10 Aug 2026, 13:53 UTC181 views2 reactionsread 4 September 2026 የቅዱስ ኤፍሬም ድርሳናት ፍሬ
በትውልድ እንግሊዛዊው እና ለብዙ ዘመናት የፕሮቴስታንቲዝም አንዱ ቅርንጫፍ በሆነው የአንግሊካን እምነት ውስጥ የቆየው ዕውቁ ሊቅ ሰባስትያን ብሮክ ቅዳሜ ግንቦት 18 (May 25)፣ 2024 ዓ. እ.የሶርያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባል በመሆን በቅብዓ ሜሮን ከብሮ ዋለ።
ሰባስትያን በኦርቶዶክሱ ዓለም በሶርያ የሚገኙ ጥንታዊ የሆኑ የነ ቅዱስ ኤፍሬም ድርሳናትን ከጥልቅ ሐተታዎች ጋር በመተርጎም እና የሶርያን ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ሕይወት በማጥናት በሰፊው ይታወቃል። በዚህ ዙሪያ የሠራቸው እና ያሳተማቸው የጥናት እንዲሁም ትርጉም መጻሕፍት ዝርዝር ብቻ ወደ ሠላሳ ገጽ ይሆናሉ። የሶርያም ቤተ ክርስቲያንም ለዚህ ድካሙ የ…
❤2
Signed ESET
5 Aug 2026, 17:53 UTC237 views2 reactionsread 4 September 2026 "ከንስሐ አባትህ ጋር ስትሆን ጥያቄህን እንጂ ውሳኔህን አታቅርብላቸው፤ በልብህ ካሰብከው ጋር እንዲስማሙ ሳይሆን በሐሳብህ ላይ ሐሳባቸውንና ምክራቸውን እንዲሰጡህ አድርግ።"
ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሣዊ
❤2
Signed ESET
30 Jul 2026, 05:51 UTC312 views2 reactionsread 4 September 2026 በጸሎት ኃይል የሚያምን አንድ ጽኑዕ ክርስቲያን ነበር፡፡ ይህም ክርስቲያን ጥሪት የሌለው ደሃ፣ የሚበላ የሚቸግረው ረሃብተኛ፣ ልብሱ በላዩ ላይ አልቆ የታረዘ ምስኪን ነው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በጸሎት ሕይወቱ የነበረውን ትጋት በቅርበት ያውቅ የነበረው አንድ ወዳጁ እየተቆጣ 'ቢያንስ ለረሃብህ ማስታገሻ ቁራሽ ዳቦ እንኳን ማሰጠት ካልቻለ የአንተ ጸሎት ፋይዳው ምንድር ነው? ይቅርብህ በቃ! ፈጣሪህ አይሰማህም ማለት ነው' ሲል ተስፋ በሚያስቆርጥ ቃል ተናገረው፡፡ ያም ምስኪን ክርስቲያን እንዲህ ሲል መለሰለት፦ 'እግዚአብሔርማ አልረሳኝም። ለአንዱ ሰው ከዕለት እንጀራው የበለጠ አትርፎ በመስጠት ለእኔ እንዲያካፍለኝ መልእክተኛ አድርጎት ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን አደ…
❤2
Signed ESET
14 Jul 2026, 04:18 UTC384 views5 reactionsread 4 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤5
Signed ESET
14 Jul 2026, 04:18 UTC346 views2 reactionsread 4 September 2026 #ቅድስት_ሥላሴ (#ሐምሌ_7)
ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን …
❤2
Signed ESET
1 Jul 2026, 12:03 UTC348 viewsread 4 September 2026 "በማዕበል መሀል እንዳለች ታንኳ ልብህ በጭንቀት ስትናወጥ፣ ማዕበሉን ጸጥ ማድረግ ወደሚችለው ወደ ክርስቶስ ፊት ቅረብ። ጭንቀትህ የቱንም ያህል ከባድ ቢሆን፣ የእግዚአብሔር ቸርነት ግን ከዚያ ይበልጣል። እርሱ ስለ አንተ የሚያስብ አባት ነውና ነገ ምን እሆናለሁ ብለህ አትጨነቅ፤ የዛሬን ቀን የሰጠህ አምላክ የነገውንም ማዕበል በጥበቡ ያሳልፈዋል። ብዙ ጊዜ የምንጨነቀው ሁሉንም ነገር በራሳችን አቅም ለመወጣት ስንሞክር ነው፤ ነገር ግን ሸክምህን በጸሎት ወደ እርሱ ስትጥለው፣ እርሱ በልብህ ውስጥ ሰላምን ያሳድራል። ቅዱሳን ሐዋርያት በዓለም ሳሉ ብዙ መከራና ጭንቀት ገጥሟቸዋል፤ ነገር ግን ልባቸው አልፈራም፤ ምክንያቱም ከእነርሱ ጋር ያለው ጌታ ከዓለም ሁሉ እንደሚበ…
Signed ESET
21 Jun 2026, 16:16 UTC463 viewsread 4 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed ESET
31 May 2026, 05:51 UTC910 views3 reactionsread 4 September 2026 በዓለ መንፈስ ቅዱስ / ጰራቅሊጦስ
ይህች ታላቅ ዕለት ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል የሆነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለቅዱሳን ሐዋርያት፣ ለቅዱሳን አርድእትና ለቅዱሳት አንስት የተገለጠባት ዕለት ናት፡፡ እነዚህ ሁሉ በጸሎት ተግተው በሚጸልዩበት ወራት መንፈስ ቅዱስ በተከፋፈሉ የእሳት ልሳን አምሳል የወረደበት ቅዱስ ቀን ነው፡፡ አስቀድሞ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት ደብረ ዘይት በተባለ ታላቅ ተራራ ላይ ሳሉ እንዲህ ብሎ አስተምሯቸው ነበር “ኃይልን ከአርያም እስክልክላችሁ ድረስ በኢየሩሳሌም በጸሎት ቆዩ፡፡”/ሉቃ 24፡36/ መቶ ሃያው ቤተሰብም በኢየሩሳሌም ሀገር በምትገኝ በቤተ መቅደስ በአንድነት ሆነው በጸሎት በመትጋት ቆዩ፡፡ 120…
❤2🥰1
Signed ESET
28 May 2026, 05:12 UTC514 views1 reactionsread 4 September 2026 ወዳጆቼ ሆይ! መከራን በመቀበላችን ክፉ ደረሰብን ብለን አንመረር፤ ነገር ግን ኃጢአትን በፈጸምን ወቅት መከራ እንደመጣብን እንቁጠር፡፡ ይህ ነው መራሩ መከራ፡፡ እኛ ግን በዚህም ምድር ኑሮአችንን በቅንጦት እያሳለፍን የሚመጣውን ዓለም ሕይወት ለመስበክ አንሻም፡፡ እንዳውም በሚመጣው ዓለም የምንኖረው እንዲህ ዓይነት ሕይወት እንደሆነ እናስተምራለን፡፡ ሕሊናችን እንዴት በኃጢአት እንደተጨማለቀ እስቲ ቆም ብለን እናስብ ፡፡ ይህ ከሌሎች ቅጣቶች ይልቅ እጅግ ከባዱ ቅጣት አይደለምን?
