8 Aug 2026, 05:56 UTC18 views2 reactionsread 8 August 2026 🧠 የዛሬ ሀሳብ
"ሰነፍ ነኝ።"
ይህን አባባል ስንት ጊዜ ለራስህ ተናግረሃል?
እኔም ብዙ ጊዜ ተናግሬዋለሁ።
ነገር ግን አንድ ቀን እራሴን ጠየቅሁ፦
"በእውነት ሰነፍ ነኝ? ወይስ ራሴን በትክክል አልተረዳሁም?"
ይህ ጥያቄ ነበር የመጽሐፌ መጀመሪያ።
ብዙ ጊዜ ችግራችን እውቀት ማጣት አይደለም።
ራሳችንን በስህተት መተርጎማችን ነው።
ስልክህን ስለተጠቀምክ...
አንድ ቀን ስላልተማርክ...
ወይም እቅድህን ስላልፈጸምክ...
ወዲያውኑ "እኔ ሰነፍ ነኝ" ብለህ አትደምድም።
አንድ ስህተት...
ማንነትህን አይወስንም።
📖 ከመጽሐፌ
"ራስህን በምትናገረው ቃል ተጠንቀቅ።
አእምሮህ ብዙ ጊዜ ያንን ቃል እንደ እውነት ይቀበለዋል።"
🎯 የዛሬ ተግባር
ዛሬ ራስህን በመውቀስ ፋንታ..…
❤1👍1
7 Aug 2026, 16:34 UTC304 views14 reactionsread 8 August 2026 Photo
# 🧠 የአእምሮህ ጦርነት | አዲስ ምዕራፍ
ዛሬ አንድ ነገር ላካፍላችሁ እፈልጋለሁ።
ለረጅም ጊዜ አንድ ጥያቄ እያሰብኩበት ነበር።
ሰዎች ለምን ሕይወታቸውን መቀየር እንደሚፈልጉ እያወቁ...
አሁንም በተመሳሳይ ቦታ ይቆያሉ?
ለምን ጥሩ እቅድ እናወጣለን ነገር ግን አንከተለውም?
ለምን በራሳችን ላይ ተስፋ እንቆርጣለን?
ይህን ለመረዳት ስለ ዲሲፕሊን፣ ልማድ፣ ሰውነትና አእምሮ ላይ ጥናት አደረግሁ።
ውጤቱ?
መጽሐፍ።
📖 የዲሲፕሊን ስርዓት የሚያስተምር።
ነገር ግን ይህ ብቻ ስለ ልማድ ወይም ስለ ጊዜ አጠቃቀም የሚናገር መጽሐፍ አይደለም።
ዋናው ጥያቄው ይህ ነው፦
"እንዴት ራሳችንን በተሻለ ሁኔታ እንረዳ እና እንቀይራለን?"
በሚቀጥሉት ቀናት ከመ…
❤9🔥3👍2
7 Aug 2026, 11:10 UTC426 views14 reactionsread 8 August 2026 Photo
Guys check this out እስኪ ምን ታስባላችሁ book is coming
🔥6❤4👍2👏2
7 Aug 2026, 04:57 UTC512 views14 reactionsread 8 August 2026 ሞቲቬሽን ለምን ይጠፋል?
አንድ ቀን በጣም ትነሳሳለህ።
መጽሐፍ ትገዛለህ።
ዕቅድ ታወጣለህ።
"አሁን ግን በእርግጥ እለወጣለሁ" ትላለህ።
ከጥቂት ቀናት በኋላ ግን...
ያ ስሜት ይጠፋል።
ብዙ ሰዎች በዚህ ጊዜ ራሳቸውን ይወቅሳሉ።
እውነቱ ግን ይህ ነው፦
ሞቲቬሽን የሚመጣና የሚሄድ ስሜት ነው።
ሕይወትህን በስሜት ላይ ብቻ ከገነባህ፣ ስሜቱ በሄደ ጊዜ ልማድህም ይቆማል።
ስለዚህ ጥያቄው "እንዴት ብዙ ሞቲቬሽን አገኛለሁ?" አይደለም፦
ጥያቄው "ሞቲቬሽን በሌለበት ቀንም እንዴት እቀጥላለሁ?" ነው፦
ይህን ስትመልስ...
