26 Jul 2026, 06:13 UTC235 views7 reactionsread 7 August 2026 Photo
ለሙታን ሕይወትን በሚሰጥ፣ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት አብርሃም የሁላችን አባት ነው። ዘርህ እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፥ ተስፋ ባልነበረው ጊዜ እንኳን ተስፋ ይዞ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን አመነ። የመቶ ዓመትም ሽማግሌ ስለ ሆነ፣ እንደ ምውት የሆነውን የራሱን ሥጋና የሣራን ማኅፀን እየተመለከተ እንኳን በእምነቱ አልደከመም፤ ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም። ስለዚህ ደግሞ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት። ነገር ግን፡— ተቈጠረለት የሚለው ቃል ስለ እርሱ ብቻ የተጻፈ አይደለም፥ ስለ …
❤6🔥1
Signed Tinsae
25 Jul 2026, 04:16 UTC265 views5 reactionsread 7 August 2026 Against The Weak Anthropic Principle #2
የቀጠለ...
የ WAP መርህ፣ እጅግ ደካማ መሠረት ላይ እንደቆመ የበለጠ ግልጽ የሚሆነው፣ ተመሳሳይ አካሄድ ተጠቅመን ማንኛውንም አስቸጋሪ ፍልስፍናዊ ጥያቄ መመለስ እንደምንችል ስንረዳ ነው። ለምሳሌ፣ እድሜ ለኤቲዪስቶች፣ ለብዙ መቶ ዓመታት የሥነመለኮት ልሂቃንን ሲያስጨንቅ የነበረውን የክፋት ችግር (The Problem of Evil) በዚህ መልኩ መመለስ እንችላለን፦
ከጅምሩ "ለምንድነው ፈጣሪ የክፋትን መኖር የሚፈቅደው?" የሚለውን ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ፈጣሪና ክፋት በዓለም ውስጥ መኖር አለባቸው። እግዚአብሔር አጽናፈ ዓለሙን በክፋትና በመከራ ለመሙላት ባይፈቅድ ኖሮ፣ የክፋት ችግርን የሚ…
❤4🔥1
Signed Tinsae
23 Jul 2026, 12:05 UTC262 views9 reactionsread 7 August 2026 Against The Weak Anthropic Principle #1
"ሕይወትን ለመፍጠር የፈለገ አካል (agent) ከሌለ በቀር፣ እንዴት ዓለም በዚህ መልኩ ለሕይወት ተስማሚ ልትሆን ቻለች?"
ዘመናዊ ኤቲዪስቶች ይህንን ጥንታዊ ጥያቄ ለመመለስ ከሚያቀርቧቸው ማብራሪያዎች አንዱ፣ The Weak Anthropic Principle (WAP) ተብሎ የሚጠራው አስቂኝ መርህ ይጠቀሳል። ኤቲዪስቶች እንደሚሉት ከሆነ፣ ዓለማችን ለሕይወት ተስማሚ እንደሆነች ለመታዘብ ራሱ፣ "መታዘብ የሚችሉ" ሕያውና አስተዋይ (Intelligent) ፍጥረታት ያስፈልጋሉ። ዓለም ለሕይወት ተስማሚ ባትሆን ኖሮ፣ እኛ ራሳችን በሕይወት ኑረን ስለ ዓለም ተስማሚነት ባላወራን ነበር። አሁን ግን ስለዚ…
❤5🔥3👍1
Signed Tinsae
23 Jul 2026, 12:04 UTC213 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed Tinsae
22 Jul 2026, 17:33 UTC224 views7 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @Pensees28Photo
Justice is the means by which God becomes objective— detached and remote— from the individual. By administering absolute fairness, God becomes "blind" and disinterested towards the person. Hence why Christ the Judge proclaims, "I never knew you."
