገለደውን ወታደር ቤተሰቦች እንደግፋለን" ብሏል።
የወታደሩ አባት በፌስቡክ ገፃቸው በፃፉት መል…
👍42❤16😢3👎1
13 Jun 2022, 05:20 UTC≈33,100 views44 reactionsread 3 September 2026 ተቃዉሞን ተከለትሎ ሕንድ የበርካታ ታዋቂ ሙስሊሞችን ቤት አፈረሰች
በነብዩ መሐመድ ላይ የተቃጡ ናቸው በተባሉ አሉታዊ አስተያየቶች ምክንያት ከተቀሰቀሰ ረብሻ ጋር ግንኙነት አላቸው ያሏቸውን የበርካታ ሙስሊሞች ቤቶችን የሕንድ የፀጥታ ኃይሎች አፍረሱ።
በኡታር ፕራዴሽ ግዛት የሚገኙት የቤቶቹ ባለቤቶች ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ተስጥቷቸው ነበር።
ሁለት የሕንድ ገዢ ፓርቲ ቢጄፒ ፓርቲ አመራሮች ፀረ እስልምና አስተያየቶችን ከሰጡ በኋላ ባለፈው ሳምንት ሕዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞውን ሲያሰማ ቆይቷል።
ከሁከቱ ጋር በተያያዘ ፖሊስ ከ300 በላይ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።
እነዚህ አስተያየቶች የተሰጡት በግንቦት ወር በቲቪ ክርክር ወቅት የቢጄፒ…
👍37❤7
13 Jun 2022, 05:19 UTC≈28,800 views49 reactionsread 3 September 2026 ዕድሜያቸው 40 የሞላ እና ጥቁር ወንዶች ሊያውቁት የሚገባ የካንሰር ዓይነት
ለበርካቶች ፕሮስቴት ሲባል ሁለቱ የወንድ ልጅ የዘር ፍሬዎች አካባቢ ወይም የዘር ፍሬ ከረጢቱ ውስጥ ያለ አካል እንደሆነ ነው የሚያስቡት።
የኩላሊት፣ የፕሮስቴት፣ የሽንት ፊኛ እና ቧንቧ ቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ፍፁም ሠለሞን ግን ፕሮስቴት ከሽንት ፊኛ በታች ያለ አካል ነው ይላሉ።
እንደ ዶ/ሩ ገለጻ ከሆነ ፕሮስቴት በወንድ ልጅ ብልት እና ፊኛ መካከል የሚገኝ እጢ ነው።
ፕሮስቴት የዘር ፈሳሽ የማመንጨት ጥቅም አለው። የወንድ ልጅ የዘር ፈሳሽ ወደ ውጪ ሲፈስ ሰባ በመቶ ያህሉን የሚያመነጨው ፕሮስቴት መሆኑን ዶ/ር ፍፁም ያብራራሉ።
የወንድ ልጅ የዘር ፈሳሽ ሀዋስ የሚዋ…
👍39❤10
13 Jun 2022, 05:16 UTC≈22,900 views50 reactionsread 3 September 2026 የነዳጅ ድጎማው ሲነሳ ምን ሊያስከትል ይችላል?
መንግሥት የውጭ ምንዛሬን በስስት ነው የሚያየው። እንደ ስእለት ልጅ።
የዶላር ጥሪት እንደዋዛ አይቋጠርማ። በብዙ አበሳ፣ በብዙ የወጭ ንግድ፣ በብዙ ተጋድሎ ነው የሚመጣው።
እንዲያም ኾኖ ጥሎበት ከአራት ቢሊዮን ዶላር አይዘልም። እሱም ቢኾን መጥቶ አይበረክትም፤ አብዛኛውን ነዳጅ ይጠጣዋል።
ይሁን እንጂ፣ እስከዛሬ ድረስ ለነዳጅ የሚከፈለው ዶላር በወጭ ንግድ ከሚገኘው ዶላር በልጦ አያውቅም ነበር።
አሁን ግን ታሪክ ተቀየረ፤ ነገሩ ከፋ።
ይህ በይፋ የታወቀው ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ነው። ለ2015 ነዳጅ መግዣ የሚያስፈልግህ ስንት ነው ሲባል 5.6 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል አለ።
እንዲህ ያለ አሃዝ…
👍36❤11👎2😱1
12 Jun 2022, 20:20 UTC≈20,700 views37 reactionsread 3 September 2026 🟥 BBCን ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ
━━⊱✿⊰━━
📌 BBC News አማርኛ
ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች እና ቴሌግራም ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም.
