4 Feb 2024, 18:54 UTC≈1,830 viewsread 6 August 2026 ኤልሮኢ፡ (⚜ብሒለ አበው⚜)
⚜ የተባረከች ዓይን የእግዚአብሔርን ቃል በማንበብ ትጠመዳለች
⚜ የተባረከች ጆሮ የንስሃ መዝሙር በመስማት እራሷን ታነፃለች
⚜የተባረከች ጉሮሮ ላይ የተቀደሰ ውሃ ይንቆሮቆርበታል።
⚜የተባረከች ምላስ የአምላኳን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም ትቀበላለች።
⚜የተባረከ አንደበት ላይ እግዚአብሔር ይመስገን የሚል ቃል አይጠፋበትም
⚜የተባረከች አንገት የአምልኮ ደም የፈሰሰበትን ቅዱስ መስቀል ትሸከማለች
⚜የተባረከች ልብ ኢየሱስን እስከ እናቱ አንግሣ በፍቅር ትሞላለች
⚜የተባረከች እጅ የቀረበላትን ምግብ በአምልኮ ስም ትባርካለች
⚜የተባረከች እግር ጠዋትና ማታ የአምላኳን መቅደስ ትረግጣለች
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
@aleroe
@ale…
Signed TESFABEL
29 Jan 2024, 18:19 UTC≈1,830 viewsread 6 August 2026 ኤልሮኢ፡ (⚜ትምህርት⚜)
” አስተርእዮ ማርያም “
አስተርእዮ ማለት መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት(የታየበት) ፣ አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል። የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር “አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል።
ልቡናዋ በይኩነኒ የጸና ንጽሐ ሥጋ ፣ ንጽሐ ነፍስ ፣ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ የያዘች ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈን…
Signed TESFABEL
7 Oct 2023, 12:47 UTC≈1,750 viewsread 6 August 2026 ኤልሮኢ፡ (⚜ትምህርት⚜)
ወርሃ ፅጌ የእመቤታችን ስደት
የእናታችን የድንግል ማርያም ስደት ታሪክ
ከመስከረም 26 እስከ ህዳር 5 ያሉት ቀናተ, ሳምንታት "ወርሃ ፅጌ"በመባል ይታወቃል።ብዙዎች "ፆመ ፅጌ" ብለው ይጠሩታል ነገር ግን በቤተ ክርስቲያናች በፍትሃ ነገስት የተደነገጉት 7 አፅዋማት አሉ።
ይህ ወቅት ፆመ ፅጌ ለመባል በቤተክርስቲያናችን ቅኖተ መሰረት ከእነዚህ ከ 7ቱ አፅዋማት ጋር አልታወጀም ስለዚህም "ወርሃ ፅጌ እንላለን" ነገር ግን ማንኛውም ክርስቲያን በፈቃደኝነት የእመቤታችን ፍቅሯን ለመግለፅ ስደቷን ለማሰብ ከልጇ ዘንድ ምህረትን ለማግኘት ከድንግል ማርያም በረከትና ምልጃ ረድኤትንም ለማግኘት መፆም ይችላል።
እነሆ የእግዚአብሔር …
Signed TESFABEL
23 Sept 2023, 20:30 UTC≈1,140 viewsread 6 August 2026 ኤልሮኢ
*ብሒለ አበው*
አንድ ሰው አንድ አባት ጋር ቀርቦ አንዳንዶች መላእክት ተገለጡልን ይላሉ ብሎ ጠየቃቸው።
እሳቸውም ከዚህ የበለጠ ደስ የሚያሰኘውስ ሁልጊዜ በኃጢአታቸውን ቢያዩ ቢያስቡ ነበር ሲሉ መለሱለት።
አንድ አባት እንዲህ አሉ ስሕተተኛ በሆናቹ ጊዜ ሁሉ ሌላውን አትወንጅሉ። ይህ የሆነው በራሴ ኃጢአትና ድክመት ምክንያት ነው በሉ። ቅዱሳን አባቶቻችን እንዲህ በማለት ተናግረዋል በርግጥ መላእክት ሊታዩክ ቢችሉ እንኳን አትቀበል ራስህን አዋርድ። እኔ ሃጢአተኛ ነኝና መላእክትን ባይ ምን ይጠቅመኛል በል።
@aleroe
Signed TESFABEL
1 Aug 2023, 09:43 UTC≈1,470 viewsread 6 August 2026 ኤልሮኢ:(⚜ትምህርት⚜)
#ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው ?
#ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል?
#ሙልሙል ለምን ይታደላል?
#ጅራፍ ለምን ይጮሃል ?
#ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡
#ጅራፍ
በደብረ ታቦር በዓል በት…
Signed TESFABEL
3 Jul 2023, 13:56 UTC≈1,290 viewsread 6 August 2026 ኤልሮኢ:(⚜ትምህርት⚜)
ይህን ያውቁ ኖሯል?
ለሰባኪያን መቆሚያ ከፍ ያለ ቦታና አትሮንስ በቤተክርስቲያን መጠቀም የተጀመረው ከ386 ዓ.ም አከባቢ ባለው ዩሐንስ አፈወርቅ ነው። ቅዱስ ዩሐንስ አፍወርቅ ቀሚያስተምርበት ጊዜ ሕዝቡ በብዛት ይሰበሰብ ነበር። ነገር ግን የዩሐንስ ቁመት አጭር ነቀረና ከፍ ብሎ ለሕዝብ እንዲታይና ድምፁም እንዲሰማ መቆሚያ ስፍራና ያጽሐፍት ማንበቢያ አትሮንስ ተሰራች። ቤተክርስቲያንም ከዚያ ዘመን ጀምሮ አትሮንስን ትጠቀምበት ጀመር።
ኑዛዜ በቤተክርስቲያን የተጀመረው ሕጋዊና ድንግል ከሆነው የእስክንድርያ 12እኛ ፓትራያርክ ከአባታችን ከቅዱስ ድሜጥሮስ ወዲህ ነው።አባታችን በከንቱ አምተውት የነበሩ ምእመናን በእግዚአብሔር …
Signed TESFABEL
18 Jun 2023, 16:04 UTC≈1,140 viewsread 6 August 2026 ኤልሮኢ:(⚜ምክር⚜)
ዝምተኛው መነኩሴ (#ራስአገዝ)
ከዝምተኛው መነኩሴ አባ ዮስጦስ ፀሎት አንዱ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ቅዱሳን በተጓዙበት ጎዳና ምራኝ" ነበር፡፡ የዚህ ጸሎት ትርጉም ቅዱስ አድርገኝ ማለት እንደነበር በህይወታቸው ፍፃሜ በሚገባ ተረድተናል፡፡ ቅዱስ እንደሆኑ ማሰብ እንጂ ቅዱስ ለመሆን ማሰብ ወይም በቅድስና መንገድ ለመጓዝ መሻትና መጸለይ መልካም ነው፤ ምክንያቱም ከፈጣሪያችን ትእዛዛትና ፈቃድ አንዱን ለመፈጸም መመኘት ነውና እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል፡፡ እግዚአብሔር በቃሉ "እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ" እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስም "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ" በማለት የቅድስናን ህይወት እንድንኖር እንደመከረ…
Signed TESFABEL
17 Jun 2023, 19:54 UTC≈1,010 viewsread 6 August 2026 ኤልሮኢ:(⚜ምክረ አበው⚜)
የአንድ አባት ምክር
በአንድ ወቅት በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ተገኚቼ ነበር፡፡ በዚያ ገዳም የሚኖሩ አባት የነገሩኝ ነገር ለሕይወት መመርያ የሚሆን ነው፡፡ አሁን ከደረስንበት ወቅት ጋር የሚሄድ ነውና ላካፍላችሁ፡፡
