17 Jul 2026, 11:42 UTC448 views2 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @gebeyanewsPhoto
አዲስ አስመጪዎችና ላኪዎች የብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥርን በአንድ መስኮት አገልግሎት እንዲያገኙ ተፈቀደ
ሐምሌ 10/2018 (ገበያ ሚዲያ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ አስመጪዎችና ላኪዎች የብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥርን በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአንድ መስኮት አገልግሎት በኩል እንዲያገኙ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡
ባንኩ ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር አዲስ ፍቃድ ላወጡ አስመጪዎችና ላኪዎች የብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥር አሰጣጥን የሚያቀል አዲስ የዲጂታል አገልግሎት አስተዋውቋል፡፡
አገልግሎቱ የባንኩ የሂሳብ ቁጥሮች በጉምሩክ ኮሚሽን አንድ መስኮት አገልግሎት በኩል ያለምንም ውጣ ውረድ እንዲሰጥ በማስቻል አስተዳደራዊ ሂደቶችን የሚቀንስና ፈጣን የንግ…
❤2
14 Jul 2026, 15:34 UTC537 views1 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @gebeyasportPhoto
የዳኝነት ውዝግብ በእንግሊዝ እና በአርጀንቲና ግማሽ ፍፃሜ በእንግሊዝ ሚዲያዎች የቀረበው የሰላ ትችት !
ሐምሌ 07፤2018 (ገበያ ስፖርት)
ለአርጀንቲና እና ለእንግሊዝ የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ አሜሪካዊው ዳኛ ኢስማኤል ኤልፋት መመረጣቸው በእንግሊዝ ሚዲያዎች ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያ እና ቅሬታን ፈጥሯል።
የብሪታኒያ ታዋቂ ጋዜጦች በየግንባር ገጾቻቸው ላይ እንደዘገቡት የዳኛው መመረጥ አድሏዊነት የተሞላበት መሆኑን በመግለጽ ጥርጣሬያቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።
ዴይሊ ሜይል በዘገባው በዓለም ዋንጫው ላይ "ማጭበርበር አለ" የሚሉ ወሬዎችን በመጥቀስ፣ ሊዮኔል ሜሲ በግማሽ ፍጻሜው "የራሱን ተወዳጅ ዳኛ" ማግኘቱን በግልጽ አስፍሯል።
በበኩሉ ዘ ሰን የተሰኘ…
❤1
13 Jul 2026, 12:36 UTC523 viewsread 7 August 2026 Forwarded from @gebeyanews
https://gebeyaethiopia.com/p/127
ሳዑዲ አረቢያ 1 ሺህ 971 ኢትዮጵያውያንን በንጉሣዊ ምሕረት እንደለቀቀች ተገለጸ
በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመታደግ በተደረገው የዲፕሎማሲ ጥረት 1 ሺህ 971 ኢትዮጵያውያን የንጉሣዊ ምሕረት ተጠቃሚ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
እነዚህ ዜጎች በሳዑዲ አረቢያ የሕግ ሒደትና የፍርድ ውሳኔ ላይ የነበሩ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በተከታታይ በረራዎች ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ እንደሚገኙ ሚንስቴሩ ገልጿል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው የኢትዮጵያ መንግሥት በውጭ አገር ለሚኖሩ ዜጎቹ ደኅንነ…
12 Jul 2026, 17:51 UTC534 views1 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @gebeyasportPhoto
ዝላታን ሰለ ለሊቱ ጨዋታ ዳኝነት ...!
ሐምሌ 04፤2018 (ገበያ ስፖርት)
የእግር ኳስ ኮከቡ ዝላታን ኢብራሂሞቪች በዓለም ዋንጫው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ላይ የሲውዘርላንዱ ተጫዋች ኤምቦሎ በፈጸመው የተጋነነ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ዳኛው የወሰዱትን እርምጃ አድንቋል።
ዝላታን በሰጠው አስተያየት ዳኛው የወሰዱት ውሳኔ ትክክለኛ መሆኑን በመግለጽ፣ እንደ ኤምቦሎ ያለ የሰውነት ቁመና እና ልምድ ባለው ተጫዋች በዓለም ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ደረጃ እንዲህ አይነት ህጻንነት የሚታይበት ድርጊት መፈጸም ተገቢ አለመሆኑን ተናግሯል።
በቅርብ ጊዜያት ብዙ ሰዎች የቪዲዮ ረዳት ዳኛንት (VAR) በተመለከተ አሉታዊ አመለካከት እያሳዩ ቢሆንም፣ በዚሁ ጨዋታ ላይ የታየው የቴክኖሎጂ …
❤1
9 Jul 2026, 16:13 UTC671 views1 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @gebeyasportPhoto
መድፈኞቹ ከጉማሬሽ ጋር ስምምነት ላይ ደረሱ!
