19 Aug 2026, 12:07 UTC486 views22 reactionsread 4 September 2026 ከፈጣሪ ጋር ፍጡር ማየት የማይፈልግ ሰው በታቦር ተራራ ዕድል ፈንታ የለውም።
ሙሴ የአምላኩን ፊት ለማየት ጸለየ።
"ጀርባየን ታያለህ እንጂ ፊቴን አታይም" ተብሎ የተመኘውን የአምላኩን ፊት ሳያይ ቀረ።
ከሺ 600 ዐመታት በኋላ ግን ምኞቱ ተፈጽሞለት የጌታውን ፊት በደብረ ታቦር አየ።
ሙሴ የፈጣሪውን ፊት ብቻ አላየም። ፈጣሪ ያከበራቸው የኤልያስንና የሐዋርያቱንም ፊት አይቷል።
ጌታችን ክርስቶስ ክብሩን በገለጠበት በታቦር ተራራ እንዲሁም ዐለምን ለማሳለፍ መጥቶ ሲገለጥ ካከበራቸው ቅዱሳን ጋር ነው።
"ናና ኢየሱስ" ብለህ በተገለጠበት ቦታ ሁሉ የገለጣቸውን ወዳጆቹን ከጠላህ ቁርጥህን እወቅ። ብቻውን አይገለጥም!
እንዲህ አይነት እምነት ካለህ፥ ቦታህ ጥብርያዶስ …
👏12❤4👍3🥰3
3 Aug 2026, 15:52 UTC932 views34 reactionsread 4 September 2026 Photo
መድኃኔዓለም ማለት የዓለም መድኃኒት፣ የፍጥረት ሁሉ አዳኝና ታዳጊ ማለት ነው። በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነትና አስተምህሮ መሠረት መድኃኔዓለም የሚለው ስም የጌታችን፣ የመድኃኒታችንና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ግብሩን፣ ፍቅሩንና ቸርነቱን የሚገልጽ ታላቅና ክቡር ስም ነው።
መድኃኔዓለም በሰው ልጅ ውድቀትና በኃጢአት ምክንያት የመጣውን የሞት ፍርድ በፍጹም ፍቅሩ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በመሞት ያስወገደ፣ ዓለምን ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከባርነት ወደ ነፃነት ያሸጋገረ አምላክ ነው።
መድኃኔዓለም የኃጢአተኞች መጠጊያና የምሕረት አምላክ ነው። ምንም ያህል ብንበድል እንኳ በተሰበረ ልብ ወደ እርሱ ስንመለስ በክንዱ ታቅፎ የሚቀበል አባት ነው።
"መድኃ…
❤21🙏11🔥1🥰1
25 Jul 2026, 19:11 UTC≈1,180 views39 reactionsread 4 September 2026 Photo
"ሕፃን ልጅ እንደ ትልቅ ሰው ሲናገር ያስደንቃል።
ትልቅ ሰው እንደ ሕፃን ሲናገር ግን ያሳቅቃል"።
ዛሬ ብላቴናው ቂርቆስ፥ "እናቴ ሆይ ገድላችንን እንፈጽም ዘንድ ጨክኚ"። ብሎ እንደ ትልቅ ሰው የተናገረበት ዕለት ነው።
ትልቅ ሰው ሆነው እንደ ሕፃን የሚናገሩትን ያሳድግልን።
🙏30❤9
22 Jul 2026, 05:46 UTC≈1,300 views35 reactionsread 4 September 2026 ፍቅር ቊስል ነው
እውነቱ ይህ ነው ፣ ፍቅር የሚለካው በልባችን ላይ በተወው ቊስል ልክ ነው።
እጅግ የምንወዳቸው ሰዎች አሳምመውን ይሆናል።
እኛም እጅግ የሚወዱንን ሰዎች አሳምመን ይሆናል።
ምክንያቱም ፍቅር የሚታየው በታገስነው ቊስል ውስጥ ነው::
ፍቅር የሚታወቀው በተለዋወጥናቸው ቃላት ሳይሆን በታገስነው ቊስል ፣ በተሰማን የውስጥ ሕመም ፣ በከፈልነው መሥዋዕትነትና በተካፈልነው ብርሃን ነው።
ከትንሣኤው በኋላ በሐዋርያቱ ፊት የተገለጠው ክርስቶስ እርሱ የሚወዱት ጌታ እንደሆነ ለማስረዳት ያሳያቸው የትንሣኤውን ድል ማብሠሪያ መለከት ሳይሆን ፣ የፍቅሩ ማስረጃው ቁስሉ ነበር።
Henok Haile
❤27👍5👏3
14 Jul 2026, 14:30 UTC≈1,250 views13 reactionsread 4 September 2026 በአብርሃም ደጅ የተገለጡ ሥላሴ ብቻ አይደሉም።
እኒህ ሁሉ ተገልጠዋል እንጂ።
1ኛ ምስጢረ ሥላሴ፦
"ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ" ዘፍጥረት ምዕ 18፥2
ይህ መገለጥ ምስጢረ ሥላሴ ይባላል።
ጥንት ሰውን በአምሳላቸው የፈጠሩ ሥላሴ፥ዛሬም ለአብርሃም በሰው አምሳል ተገልጠዋል።
መሆንና መምሰል እንደሚለያይ ልብ ይሏል።
2ኛ ምስጢረ ሥጋዌ/የአምላክ ሰው መሆን ምስጢር፦
ልጁ ይሥሐቅን ሊሠዋ ወደሞርያም ተራራ ወጥቶ ነበር። በልጁ ፈንታ በግ ሠውቶ ተመለሰ። ዘፍጥረት 22፥1-14።
