7 Aug 2026, 13:14 UTC260 views14 reactionsread 8 August 2026 Photo
"መፍቀሬ ሰብእ አቅረበነ ኀቤሁ - ሰውን የሚወድ ሰው የሚወደው እርሱ ከአባቱ ጋራ አስታረቀን። "
ከራድዮን የሚባል ፀዓዳ ዖፍ አለ ከነገሥታቱ ቤት ይኖራል። ሰው ሲታመም አምጥተው ከፊቱ ያኖሩታል። የሚሞት እንደሆነ ፊቱን ይመልስበታል የሚድን እንደሆነ ቀርቦ አፉን ከአፉ አድርጎ አስተንፋሱን ይቀበለዋል ነጭ የነበረው ይጠቁራል። ዋዕይ ፀሐይ ሲሻ ወደ ዓየር ይወጣል፤ ፫ት ሰዓት ዋዕየ ፀሐይ ተመቶ ወደ ባሕር ይወርዳል። ፫ት መዓልት ፫ት ሌሊት በከርሠ ባሕር አድሮ የ ቀደመ ጠጉሩን መልጦ ታድሶ ይወጣል።
ዖፍ ፀዓዳ የተባለ ጌታ ነው ፀዓዳ በመለኮቱ እንዲለው። ድውይ የተባለ አዳም ነው ቀርቦ አስተንፋሱን እንደመቀበል ባሕርዩን ባሕርይ አድርጓል ደዌ በእስትንፋሱን…
❤14
7 Aug 2026, 08:16 UTC539 views19 reactionsread 8 August 2026 Photo
የነሐሴ ፩
ምስባክ
"ወእነግር ስምዐከ በቅድመ ነገሥት ወኢይትኀፈር ።
ወአነብብ ትእዛዘከ ዘአፍቀርኩ ጥቀ።
ወአነሥእ ዕደውየ ኀበ ትእዛዝከ ዘአፍቀርኩ"።
መዝ 118፥46-47
መዝሙር 118
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴⁶ በነገሥታት ፊት ምስክርህን እናገራለሁ፥ አላፍርምም፤
⁴⁷ እጅግም በወደድኋቸው በትእዛዛትህ ደስ ይለኛል።
⁴⁸ እጆቼንም ወደ ወደድኋቸው ወደ ትእዛዛትህ አነሣለሁ፤ ሥርዓትህንም አሰላስላሁ።
ምንባባት
1ኛ ጢሞ 5፥1-11
1ኛ ዮሐ 5፥1-6፣
የሐዋ ሥራ 5፥26-34
ዮሐ 19፥38 - ፍ.ም
ቅዳሴ
ቅዳሴ ዘእግዝእትነ ማርያም
የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው።
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሰን። የበረከት ጾም ያድርግልን።
❤19
6 Aug 2026, 07:19 UTC467 views16 reactionsread 8 August 2026 በቅዱስ ቁርባን ዙሪያ ለተጠየቁ ጥያቄዎች መልስ
📍ጥያቄ፦ በየስንት ጊዜው ቅዱስ ቁርባን መቀበል ይገባል?
መልስ፦ በቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት አስተምህሮ መሠረት አንድ ክርስቲያን ለመቁረብ ጊዜ አይገድበውም። ንስሐ ገብቶ ቀኖና ከጨረሰ በኋላ ቅዱስ ቁርባንን መቀበል ይችላል። አንድ ምዕመን ካመነና ከተጠመቀበት ዕለት ጀምሮ ቢቻል በየዕለቱ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ፣ ካልተቻለ ደግሞ በየ፫ ወሩ ከቅዱስ ቁርባን መቀበል አለበት።ከሁሉም በላይ በዚህ ጉዳይ ላይ የንሰሐ አባታችንን ምክር መጠየቅ ይጠበቅብናል እነርሱ ካለን መንፈሳዊ ደረጃ እና ሁኔታዎችን አገናዝበው በስንት ጊዜ መቀበል እንዳለንብን እንዲወስኑ ማድረግ መልካም ነው።
የጥንት ክርስቲያኖች ዕለተ ዕሑድን የጌታ ዕ…
❤15👍1
5 Aug 2026, 11:09 UTC515 views0 reactionsread 8 August 2026 https://meet.google.com/jpe-kuyr-joo
5 Aug 2026, 10:57 UTC530 views1 reactionsread 8 August 2026 Engineering Freshman Orientation
Aug 5 • 2 – 5 PM • https://calendar.app.google/pVkvBksonvrCf3kJ9
❤1
5 Aug 2026, 03:39 UTC571 views4 reactionsread 8 August 2026 Photo
🚨 ለPre-Engineering ተማሪዎች በሙሉ!
ነገ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ ስለ ዲፓርትመንት መረጣ የሚሰጥ የኦንላይን ኦሬንቴሽን (Online Orientation) ፕሮግራም ተዘጋጅቷል !