መከራን መቀበል በራሱ ክፉ አይደለም፡፡ ክፉ ነገር ኃጢአት መሥራት ነው - አዎን! እጅግ መራራው መከራ ኃጢአት መሥራት ነው! ኃጢአት ከመሥራታችን የተነሣ በወዲያኛው ዓለም የሚያገኘንስ …
❤1
Signed ESET
5 Mar 2026, 14:12 UTC900 views6 reactionsread 4 September 2026 #ለወላጆች #ይነበብ
"ልጅህን በሚገባ ካሳደግኸው አንተም ትከበራለህ፤ እርሱም ለራሱና ለቤተክርስቲያን ኩራት ይሆናል፤ እግዚአብሔርም በእናንተ ምክንያት ይከበራል። ልጅህን ችላ ካልኸው ግን አንተም ትዋረዳለህ፤ በእርሱ ጥፋት ምክንያት እግዚአብሔር ይሰደባል፤ ማኅበረሰቡም በክፉ ጠባዩ ይጎዳል።
ልጆችህን ስታሳድግ ራስህን እንደ አንድ ታላቅ ቀራፂ ቁጠር። አንድ ቀራፂ ድንቅ ምስልን ለመፍጠር በድንጋዩ ላይ እንደሚተጋ፣ አንተም በልጅህ ነፍስ ላይ የክርስቶስን መልክ ለመሳል ትጋ። ከመጀመሪያው ጀምረህ ክፉ ሐሳቦች በልቡ ውስጥ ሥር እንዳይሰዱ፣ የማይረቡና ቆሻሻ ቃላትም ከአንደበቱ እንዳይወጡ በንቃት ጠብቀው።
ለልጅህ ምድራዊ ሀብትን ለማከማቸት አትጨነቅ፤ ይልቁንም …
❤3👍3
Signed ESET
11 Feb 2026, 12:46 UTC≈1,240 views4 reactionsread 4 September 2026 ባለህ ተደሰት
በዚህ ዓለም ላይ ትልቁ ፍልስፍና ፣ ትልቁ ጥበብ፣ ትልቁ እምነት “እንደ ፈቃድህ” ማለት ነው። በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደዚህ ዓለም መጥተናል፣ በእግዚአብሔር ፈቃድ ከዚህ ዓለም እንሄዳለን። የእግዚአብሔር ፈቃድ ገዥ ነው። ፈቃድህ ይሁን ባንልም ፈቃዱ ይሆናል። ፈቃዱ ይሁን በማለት ግን ሕይወት ጥያቄ ሳይሆን መልስ እንድትሆን ያደርጋል። ትልቅ ፍልስፍና ራስን መጣል አይደለም፣ ራስን መጣል ስንፍና ነው። ፈላስፎች ከምድር ጀምረው በምድር ይጨርሳሉ። ያለ ክርስቶስም ለዚህ ዓለም ስለሚሞቱ ትንሣኤ የላቸውም። ዓለም ከንቱ ናት ቢሉም ብርቱ በሆነው በክርስቶስ ግን አልቀየሩአትም። ትልቅ ፍልስፍና የሕይወቴን መግቢያና መውጫ ለያዘው እግዚአብሔር መንገድ መልቀቅ …
❤3👍1
Signed ESET
27 Jan 2026, 16:46 UTC666 views0 reactionsread 4 September 2026 የቀጠለ....
"እንግዲህ ሚስትህ ውበት ቢጎድላት እንኳ አትናቃት። ስማኝ፤ ከሰውነቱ ክፍል አንዱ ቢታመም አካሉን የሚጥል ማነው? ማንም! ይልቁንም ያንን የታመመውን የአካል ክፍሉን ይበልጥ ይንከባከበዋል እንጂ። ሚስትህም አካልህ ናትና ድክመት ቢኖርባት በፍቅር አክማት።
ባል ሆይ! ሚስትህን ስትመክራት በታላቅ ርኅራኄ ይሁን። አትጩህባት፤ ይልቁንም በፍቅር ቃላት አቅርባት። 'ውዴ ሆይ! እኔና አንቺ አንድ አካል ነን፤ ሕይወታችንም አንዲት ናት። አንቺን ማስከፋት ራሴን እንደ መጉዳት ነው' በላት። እንዲህ ያለ ቃል ከብረት ይልቅ የጸናን ልብ ያቀልጣል።
ሚስትም ባሏን ስታከብር 'እንደ ባሪያ' ሳይሆን 'እንደ አካል' ይሁን። አካል ለራስ እንደሚታዘዝ፣ አንቺም ለባል…
Signed ESET
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @meazasenay. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.