አባ ወዳገራቸው መመለስ እንዳሰቡ ልብስ እንዲሩላቸው ከሸማኔዎች ጋር ይዋዋላሉ፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላም በበቅሎ ታጅበው ወደቤተመንግስት ሲወርዱ ሸማኔዎ እንዳዩዋቸው ‹‹ጃንሆይ የሚያከብሯቸው ቄስ መጡ›› ብለው ፈጥነው ሲነሱ አንዱ አመለጠው፡፡ ይኽኔ አባ ሆዬ ‹‹ልብሴን እስካሁን ሳትሰሩልኝ መቆየታችሁ ሲገርመኝ አሁንማ እስከመቋጠሩም ተዋችሁታ!›› አሏቸው፡፡

Channel
አለቃ ገብረሐና | 📖😆
@AlekaGebreHana
On this record: Topic · Growth · Engagement · Posts · Cite this entry
1,184subscribers
-6 since we began measuring on 6 August 2026
Risers and fallers across the register · movement among entries of 1,000–3,162.
Register entry
| Telegram ID | -1001263259911 |
|---|---|
| Type | Channel |
| Username | @AlekaGebreHana |
| Created | 23 December 2017 — measured — dated from the channel’s first post |
| First recorded | 6 August 2026 |
| Last confirmed live | 17 September 2026 |
| Measurements held | 14 |
| Confirmed unchanged | 1 time, most recently 17 September 2026 |
| On Telegram | t.me/AlekaGebreHana |
Topic
Literature — a classification, not a measurement. An on-box language model (Qwen3.6-35B-A3B-FP8, prompt version 1) read this channel’s own recent posts on 18 September 2026 and assigned it the closest of 31 fixed categories, at 51% confidence. This is a model’s judgement about what the channel is likely to be about, not a fact this register measured the way a subscriber count or a view count is measured — it can be revised on a later pass, and it carries no weight anywhere else on this page. How this classification works, and why it has no browse page of its own yet.
Growth
| Measured (UTC) | Subscribers | Change |
|---|---|---|
| 17 Sept 2026, 13:40 | 1,184 | -3 |
| 13 Sept 2026, 13:02 | 1,187 | +2 |
| 9 Sept 2026, 23:41 | 1,185 | +3 |
| 4 Sept 2026, 14:17 | 1,182 | -4 |
| 1 Sept 2026, 02:46 | 1,186 | -2 |
| 28 Aug 2026, 22:46 | 1,188 | -2 |
| 26 Aug 2026, 05:48 | 1,190 | -2 |
| 23 Aug 2026, 08:58 | 1,192 | -4 |
| 19 Aug 2026, 17:34 | 1,196 | +1 |
| 16 Aug 2026, 08:18 | 1,195 | +1 |
| 12 Aug 2026, 16:37 | 1,194 | +1 |
| 10 Aug 2026, 00:02 | 1,193 | +3 |
| 6 Aug 2026, 08:49 | 1,190 | no change |
| 6 Aug 2026, 06:06 | 1,190 | first reading |
Engagement
14 posts held, back to 23 December 2017 — the reader has not yet reached the start of this channel’s public history, so older posts may sit further back, unread. Read across 1 page of Telegram’s post history, 20 posts per page.
Nothing published in the last 30 days. ERR and ER are rolling 30-day measures, so there is nothing to compute — we hold 14 posts for this entry, the most recent from 21 March 2020. An engagement rate over an empty window would be a number about nothing.
