7 Aug 2026, 17:03 UTC203 views6 reactionsread 7 August 2026 Photo
#EHPLE #Result
ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር የተሰጠውን የተግባር ፈተና የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ።
https://hple.moh.gov.et ላይ በመግባት የብሔራዊ መለያ ቁጥር (FAN) እና Password በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ከዛሬ ነሐሴ 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት በነጻ ስልክ ቁጥር 952 በመደወል ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በመግለፅ ቅሬታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ።
@uni_campus1
❤5🥰1
7 Aug 2026, 10:15 UTC343 views6 reactionsread 7 August 2026 Photo
#JimmaUniversity
ጅማ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ፕሬዝዳንት ተመድቦለታል።
አዲስ የተመደቡት ፕሬዝዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር)፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲን ላለፋት ሰባት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት ካገለግሉት ጀማል አባፊጣ (ዶ/ር) በትናንትናው ዕለት የሥራ ርክክብ አድርገዋል።
ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) ላለፉት ሰባት ዓመታት የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በመሆን ማገልገላቸው ይታወቃል።
@uni_campus1
👏2🔥2❤1👍1
6 Aug 2026, 09:30 UTC496 views5 reactionsread 7 August 2026 Photo
#AksumUniversity
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ቤት የሁለተኛ ዓመት የሕክምና ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን መደበኛ ትምህርት ማክሰኞ ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡
በመሆኑም ሰኞ ነሐሴ 04/2018 ዓ.ም በጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ በአካል በመገኘት ምዝገባችሁን እንድታካሂዱ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡
@uni_campus1
❤5
4 Aug 2026, 11:23 UTC966 views10 reactionsread 7 August 2026 Photo
#MekelleUniversity
በ2018 ዓ.ም ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ የክረምት ስልጠና መርሐግብር ለመከታተል በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ መምህራን ምዝገባ ከሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት በዩኒቨርሲቲው ዓዲ ሓቂ ግቢ ይካሔዳል፡፡
ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
👉 አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ
👉 የ8ኛ ክፍል ካርድ፣ የCOC IV ምስከር ወረቀት ዋናውና ኮፒው
👉 የመታወቂያ ካርድ እና ጉርድ ፎቶግራፍ
@uni_campus1
❤5👍2🙏2🔥1
4 Aug 2026, 11:23 UTC≈2,890 views5 reactionsread 7 August 2026 https://t.me/uni_campus1
https://t.me/uni_campus1
https://t.me/uni_campus1
https://t.me/uni_campus1
https://t.me/uni_campus1
https://t.me/uni_campus1
https://t.me/uni_campus1
https://t.me/uni_campus1
https://t.me/uni_campus1
https://t.me/uni_campus1
https://t.me/uni_campus1
https://t.me/uni_campus1
❤3👍1🔥1
2 Aug 2026, 17:38 UTC967 views5 reactionsread 7 August 2026 Photo
#OromiaStateUniversity
የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 927 ተማሪዎች አስመርቋል።
ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።
@uni_campus1
❤3👍1👏1
2 Aug 2026, 09:07 UTC884 views7 reactionsread 7 August 2026 Photo
#JinkaUniversity
በጂንካ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የቆያችሁ የ1ኛ፣ የ2ኛ፣ የ3ኛ እና የ5ኛ ዓመት ነባር የእንስሳት ህክምና (DVM) ተማሪዎች በ2018 የትምህርት ዘመን ያልተጠናቀቁ ኮርሶችን ለመውስድ ምዝገባ የሚካሔደው ነሐሴ 04 እና 05/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
በተጠቀሱት ቀናት በአካል ቀርባችሁ ሪፖርት አድርጉ የተባለ ሲሆን፤ ትምህርት ነሐሴ 06/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።
@uni_campus1
❤3👍2🔥1🙏1
1 Aug 2026, 09:32 UTC993 views7 reactionsread 7 August 2026 Photo
#SIT
በ2019 የትምህርት ዘመን ወደ ሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (SIT) ለመግባት የማመልከቻ ጊዜው ተራዝሟል።
የማመልከቻ ጊዜው እስከ ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም መራዘሙን ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።
የትምህርት መስኮች :-
● Electrical Engineering
● Biotechnology
● Space Science
● Mechanical Engineering
● AI
● Nuclear engineering
መስፈርቶች :-
👉 የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል አማካኝ ውጤት 90%
👉 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት 95 ፐርሰንታይል
👉 ከ500-700 ቃላት የግል መግለጫ መጻፍ ይኖርብዎታል
👉 የድጋፍ ደብዳቤ ከ2ኛ ደረጃ መምህርዎ/ሜንተርዎ ማጻፍ
👉 የማኅበረሰብ በጎ አገልግሎ…
❤5🔥1🥰1
31 Jul 2026, 16:09 UTC≈1,050 views6 reactionsread 7 August 2026 Photo
#NationalExam #Update
ላለፉት ሦስት ቀናት በመቐለ፣ በአክሱም እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች ሲሰጥ የቆየው የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የማጠቃለያ የወረቀት ፈተና ተጠናቋል።
30 ሺህ የሚጠጉ የክልሉ ተማሪዎች በሦስቱ ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናቸውን እንደሚወስዱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወሳል።
@uni_campus1
❤4👍1👏1
31 Jul 2026, 12:48 UTC≈1,040 views6 reactionsread 7 August 2026 Photo
#HaramayaUniversity
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በአካውንቲንግና ፋይናንስ እና በማኔጅመንት የትምህርት መስኮች አዳዲስ የዶክትሬት ዲግሪ ፕሮግራሞችን ለመጀመር የስርዓተ-ትምህርት አገር አቀፍ ግምገማ አካሒዷል፡፡
ፕሮግራሞቹ በገበያው ላይ ያለውን በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎት በማጥናት፣ ዓለም አቀፍ ይዘት ያላቸው የስርዓተ ትምህርቶች ቀረፃ መደረጉ ተገልጿል፡፡
@uni_campus1
❤4👍1🔥1
28 Jul 2026, 15:17 UTC≈1,260 views9 reactionsread 7 August 2026 Photo
#GondarUniversity
#AASTU
ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመደቡ፡፡
ላለፉት ከሰባት ዓመታት በላይ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በመሆን ያገለገሉት አሥራት ዓፀደወይን (ዶ/ር) የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው መመደባቸው ታውቋል፡፡
አዲሱ ፕሬዝዳንት የትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሠረተ ልማት ዋና ስራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) በተገኙበት በዛሬው ዕለት የስራ ርክክብ ያደረጉ ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲው በትምህርት፣ በምርምር፣ በማኅበረሰብ አገልግሎት እና በተቋማዊ አስተዳደር ያስመዘገበውን ውጤት በማስቀጠል የተሻለ አፈጻጸም ለማረጋገጥ በትብብር መስራት …
❤4👏2😱2👍1
26 Jul 2026, 15:49 UTC≈1,230 views6 reactionsread 7 August 2026 Photo
#AdmasUniversity
አድማስ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ያስተማራቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው በአዲስ አበባ በሚገኙ 6 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆቹ ትምህርታቸውን ከደረጃ ሁለት እስከ ደረጃ አራት ተከታትለው ያጠናቀቁ ከ3 ሺህ በላይ የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞችንም በትላንትናው እለት ማስመረቁ ይታወሳል።
@uni_campus1
❤3🏆2👏1
Showing the 12 most recent of 15 posts we hold for @uni_campus1. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.