እውነተኛ ዲሲፕሊን መገንባት ትጀምራለህ።
💬 አንናንተስ በሞቲቬሽን ላይ ብዙ ጊዜ ትመካላችሁ? ወይስ ልማድ ለመገንባት ሞክራችኋል
❤9👍5
6 Aug 2026, 03:59 UTC645 views18 reactionsread 8 August 2026 👉👉ከነገ ጀምሮ...
ይህን ሐረግ ስንት ጊዜ ተናግረናል?
"ከነገ ጀምሮ አጠናለሁ።"
"ከነገ ጀምሮ እለወጣለሁ።"
"ከነገ ጀምሮ እጀምራለሁ።"
ችግሩ ነገን መጠበቅ ብቻ አይደለም።
ብዙ ጊዜ ከባድ ስራን ወደ ፊት ስናስተላልፍ፣ የአሁኑ ጫና ለጥቂት ጊዜ ይቀንሳል።
ያ ጊዜያዊ እፎይታ ደግሞ መዘግየትን ሊያጠናክር ይችላል።
ስለዚህ ለውጥ ሁልጊዜ በነገ አይጀምርም።
በዛሬ በምትወስደው ትንሽ እርምጃ ይጀምራል።
ዛሬ ራስህን እንዲህ ብለህ ከመጠየቅ፦
"ሙሉ ሥራውን እንዴት እጨርሳለሁ?"
ይልቅ ይሄንን ጠይቅ፦
"ዛሬ ለ2 ደቂቃ ምን መጀመር እችላለሁ?"
💬 በሕይወትህ "ከነገ ጀምሮ" እያልክ የምታስተላልፈው አንድ ነገር ምንድን ነው?
❤14👍4
5 Aug 2026, 17:29 UTC670 views13 reactionsread 8 August 2026 👉ለምን ቀላሉን መንገድ እንመርጣለን?"
ብዙ ሰዎች ይህን ጥያቄ ይጠይቃሉ።
"ለምን እያወቅሁ አላደርግም?"
ምናልባት መልሱ እንደምታስቡት አይደለም።
አእምሮህ የተፈጠረው ለአንድ ዋና ዓላማ ነው፦
ኃይል መቆጠብ እና ፈጣን ሽልማትን መፈለግ።
ለዚህ ነው ስልክህ በቀላሉ የሚስብህ።
ለዚህ ነው ጥናትን ወይም ከባድ ሥራን መጀመር አስቸጋሪ የሚመስለው።
ይህ ማለት ግን...
"ለውጥ አይቻልም" ማለት አይደለም።
ማለት ያለብን...
አእምሮን በመውቀስ ሳይሆን፣ በመረዳት መስራት አለብን።
ይህ የዚህ ገጽ ዋና ሀሳብ ነው።
እኛ ራሳችንን ለመውቀስ አልመጣንም።
ራሳችንን ለመረዳት እንጂ።
💬 አሁን ደግሞ እናንተን እጠይቃለሁ፦
በቀናችሁ ውስጥ ትኩረታችሁን በ…
❤11👍2
5 Aug 2026, 04:40 UTC751 views15 reactionsread 8 August 2026 🧠 ዲሲፕሊን ማለት ራስን ማስገደድ አይደለም!
ይሄን ልጠይቅህ...
በሕይወትህ ስንት ጊዜ እንዲህ ብለሃል?
"ከዛሬ ጀምሮ እለወጣለሁ።"
ከዚያ...
ለ2 ወይም 3 ቀን ትጥራለህ።
ከዚያ ድካም ይመጣል።
ሞቲቬሽኑ ይጠፋል።
"ዲሲፕሊን የለኝም።"
ብለህ ራስህም ላይ ትፈርዳለህ፦
ነገር ግን...
ምናልባት ችግሩ ዲሲፕሊን አለመኖሩ አይደለም።
ችግሩ የተሳሳተ የዲሲፕሊን ትርጉም ሊሆን ይችላል።
ብዙዎቻችን ዲሲፕሊንን "ራስን በኃይል ማስገደድ" ነው። ብለን እናስባለን።
ግን ራስህን በየቀኑ በኃይል ማስገደድ የሚያስፈልግህ ከሆነ...
