12 Nov 2025, 11:17 UTC73 viewsread 9 August 2026 Photo
እየዋኘ ካዕባን ጠዋፍ ያደረገው የአሏህ ባሪያ ... 🌹
.
በ1941 መካ ከባድ ዝናብ ለሳምንት ያህል ያለማቋረጥ ጥዋት ማታ ዘንቦ ነበር። በዚህም ምክንያት የዝናቡ ውሃ መስጊደል ሐራምን ሞላው።መስጂደል ሐረምን የሞላው የውሃ መጠን ከአንድ ሜትር ተኩል በላይ ከፍ አለ።እንዲያውም ሐጀር አል አስወድ (ጥቁሩ ድንጋይ) ደርሶ ውጦት ነበር ተብሏል።
በዚያ ልዩ ሁኔታ ውስጥ ባህሬናዊ የሆነው የያኔው ወጣት አሊ አል-አዋዲ እየዋኘ በካዕባ ጠዋፍ ሲያደርግ (ሲዞር) የሚያሳይ ብርቅዬ ፎቶ ተነሳ። ይህም ትዕይንት በመስጊደል ሐራም የማይረሳ ነው ታሪክ ሆነ።
ይህ የሆነውም ከባሕሬን መካ የተገኙት አሊ አል-አዋዲ ከወንድሙ፣ ጓደኞቹ እና ከመምህሩ ጋር በመሆን ወደ መስጊደል ሐራ…
Signed #اوتا حكم 🇵🇸
11 Nov 2025, 15:20 UTC59 viewsread 9 August 2026 Photo
ልምከርህ!
ይህ ፈተና በበዛበት ዘመን በማንም ፍቅር አትዋልል። ከሰዎች ጋር ያለህን ውዴታ ፈር አስይዘው፤ ስትወድም ድንበር አትለፍ ስትጠላም እንደዝያው። ሚዛንህንም ጠብቅ።
ዛሬ ያለ ገደብ የወደድኸው ነገ ዋና ጠላትህ፤ ዛሬ ያለ ገደብ የጠላኸው ነገ ዋና ወዳጅህ ሊሆን ይችላል'ና ገደብ ይኑርህ።
የትኛውንም አካል በገዛ የልብህ ዙፈን ላይ ተቆጣጣሪ አድርገህ ለፍቅር አትሹመው፤ አላህ እና ነቢ ሰዐወ ሲቀሩ። ከዘመድም ይሁን ከወዳጅህ ፈፅሞ መልካምን ውለታ ብቻ አትጠብቅ። መሬቶች ናቸው'ና የዘራህባቸውን ነው እሚያበቅሉልህ።
‹‹ከአላህ ወልዮች አንዱ ነህ›› ብለው ቢያወድሱህ ወይም ‹‹የመናፍቃን ቁንጮ ነህ ›› ብለው ቢዘልፉህ ለውዳሴውም ለዝልፍያውም ግድ እንዳይ…
Signed #اوتا حكم 🇵🇸
6 Nov 2025, 07:40 UTC69 viewsread 9 August 2026 1. አንድን ሰው (እንደሰማህ እያወቅክ) በተከታታይ ከሁለት ጊዜ በላይ አትጥራው፡፡ መልስ ካልሰጠህ ምናልባት የሆነ እየሰራው ያለው ነገር ሊኖር እንደሚችል ወይም በራሱ ምክንያት መልስ ሊሰጥህ እንዳልፈለገ ይግባህ፡፡
2. የተበደርከውን ገንዘብ አበዳሪህ ከመጠየቁ በፊት መልስ፡፡ ምን ያህል ለቃልህ ታማኝና ሃላፊነት የሚሰማህ ሰው እንደሆንክ ማረጋገጫው እሱ ነው፡፡በአንጻሩ የተበደርከውን ጃንጥላም ቢሆን እስክሪፕቶ ሳትጠየቅ መመለስ ቁምነገረኝነትህን ያሳያል፡፡
3. ማንም ሰው ሊጋብዝህ ወደሆቴል ቢወስድህ ከሜኑው ውስጥ ውድ ዋጋ የሚያወጣውን ምግብ አትዘዝ፡፡ሰዎች ምን ደግ ቢሆኑ ይሉኝታ የሌለው ሰውን መታዘባቸው እንደማይቀር አትርሳ፡፡
4. ማንንም ሰው “ለ…
Signed #اوتا حكم 🇵🇸
9 Sept 2025, 07:52 UTC105 viewsread 9 August 2026 ጀሀነም የሚገባው ወደ ጀሀነም ጀነት የሚገባውም ወደ ጀነት
ከገባ በኋላ አንድ ተጣሪ እንዲህ ሲል ይጣራል!
