3 Jul 2026, 12:35 UTC≈4,260 views15 reactionsread 7 August 2026 ... ‹‹የሥላሴ አባለ ዘርዕ የላቸውም ካሉ ‹ንግበር ሰብአ
በአርአያነ ወበአምሳሊነ› ብለው የፈጠሩት አዳም አባለ ዘርዕ ይዞ ተገኘሳ?! ‹ለሥላሴ (አባለ ዘርዕ) የላቸውም ማለት አካል ማጉደል አይሆንምን?!› ቢሉ ይህስ አካል ማጉደል አይባልም፡፡የማንኛቸው አለባቸው ይሏላ?! የአዳም አለባቸው እንዳንል ሔዋንን ፈጥረዋታል፡፡ የሁለቱም አለባቸው ማለት ስድብ ነውና (ለሥም አጠራራቸው ምስጋና ይሑንና ‹ፍናፍንት› ያሰኝብናል)፡፡ ስለዚህ ነገር #ለሥላሴ_አባለ_ዘርዕ_የወንድም_የሴትም_የላቸውም ብሎ ያምኑ ዘንድ ይገባል፡፡የወንድም የላቸውም ካልን ‹አዳምን በማን አምሳል ፈጠሩታ?!› ቢሉ አዳምንስ መዋቲ ስለሆነ እንዲዋለድ ዘር እንዳይጠፋ አባለ ዘርዕ ያለው አድርገው ፈጥረ…
❤14👏1
9 Jun 2026, 16:49 UTC≈2,780 views5 reactionsread 7 August 2026 Photo
ፕሮፌሰር ጌታቸው ከተለዩን ፭ ዓመት መሙላቱን በኃይሉ ዘአዋሽ መልካሳ አስታወሰን። አሁን ላይ ሳስበው፥ 'ደስታቸውና ተስፋቸው ሳይበረዝ በዚያ ጊዜ መጠራታቸው ለበጎ ኖሯል!' እላለሁ።
እግዚኦ አእርፍ ነፍሰ ገብርከ ሣህለ ማርያም።
#ማስታወሻ ፩:- ፎቶው በ1940ዎቹ አጋማሽ አካባቢ ካይሮ ላይ የተነሡት ነው። አቡነ ቴዎፍሎስ፣ ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም (ኋላ አቡነ መልከ ጼዴቅ) እና በመካከል (እንደ አስተርጓሚ?) ፕሮፌሰር ጌታቸው ይታያሉ።
#ማስታወሻ ፪:- ብዙ ሰው ፕሮፌሰር ጌታቸው ከሊቀ ሊቃውንት መሓሪ ትርፌ (ኋላ አቡነ ጴጥሮስ) የሐዲሳት ትርጓሜ መማራቸውንና በካይሮ የቲዎሎጂ ምሩቅ፣ ከዚያ አስቀድሞም የ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ- Holy Trini…
❤4🥰1
8 Jun 2026, 05:58 UTC≈8,730 views10 reactionsread 7 August 2026 + The New Normal ስለሚባለው ነገር +
( Maryamawit Henok Lemessa )
ታውቃላችሁ? በአማርኛ ቀጥተኛ ትርጉም ላገኝለት አልቻልኩም (አዲሱ መደበኛነት/ አዲስ ልምምድ ሴንስ አልሰጥሽ አለኝ። በተሻለ የሚገልጽ ካለ ወዲህ በሉኝ) ፤ ለማንኛውም ምንድነው የሚለውን ለመግለጽ፦ አንድ ህሊናን የሚሰቀጥጥ ዘግናኝ ግፍ በተደጋጋሚ ሲከሰት፣ የሰው ልጅ አእምሮ ያለማቋረጥ የሚመጣበትን የድንጋጤ ማዕበል መቋቋም ስለሚያቅተው፣ ራሱን ለመከላከል ሲል ሰቆቃውን እንደ መደበኛ የዕለት ዜና ወደ መቀበል ይሸጋገራል።
ያልተለመደውና አሰቃቂው ግፍ ቀስ በቀስ የህይወት አካል ሲሆን፣ ትላንት ጎረቤቱ በግፍ ተገድሎና ንብረቱ ወድሞ ያደረ ሰው፣ በማግስቱ ጠዋት ምንም…
💔5❤3😍2
6 Jun 2026, 18:29 UTC≈5,540 views17 reactionsread 7 August 2026 + ምሬት +
( አለማየሁ ዋሴ እሸቴ )
ምሬት ከቁጣ ያልፋል፤ ምሬት ከብስጭት በላይም ነው፡፡ ምሬት ግብታዊ ላይሆን ይችላል፤ እንደ እሳተ ገሞራ ፈንድቶ ቀልጦ የሚቀዘቅዝ አለት ነው ብለን ማቃለል ተገቢ አይደለም፡፡ የዜጎች ምሬት ሲፈጠር እንደ ጭራሮ እሳት ነዶ አመድ የሚሆን ነው ብሎ መገመት የዋህነት ይመስለኛል፡፡