ሐምሌ 2/2018 ዓ/ም (ገበያ ስፖርት) አርሰናል ከብሩኖ ጉማሬሽ ጋር በአምስት ዓመት ኮንትራት መስማማቱ ተዘግቧል።
በዝውውር መስኮቱ በአርሰናል የዝውውር ራዳር ክትትል ውስጥ የነበረው ብራዚላዊው ቡርኖ ጉማሬሽ ወደ ሰሜን ለንደን ለማምራት ከመድፈኞቹ ጋር የተስማማ ሲሆን ለክለቡ ኒውካስትልም የልቀቁኝ ጥያቄ ማቅረቡ ተሰምቷል።
አሁን ላይ ቡርኖ ጉማሬሽ ወደ አርሰናል ለማምራት የሚያስችለውን ስምምነት ለመፈጸም የክለቦች ስምምነት ብቻ ይቀራል።
ኒውካስትል አርሰናል ያቀረበውን የ70 ሚሊዮን ዩሮ የመጀመሪያ ዙር የዝውውር ጥያቄን ውድቅ ማድረጉ ይታወቃል።
ሆኖም ግን የተጫዋቹ ጫና እና የመድፈኞቹ አዲስ የተሻሻለ የዝ…
❤1
5 Jul 2026, 12:05 UTC732 views2 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @gebeyasportPhoto
የኢትዮጵያ አትሌቶች በዓለም አቀፍ መድረኮች የሚያስመዘግቡትን ድንቅ ድል አጠናክረው ቀጥለዋል።
ሰኔ 28/2018 ዓ.ም (ገበያ ስፖርት)
በአሜሪካ በተካሄዱት የ2026 ፕሪፎንቴይን ክላሲክ (ዩጂን ዳይመንድ ሊግ) እና የ57ኛው የፒችትሪ የጎዳና ሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ በመሆን የላቀ ብቃታቸውን አሳይተዋል።
ዩጂን ዳይመንድ ሊግ (የሴቶች ሁለት ማይል)
በዩጂን በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር፣ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ብርቱ ፉክክር አድርገዋል። አትሌት አለሺኝ ባወቀ ውድድሩን በ9:20.02 በማጠናቀቅ አንደኛ ስትወጣ፣ አትሌት ሒሩት መሸሻ በ9:20.20 በሆነ ሰዓት በቅርብ ልዩነት ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች። በዚሁ ውድድር አትሌት ማርታ አ…
❤2
3 Jul 2026, 07:34 UTC771 views1 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @gebeyasportPhoto
ላሚን ያማል ለጨዋታ ወደ ስታዲየም ሲደርስ ያደረገው ውድ የጌጣጌጥ ምርጫ መነጋገሪያ ሆነ !
ሰኔ 25፤2018 (ገበያ ስፖርት)
የስፔኑ ወጣት ኮከብ ላሚን ያማል ከኦስትሪያ ጋር ላለባቸው ወሳኝ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ለማድረግ ወደ ስታዲየም ሲያቀና በአንገቱ ላይ አርጎት በነበረው ሀብል ርዕስ ሁኗል።
ያማል ከቅርብ ጊዜ ወዲ በሚያሳየው የአለባበስ ዘይቤ ተከታዮቹን እያስገረመ ቢገኝም በአሁኑ የለበሰው የለበሰው የBatman ቅርጽ ያለው የአንገት ጌጥ ከፍተኛ ትኩረትን ስቧል።
ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ይህ በብዙዎች ዘንድ ባትማን ተብሎ እየተጠራ ያለው የአንገት ጌጥ ዋጋ 350 ሺ የአሜሪካ ዶላር ወይም በግምት 62 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር እንደሆነ ተገልጿል።
በሮ…
❤1
28 Jun 2026, 17:39 UTC941 views3 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @gebeyasportPhoto
ማኑኤል ኡጋርቴ ለ9 ወር ከሜዳ ይርቃል !