In comparison, love/mercy is the means by which God becomes subjective, close, and interested in the individual. Hence why Christ the Shepherd proclaims, "I know my own a…
❤7
Signed Tinsae
22 Jul 2026, 05:45 UTC298 views11 reactionsread 7 August 2026 Photo
...በሩሲያ አብዮታዊ ታሪክ ላይ ወደ 50 ዓመታት ያህል ሰርቻለሁ፤ በዚህ ሂደት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ መጻሕፍትን አንብቤያለሁ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የግል ምስክርነቶችን ሰብስቤያለሁ፣ ከዚህ ውጥንቅጥ የተረፈውን ፍርስራሽ ለማጽዳት በሚደረገው ጥረትም ስምንት የራሴን ጥራዞች አበርክቻለሁ። ታዲያ ዛሬ 60 ሚሊዮን የሚሆኑ ሕዝቦቻችንን የቀጠፈውን የጥፋት አብዮት ዋና መንስኤ በአጭሩ እንዳስቀምጥ ብጠየቅ፣ ይህንን አንድ ኃይለቃል ከመድገም የተሻለ ምንም ማለት አልችልም፡- “ሰዎች እግዚአብሔርን ረስተዋል፤ ይህ ሁሉ የተፈጠረው ለዚህ ነው።"… አዎ፣ በዚህ ክፍለዘመን ለነበሩት ታላላቅ ወንጀሎች ሁሉ መሠረታዊ መንስኤ፣ መለኮታዊ ገጽታውን የተነፈገው የሰው ልጅ ንቃተ ህሊና…
❤11
Signed Tinsae
21 Jul 2026, 16:53 UTC348 views9 reactionsread 7 August 2026 Photo
ቃል እንደገባነው፣ እነሆ 🙂
ሶረን ኪርክርድና፣ ፊዮዶር ዶስቶዬቭስኪን ማንበብ የምትፈልጉ ወይም በማንበብ ላይ ያላችሁ፣ ይህንን ካርታ ብትጠቀሙበት አሪፍ የሀሳብ ፍሰት ታገኛላችሁ።
አረንጓዴ= ለማንበብ ቀላል
ቢጫ= መካከለኛ ክብደት
ብርቱካናማ= ጠጠር ያለ
ቀይ= በጣም ከባድ
ክብደቱ/ቅለቱ የተመዘነው ከመጽሐፉ ብዛት (Volume) እና ለማንበብ ከሚጠይቀው የመረዳት አቅም አንጻር ነው። አብዛኞቹ መጽሐፍትን ኦንላይን ለማግኘት ቀላል ናቸው፤ ለማግኘት የሚያስቸግሯችሁ መጽሐፍት ካሉ ግን፣ ኮመንት ላይ ጠይቁኝና እልካቸዋለሁ።
❤7👍1🔥1
Signed Tinsae
19 Jul 2026, 17:18 UTC340 views10 reactionsread 7 August 2026 Photo
...ከክርስቶስ ጋር የሚኖረን ግንኙነት ይህንን ይመስላል። አንድ ሰው "ከክርስቶስ የሚበልጥብኝ ነገር አለን?" ብሎ ራሱን ይፈትሻል። ከዚያም እንዲህ ይላል፦ “ሁሉንም ነገር በክርስቶስ ላይ እጥላለሁ”። ከዚህ ባለፈ ከክርስቶስ ጋር ስላለኝ ግንኙነት ምንም አይነት ቀጥተኛ ማረጋገጫ ሊኖረኝ አይችልም። እምነት እንዳለኝ ወይም እንደሌለኝ እንኳን እርግጠኛ መሆን አልችልም — ሲጀመርም እምነት ማለት በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ ውስጥ እየኖሩ፣ ፈጽሞ አለመጠራጠር ነውና... "በእርግጥ እምነት አለኝን?" የሚለው ስጋት ራሱ አንዱ የእምነት አካል ነው።
- ኪርክጋርድ
@Jacobite_apologetics27
❤8🔥2
Signed Tinsae
14 Jul 2026, 04:34 UTC575 views10 reactionsread 7 August 2026 Photo
በሳይንስ ላይ ያለን እምነት አሁን ድረስ በዲበአካላዊ (metaphysical) እምነት ላይ የተመሠረተ ነው - እኛ የዛሬ አዋቂዎችና፣ አምላክ የለሽ ጸረ-ዲበአካላውያን ሳንቀር፣ አሁን ድረስ እሳታችንን የምንወስደው ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ከተለኮሰው የክርስቲያኖች እምነት ነው። "እግዚአብሔር እውነት ነው፣ እውነት መለኮታዊ ነው" ...ይህ ሀሳብ እስካሁን በሁሉም ፍልስፍና ላይ የበላይ ሆኗል... በዚህ ምክንያት የእውነት ዋጋ ለጥያቄ እንዲቀርብ እንኳን አልተፈቀደም። በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት ከተካደበት ቅጽበት ጀምሮ ግን፣ አዲስ ችግር አብሮ ይነሳል፦ እውነት ዋጋዋ ምንድነው?
