6 Aug 2026, 18:32 UTC223 views6 reactionsread 7 August 2026 3:26-29 የእግዚኣብሔር ልጆች
ቁ.26-29 የእግዚኣብሔር ልጅ ለመሆን አይሁዳዊ መሆን ወይም መገረዝ አያስፈልግም። በእምነት በኩል ሁላችን በክርስቶስ እየሱስ የእግዚኣብሔር ልጆች ነን።
- በእግዚኣብሔር መንግስት ውስጥ አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፣ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፣ ወንድ ወይም ሴት የለም፤ ሁላችንም በክርስቶስ እየሱስ አንድ ሰው ነን። ኤፌ 2፥13-18
INSTAGRAM | YOUTUBE | TIKTOK
#summer_bs #galatians
#astu_ecsf #digital_strategy
❤6
6 Aug 2026, 18:32 UTC210 views3 reactionsread 7 August 2026 Photo
3:15-25 የኦሪት ሕግ እና የተስፋው ቃል
ቁ.15-18 እግዚኣብሔር በዘፍ 15፥13-21 ለአብርሃም በተስፋው ቃል ለብዙ እንደሚናገር ለዘሮችህ ሳይሆን "ለዘርህ" ብሎ ተናገረው፤ እርሱም ከአብርሃም ዘር የሆነው ክርስቶስ ነው።
- ሕጉ ለአብርሃም ከተሰጠው ከተስፋው ቃል ከ430 ዓመት በኃላ ነው የተሰጠው። ይህ ሕግ የተስፋውን ቃል ሊሽር ወይም ሊያፈርስ አይችልም።
- የእግዚኣብሔር ልጆች በመሆናችን የምንቀበለውን ርስት የምናገኘው በሕጉ በኩል ሳይሆን የተስፋውን ቃል በሰጠው በእግዚኣብሔር ላይ ባለን እምነት ነው።
ቁ.19-25 ሕጉ የተሰጠው በመላእክት እጅ መካከለኛ በሆነው በሙሴ በኩል ነው።/ዘዳ 33፥2, ሐዋ 7፥38,53/
• ሕጉ ለምን ተሰጠ?
• …
❤3
4 Aug 2026, 07:52 UTC327 views8 reactionsread 7 August 2026 Photo
የሶማሊ ህዝብ ክፍል
💥ሶማሌዎች አንድ ቋንቋ ይጋራሉ፣ ነጠላ እምነትን ይከተላሉ፣ የዘላን አኗኗር ስርዓትን ይከተላሉ። አንድ ሰው ባሉት ግመሎች ብዛት ቁጥር ክብሩን ይጨምራል የሚል አመለካከት አላቸው። በጎሳ የተከፋፈሉ ህዝቦች ናቸው።
እምነታቸው ምንድነው?
ምንም እንኳን ሶማሌዎች ከሞላ ጎደል ሁሉም የሻፊዒት ሙስሊሞች ቢሆኑም፣ ብዙ እምነቶች እና ወጎች ከእስልምና ልማዶቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል። መደበኛ የእስልምና ጸሎቶች ብዙውን ጊዜ ይከበራሉ። ሶማሌዎች ደጋግመው ወደ ሼሁ(የሀይማኖት አስተማሪ) በመሄድ በረከቶችን ይቀበላሉ።
👉በሶማሌ ሕዝቦች መካከል ያለ መንፈሳዊ መታወር እንዲፈርስ የሚማልዱ የጸሎት ቡድኖችን እንዲያነሳ እግዚአብሔርን እየለመንን እንጸልይ!