ያ ስርዓት ለረጅም ጊዜ አይቆይም።
እውነተኛ ዲሲፕሊን የሚጀምረው ከአንድ ጥያቄ ነው፦
"ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ቀላል እንዲሆን አካባቢዬን …
❤13👍2
4 Aug 2026, 09:18 UTC854 views31 reactionsread 8 August 2026 📖 ዛሬ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ...
እስቲ በሐቀኝነት መልሱልኝ።
ስንት ጊዜ ለራሳችሁ እንዲህ ብላችሁ ቃል ገብታችኋል?
"ከነገ ጀምሮ እለወጣለሁ።"
"ከነገ ጀምሮ አጠናለሁ።"
"ከነገ ጀምሮ ጠዋት እነሳለሁ።"
"ከነገ ጀምሮ ስልኬን እቀንሳለሁ።"
ከዚያስ...
ነገው ሲመጣ ምንም አይቀየርም።
ብዙ ሰዎች ይህ ሲሆን "ሰነፍ ነኝ" ብለው ራሳቸውን ይፈርዳሉ።
እኔ ግን እንደዚያ አላምንም።
ምናልባት...
ችግራችሁ ስንፍና ሳይሆን አእምሯችሁ እንዴት እንደሚሠራ አለማወቃችሁ ሊሆን ይችላል።
በዚህ channel ያለኝ ዓላማ ሰዎችን ለጥቂት ደቂቃዎች ማነሳሳት አይደለም።
ዓላማዬ ሰዎች ራሳቸውን እንዲረዱ፣ ዲሲፕሊንን በአዲስ መንገድ እንዲመለከቱ፣ እና በቀስታ ግን በቋሚነት ሕይ…
👍19❤12
3 Aug 2026, 09:40 UTC991 views11 reactionsread 8 August 2026 Photo
https://youtube.com/channel/UCdIfzzsKLw91Fwuu6MYm9rw?si=fh3BAGGLqBc3snlH
guys YouTube channel ከፍተናል
Subscribe ማድረግ አትርሱ እና እንዲሰራላችሁ
የምትፈልጉትን ሀሳብ comment አድርጉ
thank you❤️
👍5❤4👏1🔥1
3 Aug 2026, 04:56 UTC≈1,120 views25 reactionsread 8 August 2026 Photo
ስለ Discipline ያመናችሁት ትልቁ ውሸት
ምናልባት ከዚህ በፊት ለራስህ እንዲህ ብለህ ይሆናል፦
"እኔ Discipline የለኝም።"
ለማጥናት በተሳነህ ቁጥር...
ለራስህ የገባኸውን ቃል በጣስክ ቁጥር...
በጀመርክ ቁጥር ከዚያም ስታቆም...
ራስህን ወቅሰሃል።
ግን ችግሩ ያለው ካንተ ባይሆንስ?
ችግሩ ሰነፍ መሆንህ ካልሆነስ?
Discipline እንዴት እንደሚሰራ በትክክል አልመረዳትህ ቢሆንስ?
ስለዚህ ጉዳይ አስቡት።
✓ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጥሩ ነው።
✓ ማንበብ ይረዳል።
✓ መማር እድሎችን ይፈጥራል።
እነዚህን ነግሮች አስቀድመህ ታውቃለህ
ለዚህ ችግሩ እውቀት አይደለም ማለት ነው።
ትክክለኛው ጥያቄ፡-
ምን ማድረግ እንዳለ…
❤14👍11
2 Aug 2026, 16:11 UTC≈1,210 views15 reactionsread 8 August 2026 ሰላም ሰላም guys we are back!!!
ለጥፋንባቸው ጊዜያት በጣም ይቅርታ እንጥይቃለን🙏🙏🙏
ከዚህ በኋላ በሚኖሩን ጥሩ ጥሩ ስራዎች እንደምትደሰቱ እርግጠኞች ነን።
የሚከተለውን ጥያቄ comment ላይ መልሱ
👉Discipline ምን ማለት ይመስላችኋል?
👉እንዴትስ ሊኖረን ይቺላል ብላችሁ ታስባላችሁ?
❤12👍3
30 Apr 2026, 10:03 UTC≈4,480 views30 reactionsread 8 August 2026 ተጠያቂነታችን ስላደረግነው ብቻ አይደለም። ስላላደረግነውም ጭምር እንጂ።
“It is not what we do, but also what we do not do, for which we are accountable.” – Molière
👍16❤14
Showing the 12 most recent of 22 posts we hold for @mindothe. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.