በወቅቱ እንደ ዛሬው በቤተ ክርስቲያን ላይ የፈተና ማዕበል ተነሥቶ ነበር፡፡ ያ ወቅት የፖለቲካው ማዕበልም እጅግ ያየለበት ጊዜ ነው፡፡ አንዳንዶቻችን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምንሰጠው አገልግሎት ምን ፋይዳ ይኖረዋል? ምንስ ለውጥ ያመጣል? ችግሩ እንደሆነ እየባሰው እንጂ እየተሻለው አልሄደም፤ ታድያ ጊዜያችንን፣ ገንዘባችንን እና ዕውቀታችንን ዝም ብለን እየከሰከስን ይሆን? አሁን የኛ ልፋት የክፉ ሰዎች…
Signed TESFABEL
15 Jun 2023, 09:18 UTC932 viewsread 6 August 2026 File
File, posted without a caption
Signed TESFABEL
15 Jun 2023, 09:18 UTC≈1,090 viewsread 6 August 2026 ኤልሮኢ ፡ (⚜ዝማሬ⚜)
የተወደደ ስምሽ ማርያም
የተወደደ ስምሽ ማርያም
እንደአንቺ ንፁህ በዓለም የለም
አሳስቢልን እንዲምረን መድኃኔዓለም
በንፅህናሽ በመመረጥሽ
ድንግል በእውነት እፁብ ድንቅ ነሽ
አሳስቢልን እንዲምረን መድኃኔዓለም
ፍጥረታት አንቺን ይማፀኑሻል
ከሲኦል ዓለም አውጪን ይሉሻል
አሳስቢልን እንዲምረን መድኃኔዓለም
አስራትሽን ኢትዮጵያን
ጠብቂልን ድንግል ህዝቧን
አሳስቢልን እንዲምረን መድኃኔዓለም
@aleroe
@Alerobot
Signed TESFABEL
17 Apr 2023, 15:02 UTC≈1,200 viewsread 6 August 2026 ኤልሮኢ :(⚜ስነፅሁፍ⚜)
ግዑዙ ከበሮ
ሁለት ወራት ሙሉ እጥፍ ቅልጥፍ ብሎ
በጾምና ጸሎት ከስራው ተገልሎ
በሐዘን በድማሜ ዘውትር አዘንብሎ
የቆየው ከበሮ ዛሬ ዜና ሰማ
የራቀው ቅላጼ በርጋታ ተሰማ
ከሩቅ አስተጋባ በሚነሽጥ ዜማ
ድምጹ ከአጽናፍ አለም ፈሰሰ በግርማ
በአምሳለ እየሩሳሌም በቅድስት ከተማ
ግዑዙ ከበሮ እንዲ ከረቀቀ
በሁዳዴ ተኝቶ ትንሳኤን ካወቀ
የሰው ልጅ ምን ነካው እንቅልፉ ጨመረ
በትንሳኤ ማግስት እንደተኛ ቀረ።
@aleroe
@Aleribot
Signed TESFABEL
23 Feb 2023, 04:17 UTC≈1,200 viewsread 6 August 2026 ⚜ መልአኩ ቅዱስ ገብርአል በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም ባለሟል በመኾኑ የድኅነትን ምሥጢር አብሣሪ ኾኗል /ሉቃ. ፩፥፲፱-፳፮/፡፡
⚜አስቴር የንጉሡ አርጤክስስ ሚስት በመኾኗ በወገኖቿ አይሁድ የታወጀውን የሞት አዋጅ አስለውጣለች /መጽሐፈ አስቴር ፫፥፲/፡፡
⚜ ነቢዩ ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት ባለሟል በመኾኑ ‹‹ይህንን ኀጢአታቸውን ይቅር በላቸው፤ ያለዚያ ግን እኔን ከጻፍከው መጽሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ?›› በማለት ለእስራኤላውያን ምሕረትን አሰጥቷል /ዘፀ.፴፪፥፲፬/፡፡
@aleroe
@Alerobot
Signed TESFABEL
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @aleroe. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.