…
❤8
1 Aug 2026, 18:11 UTC539 views8 reactionsread 7 August 2026 - እንዲሁ አብርሃም በእግዚኣብሔር እንዳመነ በእግዚአብሔር የሚያምኑ የአብርሃም ልጆች ናቸው(ሮሜ4፥12)።የአብርሃም ልጅ መሆን በዘር ሳይሆን በእግዚኣብሔር በማመን ነው።
ቁ.10-14 በሕግ ስር ያለ ሰው ሁሉ ከእርግማን በታች ነው(ዘዳ 27፥26, 28፥58)፣ በሕጉ የተጻፉትን ሁሉ የማያደርግ የተረገመ ነው ተብሎ ስለተጻፈ።
- በዘዳግም 21፥23 እንደተጻፈው በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው። ክርስቶስ ስለእኛ በመስቀል ሲሰቀል ስለእኛ እርግማን ሆነ። ክርስቶስ ስለእኛ እርግማን የሆነው እኛን ከሕግ እርግማን ነፃ ሊያወጣን ነው። ስለዚህ መልሰን ከሕግ ባርነት ስር መሆን የመስቀሉን ስራ ዋጋ ማሳጣት ነው።
INSTAGRAM | YOUTUBE | TIKTOK
#su…
❤8
1 Aug 2026, 18:10 UTC489 views4 reactionsread 7 August 2026 Photo
ላለፉት 2 ሳምንታት በአንድ አንድ ምክንያቶች ተቋርጦ ስለነበር ከልብ የሆነ ይቅርታ እንጠይቃለን እናም ጥናታችን እንደገና መጀመራችንን ልናበስራችሁ እንወዳለን፤ተባረኩ።
ምዕራፍ-3
3:1-14: እምነት ወይስ የኦሪትን ሕግ መጠበቅ
ቁ.1-5 ጳውሎስ ከሰበከላቸው ወንጌል የገላትያ ሰዎች ወደኃላ በማለታቸው በጣም ተገርሞ ተከታታይ የሆኑ ጥያቄዎችን ይጠይቃቸዋል።
- የክርስቶስ መሰቀል በጳውሎስ ጽሑፎች ወንጌልን የሚያመለክት ሲሆን(1ቆሮ 1፥23) ይህን የተሰበከውን እውነተኛ ወንጌል እንዳያስተውሉ ያደረጋቸው ምን እንደሆነ ይጠይቃቸዋል።
- አስቀድሞ በመጀመሪያ ጳውሎስ ወንጌልን ለገላትያ ሰዎች በሰበከ ጊዜ ከመስማት በሆነ እምነት አምነው የእግዚኣብሄርን መንፈስ ተ…
❤4
28 Jul 2026, 15:58 UTC690 views10 reactionsread 7 August 2026 Photo
የሱሪ ህዝብ ክፍል
💥ሱርማ ወይም ሱሪ በመባል የሚታወቁት ሕዝቦች የሚኖሩት በኢትዮጵያ ደቡብ ምዕራብ ዳርቻ አካባቢ ነው። በእነዚህ ሕዝቦች መካከል የሚስዮን አገልግሎት የተጀመረው በ1970ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ነበር። ሆኖም ግን፣ በተለያዩ ውጫዊ ተጽዕኖዎች ምክንያት አገልግሎቱ ለጥቂት ዓመታት ብቻ ቆይቶ ሊቋረጥ ችሏል።
የፀሎት ርዕሶች
👉የሱሪ ህዝብ ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲያውቁና በእርሱ ከዘላለም ጥፋት እንዲያመልጡ እንጸልይ!
👉ወደዛ አከባቢ የሚላኩ የወንጌል ሰራተኞች እግዚአብሄር እንዲያብዛ እንጸልይ!
👉በዛ አከባቢ ያሉት ጥቂት ደቀመዝሙራት ለሌሎች ይህን ብርሃን እንዲገልጡ እንፀልይ!
❤10
23 Jul 2026, 11:20 UTC962 views7 reactionsread 7 August 2026 https://youtu.be/mHNfvZDlYE8?si=_7-R02m5xIQQJQMr
Out now!
#astu_ecsf #digital_strategy #lad
❤7
22 Jul 2026, 04:05 UTC842 views19 reactionsread 7 August 2026 Video
📣 Our final drop hits thursday, stay tuned!
