9 Sept 2025, 09:37 UTC74 views4 reactionsread 9 August 2026 እዚህ ላይ የሚያስደንቀው የማርያም ዝምታ ነው፡፡ ማርታ ስትከስሳት ጌታችን መልስ ሠጠላት እንጂ ማርያም አንድም ቃል አልተነፈሰ
ችም፡፡ ‹ቃሉን መስማት ይበልጣል ብዬ ነው!› ብላም አልተመጻደቀችም፡፡ ዝም አለች፡፡ በእርግጥ እኅትዋ ስትከስሳት ምን ተሰምቷት ይሆን? በአፍዋ ዝም ብላ በልብዋ እየተሳደበች ይሆን እንዴ? አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው ‹የለም በውስጥዋም ክፉ ሃሳብ አልነበረም› ይላል፡፡ ‹እንግዲህ እንደ ማርያም አርምሞና ትዕግሥትን ገንዘብ እናድርግ› (ናጥሪ እንከ አርምሞ ወትዕግሥተ ከመ ማርያም) በማለት በአፍዋ አርምሞን (ዝምታን) ብቻ ሳይሆን በልብዋም ትዕግሥትን ገንዘብ አድርጋ እንደነበር ይመሰክራል፡፡
ያስደንቃል! እጅግ በምታከብረው ጌታ ፊት የገዛ እ…
❤1👍1🥰1🙏1
Signed 𝕐㋛︎ꋊ𝔸꓄ℍ㋛︎Ⱬ
9 Sept 2025, 09:37 UTC52 views1 reactionsread 9 August 2026 +++ ማርታም ታገለግል ነበር+++
ማርያምና ማርታ እኅትማማቾች ናቸው፡፡ ‹ኢየሱስም ማርታንና እኅትዋን ፣ አልዓዛርንም ይወድ ነበር› (ዮሐ. 11፡5) ስለዚህም በቢታንያ በሚገኘው ቤታቸው እንግዳ ሆኖ ተገኘ፡፡ እጅግ ለሚወዱት ጌታ ፍቅራቸውን ለመግለጽ እኅትማማቾቹ ይሻላል ብለው ያሰቡትን ሁለት የተለያየ ዓይነት አቀባበል አድርገውለት ነበር፡፡ ማርታ ለምትወደው እንግዳዋ ምግብ ለማቅረብ ብዙ ተጨንቃ በጓዳ ሥራ ላይ ተወጠረች፡፡ ‹ለታላቁ ጌታ ምን ላቅርብለት ይሆን?› ብላ ተጠበበች፡፡
መቼም የምናከብረው ሰው እንግዳ ሆኖ ሲመጣ ሙያውም ሊጠፋብን ይችላል፡፡
ማርታም የገጠማት ይኼው ነው ፣ ምኑን ከምኑ አድርጋ እንደምታቀርብ ግራ ገባት ፤ ጌታችን እንዳለው ‹በብዙ ነ…
❤1
Signed 𝕐㋛︎ꋊ𝔸꓄ℍ㋛︎Ⱬ
2 Dec 2024, 09:07 UTC109 views2 reactionsread 9 August 2026 መላእክት ከጌታ ጋር ነበሩ:: በዲያቢሎስ በተፈተነ ጊዜ “ቀርበው አገለገሉት” (ማቴ. 4:11) ወደ መስቀል ሲሔድ ተጨንቆ ሲጸልይ “የሚያበረታው መልአክ ታየው” (ሉቃ. 22:43) ዕርቃኑን ሲሰቀል አዝነው “በማይታይ ክንፋቸው ጋረዱት” (መጽሐፈ ቅዳሴ) ከሞት ሲነሣ በባዶ መቃብሩ ነጭ ለብሰው ቆሙ:: እንደሞተ አስበው ሽቱ ሊቀቡት ለመጡት ሰዎች “ሕያዉን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል” ብለው መለሱአቸው:: ሲያርግም በእልልታና በመለከት ድምፅ አጀቡት::
መላእክት ለክርስቲያን ሁሉ እንዲህ ናቸው:: በዲያቢሎስ ስትፈተን ቀርበው ይደግፉሃል:: በመከራ ስትጨነቅ ያበረቱሃል:: ዓለም ዕርቃንህን ስትሰቅልህ ከውርደት በክንፋቸው ጥላ ይከልሉሃል:: ከኃጢ…
👀1👍1
Signed ꪗꪮ᭢ꪖᡶꫝꪮɀ 🌱SEED
28 Nov 2024, 09:21 UTC60 viewsread 9 August 2026 #ጾመ_ነቢያት
እግዚአብሔር አምላካችን ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ መልበሱን፣ ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ወደ ግብጽ ግብር መሰደዱን፣ በባሕረ ዮርዳኖስ መጠመቁን፣ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ማብራቱን፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል ልዩ ልዩ ዓይነት መከራ መቀበሉን፣ መሰቀሉን፣ መሞቱን፣ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ ማረጉንና ዳግም ለፍርድ የሚመጣ መኾኑን በአጠቃላይ የማዳን ሥራውን በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው አስቀደመው በትንቢት ተናግረዋል፡፡ ትንቢቱ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው ኾኖ ዓለምን የሚያድንበትን ጊዜ በ…
