21 Aug 2026, 18:58 UTC92 views1 reactionsread 22 August 2026 ✍️ ወስማ ፡ለይእቲ ፡ድንግል፡ ማርያም።
የድንግሊቱም፡ ስም ፡ማርያም ፡ነበር ፡፡
ሉቃ ፩ ፳፯
✍️ወላዲተ -አምላክ ፡በሥላሴ፡ ዘንድ ።
እመቤታችን ፡ስሟ ፡ማርያም ፡ሲሆን ፡ይህን፡ ስም ፡ፍጥረታት፡ ሁሉ ፡በእንግዳ ፡ልማድ፡ ያይደለ ፡በልጅነት፡ መንፍስ ፡ይጠሩታል ።
✍️ በዚህ፡ ዓለም ፡የኖረችበት ዘመንም፡ የተመጠነ ፡ነው ። ዘጠኝ፡ መቶ ፤ ሰባት ፡መቶ፡ እድሜ። እንዳላቸው ፡አባቶቷ፡ የረዘመ፡ እድሜ፡ የላትም። ከእኛ ፡ያነሰ ፡እድሜ ፡ነው ፡ያላት። እኛም ፡ይህን ፡እድሜ ፡ እንኖርበታለን፡ ብለን፡ እንጅ፡ እንሞትበታለን ፡ብለን ፡አስበን፡
አናውቅም።
✍️ ይህም፡ ማለት …
❤1
Signed ዲ.ን ኢንጂነር ሽፈራው መንግስቱ
21 Aug 2026, 18:57 UTC82 viewsread 22 August 2026 Photo
የእመቤታችን ሞት ከክርስቶስ ሞት በላይ ይደንቀኛል።
የእመቤታችን ሞት፦ ለምን ሞተች? ሞት የኃጢአት ውጤት ከሆነ እመቤታችን ደግሞ ዳግሚት ሔዋን ናትና ምንም ኃጢአት የለባትም ስለዚህ ለምን ሞተች?
ክርስቶስስ ለምን ሞተ ኃጢአት የለበትምና የሚል ሐሳብ ሊነሳ ይችላል ነገር ግን የክርስቶስ ሞት ቤዛ አዳምነት ነውና በሞቱ ሞተ አዳምን ሞተ አዳምንም አዳነ፤
እመቤታችንስ ቤዛ ሔዋን አይደለችምን የሚል ሐሳብ ቢነሳም ቤዛ ሔዋንነቷ ሔዋን ያጣችውን ይዛ በመገኘት ክርስቶስን በማስገኘት ቤዛ ሔዋን ትባላለች እንጂ በሞቷ ቤዛ ዓለም መሆን አይደለምና፤ ስለዚህ የእመቤታችን ሞት በጣም ይደንቀኛል።
ሞት በክርስቶስ ቤዛነት በአዳም የኃጢአት ውጤት ነውና።
በእርግጥ እመቤታችን …
Signed ዲ.ን ኢንጂነር ሽፈራው መንግስቱ
19 Aug 2026, 16:56 UTC191 viewsread 22 August 2026 ለማንም አትንገሩ
ጌታችን በፊታቸው ሲለወጥና ከላይ ድምፅ ሲሰሙ ፫ቱ ደቀመዛሙርት በፊቱ ፍግም ብለው ወደቁ፥ በእጅጉም ፈርተው ነበርና የሚናገሩትንና የሚያደርጉትን ሁሉ አያውቁም ነበር። ከዚያ ጌታችን ሐዋርያቱን ዳሰሳቸውና «ተነሡ አትፍሩ» ብሎ አጽናናቸው፡፡ እነርሱም ተነሥተው ባዩ ጊዜ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስና ከእነርሱ በስተቀር ማንንም አላዩም፡፡ ጌታችንም እንዲህ አላቸው፦ ❝የሰው ልጅ ከሙታን ተለይቶ እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ሁሉ ለማንም አትንገሩ❞ ብሎ አስጠነቀቃቸው፡፡
ጌታችን ስለምን 'ለማንም አትንገሩ' ብሎ አዘዛቸው? ቢሉ ውዳሴ ከንቱን የሚሻ አይደለምና (ለእኛ አብነት ለመሆን) ከፊቱ የሚቀበለውን መከራ ያውቃልና ከውርደት በኋላ ወደ ክብር መሄዱ…