አንተ ሙሐመድ! ተደሰተክ ወይ?
እርሳቸው እንዲህ ይለሉ«ጌታዬ! ወላሂ አልተደሰትኩም። ከኡመቶቼ
እሳት ውስጥ የቀረ አለ»
አላህም ለመላኢኮች «ቅንጣት ታክል ኢማን በቀልቡ ያለውን ሁሉ
ከእሳት አውጡ» በማለት ያዛቸዋል። ከዚያም ጀሀነም በሯ
ይከፈትና የተወሰነው የሙስሊሙ ክፍል ወጥቶ ወደ ጀነት
ይተማል።
አላህ በድጋሚ «ሙሐመድ ሆይ! ተደሰትክ?» ይላቸዋል።
«ጌታዬ ባንተ እምላለሁ! አሁንም ከህዝቦቼ የቀሩ አሉ» ብለው
ያለቅሳሉ!
አላህም ለመላእክቱ «አይኑ የትንኝ ራስ የምታክል እንባም ብትሆን
እኔን ፈርታ ያነባችን ሁሉ አውጡ» በማለት ያዛል።
ከዚያም «ያ ሙሐ…
Signed #اوتا حكم 🇵🇸
27 Aug 2025, 18:57 UTC113 viewsread 9 August 2026 File
ስጦታህ ብዙ ነው...አላህ....
እንደምርጫህ ብለህ ትተኸኝ በነበር
በህይወት መንገዴ ስህተት ያይል ነበር
አልሀምዱሊላሂ
ለነሳኸኝ ሁሉ ጠይቄህ ላጣሁት
ስጦታህ ብዙ ነው
ያላንዳች ጥያቄ ካንተ ያገኘሁት
እስልምኗን እንኳን
አድለኸኝ እንጂ መች እኔ መረጥኩት
ታዲያ ከዚህ በላይ
መሠጠት መች ኖሮ ምን እሻለሁ ባለም
አንተንም ለማምለክ
መመረጥ ግድ ነው ለሁሉም ባይገባም
#Awitahikem
#2017
Signed #اوتا حكم 🇵🇸
1 Jun 2025, 06:11 UTC171 viewsread 9 August 2026 ዝምድናን የመቀጠል ጥቅሞች፡
1- ዝምድናን መቀጠል ከአላህ ጋር ለመገናኘት ሰበብ ይሆናል፡፡ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹ አላህ ፍጡራንን ፈጥሮ ሲጨርስ ዝምድና ከመቆረጥ በአንተ እጠበቃለሁ በማለት ጌታዋን ተማፀነች፤ አላህም አዎ! የቀጠለሽን ብቀጥለው የቆረጠሸን ብቆርጠው አያስደስትሽምን? አላት፤ አዎ ያስደስተኛል አለች፤ አላህም እሱን አድርጌልሻለሁ አላት፡፡››
2- ዝምድናን መቀጠል ጀነት ለመግባት ሠበብ ነው፡፡ አንድ ሰው ጀነት የሚያስገባውንና ከእሳት የሚያርቀውን ተግባር ነቢዩን (ሶ.ዐ.ወ) ጠየቀ፡፡እንዲህም ሲሉ መለሱለት፡ ‹‹ ምንንም ሳታጋራ አላህን ብቻ ታመልካለህ፤ ሶላትን ጠብቀህ ትሰግዳለህ፤ ዘካን ታወጣለህ፤ ዝምድናን ትቀጥላለህ፡፡››…
Signed #اوتا حكم 🇵🇸