ይልቁንም ፡-
ምሬት ከድህነት (Poorness) የተናጠ የውርደት ስሜት ነው፤
ከትዕግስት በላይ የሆነ የመገፋት ስሜት ነው፤
ከሰላም እጦት የተቀዳ የተስፋ ማጣት ስሜት ነው፤
ምሬት ከኢፍታዊነትና ከአስተዳደር በደል የሚመነጭ የተበዳይነት በጥቅሉ ወገንን/ሀገርን የማጣት ስሜት ነው፡፡
እናም ምሬት የልብ ቅያሜ ነው፡፡ ምሬት የማይጠፋ እሳት…
❤13👍4
4 Jun 2026, 16:49 UTC≈8,620 views34 reactionsread 7 August 2026 ይድረስ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት።
( መስከረም ጌታቸው )
/ይፍቱኝ አባቴ-ቡራኬዎም ይድረሰኝ/
ከአንዲት የመንፈስ ልጅዎ የተጻፈ!
+++++++++++++++++++++++++++++
ይህንን ለመጻፍ ስንት ቀናት አሰብሁ? ተጨነቅሁ? ለዚህም በአምላኬና በአምላክዎት ሥም እምላለሁ፡፡
ለምን ቢሉኝ መልሴ ይህ ነው፡፡ አባቶቻችንን በማኅበራዊ ሚዲያ እየተናገርናቸው የጵጵስና ክብር እየቀነሰ፣ ክህነት አክብረው የሚኖሩትንም እያሸማቀቅናቸው ምልክት እያጣን ነው ብዬ ስለማምን ነው፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ አንዱ የቤተ ክርስቲያን ጠላት አላማ ክብረ ክህነትን የሚ…
❤20👍8🔥3🙏3
4 Jun 2026, 16:48 UTC≈5,150 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
4 Jun 2026, 12:20 UTC≈6,150 views19 reactionsread 7 August 2026 + የተገለጠው እውነታ +
(ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ )
በምሥራቃዊው ኢትዮጵያ ይልቁንም በሐረር፣ አርሲና ባሌ አካባቢዎች ላይ ትኩረት አድርጎና አቅዶ ክርስቲያኖችን የሚገድል፣ የሚያፈናቅል እና የሚያሳድድ የአክራሪ ክንፍ መኖሩ ተደጋግሞ ሲነገር ኖሯል። ይህ አካል ደርግ ወድቆ ኢህአዴግ ከተተካበት ጊዜ ጀምሮ ማንኛዋንም የለውጥ፣ የምርጫ እና የመሳሰሉትን የጫና ወቅቶች ጠብቆ አደጋ ያላደረሰበት ጊዜ የለም።
ከተቻለ የመንግሥት መዋቅርን በመጠቀምና በየዘመኑ ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም እና ለሚገድላቸው አካላት ከወቅቱ ፖለቲካ አንጻር የሚስማማ ታርጋ በመስጠት የሚቻለውን ያህል ይገድላል፣ ያፈናቅላል፣ ያሳድዳል።
ይህ የተገለጠ እውነት ነው። …
🙏8👍5❤3😭3
4 Jun 2026, 12:20 UTC≈4,830 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
26 May 2026, 13:41 UTC≈8,960 views11 reactionsread 7 August 2026 Photo
የማምሻ ዕድሜ ወግ
( ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ )
ከ"ትዝታ ዘአለቃ ለማ" መጽሐፍ በኋላ በቤተ ክህነት ሊቃውንት ዘንድ ተዘጋጅቶ የቀረበ እንደዚህ ያለ ሌላ መጽሐፍ እኔን አልገጠመኝም።