Signed ዲ.ን ኢንጂነር ሽፈራው መንግስቱ
18 Aug 2026, 13:34 UTC355 views8 reactionsread 22 August 2026 “ቡሄ በምሥጢረ ፊደላት’’
👉ቡሄ(ቡሔ) ከደብረ ታቦር ጋራ የተያያዘ ምሥጢር ያለው ሲሆን የሚከበረውም ነሐሴ ፲፪ ምሽት ወይም የደብረ ታቦር ዋዜማ ጀምሮ ነው።ቡሄ(ቡሔ)በምሥጢረ ፊደላት እንዲህ ይታያል፦
👉ቡሄ’’ተብሎ በሃሌታው “ሀ’’ኀምስ ፊደል ሲጻፍ የደመቀ የጎላ ብርሃን የብርሃን በዓል የሚል ትርጓሜ ይሰጣል።
👉ይህም በደብረ ታቦር የጌታ ገጹ እንደ ብርሃን ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ መሆኑን ይገልጻል።ማቴ ፲፯÷፪።
👉ይህን በማስመልከትም የደብረ ታቦር ዋዜማ ችቦ ይበራል።በልጆች ጨዋታም ቡሄና፣ ቡሄ በሉ ልጆች ሁሉ፣ቡሄ በሉ ዝም አትበሉ፣ ቡሄ መጣ ያ መላጣ፣ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ ይባላል።
👉በሌላ በኩል “ቦኸየ’’ ማለት ተገለጠ ነጣ በራ ሆነ የሚል ትርጉም ሲኖረ…
❤6🙏2
Signed ዲ.ን ኢንጂነር ሽፈራው መንግስቱ
17 Aug 2026, 14:19 UTC259 viewsread 22 August 2026 2ኛ ይቅርታ፦ከፈጣሪ ውጭ ያሉ ፍጥረታት በሙሉ ፍጹም አይደሉም ሊሳሳቱ ይችላሉ።በዚህን ጊዜ እኛም ብዙ ስህተቶችን እንደሰራን በማስታወስ ፈጣሪ ግን በቸርነቱ በይቅርታ ይቅር እንዳለን በማሰብ እኛም በሌሎች ላይስህተት የመሰለ ነገር ስናይ ከቂም ከበቀል ይልቅ በይቅርታ ልብ አይተን ፈጣሪ እኛን ይቅር እንዳለን እነርሱንም ይቅር እንዲላቸው በርኅራኄ ማየት ነው።
3ኛ ፍቅር፦ ይህ እግዚአብሔርን መውደድ እና ሰውን መውደድ ተብሎ ይከፈላል። እግዚአብሔርን መውደድ ማለት ለትእዛዞቹ መገዛት ሲሆን ሰውን መውደድ ማለት ደግሞ በእኛ ሊደረግብን የማንፈልገውን በሌሎች እንዲደረግ አለመፈለግ እና አለማድረግ ሲሆን በአንጻሩ ለእኛ ሊደረግልን የምንፈልገውን የምንመኘውን ነገር ለሌሎች…
Signed ዲ.ን ኢንጂነር ሽፈራው መንግስቱ
17 Aug 2026, 14:19 UTC179 viewsread 22 August 2026 ዲያቆኑ በቅዳሴ መካከል ከሚላቸው አንዱ ነው፡፡ምሥራቅ የማኅደረ እግዚአብሔር ምሳሌ ነው።አንድም የጌታችንን ነገረ ምጽአቱን አስቡ ሲል ነው፡፡በቅዳሴ ጊዜ ሌላ ዓለማዊ ሀሳብ ልናስብ አይገባም።ከመላእክቱ ጋር እግዚአብሔርን እያመሰገንን መሆኑን መዘንጋት የለብንም።በሥጋ ከቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነን በሀሳብ ግን ሌላ ቦታ ልንሆን አይገባም።ነገራተ እግዚአብሔርን በቅዳሴው ሰዓት የሚነበቡ የወንጌል እና የሐዲሳት እንዲሁም የመልእክተ ጳውሎስ ክፍላትን እንዲሁም አጠቃላይ ካህኑ ዲያቆኑ የሚለውን እኛም የምንመልሰውን ጠንቅቀን ማወቅ አለብን። ለተመስጦ እንዲረዳን ግእዝ ቋንቋውን እንወቀው። እያንዳንዱ የሚደረገው ድርጊት ምሳሌ እና ምሥጢር ስላለው ያንን ጠይቀን ተምረን እንወቀው…
