26 Jul 2026, 19:20 UTC393 views27 reactionsread 7 August 2026 የተለዬ ምልከታ ...
ዙለይካ ዩሱፍን ስለወደደችው ነው? አይመስለኝም!
ብዙ ጊዜ ዙለይካ ለዩሱፍ ያላትን ፍቅር ሮማንቲሳይዝ አድረገው ያቀርቡታል። እኔ እዚጋ የተለየ ምልከታ አለኝ!
አንድን ሰው ስትወደውኮ ስለሱ ትጨነቃለክ ። ለሱ ምርጥ የሆነውን ትመኝለታለክ ፣ ክብሩን እንዲያጣ አትፈልግም ፣ እንዲጠበቅ ትፈልጋለክ ..ወዘተ
እዚጋ ግን አንድም ለእርሱ ብላ ያደረገቸው ነገር የለም ። ሙሉ ለሙሉ ስለራሷ ብቻ ነው ያሰበችው .. እኔን እንቢ የሚለው እሱ ማን ስለሆነ ነው? አለ አይደል Object of attention መሆን ነው የፈለገችው ። በሱረቱ ኑር አሏህ ሴቶችን ውበታቸውን እንዲሸፍኑ ካዘዛቸው ሰበብ አንዱ ኩራት እንዳይሰማቸው ነው ። ሰው ሲመለከታቸው ፣…
🥰11👌8👍4❤2🏆1🔥1
12 Jul 2026, 17:40 UTC702 views15 reactionsread 7 August 2026 « وَرَٰوَدَتۡهُ ٱلَّتِى هُوَ فِى بَيۡتِهَا عَن نَّفۡسِهِۦ »
"ራወደ" ማለት ተደጋጋሚና ቀስ በቀስ የሆነ ውትወታ ነው ። በሱራው ውስጥ ሌላም ቦታ ላይ ይህን ቃል ይጠቀመዋል፦ "ሰኑራዊዱ አንሁ አባና" ሲሉ ማለት ነው ።
ዩሱፍ ገና ወደ ቤት ሲመጣ "ኢምራዓቲሂ" ብሏት ነበር ። በዛው ቃል ይቀጥላል ተብሎ ቢጠበቅም እዚጋ ግን ሌላ ቃል ተጠቀመ ። "ፊበይቲሃ" አለ።
ቤቱ የሰውዬው ይሆናል ተብሎ ነው የሚጠበቀው አይደል? ታዲያ ለምን የሷ አድርጎ ተናገረው?
ምናልባትም ሰውዬው ብዙ ሚስቶች ይኖሩትና ሚስቶቹ የተለያየ ቤት ሊኖራቸው ይችላል። ወይም ደግሞ በጋራ ቤትም እንዳላቸው ሁሉ የየብቻም ቤት ሊኖራቸው ይችላል ።
"አን ነፍሲ…
❤7🤗5💯1🔥1🥰1
5 Jul 2026, 16:37 UTC965 views17 reactionsread 7 August 2026 « وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُۥٓ ءَاتَيْنَٰهُ حُكْمًا وَعِلْمًاۚ »
#ተደቡር_ሱረቱ_ዩሱፍ
ኢማም አልራዚ የሰው ልጅን እድሜ በጨረቃ ይመስለዋል ። ጨረቃ መጀመሪያ ላይ ደካማ ናት ። ከዛ ወደ መካከል ስትደርስ ትሞላለች ። ከዛ እየቀነሰች ትመጣለች ። ሰውም ቢሆን ልክ እንደዚሁ ነው ይላል ።
በሌላ አገላለፁም ጨረቃ ከ1-7 ባለው ቀን ደካማ ናት ፣ ሰውም እስከ 7 አመቱ ደካማ ነው ። ከዛ 28 አካባቢ ጨረቃ ታልቃላች የሰውም ልጅ እዛ አድሜ ሲደርስ "አሹድ" ደረሰ ይባላል ይላል ።
"አሹድ" ማለት manhood ፣ full power እንደማለት ነው ። አንዳንዶች በሱረቱል አህቃፍ ያለውን "ወበለጘ አርበኢነ ሰናህ" የሚለውን በመጥ…
❤11👍4✍1🔥1
5 Jul 2026, 16:36 UTC616 views4 reactionsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤2👍1🥰1
23 Apr 2026, 12:03 UTC≈1,680 views34 reactionsread 7 August 2026 "ይህንን ቁርአን በተራራ ላይ ባወረድነው ኖሮ፣ ከአላህ ፍርሃት የተነሳ ተመትቶ (ተሸብሮ) ሲሰነጣጠቅ ባየኸው ነበር፤ እነዚህንም ምሳሌዎች ሰዎች ያስተነትኑ ዘንድ ለሰዎች እንመታቸዋለን።" ሱረቱል ሐሽር - አንቀጽ 21