https://youtu.be/mHNfvZDlYE8?si=EGFd05caA9E5gVXw
Who is excited, drop🔥
INSTAGRAM | YOUTUBE | TIKTOK
#astu_ecsf #digital_strategy #LAD
🔥19
20 Jul 2026, 19:39 UTC888 views11 reactionsread 7 August 2026 Photo
ለቱርካና የሕዝብ ክፍል
💥የቱርካና ሕዝቦች የሚኖሩባቸውን ቤቶች የሚገነቡት ከእንጨት በተሠሩ የዶሜድ ቡቃያዎች (ፍሬሞች) ላይ የዶም ፓልም ዛፍ ‘ሃይፋኔን ቴባይካ’፣ ቆዳ ወይም ሌጦ እና ሳር በማልበስ ነው። ቤቶቻቸው በአማካኝ ስድስት የቤተሰብ አባላትን ለማኖር በቂ እንዲሆኑ ተደርገው ይሰራሉ። ብዙውን ጊዜ በእርጥበት ወቅት ፍሬሞቹ ረዣዥም ይደረጉ እና በጭቃዎች ይሸፈናሉ። በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት አብዛኛው ቱርካና ማህበረሰብ ክፍሎች ከባህላዊ የከብት እርባታ ወደ ዘመናዊ አርብቶ አደርነት ለመቀየር ተገደዋል።
የማህበረሰብ አለቃዎች ወይም ሽማግሌዎች የሏቸውም። የፖለቲካ ተጽእኖ ማሳደር የሚችሉት እድሜ፣ ሀብት፣ ጥበብ እና የንግግር ችሎታ ያላቸው ግለሰቦ…
❤11
17 Jul 2026, 17:34 UTC≈1,020 views5 reactionsread 7 August 2026 ለህብረታችን ምሩቃን በሙሉ ...
📌 ሰላም የተወደዳችሁ የህብረታችን የምሩቃን የASTUECSF Graduates ቴሌግራም ግሩፕ join በማድረግ ከ ምሩቃን (graduates) ጋር በተያያዘ የሚለቀቁ መረጃዎችን ማግኘት ትችላላችሁ።
https://t.me/astuecsf_graduates
❤5
16 Jul 2026, 14:32 UTC≈1,060 views7 reactionsread 7 August 2026 ቁጥር 17-18. ጳውሎስ የሚሰብከው ከሕግ ነፃ የሆነ ወንጌል አንድ ጥያቄን ሊያስነሳ እንደሚችል በማወቅ አስቀድሞ መልስ ሰጥትበታል።ጥያቄውም: ወንጌል ከሕግ ባርነት ሰውን ነፃ የሚያወጣ ከሆነ ሰው ሀጥያትን እንዲያደርግ ፈቃድን አይሰጥም?፣ እኛስ በክርስቶስ የምናምን ሀጥያተኛ ሆነን ከተገኘን ክርስቶስ የሀጥያት አገልጋይ ነው? አይደለም።
ቁጥር 19-20. ጳውልስ እንዲህ በማለት መልስ ይሰጣል።ከክርስቶስ ጋር ተሰቂያለው፣እኔም አሁን ህያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፣አሁንም በስጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝ እና ስለእኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለእምነት የምኖረው ነው።
->ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለው ሲል አሮጌውን ማንነት፣የስጋን ሀሳብ…
❤7
16 Jul 2026, 14:32 UTC946 views5 reactionsread 7 August 2026 Photo
ምዕራፍ 2:11-21
ጳውሎስ ጴጥሮስን ተቃወመ
ቁጥር 11-12. አንጾኪያ በሶርያ ውስጥ የምትገኝ ከእየሩሳሌም 480KM ርቀት በስተ ሰሜን የምትገኝ ከተማ ናት።በአንጾኪያ ብዙ አህዛብ የሚገኙ ሲሆን ብዙ የወንጌል ሰባኪዎች ከአንጾኪያ ወደተለያዩ አህዛብ የሚገኙባቸው ስፍራዎች ይላኩ ነበር (ሐዋ 13:1-3)።
-> በሐዋርያት ስራ 10(10:28) እግዚኣብሔር ጴጥሮስን ከአህዛብ ጋር ሕብረት ማድረግን ካስተማረው በኃላ ጴጥሮስ ከአህዛብ ጋር ማዕድ ይቆርስ ነበር።ነገር ግን አይሁድ የሆኑ የሐዋርያው ያዕቆብ ተከታዮች ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ እነርሱን በመፍራት ከአህዛብ ጋር ለማዕድ አንድ ላይ መቀመጥ አቆመ።
• እግዚኣብሔር ለአይሁድ የሰጠው የአመጋገብ ሕግ (dietary…
❤4🔥1
Showing the 12 most recent of 22 posts we hold for @astuecsf. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.