Signed ዲ.ን ኢንጂነር ሽፈራው መንግስቱ
17 Aug 2026, 14:19 UTC140 views2 reactionsread 22 August 2026 ስለ ቅዳሴ ክፍል ፩
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ።
አሜን ለታሪክ ሲሆን እውነት፣
አሜን ለሃይማኖት ሲሆን አዎ፣
አሜን ለምረቃ ሲሆን ይደረግልኝ ማለት ነው፡፡
ቅዳሴ ማለት ልዩ ምሥጋና ማለት ነው፡፡የሰው ልጅ የተፈጠረው ፈጣሪን እያመሰገነ በደስታ ይኖር ዘንድ ነው። በቅዳሴ ጊዜ ተሠጥዎ ለመመለስ ብቻ ካልሆነ በቀር ድምጽ ማሰማት አይገባም። አዳም ከተፈጠረ በኋላ በገነት መካነ ጸሎት ለይቶ ይጸልይ ያመሰግን ነበር። ጸሎት ማለትም ምሥጋና ያለበት ልመና ማለት ነው፡፡በሰይጣን ተንኮል አዳም ከገነት በተባረረ ጊዜ እንዲሁ በደብር ቅዱስ የጸሎት ቦታ ለይቶ መሥዋእት ያቀርብና ይጸልይነበር። አዳም ከሞተ በኋላ አጽሙን እንደታቦት አድርገው በዚያ መ…
❤2
Signed ዲ.ን ኢንጂነር ሽፈራው መንግስቱ
17 Aug 2026, 04:10 UTC179 views1 reactionsread 22 August 2026 ❝ሰአሊ ለነ ማርያም — ማርያም ሆይ ለምኚልን❞
❝ሰአሊ ለነ ማርያም ማኅቶተ ዓለም ስብሕት በአርያም — በአርያም የተመሰገንሽ የዓለም መብራት ማርያም ሆይ ለምኚልን❞
(ትርጓሜ)፡-
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በዚህኛው የሰዓታት ክፍል ላይ ጌታችን:-
❝አነ ውእቱ ብርሃኑ ለዓለም — እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ❞
ብሎ በወንጌል ካስተማረው በተጨማሪ ቅዱሳኑንም ደግሞ:-
❝አንትሙ ውእቱ ብርሃኑ ለዓለም — እናንተ የዓለም ብርሃኑ ናችሁ❞
ያለውን ጌታ በኅቱም ድንግልና ፀንሳ በመውለዷ «እመ ብርሃን» ተብላ የምትጠራው በአርያም በቅዱሳን መላእክት የምትመሰገነው ቅድስት ድንግል ማርያም እንድታማልደው ይማፀናታል።
❝ሰአሊ ለነ ማርያም ምዕዳው እምሠርም ዘጽድቅ ተንከተም — የጽ…
❤1
Signed ዲ.ን ኢንጂነር ሽፈራው መንግስቱ
16 Aug 2026, 16:09 UTC232 views2 reactionsread 22 August 2026 ቅዱስ ቁርባን በአፍ እያለ የሚጸለይ ጸሎት ንባቡና ምሥጢሩ
ወእምድኅረ ተመጥዎ ቁርባን እንዘ ሀሎ በአፉሁ ይበል ኩሉ ለለአሐዱ፣ አሐዱ ...