✨የተራራው ግርማና የቁርአን ክብደት…
ተራራ በምድር ላይ የጥንካሬ፣ የጽናትና የከፍታ ምሳሌ ነው። በአይናችን ስናየው የማይናወጥና የማይሰነጣጠቅ ግዙፍ አካል ነው። ነገር ግን አላህ ምን ይላል? ይህ ረቂቅ የሆነው የአላህ ቃል (ቁርአን) ነፍስ ባለው አካል ላይ ሳይሆን ነፍስ በሌለውና በዚያ ግዙፍ ተራራ ላይ ቢወርድ ኖሮ፣ ተራራው ቃሉን መሸከም አቅቶት ይፈረካከስ ነበር። ይህ የሚያሳየው የቁርአንን መንፈሳዊ ክብደትና ኃይል ነው።
✨የሰው ልጅ …
❤🔥19❤11🥰3🔥1
22 Apr 2026, 17:21 UTC≈1,770 views39 reactionsread 7 August 2026 ቆይ አናሳዝናቹም እንዴ? ዝምተኛ እና ፀባየኛ ስለሆንን ነው?¡🙄
ይቺን ቻናል ቢያንስ 20k ማነው 2k እናስገባት እና የኸይር ተካፋይ እንሁን ብንላቹ እምቢ አላቹ አይደል ልጆቼ¡? ተዉ ታዘዙ¡
ባረከላሁ ፊኩም… እስቲ ቻላኑን አንቀሳቅሱት እኛንም አበረታቱን 'አለን አለን' በሉን… እኛም በቻልነው እና ባወቅነው ያክል የአላህ ቃል ለልባችን ለቀልባችን ምግብ እንዲሆን ቀምመን እናቅርብላቹ…🥰
Share:- @tedeburr
❤26🥰9👍4
20 Apr 2026, 19:07 UTC≈1,410 views28 reactionsread 7 August 2026 ...قَالَ أَوَلَمْ تُؤْمِن ۖ قَالَ بَلَىٰ وَلَٰكِن لِّيَطْمَئِنَّ قَلْبِي...
"...(አላህም) 'አታምንምን?' አለው። (ኢብራሂምም) 'በጭራሽ (አምናለሁ)፤ ግን ልቤ እንዲረጋ (ለማየት ነው)' አለ።" (አል-በቀራህ 2:260)
ነቢዩ ኢብራሂም "አላህ ሆይ! ሙታንን እንዴት እንደምታስነሳ እስቲ አሳየኝ" ብለው ጠየቁ። አላህ ደግሞ "አታምንም እንዴ?" ብሎ ጠየቃቸው። ኢብራሂም (ዐ.ሰ) የሰጡት መልስ ነው ፈገግ የሚያደርገው፤ "አምናለሁ እኮ... ግን ልቤ እንዲረጋ ብዬ ነው" አሉ። ልክ እኛ አንድ ነገር እርግጠኛ ሆነን እያወቅን፣ ግን ደግሞ በአይናችን ካላየን ብለን እንደምንጎረጉረው ማለት ነው🙂
አላህም "እሺ…
🥰20❤6👍2
17 Apr 2026, 19:07 UTC≈1,480 views19 reactionsread 7 August 2026 #ተደቡር
ጥንካሬውንም (ጉልምስናውን) በደረሰ ጊዜ ጥበብንና እውቀትን ሰጠነው፤ እንደዚሁም በጎ ሰሪዎችን እንመነዳለን።"
#ጥንካሬው( ጉልምስናውን) በደረሰ ጊዜ…
✨ዩሱፍ (ዐ.ሰ) ከመቶ በላይ ለሚሆኑ ዓመታት ቢኖርም፣ ቁርአን ግን በዝርዝር የሚነግረን ስለ ጥቂት ዓመታት ብቻ ነው። ይህ አያ የዩሱፍን የጉርምስና እና የዝግጅት ጊዜ ያሳያል። አላህ ዩሱፍን በቀጥታ ወደ ስልጣን አላወጣውም፤ ይልቁንም በባርነትና በፈተና ውስጥ እንዲያልፍ አደረገው። አላህ ለትልቅ ኃላፊነት ከመምረጡ በፊት ባሪያውን በትዕግስትና በጽናት ይቀጠቅጠዋል። አላህ ትልቅ ነገር ሊሰጥህ ሲፈልግ፣ መጀመሪያ ያንን ነገር ለመሸከም የሚያስችል ትከሻ እንዲኖርህ ያደርጋል።
#ጥበብና እውቀት
✨ዩሱፍ በወ…
❤17🔥2
22 Mar 2026, 17:48 UTC≈1,690 views26 reactionsread 7 August 2026 “እንደዚሁም ለዩሱፍ (ገዥ ልናደርገውና) የሕልሞችንም ፍች ልናስተምረው በምድር ላይ አስመቸነው”
#ተደቡር
ቆይ ቆይ ✋በባርነት መሽጡ ከማስመቸት ይቆጠራልን?