መጽሐፉ ታሪኩና ትረካው ልዩ ጣዕም ያለው መሆኑ እንደ ተጠበቀ ሆኖ በሕይወታቸው ገጠመኝነት የሚያነሷቸው አንዳንድ ጉዳዮች ግን በግሌ ብዙ ግርምቶችን ፈጥረውብኛል፣ ትልልቅ ትምህርቶችንም ሰጥተውኛል። እውነቱን ለመናገር እያረጀሁ ይሁን ወይም በሌላ ድክመቶቼ ወይም በመጽሐፉ ድክመቶች ምክንያት አንዳንድ መጻሕፍትን በጉጉት ለማንበብ ጀምሬ መቀጠል አቅቶኝ አቆማለሁ።
ይህን መጽሐፍ ረቂቁ ደርሶኝ ስመለከት ግን እንደ ዋዛ ማታ ላይ ጀምሬው ሳልጨርሰው ሌላ መጽሐፍ ለማስገባት አላስችል ብሎ…
❤11
23 Mar 2026, 12:41 UTC≈4,900 views30 reactionsread 7 August 2026 "አንዳንድ ነገሮችን ደፍሮ መናገር ያስፈልጋል፣ ብዙ ቅድስና ያላቸው መኮሳት፣ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ምዕመናን አሉን እንደ ህብረት ግን ተበላሽተናል።
አሁን ባንዲራው መሃሉ ላይ አርማ ተደርጎበት የሚውለበለበው ባንዲራው መከራከሪያ ስለሆነ ነው። የቤተ ክርስቲያን እኮ ባንዲራዋ አርማዋ መስቀል እንደሆነ ስንቱ ሰው ያውቃል? አንዳንዶች ጭራሽ በጉልላቱ በላይ ባንዲራ ይሰቅላሉ ይህ አስገራሚ ነው። እኔ ባንዲራዬን ሀገሬን እወዳለሁ ግን ቤተክርስቲያን ሊያጎናጽፋት የሚገባው ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ነው።
ይህቺ ቤተክርስቲያን ቤተመቅደሷ በሜሮን ከተቀባች በኋላ ይቺ ቦታ የእግዚዓብሄር ናት ኢትዮጵያ ውስጥ አለች እንጂ የኢትዮጵያዊያንም አይደለችም። እምነታችንን አስተካክለን አቃን…
❤21👍6🙏3
23 Mar 2026, 12:40 UTC≈3,650 views7 reactionsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤7
2 Feb 2026, 08:14 UTC≈1,720 views10 reactionsread 7 August 2026 ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ዕውቀትን በተመለከተ
( ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ )
አንድ ወንድም ከቲክታክ ውይይት ሰማሁት ብሎ የጠየቅኝ ጆሮጅዬን ጭው ነው ያደረገኝ። አንዳንድ ተወያዮች እድገት ያመጡ እና ከፍ ያለ ዕውቀት ላይ የደረሱ እየመሰላቸው ነው መሰል በአብና በወልድ መካከል ገብተው ሁሉ አስተያየት እየሰጡ መሆኑን (የጠየቀኝ ሰው ያለኝን ቃለ በቃል መድገም አልፈለግሁም) ከጥያቄው ተረድቻለሁ። ኪሩቤል ቀና ብለው ወደማያዩት ዙፋን፣ ሱራፌል በሁለት ክንፎቻቸው እግራቸውን በሁለት ክንፎቻቸው ፊታቸውን ሸፍነው ሁለት ክንፎቻቸውን ደግሞ ዘርግተው ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ብለው ከማመስገን ውጭ ወደ ማይደፍሯት ዙፋን ወይም ገናንነት መግባት የሚፈልግ ሕሊና በፍጥነት በንስሐ መመለስ…
❤10
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @birhanuadmassa. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.