❝ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሥሉስ ዘኢይትነገር ሀበኒ ከመ እንሣእ ለሕይወት ዘንተ ሥጋ ወደመ ዘአንበለ ኩነኔ። ሀበኒ ዕግበር ፍሬ ዘያሠምረከ ከመ አሥተርኢ በስብሐቲከ ወእሕየው ለከ እንዘ እግብር ዘዚአከ ፈቃደ። በተአምኖ እፄውዐከ አበ ወእጼውዕ መንግሥተከ ይትቀደስ እግዚኦ ስምከ በላእሌነ። እስመ ኃይል አንተ እኩት ወስቡሕ ወለከ ስብሐት ለዓለመ ዓለም።❞
(ትርጉም):-
ቁርባኑን ከተቀበለ በኋላ በአፉ ሳለ ሁሉም እያንዳንዱ እንዲህ ይበል ...
❝የማይነገር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሦስት የምትሆን ይህን ሥጋና ደም ሕይወት ሊሆነኝ ሳይፈ…
🙏2
Signed ዲ.ን ኢንጂነር ሽፈራው መንግስቱ
16 Aug 2026, 16:08 UTC222 viewsread 22 August 2026 ከቁርባን በፊት የሚጸለይ ጸሎት ንባቡና ምሥጢሩ ...
ሥጋውን ደሙን ለመቀበል የቀረቡ ሰዎች ከመቀበላቸው በፊት የሚጸልዩት ጸሎት በአማርኛ ብቻ እንደሚከተለው ነው:-
❝አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ርኩስ ከሆነች ከቤቴ ጠፈር በታች ትገባ ዘንድ የሚገባኝ አይደለሁም፤ እኔ አሳዝኜሃለሁና፥ በፊትህም ክፉ ሥራ ሠርቻለሁና በአርያህና በአምሳልህ የፈጠርኸው ሥጋዬንና ነፍሴን ትእዛዝህን በማፍረስ አሳድፌአለሁና፡፡ መልካም ሥራ ምንም ምን የለኝምና፤ ነገር ግን ስለመፍጠርህና እኔን ለማዳን ሰው ስለመሆንህ ስለ ክቡር መሰቀልህም ማህየዊ ስለምትሆን ስለ ሞትህ፣ በሦስተኛውም ቀን ስለመነሳትህም ጌታዬ ሆይ ከበደልና ከመረገምም ሁሉ፤ ከኃጢአትና ከርኩሰትም ሁሉ ታነጻኝ ዘን…
Signed ዲ.ን ኢንጂነር ሽፈራው መንግስቱ
16 Aug 2026, 15:57 UTC206 views2 reactionsread 22 August 2026 «አሜን» በሥርዐተ አምልኮ
፩.
በቃሉ ታማኝ የሆነው፥ የነገሥታት ንጉሥ፥ የጌቶች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ «አሜን» ይባላል። የኢየሱስ ከርስቶስ መጠሪያ ቃል ነው።
❝አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስከር … እንዲህ ይላል❞
— እንዲል ራእ ፫፥፲፬።
፪.
«አሜን» የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ከ፶፱ ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ አሜን ትርጉሙ ብዙ ነው፤ አሜን ማለት እውነት፣ እስማማለሁ፣ ቃልህ ቃሌ - ውሳኔህ ውሳኔዬ ነው - ምስጋናህ ምስጋናዬ ነው ማለት ይሆናል።
፫.
«አሜን» ማለት የተረጋገጠና የታመነ ሊቀበሉትም የተገባ ሐቅ ማለት ነው። አሜንና እውነት ትርጉማቸው አንድ የሆነ ተመሳሳይ ቃላት ናቸው። «ለይኩን» የሚለው የግእዝ ቃል አሜን የሚለውን የእብራይ…
❤1🥰1
Signed ዲ.ን ኢንጂነር ሽፈራው መንግስቱ
16 Aug 2026, 08:14 UTC197 views7 reactionsread 22 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
🥰7
Signed ዲ.ን ኢንጂነር ሽፈራው መንግስቱ
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @shiferaw2123. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.