Recent posts
የረሃቡ ዘመን እንደተገባደደ አንዲት የጎጃም ሴት የቃና ዘገሊላን በዓል ምክንያት በማድረግ ጠበል ጠዲቅ እንዲቀምሱ ትጠራቸዋለች፡፡ አባ ገብረሐናም ጥሪውን አክብረው እንደደረሱ ሴትዬይቱ ጠላውን እየቀዳችላቸው፣ ‹‹አባቴ የችኮላ ስራ ሆኖ ጠላው ትንሽ ቀጠን ብሏል፡፡›› ብትላቸው፣ ‹‹አይ አካላቴ የምናከብረውስ የውሃ በዓል አይደል?›› አሏት ይባላል፡፡
አለቃን አንዲት ጉብል ነች አሉ ያሸነፈቻቸው።ዝናዋን ይሰሙና ልጅቱዋ ቤት ሄድው አሳድሩኝ ይላሉ። ቤት ለእንግዳ ይባሉና እራትም በልተው የሚተኙበትን መደብ ጉብሊቱዋ ታሳያቸውና ትንሽ አጎዛ (የበግ /የፍየል ቆዳ) አምጥታ ትሰጣቸዋለች። አለቃም ይቺማ ታንሰኛለች ሌላ ጨምሪልኝ ይላሉ። ጉብሉዋም እሱን ይጨርሱና አክልሎታለሁ አለቻቸው አሉ።
አንደዜ ደግሞ እዚያው ጎጃም እንዳሉ የንጉሥ ተክለሃይማኖት ወዳጅ ይሞታሉ፡፡ ከቅዳሴ ውጭ ዜማውና ለቅሶው ቀልጦ ሳለ አንዱ ያገሬው ተወላጅ አባን «ዜማው እንዴት ነው?» ብሎ ቢጠይቃቸው ፣ «ካገራችሁ ደብተራስ ያገራችሁ አልቃሽ ትሻላለች!» ብለው መለሱለት፡፡
አጤ ቴዎድሮስ ከስልጣን እንዲገለበጡ ካሴሩት ቀንደኛ ካህናት ኣንዱ አባ ገብረሐና መሆናቸው እንደተደረሰበትም አባ ገብረሐና እንዲታሰሩ አዘዙ፡፡ ይህን የሰሙት ገብረሐናም ሸሽተው ዘጌ ገጻም ተደበቁ፡፡ አባ ገብረሐና እዚያው ሁለት አመታት በስደት እንደተቀመጡ ይወሳል፡፡ በዚህ ህይወታቸው ወቅት ረሃብ ይገባና ይቸገራሉ፡፡ አንድ ቀን ለወስፋት ማስታገሻ የምትሆን ቁራሽ ዳቦ ከአገልጋያቸው ጋራ ተካፍለው ከበሉ በኋላም ዲያቆኑ ተነስቶ «ጌታዬ ስብሃት ልበል? (ምስጋና ላቅርብ)» ቢላቸው ፣ «ተው ልጄ ቀለዳችሁብኝ ብሎ ይቆጣል፡፡» አሉት ይባላል፡፡
የአለቃ ገብረሐና ጥርስ አያስከድኔ ጨዋታ ያነሆለላቸው አንዱ ደጃዝማች አባን ወዳጅ ያደርጓቸዋል፡፡ በየጊዜው ቤታቸው እየወሰዱም ያበሏቸው ፤ ያጫውቷቸውም ነበር፡፡ እንደተለመደው አንድ ቀን እራት ጋብዘዋቸው ጮማ እየቆረጡ ሲያወጉ ደጃዝማች ግብዣውን ያሳመሩ መስሏቸው ‹‹ይብሉ እንጂ ፤ ሰው እኮ ደስ የሚለው የደገሰውን ሲበሉለት ፡ የወለደው ሲስሙለት ነው›› ቢሏቸው ፤ አባ ብድግ ብለው የደጃዝማቹን ቆንጅዬ ልጅ ሳም ፤ ሳም ፤ ደጋመው ሳም አደረጓት፡፤ ‹‹መነው አባ?›› ብለው ቢጠይቋቸው፤ ‹‹ጌታዬ ምግቡን እስኪበቃኝ ተመገብሁ፡፡ የወለደውን ሲስሙለት ደስ ይለዋል ስላሉኝ ደግሞ ለርስዎ ስል የሚወዱዋትን ልጅዎን ሳምኩልዎ እንጂ ምን አጠፋሁ?›› በማለት መለሱላቸው፡፡
ሰንበት ብላ ደግሞ ድንቡሼዋ ጎረቤታቸው አዲስ ልብሷን ልታስመርቅ እየሮጠች ወደ ቤታቸው ስትመጣ አመለጣትና መአዛው ቤቱን አወደው፡፡ አባ ገብረሐና ግን እንዳላወቀ ሰው ‹‹በውሃ ይለቅልሽ ፤ ጥሎሽ ይሂድ›› ብለው ከመረቋት በኋላ ‹‹እንግዲህ ይህችን ከሰው ዘንድ ስትደርሽ ብን እያደረግሽ ኩሪ›› ብለው አሰናበቷት፡፡
ከጥቂት ቀናት በኋላም ያቺው ገልቱ ሴት ምሣ ትጋብዛቸዋለች፡፡ ሊቀ ካህናት እግራቸውን አንፈራጠው ዶሮአቸውን ሲኮሞኩሙ ነበር የደረሱት፡፡ አለቃ የዶሮውን ጭንቅላት ድስቱ ውስጥ እንዳለ አይኑ ፈጦ ታያቸው፡፡ ይኸኔ አጅሬ ሳቅ ብለው ፤ ‹‹ዶሮ ምን እኔ ላይ ታፈጥብኛለህ? እኔ አላረድኩህ!›› አሉት፡፡ ገበታው ከፍ እንዳለም ጠላ ቀርቦላቸው ሲጠጡ ቢያጣጥሙት ቀጭን ሆነባቸው፡፡ ታዲያ ይህንኑ እያቅማሙ ሳሉ ሴትዩዋ መጥታ ‹‹ኸረ ይጠጡ ፤ አንድ ተይዞ ቁጭ አይባልም›› እያለች ብታጣድፋቸው ፤ ‹‹እሺ እጠጣለሁ ፤ ለመሆኑ ይህን እህል-ውሃ ያደረግሽው አንቺ ነሽ?›› አሏት! [እህል ውሃ ያረግሽው - ዶሮ እና ጠላውን የሰራሽው / ወጡንም ጠላውንም ቀጭን ያደረግሽው]