8 Jun 2024, 08:19 UTC325 viewsread 9 August 2026 አንድ ሰው ነበረ እጅግ በጣም ትንሽ መሬት የነበረችው፡፡ ከመሬቷ ማነስና ከኑሮው መጉደል የተነሣ ሲቆፍር በምሬት "ወይ አዳም... ወይ አዳም... ወይ አዳም" ማለትን ያዘወትር ነበር፡፡ ይህን ደጋግሞ የሰማ አንድ ባለፀጋ ለምን እንዲህ እንደሚል ሲጠይቀው "ከተዋበ ገነት በገዛ ጥፋቱ ወጥቶ ለእኛ መከራ ያተረፈ አዳም ነው፡፡ የአምላኩን ትዕዛዝ ቢሰማ ኖሮ ይህ የኑሮ ችግር በእኔ ባልደረሰ ነበር" በማለት ገለፀለት፡፡ ባለፀጋውም እኔ ብዙ ሀብት ያለኝ ብሆንም ወራሽ የለኝምና እኔ ቤት ገብተህ ውረሰኝ አለውና ወደ ቤቱ ወስዶ ያለውን ሁሉ ወርቁን፣ ብሩን፣ ከብቱንና እህሉን፣ አንዲት ጠርሙስ ስትቀር አስረከበው፡፡ ይህች የእኔ ንብረት ናትና እንዳትነካብኝ በማለት ጠርሙሷን…
Signed #اوتا حكم 🇵🇸
13 Apr 2024, 10:22 UTC288 viewsread 9 August 2026 #ከእለታት አንድ ቀን አንድ የፐርሺያ ንጉሥ ሁለት ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ ፈረደባቸው፡፡
በመጨረሻም፤ “የሞት ፍርዱ ከመፈፀሙ በፊት የፈለጋችሁትን ተናገሩ” ሲል እድል ይሰጣቸዋል፡፡ አንደኛው፤ “ምንም የምናገረው የለኝም” አለ ሁለተኛው፤ ንጉሡ ምን ያህል ፈረሳቸውን እንደሚወዱት ስለሚያውቅ፤“ንጉሥ ሆይ፤ የአንድ ዓመት ጊዜ ከሰጡኝ ፈረስዎ ወደ ሰማይ እየከነፈ እንዲሄድ ላስተምረው እችላለሁ” አላቸው፡፡
ንጉሡ በሰማይ ላይ የሚከንፍ ፈረስ እየጋለቡ ሲሄዱ ታያቸው፡፡ ካሁኑ ነሸጣቸውና ይቁነጠነጡ ጀመር፡፡“ይሁን አንድ ዓመት ሰጥተንሃል፡፡ ፈረሱን አምጥተው እንዲያስረክቡህ አደርጋለሁ” አሉ፡፡ የመጀመሪያው እሥረኛ በምንም አይነት ፈረስ እንደማይበር ስለሚያውቅ ፈረስ አ…
Signed #اويتا حكم
8 Apr 2024, 13:36 UTC244 viewsread 9 August 2026 Photo
እንደዚያች "ሴትዮ" አትሁኑ!
_____
ረመዷን፣ ሲገባ ዝም ብሎ አልገባም ነበር። በኢባዳዎች እንድንበራታና ከወንጀሎች እንድንርቅም ሰበብ ሆኖ የመልካም ሰሪነቱን፣ አሏህን የማስታወስና የመፍራቱን ትጥቅ እንደዬልካችን አስታጥቆን እንጂ።
ታዲያ ረመዷንን ስንሸኝ፦ ረመዷን ሲሄድ፦
"በመግባቱ" ያለበሰን የመልካም ሰሪነት ሸማ እና ያስታጠቀን የዒባዳ ትጥቅ ከኛው ጋር አብሮን ሊዘልቅ እንጂ መውጣቱን ተከትሎ ሊወጣብንና
ሊወልቅ ሊፈታብን አይገባም!
አዎን! ረመዷን ሲገባ፦ የጌታችን ትዕዛዝ ተግባሪና ክልክላቱን ራቂዎች ልንሆን ዘንድ የገባነው ቃልኪዳን
ሊፈርስብን አይገባም!