ይህ ምስጢረ ሥጋዌ ይባላል።በእኛ ስለእኛ የሚሰዋው የቀራንዮ በግ- ክርስቶስ ምሳሌውን በዚያ ተራራ አሳይቶናልና።
በደጁ ምስጢረ ሥላሴን
በልጁ ምስጢረ ሥጋዌን ተረዳን።
3ኛ ምስጢረ ጥምቀት…
❤12👍1
10 Jul 2026, 06:41 UTC≈1,210 views12 reactionsread 4 September 2026 "ጠባቂ እንደሌለው በግ እንዳንኾን አባግዕን በዚያም፥ በዚያም ዘልቀው አራዊት እንዲነጣጠቋቸው ተኵላ እንዳይነጥቀን አለ፤ መናፍቃን እንዳያስክዱን። በሃይማኖት ከኛ የተለዩ አሕዛብ መናፍቃን እንዳይነቅፉን። እኒኽ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ጳጳስ ደግ ንጉሥ የማያስነሣላቸው ሃይማኖታቸው የቀና ባይኾን እንጂ ነው ብለው፤ ሐተታ፦ ሕዝቡ ቢከፉ ባይመለሱ በሕዝቡ ክፋት ዓላዊ ንጉሥ መናፍቅ ጳጳስ ያስነሳባቸዋል። ወያነግሥ ብእሴ መደልወ በእንተ እከየ ሕዝብ እንዲል። ሕዝቡ ግን ደግ ቢኾኑ ቢመለሱ በሕዝቡ ደግነት ደግ ራትዕ ንጉሥ ሃይማኖታዊ ጳጳስ ያስነሳላቸዋል፤ ወያነግሥ ብእሴ ራትዓ በእንተ ሠናይተ ሕዝቡ እንዲል፤ ይኽ ከሞተበት ጀምሮ እስኪ ሾም ድረስ የሚጸልይ ነው።"[ሥርዐተ …
❤12
3 Jul 2026, 16:46 UTC≈1,400 views18 reactionsread 4 September 2026 + በእግዚአብሔር መንግሥት አንድ ቀን +
ጸአተ ነፍስ (The departure of Soul) ከተሰኘው የኦርቶዶክስ ቴዎሎጂ ምሁራን የጋራ ሥራ የሆነ ዳጎስ ያለ ድንቅ መጽሐፍ መግቢያ ላይ አንድ አባት ስለ አንድ ሰው ታሪክ የጻፉት ነገር በጣም አስገራሚ ነበር:: እጅግ መጥፎ የነበረ አንድ ሰው ድንገት በጠና ይታመምና በአልጋ ላይ ይውላል:: ሕመሙ እጅግ የጠና ቢሆንም የማይገድለው ሆነና ለሠላሳ ዓመታት ተሠቃየ:: በክፉ አመል ላይ ክፉ ሕመም ተጨምሮ ለሌሎችም ችግር ሆነ:: በአልጋው ላይ ሆኖም ደጋግሞ ሰውንም ፈጣሪውንም ይሳደብ ነበር::
ከሠላሳ ዓመታት ሥቃይ በኁዋላ ግን ይህ ሰው ነፍሱ ከሥጋው ተለየች:: የመንደሩ ሰው ተሰበሰበና ማልቀስ ጀመረ:: "ውይ ተገላ…
❤18
28 Jun 2026, 09:38 UTC≈1,410 views32 reactionsread 4 September 2026 Photo
ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች!!!
"ያዘነች ስትሆን በልጅሽ በወዳጅሽ ትንሣኤ የተጽናናችው፡፡ የተዋረደች ስትሆን በድንግልናሽ ቡቃያ መውጣት ከፍ ከፍ ያለችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች፡፡በዕለተ ዓርብ ከልጅሽ ቀኝ በፈሰሰው ውኃ ተጠምቃ የውግታቱን ደም ተቀብታ ቅድስት ቤተክርስቲያን ታመሰግንሻለች።የልዑል እግዚአብሔር በግ የተባለ ልጅሽ አማኑኤል የተሞሸረባት መርዓዊ ሰማያዊ የተባለባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
እንኳን እመቤታችን ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን!
❤32
27 Jun 2026, 05:23 UTC≈1,100 viewsread 4 September 2026 https://youtu.be/m-gQFYAacdc?si=GnRrea8w-iQT0bqn
24 Jun 2026, 09:45 UTC≈1,380 views16 reactionsread 4 September 2026 Photo
የቅዱስ ጳውሎስ ልብስ!
በዚህ የሐዋርያት ጾም ሐዋርያው ጳውሎስን እንዴት እያነበባችሁ ነው?
❤12💯4
24 Jun 2026, 08:27 UTC≈1,500 viewsread 4 September 2026 File
File, posted without a caption
24 Jun 2026, 08:16 UTC≈1,330 viewsread 4 September 2026 🎈በምን እጽናናለሁ?🎈በዘማሪ ሚክያስ አረጋዊ 🎈አዲስ መዝሙር 🎈New Mezmur
https://youtube.com/watch?v=dJieVgi0-84&si=bRCTL8gCgTZ8RV_m
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @henokhaile_dn. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.