ሰኔ 21፣2018 (ገብያ ሚዲያ)
የማንቸስተር ዩናይትድ እና የኡራጓይ ብሔራዊ ቡድን አማካይ ማኑኤል ኡጋርቴ በዓለም ዋንጫው የምድብ ጨዋታ ወቅት በደረሰበት የACL ጉዳት ለብዙ ወራት ከሜዳ ተሰናብቷል።
እንደ ጋዜጠኞቹ ሮድራ ቫዝኬዝ እና ዴቪድ ኦርንስታይን ዘገባ ፥ ኡጋርቴ በዓለም ዋንጫው የምድብ ጨዋታው ላይ ከስፔን ጋር በተደረገው ፍልሚያ ከፔድሪ ጋር በተፋጠጡበት አጋጣሚ የጉልበቱ ፊት ላይ ያሉት ጅማቶች መበጠሳቸው ተግልጿል።
ምርመራዎች እንደሚያሳዩትም ጉዳቱ ከባድ በመሆኑ ተጫዋቹ ከ6 እስከ 9 ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ተረጋግጧል።
ይህ አሳዛኝ ክስተት ኡጋርቴን ከዓለም ዋንጫው ውጪ ብቻ ሳይሆን ለማንቸስተር ዩና…
❤3
26 Jun 2026, 19:12 UTC≈1,000 views1 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @gebeyasportPhoto
አርሰናል የኒውካስትል ዩናይትድ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ተዘጋጅቷል!
አርሰናል ብሩኖ ጉማሬሽን እና ቶናሊን ከኒውካስትል ዩናይትድ በአንድ የዝውውር መስኮት መውሰድ እንደሚፈልግ ተዘግቧል።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ አርሰናል ለብሩኖ ጉማሬሽ ድንገተኛ የ55 ሚሊዮን ፓውንድ የቃል ጥያቄ ቢያቀርብም በኒውካስትል ወዲያውኑ ውድቅ ተደርጓል።
ኒውካስል ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ብሩኖን በቡድኑ ውስጥ ማቆየት እንደሚፈልግ ገልጿል።
በተጨማሪም ተጨዋቹ ለሽያጭ ቢቀርብ እንኳን በዚህ የዋጋ መጠን እንደማይሸጥ ለአርሰናል ግልፅ አድርጎለታል!
ሆኖም ግን ጥያቄው ውድቅ የተደረገበት አርሰናል ለጉማሬሽ ሁለተኛ ጥያቄ ለማቅረብ እየተዘጋጀ ስለመሆኑ ታውቋል።
የማርቲን ኦዴጋርድ ቆይታ…
❤1
4 May 2026, 06:29 UTC≈1,350 views4 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @gebeyanewsPhoto
መልካም ቀን!
#ገበያ_ሚዲያ
#gebeyanews
❤4
29 Apr 2026, 07:23 UTC≈1,320 views1 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @gebeyanewsPhoto
ከዛሬ ጀምሮ የናፍጣ አቅርቦት ወደነበረበት እንዲመለስ ተወሰነ
ሚያዚያ 21 /2018 (ገበያ ሚዲያ) የናፍጣ አቅርቦት ከዛሬ ጀምሮ ቀድሞ ወደ ነበረበት እንዲመለስ መንግሥት መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በኢትዮጵያ የአንድ ቀን የናፍጣ አቅርቦት ከመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት በፊት ወደ ነበረበት 9 ሚሊዮን ሊትር እንዲመለስ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
በመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት ምክንያት የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መጨመር እና አቅርቦት ላይ መስተጓጎል መፈጠሩን ተከትሎ በኢትዮጵያ የአንድ ቀን የናፍጣ አቅርቦት ወደ 4.5 ሚሊዮን ሊትር ወርዶ እንደነበር ይታወሳል።
ሆኖም አሁን ላይ የአንድ ቀን የናፍጣ …
👍1
13 Apr 2026, 08:41 UTC≈1,500 views3 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @gebeyanewsPhoto
የአሜሪካን እገዳ ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ናረ
ሚያዚያ 5/2018 (ገበያ ሚዲያ)አሜሪካ በኢራን የወደብ መስመሮች ላይ ጥብቅ የባህር ላይ እገዳ እንደምትጥል ማስታወቋን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ገበያ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ አሳየ።
በዚህም የአሜሪካ ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ8 በመቶ በመጨመር በአንድ በርሜል 104.24 ዶላር ደርሷል።
የዓለም አቀፍ መለኪያ የሆነው የብሬንት (Brent) ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋም በተመሳሳይ የ7 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በአንድ በርሜል 102.29 ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል።
ይህ የዋጋ ንረት የተከሰተው ዋይት ሀውስ ከዛሬ ጀምሮ በኢራን ወደቦች ላይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለማገድ መወሰኑን ይፋ ካደረገ በኋላ ነው።
እን…
❤3
Showing the 12 most recent of 12 posts we hold for @gebeyamedia. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.