ድረ-ገፅ:- https://www.bbc.com/amharic
የቴሌግራም ገፅ:- https://t.me/BBC_Amharic_News1
የፌስቡክ አድራሻ:- https://m.facebook.com/BBCnewsAmharic/
@BBC_Amharic_News1
👍21❤9😱4🎉3
12 Jun 2022, 17:58 UTC≈18,400 views35 reactionsread 3 September 2026 ከዩኬ ወደ ሩዋንዳ የሚደረገው የስደተኞች ጉዞ ጉዳይ ይግባኝ ሊጠየቅበት ነው
የዩኬ መንግሥት ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ማጋዝ መጀመሩን የተቃወሙ ሰዎች ጉዳዩን ሰኞ ዕለት ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ይግባኝ ሊጠይቁ ነው።
ከፍተኛው ፍርድ ቤት የመጀመሪያው ዙር ስደተኞችን የማጓጓዝ ሥራ እንዲካሄድ ፈቃድ መስጠቱ ተሰምቷል።
31 ሰዎች ማክሰኞ ዕለት በአውሮፕላን ተጭነው ወደ ሩዋንዳ እንደሚወሰዱ ተነግሯቸዋል።
በዚህ ዓመት ተጨማሪ አውሮፕላኖች ስደተኞችን ጭነው ወደ ሩዋንዳ ይሄዳሉ።
የዌልሱ ልዑል ቻርልስ በዚህ የመንግሥት ዕቅድ ደስተኛ እንዳልሆኑ የዩኬ ጋዜጦች አስነብበዋል።
ልዑሉ በያዝነው ወር ወደ ምስራቅ አፍሪቃዊቷ ሃገር ንግሥቷን ወክለው እንደሚያቀኑ ታውቋል።
…
👍24❤11
12 Jun 2022, 17:57 UTC≈15,900 views9 reactionsread 3 September 2026 በአሜሪካ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ጠበቅ ያለ የመሳሪያ ህግ እንዲተገበር ለተቃውሞ ወጡ
በቅርቡ የተፈጸሙ ሁለት የጅምላ ግድያዎችን ተከትሎ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን ነዋሪዎች ጠበቅ ያለ የጦር መሳሪያ አጠቃቀም ህግ እንዲተገበር ለተቃውሞ ወጡ።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፎች የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ አብዛኛዎቹ እንዲተኮስብኝ አልፈልግም የሚሉ መፈክሮችን ይዘው ነበር።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ተቃውሞውን ደግፈው ኮንግረሱ “በጦር መሳሪያ አጠቃቀም ላይ የደህንነት ህግ እንዲያወጣ” ጠይቀዋል።
ምንም እንኳን የህግ ለውጥ ይመጣል ተብሎ ተስፋ ቢደረግም በሌላ በኩል የጦር መሳሪያ የህግ ለውጥ በማይፈልጉ ሪፐብሊካኖች …
❤5👍4
12 Jun 2022, 06:00 UTC≈14,900 views28 reactionsread 3 September 2026 “የልጃችንን ገዳይ ሳናውቅ አናርፍም”
ወቅቱ እንደ አውሮፓውያኑ 1984 ነው።
የ15 ዓመቱ ማርክ ቢሊንግተር በእንግሊዟ በርሚንግሃም ቤቱ አቅራቢያ በአየር ላይ የሚበረውን ‘ካይት’ ይዞ ብስክሌቱን እያሽከረከረ ወጣ።
ያችም ዕለት በሕይወት የታየበት የመጨረሻ ቀን ነበረች። ከሳምንታት በኋላ አስክሬኑ ከዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ተገኘ።
በመጀመሪያ ራሱን አጥፍቷል ተብሎ ቢታይም ከዓመታት በኋላ ግን የግድያ ምርመራ ተከፈተ።
ሆኖም አሥርት ዓመታት የፈጀ ምርመራ ቢደረግም እስካሁን በታዳጊው ግድያ የተከሰሰ ሰው የለም።
የልጃችንን ገዳይ ሳናውቅ አናርፍም ያለው ቤተሰቡ ከ38 ዓመት በኋላ ገዳዩን ለማግኘት የራሳቸውን ምርመራ ጀምረዋል።
የማደጎ ቤተሰቦቹ ሮይ እና ዊንፍ…
👍20❤6😢2
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @BBC_Amharic_News1. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.