- ፍሬድሪክ ኒቼ
@Jacobite_apologetics27
❤9🔥1
Signed Tinsae
10 Jul 2026, 13:55 UTC498 views8 reactionsread 7 August 2026 በአልበርት ካሙ "The Rebel" መጽሐፍ ውስጥ ከምናገኛቸው ጠቃሚ ትምህርቶች አንዱ የ "ገደብ" ጽንሰ ሐሳብ ነው። በካሙ መሠረት፣ ሁሉም ርዕዮተዓለሞች (ideologies) ፍልስፍናዊም ሆኑ፣ ፖለቲካዊ፣ ወይም ሃይማኖታዊ፣ ተከታዮቻቸው ሊተላለፉት የማይገባ ገደብ ያስፈልጋቸዋል። ርዕዮተዓለሙ ትክክልና መቶ ፐርሰንት እውነት እንደሆነ እርግጠኛ ብንሆን እንኳን፣ ሰው እንደመሆናችን፣ ለስህተትና ግላዊ ግድፈቶች የተጋለጥን ስለሆን፣ ርዕዮተዓለምን ተገን አድርገን የምናካሂደው ግብረገባዊ ጥሰት በሙሉ ከጅምሩ ውድቅ መደረግ አለበት።
ጭፍን ርዕዮተዓለማዊ አምልኮን በተመለከተ፣ ክርስትና የሚያቀርበው የራሱ ማስጠንቀቂያ አለ። በማርቆስ ወንጌል እንዲህ እናነባለን፦
"…
❤8
Signed Tinsae
10 Jul 2026, 13:55 UTC399 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed Tinsae
9 Jul 2026, 05:42 UTC536 views8 reactionsread 7 August 2026 ብዙ ጊዜ ተቃራኒው ቢነገረንም፣ "እኩልነት" የሚባለው ዘመናዊ ጽንሰ ሐሳብ፣ ተፈጥሯዊ እንዳልሆነና ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ጋር እንደሚጣረስ ማስታወስ ያስፈልጋል። ተዋረድ (Hierarchy) የሰው ልጆች አንዱ በሌላው ላይ ለመሰልጠን ብለን የፈበረክነው ነገር ሳይሆን፣ ከተፈጥሯችን ጋር በጥብቅ የተቆራኘ አመጣጥ ያለው፣ "ሕይወት" የምንለው ነገር በምድር ላይ እስካለ ድረስ የሚኖር አስፈላጊ መስተጋብር ነው።
ተዋረዶች (hierarchies) ሊጠፉ የማይችሉበት ምክንያት ቀላል ነው። በዚህ ውስብስብ ዓለም ውስጥ በአግባቡ ለመንቀሳቀስ ከፈለግን አንዳንድ ነገሮችን ከሌሎች አስበልጠን ማየት አለብን። ለምሳሌ ሳይንቲስት መሆን የሚፈልግ ሰው ምርምርን ከመሃይምነት …
❤4🔥3👍1
Signed Tinsae
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @jacobite_Apologetics27. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.