ከእያንዳንዱ ዲፓርትመንት የመጡ Senior ተማሪዎች ስለ ዲፓርትመንቱ ገለጻ ይሰጣሉ እንዲሁም ለምትጠይቋቸው ጥያቄዎቻች መልስ ይሰጣሉ ።
⏰ ሰዓት፦ ቀን 8:00
፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
❤4
3 Aug 2026, 11:43 UTC≈1,110 views16 reactionsread 8 August 2026 Photo
ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ። ዮሐንስ 6፥54
📍የንስሐ ወር :- 4ኛ ሳምንት
ንስሐ ንዑስ ክፍል
፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
❤16
30 Jul 2026, 01:59 UTC763 viewsread 8 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
30 Jul 2026, 01:59 UTC960 views15 reactionsread 8 August 2026 ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕተ ኢትዮጵያ
ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ስለ ሀገር ነፃነትና ስለ ሃይማኖት ጽናት ሲባል ሕይወትን አሳልፎ የመስጠት ታላቅ የጀግንነትና የሰማዕትነት ምሳሌ ናቸው። በ፲፱፳፰ ዓ.ም. አረመኔው የኢጣልያ ፋሺስት ሀገራችንን በግፍ በወረረበት ወቅት፣ ብጹዕነታቸው እንደ የቤተክርስቲያን አባትነታቸው ሕዝቡን በጸሎትና በትምህርት በማጽናት ብቻ ሳይሆን፣ ከግርማዊ ንጉሠ ነገሥቱ ጋር በመሆን እስከ ማይጨው ዘመቻ ድረስ በመሄድ አርበኞችን አበራታተዋል። በወቅቱ ጠላት የመርዝ ጋዝ ጥቃት በመክፈቱ ምክንያት ሠራዊቱ ወደ ኋላ ሲያፈገፍግ ከንጉሡ ጋር ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው ነበር።
ይሁን እንጂ በጠላት የወረራ ግፍ ክፉኛ ያዘኑት አቡነ …
❤11🙏4
29 Jul 2026, 17:07 UTC≈1,220 views8 reactionsread 8 August 2026 ቊርባን ምን ማለት ነው?
🔅ቊርባን፦ ቃሉ ከሱርስት የተወሰደ ሲሆን፣ መስዋዕት ማለት ነው። እንዲሁም ቊርባን ሙሉ ትርጉሙ ለአምላክ የሚቀርብ መንፈሳዊ መባዕ ፣ ስጦታ፣ አምኃ፣ ማለት ነው። አንድም ሥጋውና ደሙ የተሰጠን በነፃ ያለ ዋጋ በችሮታ ነውና ቁርባን ስጦታ ይባላል።
🔅ምሥጢረ ቁርባን ክርስቶስ ስለ እኛ ኃጢአት በመስቀል ላይ መሥዋዕት ሆኖ በሥጋው በመሞቱ የዓለምን ኃጢአት ያስወገደበት፥ የዘላለም ሕይወትን ያስገኘበት የመዳናችን መሠረት፥ የጸጋችን ሁሉ ምንጭ የሆነውን የቅዱስ ሥጋውንና የክቡር ደሙን የማዳን ስራ የምንማርበት ታላቁ የሃይማኖታችን ትምህርት ነው።
ማንኛውንም ጥያቄ ካላችሁ እኛን ማግኘት ትችላላችሁ፦
👉 ዲ/ን ኅሩይ
0939776522 | @…
❤5🙏3
27 Jul 2026, 08:35 UTC737 views36 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @SSC_KIdme_Gibi_GubaePhoto
አቤል ይባላል የግቢ ጉባኤያችን አባልና የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነው። አሁን ግን እንደምትመለከቱት አደጋ አጋጥሞት የእኛን እርዳታ ይፈልጋልና የምንችለውን ያህል ከላይ በተጠቀሱት አካውንቶች በመላክ እናግዘው።
ማጋራትም እርዳታ ነውና ይህን ፖስት ለምናውቃቸው ሰዎች በማድረስ እነርሱም እንዲያግዙ እናድርግ
❤27🙏9
27 Jul 2026, 08:31 UTC≈1,480 views4 reactionsread 8 August 2026 Photo
በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። 1 ዮሐንስ 1፥9
ውድ የግቢ ጉባኤ ቤተሰቦች ከሐምሌ 6 ጀምሮ የተጀመረው የንስሐ ወር ተጋምሷል።
"እስካሁን የንስሐ አባት የሌለን አባት በመያዝ፣ ያለን ደግሞ ወደ አባቶቻችን በመቅረብና በመናዘዝ ሕይወታችንን እናድስ።"
📍የንስሐ ወር :- 3ኛ ሳምንት
ንስሐ ንዑስ ክፍል
፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
❤4
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @amstkiloGG. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.