አለቃ ገብረሐና በሃያ ስድስት አመታቸው ጎንደር ውስጥ ሊቀ ካህናት ሆነው ተሾሙ፡፡ በዚህ ጊዜ አንዲት ጎንደሬ ዘንድ ጠበል ተጠርተው ቢሄዱ የሚወጡት ሰዎች ሁሉ ‹‹ጠላው ጥሩ አይደለም›› ሲሉ ይሰሙና ተመልሰው ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡ ሴትዩዋም በመቅረታቸው አዝና ቤታቸው ሄዳ ‹‹ምነው አለቃ ጠበል ጠርቼዎት ሳይመጡ ቀሩ?›› ብላ ብትጠይቃቸው ፡ ‹‹ኸረ መጥቼ ሰው ግም ፤ ግም ሲል ጊዜ ነው የተመለስኩት›› አሉዋት ይባላል፡፡ [ግም ፤ ግም - መርመስመስ / መጥፎ ሽታ]
በተከታይ ቀን አለቃ ምሳዬን ልካስ ብለው ቢሄዱም ወጡም ጠላውም ቀጠንጠን ያለ ሆነባቸው፡፡ አለቃ የሆዳቸውን ነገር እያቅማሙና የወትሮ ጫወታቸውን ቸለለል ቢሉ ምኒልክ ‹‹ምን ነካዎ ደግሞ?›› በለው ሰረቅ አድርገው ቢያዩአቸው አለቃ የተክዛሉ፡፡ ‹‹አለቃ ፣ ብላንጂ!›› ቢሏቸው ፤ ‹‹ምን ጠፍቶ ጃንሆይ ቢሻን እንበላለን ፣ ቢሻን እንጠጣለን ›› አሏቸው፡፡ [በኦሮምኛ ቢሻን ፤ ውሃ ማለት ነው]
አለቃ ግብር ላይ ቀርበው ሲበሉ ወጡ ላይ ትል ስላገኙ ተዉት፡፡ አፄ ምኒልክ ‹‹ምነው አለቃ አትበላም እንዴ?›› ብለው ቢሏቸው፣ ‹‹እበላለሁ ጃንሆይ፡፡ ምን ጎድሎ! ሁሉ ሞልቷል ዝግንትሉም ወጥቷል›› አሏቸው፡፡
አባ ገብረሐና ግብር ቀርበው ተቀምጠው ሳለ እንደልባቸው መብላት መጠጣት እንደሚችሉ ፣ ሆኖም ወደ ውጭ መውጣት እንደማይፈቀድላቸው የነግሯቸዋል፡፡ ግና የቀረበላቸው ምግብ ጨውና ቅመም የበዛበት ኖሮ በላይ በላዩ ቢጠጡ ሽንታቸው መጣ፡፡ ጨነቃቸው፤ጠበባቸው፡፡ ዳሩ ግን ጥቂት ካሰቡ በኋላ እቴጌ ጣይቱን ጠርተው፤ ‹‹እባክዎን በቁጥር ተጣልተናልና ይዳኙን፤አምስት መቶ እና አምስት መቶ ስንት ነው?›› በማለት ቢጠይቋቸው ‹‹ሺናዋ!›› በማለት መለሱላቸው፡፡ ይሄኔ አለቃ ‹‹እግዜር ይስጥልኝ እርስዎ ካዘዙኝማ መለፊያ ነው›› ብለው ወደ መፀዳጃ ቤት ሄዱ፡፡
Showing the 12 most recent of 14 posts we hold for @AlekaGebreHana. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.
Cite this entry
A live page changes as we take new readings, so a citation should name the measurement it is based on, not just the URL. The line below cites the subscriber count as measured 17 September 2026 — this entry's latest reading, not the date you are reading this.
“አለቃ ገብረሐና | 📖😆” (@AlekaGebreHana), 1,184 subscribers as measured 17 September 2026. Telegram Register, tgregister.com/channel/AlekaGebreHana.
Full measurement history, CC BY 4.0. Every reading this register holds for this entry, not just the latest one, as a dated, downloadable record: CSV · JSON. Free to use with attribution to tgregister.com. Each file carries its own generation timestamp, which is the figure to cite for exactly when the data was retrieved.