Signed 𝑺𝑰𝑴𝑬𝑹𝑺𝑶𝑵 👑
28 Nov 2024, 09:21 UTC57 viewsread 9 August 2026 “አንተ ሰው የበደለህን ይቅር ሳትል ወደ ጾም አትግባ፡፡ አንተን በበደለህ ሰው ላይ በቁጣ እያለህ የምትጾመው ጾም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርም አይቀበለውም፡፡
ጾምህን በፍቅርና እርሱን ተስፋ በማድረግ በእምነት ካላደረግኸው አንተን ፈጽሞ ሊረዳህ አይችልም፡፡ በጠብ ሆኖና በውስጡ ጠላትነትን አንግሦ የሚጾም ጸዋሚ እግዚአብሔርን ይጠላዋል፤ ከመዳንም ፈጽሞ የራቀ ነው፡፡"
(ቅዱስ ኤፍሬም)
🇯 🇴 🇮 🇳 ♻️ 🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
✥ @Atronise_tewahedo ✥
✥ @Atronise_tewahedo ✥
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
Signed 𝑺𝑰𝑴𝑬𝑹𝑺𝑶𝑵 👑
28 Nov 2024, 09:21 UTC79 viewsread 9 August 2026 "ብዙዎች ቢጾሙም ለእነርሱ መጾም ማለት የጾም ምግብ መብላት ማለት ነው። እነርሱ በጾም ወቅት ለራሳቸው የሚበሏቸውን በጣም ጣፋጭና ገንቢ ምግቦችን ያዘጋጃሉ አልፎ ተርፎም ውድና የማይገኙ ቅመማ ቅመም ይጨምሩባቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ የጾም ቅቤ፤ የጾም አይብ፤ የጾም ቸኮላታ እንዲያገኙ ይጠይቃሉ። በአጠቃላይ የጾም ምግቦቻችን ብዛትና ዓይነት ከልክ እጅግ ያለፈ ነው።
በዚህም ነብዩ ዳንኤል ስለ ጾም የተናገረውን ይዘነጉታል። "በዚያ ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ። ማለፊያ እንጀራ አልበላሁም ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም ሦስቱንም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም።" (ዳን 10፥2-3) በዚህ አባባሉ ውስጥ "ማለፊያ እንጀራም አልበላሁ…
Signed 𝑺𝑰𝑴𝑬𝑹𝑺𝑶𝑵 👑
21 Nov 2024, 03:55 UTC309 views2 reactionsread 9 August 2026 የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሢመት
ሚካኤል ማለት መኑ ከመ እግዚአብሔር ሚ ዕፁብ ነገር ማለት ነው፤ በዕብራይስጥ ‹‹እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው!›› ማለት እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠቅሳሉ፡፡
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ላይ እንዳሰፈሩት ደግሞ የስሙን ፊደላት በመተንተን እንዲህ ተርጉመውታል፤ ሚ-መኑ፣ ካ-ከመ፣ ኤል-አምላክ፤ ‹‹መኑ ከመ አምላክ፤ እንደ አምላክ ማን ነው!›› (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ)
በዚች ዕለት እስራኤልን በሙሴና በአሮን መሪነት ባሕር ከፍሎ ጠላት ገድሎ፣ መና አውርዶ፣ ደመና ጋርዶ በብዙ ሣህል ታድጎ ከምድረ ግብጽ ማውጣቱ ይነገራል፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን…
🥰1🙏1
Signed 𝑺𝑰𝑴𝑬𝑹𝑺𝑶𝑵 👑
19 Nov 2024, 18:14 UTC55 viewsread 9 August 2026 ሰው ከ1 እስከ 20 አመቱ ንፋስ ነው። ይሮጣል ይከንፋል አንዱን ይዞ ሌላኛውን ለመያዝ። ከአንዱ አምሮት ወደሌላኛው አምሮት። እድሜው እራሱ 20 ላይ እንዴት እንደደረሰ አይታወቀውም። ከ20 እስከ 40 ደግሞ እሳት ነው። ጀብደኝነት ጉልበተኝነት ሁሉንም እችላለው ባይነት ይወርሰዋል። ከእሱ ውጭ ማንም የለም የትኛውም ሰው አይታየውም።