ካፈረስን ግን፦ የዚያች "ሴትዮ" ተረት በኛ ላይም ይደገማል!
አሏሁ ተዓላ እንዲህ ይላል…
Signed #اويتا حكم
4 Apr 2024, 14:52 UTC198 viewsread 9 August 2026 Photo
አላህ ላይ መመካት
ከእለታት አንድ ቀን፤ በኢማም አህመድ ዘመን ይኖሩ ለነበሩትና በጣም በአላህ ላይ ይመኩ ለነበሩት፤ ለሃቲም ኢብኑል አሰም እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፡-
በአላህ ላይ የመመካት ሁኔታ እንዴት ሊሳካሎት ቻለ?
ከዚያም እሳቸው እንዲህ ብለው መለሱ ፡-
("በአላህ ላይ መመካት በአራት ነገሮች ምክንያት ተሳክቶልኛል፡-
አንደኛ፡- ሪዝቄን /ሲሳዬን/ ከእኔ ሌላ ማንም ሰው ሊወስደው እንደማይችል አወቅኩኝና ልቤ ተረጋጋ…
ሁለተኛ፡- ስራዬንም ከእኔ ሌላ ማንም አሳምሮ ሊሰራው እንደማይችል አወቅኩኝና በስራዬ ተጠመድኩኝ
ሶስተኛ፡- አላህ /ሱ.ወ/ እኔን ሁሌም እንደሚያየኝ አወቅኩኝና እሱን እያመፅኩት እንዳያየኝ አፈርኩኝ
አራተኛ፡- ሞት እንደሚጠብቀኝም…
Signed #اويتا حكم
1 Apr 2024, 17:06 UTC189 viewsread 9 August 2026 Photo
ፈረስ በጮሌነት አትብለጥህ!
قال ابن الجوزي: إن الخيل إذا شارفت نهاية المضمار بذلت قصارى جهدها لتفوز بالسباق .. فلا تكن الخيل أفطن منك !
በውድድር ያለች ፈረስ፣ ፍፃሜው ላይ ስትደርስ በድል ለማጠናቀቅ ስትል "ያለ የሌለ" አቅሟን ትጠቀመዋለች። እናም… ፈረስ በጮሌነት ካንተ የተሻለች አትሁን!
فإنما الأعمال بالخواتيم .. فإنك إذا لم تحسن الإستقبال لعلك تحسن الوداع !!
የስራ ውጤት የሚወሰነው በመቋጫው ነው፤
አንተ… ጅማሮው (መግቢያው) ላይ ብታጓድልም እንኳ መደምደሚያውን ልታሳምር ትችላለህ!
وقال الحسن البصري: "أحسن فيما بقي ي…
Signed #Awita Hikem
22 Mar 2024, 09:04 UTC182 viewsread 9 August 2026 Photo
የታየህን ያህል ተንቀሳቀስ አስተማሪ ታሪክ!
አንድ ምሽት ላይ አባት ልጁን ወደ ሲኒማ ቤት ሊወስደው ውጪ መንገድ ላይ መኪና ውስጥ እየጠበቀው ነው፡፡ ልጅ ከቤት እንደወጣ በጣም ስለጨለመበት ስልኩን አውጥቶ አባቱ ጋር ደወለ፡፡
• ልጅ፡- “አባዬ እንዴት ልምጣ? ጨለማ ስለሆነ አይታይም”፡፡
• አባት፡- “ምን ያህል ይታይሃል?”
• ልጅ፡- “አምስት እርምጃ ያህል ብቻ ነው የሚታየኝ”
• አባት፡- “አምስት እርምጃ ተራመድ”
• ልጅ፡- “እሺ” (አምስት እርምጃ ተራመደ)
• አባት፡- “አሁንስ ምን ያህል ይታይሃል?”
• ልጅ፡- “አሁንም ሌላ አምስት እርምጃ ያህል ርቀት ይታየኛል”
• አባት፡- “በፊትህ የሚታይህን አምስት አምስት እርምጃ እያልክ ከመጣህ እኔ ጋ ትደ…
Signed #Awita Hikem
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Awitahikem. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.