ማስመቸት የተሰኘው የኢኮኖሚ እና የገንዘብ አስተዳደርን ይማር ዘንድ ከተከበረው ባለስልጣን ቤት መግባቱ ነው፡፡ ይህ የግብጽ ባለስልጣን እንደ ልጁ አድርጎ ይንከባከበዋል። ከልምድም ያካፍለዋል፡፡
ወንድሜ ሆይ! አላህ ዩሱፍን “አስመቸነው” ያለበትን እድሜ አስተውል። ገና የ12 ዓመት ልጅ እያለ ነው፡፡ ግና ይህ ማስመቸት ከ 40 ዓመታት በኋላ ነው እውን የሆነው፡፡ አላህ አንድን ነገር ከወሰነ ውሳኔውን የሚያስቀር ኃይል የለም፡፡ ዩሱፍ ወደፊት ነብይ እንደሚሆን፤ ግብጽንም እንደሚያስተዳድር አላህ ከአሁኑ …
❤20👍6
14 Dec 2025, 20:06 UTC≈2,410 views30 reactionsread 7 August 2026 «አክሪሚ መስዋህ»
"ኢክራም" የሚለው ቃል ላይ ቆም እንበል ..
#ተደቡር
ለምሳሌ "ኢክራሙ ዶይፍ" ብንል "ለእንግዳ ማመቻቸት" ነው ። ሰውዬው ዩሱፍን እንደ ባሪያ ሳይሆን ልክ እንደተከበረ እንግዳ ተመለከተው ።
እንደሚታወቀው ባሪያዎች ደግሞ አይከበሩም ነበር ። እሱ ግን ገና ቤት እንደወሰው እንደ ሌሎቹ ባሪያዎች እንዳታይው ፣ የሚፈልገውን አሟይለት ሲል ትዕዛዝ አሳለፈ ። አላህ በሰዎች ዘንድ አንተን ተወዳጅ ማድረጉ የኢማን ምልክት ነው፡፡ አላህ ሲወድህ ሌሎችም እንዲወዱህ ያደርጋል፡፡ ሲጠላህ ደግሞ በሰዎች ዘንድ ያስጠላሀል፡፡
ቀጥለን "መስዋ" ወደሚለው ቃል እንሸጋገራለን ። "መስዋ" ማለት ማረፊያ ቦታ ማለት ነው ። "ማረፊያ" ለማለት ግን "መስዋ" ከ…
❤16👍7🔥7
14 Dec 2025, 18:06 UTC≈2,200 views24 reactionsread 7 August 2026 ይችን ቻናል 2ሺ ተከታይ ብታስገቧት ምን ይመስላችኋል?
❤16👍6🔥2
14 Dec 2025, 14:36 UTC≈2,010 views11 reactionsread 7 August 2026 «ወቃለለዚ ኢሽተራሁ ሚን ሚስረ»
#ተደቡር_ሱረቱ_ዩሱፍ
በዚህ አያ አሏህ የሰውዬውን ስም አልነገረንም ። እንዲሁም ባለስልጣን መሆኑንም አሁን ላይ አናውቅም ፤ ዋናው የነገረን ነገር ሰውዬው ከግብፅ መሆኑን ነው ። አስተውላችሁ ከሆነ በቁርአን ውስጥ ግብፅን ብቻ እንጂ ዩሱፍ የተወለደባትን ከተማ (ከንዓንን) በስም አልጠቀሳትም ። ለረሱላችንም ቀርቦላቸው የነበረው ጥያቄ "በኑ ኢስራዒሎች ወደ ግብፅ እንዴት ገቡ?" የሚል ነውና ...!
ግብፃውያን ስልጣናቸውን በየጊዜው እያሳደጉ እስከ ሙሳ ዘመን ድረስ ቀጥለዋል ። የፊርዓውን ትልቁ ንግስና ዩሱፍ ግብፅን ባያድናት አይኖርም ነበር ። ኧረ እንደውም ዩሱፍ ግብፅ ባይገባ ኖሮ አሜሪካ ዶላር ላይ ያለው የፒራሚድ ምልክት…
👍5❤3🥰3
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @tedeburr. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.