ከ40 እስከ 60 ውሃ ነው። ቅዝቅዝ ይላል ይረጋጋል። ንግግሩ ዘለግ ያለህ ዝምታ የሚያበዛ ሰው ይሆናል። ከ60 እስከ 80 መሬት ነው። ያጎነብሳል የእርጅና ግዜ ነው። አስታራቂ፣ ትዳር አስጀማሪ እና ለቅሶ አስለቃሽ ቀድሞ ተሰሚ የሚኮንበት ግዜ ነው። እዛ እድሜ ላይ ያሉ ሰዎች "አሄ አፈር ለምንሆነው" "ምንድነው ይሄ ሁሉ ይኸው ትናን…
Signed 𝐘𝐎𝐍𝐀𝐓𝐇𝐎𝐙
13 Nov 2024, 12:51 UTC72 viewsread 9 August 2026 #ትላንት_ዛሬ_ነገ
ዘመን ሳይዘምን ገና፣ ጸሐይ ሳትታይ በፊት፣ ጨረቃም ሳትወጣ ቀድሞ፣ ሰማይ ሳይዘረጋ፣ ምድርም ሳትቆም፣ ከዋክብት ሳይታዩ፣ ወንዞች ሳይፈሱ፣ ውቂያኖስ ሳይሞላ፣ አዕዋፋት ሳይበሩ፣ ፍጥረታት ሳይፈጠሩ፣ አራዊት ሳይኖሩ፣ ሰውም በምድር ላይ ሳይታይ፣ የሚታዩ እና የማይታዩት ፍጥረታት ሳይኖሩ፣ አመታት ሳይቆጠሩ፣ ወራት ሳይፈራረቁ፣ ሳምንታት ሳይቀያየሩ፣ ቀናትም አሃዱ ሳይባሉ፣ ሰዓታት ሳይቆጥሩ፣ ደቂቃና ሰከንዶች ሳይጀምሩ ብቸውን የነበረ፣ ከዘላለም በፊት የከበረ፣ ከመጀመሪያ በፊት ሆኖ መጀመሪያን ያስጀመረ፣ ከሁሉ ነገረ በፊት የነበረ፣ አንድ ተብሎ ቁጥር የማይጀመርለት፣ ለዘመኑ ቁጥር የሌለው እርሱ እግዚአብሔር ነው። ትላንት የነበረ እርሱ አምላካች…
Signed ♜ 𝚈㋡𝙽𝙰𝚃𝙷㋡𝚉 ♜ 🌱SEED 💠
10 Nov 2024, 16:45 UTC64 views1 reactionsread 9 August 2026 ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡
ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አ…
🙏1
Signed 𝑺𝑰𝑴𝑬𝑹𝑺𝑶𝑵 👑
7 Nov 2024, 18:12 UTC64 views1 reactionsread 9 August 2026 "ተወዳጁ ልጅሽ እንዲመግበኝ ትለምኝልኝ ዘንድ እማጸንሻለሁ"
እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። የመድኃኒት እናት ሆይ በመዓልትም በሌሊትም አማላጅ ትሆኝኝ ዘንድ እሰግድልሻለሁ። እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከእርሱ የሚገኘውን ኃይልን ይሰጠኝ ዘንድ ከአንቺ ወደ ተወለደው ልጂሽ እንድትለምኝልኝ እማጸናለሁ። በመወለዱ ድኅነት የተገባሽ ሆነሻልና። በሔዋን ውድቀት ሆነ። አብ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት ሰላምን የላከልሽ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። ሰላምታን ሰጠሽ ሰገደልሽም። ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ሰላምታ ይገባሻል። እነሆ ትጸንሻለሽ ልጅም ትወልጃለሽ፣ ስሙንም አማኑኤል ትይዋለሽ።…
🥰1
Signed ♜ 𝚈㋡𝙽𝙰𝚃𝙷㋡𝚉 ♜ 🐾
7 Nov 2024, 18:12 UTC49 viewsread 9 August 2026 "ብርሃን ወደ አንድ ቤት ውስጥ ሲገባ ጨለማን እንደሚያስወግድ ሁሉ፤ እግዚአብሔርን መፍራት ወደ አንድ ሰው ልብ ሲገባም አለማወቅን (በኃጢአት የሚወድቅባትን) ያስወግዳል።"
አባ እንጦንስ
🇯 🇴 🇮 🇳 ♻️ 🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
✥ @Atronise_tewahedo ✥
✥ @Atronise_tewahedo ✥
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
Signed ♜ 𝚈㋡𝙽𝙰𝚃𝙷㋡𝚉 ♜ 🐾
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Atronise_tewahedo. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.