12 Aug 2025, 12:58 UTC≈6,150 views38 reactionsread 7 August 2026 ፕሬዝደንቱ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች በሰጡት ስልጠና፣ በተለያዩ ዘመናትና ስልጣኔዎች የተለያዩ የአመራር ፍልስፍናዎች እንደነበሩ ጠቅሰዋል። በአሁኑ “ድህረ-እውነት” አለም ውስጥ፣ ሁሉም እውነት በጥያቄ ምልክት ውስጥ በመግባቱ፣ አመራር ከምንጊዜውም በላይ ብዙ ፈተናዎች እንደሚገጥሙት ገልጸዋል።
“እኛ ሰዎች ራሳችንን ለመሪነት ብቁ ማድረግ ካልቻልን፣ እኛው የፈጠርነው አልጎሪዝም ይመራናል” ሲሉ ተናግረው፣ “ነባር ነገሮች ሁሉ ፈርሰው አዳዲስ ነገሮች በፍጥነት እየተጀመሩ ባለበት በዚህ አለም፣ ረጋ ብሎ የወደፊቱን ጊዜ ለመወሰን የሚቻለው በመሪነት ብቻ ነው” ብለዋል።
ለዘመናችን የሚያስፈልገው መሪ ደፋር ብቻ ሳይሆን፣ ድፍረትንና ወኔን ከጥበ…
👍38
12 Aug 2025, 12:58 UTC≈4,690 views10 reactionsread 7 August 2026 Photo
“በዚህ ዘመን ዓለም የሚድነው ጦር በታጠቀ መሪ ሳይሆን ርዕይ በሰነቀ መሪ ነው" ዛዲግ አብርሃ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 06 ቀን 2017 ዓ.ም (አፍሌክስ)፡- ይህ ዘመን የሚጠይቀው እና የሚያስፈልገው ጦር ይዞ የሚወረውር ጋሻ ይዞ የሚመክት መሪ ሳይሆን ርዕይን የሰነቀ እና የራቀውን በምናብ አቅርቦ የረቀቀውን አጉልቶ ዕሴቱን የሚያጋራ አመራርን እንደሆነ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ተናግረዋል::
"አባቶቻችን ከጠላቶቻችን ጋር በኃላ ቀር መሳሪያ ተዋግተው ያቆዩልንን ሀገር ለቀጣዩ ትውልድ የምናሻግረው ጦር በመምዘዝ ሳይሆን ዕሴት ላይ የተመሰረተ ወኔ እና ድፍረትን የተላበሱ አመራር እያፈራን ስንሄድ ነው" የሚሉት አቶ ዛዲግ ፣ "…
👍10
12 Aug 2025, 09:56 UTC≈3,300 views8 reactionsread 7 August 2026 https://youtu.be/uU1Zm5gVcso?feature=shared
👍8
11 Aug 2025, 07:40 UTC≈3,070 views4 reactionsread 7 August 2026 Photo
የትምህርት ኃይል እና የመጪው ጊዜ ዕድል-ፈንታው
በዛዲግ አብርሃ
ዛሬ ምሽት
በአፍሌከስ የፌስቡክ እና የዩቲዩብ ገጾች👇
Facebook: https://web.facebook.com/aflexacademy.gov.et
YouTube: https://www.youtube.com/@AfricanLeadershipExcellenceAca
ትምህርት እውቀትና ወረቀት ከማግኘት በላይ ማንነታችንን የሚቀርጽ፣ የምናደርገውን፣ የምንኖርበትን መንገድ እና ወደፊታችንን የሚወስን ነገር ነው❗️
የሚያስፈልገን ምን እንደምናስብ ሳይሆን እንዴት እንደምናስብ የሚያስረዳን ትምህርት ነው!
📚ትምህርት ከትናንት እስከ ነገ
👨🔬የመምህራን ሚና፡ ከግለሰብ እስከ ማህበረሰብ
በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ …
👍4
3 Aug 2025, 19:47 UTC≈2,820 views13 reactionsread 7 August 2026 "የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሰባሳቢ ትርክት ኮንክሪት እና ብረት ወደ እምነት እንዲቀየር አድርጏል" የሚሉት አቶ ዛዲግ "ግድቡን ጀምረው ያስረከቡንን አመስግነን ፣ የነበሩበትን ችግሮች በሳይንሳዊ መንገድ ለይተን ፣ ያለንን እምቅ የመሪነት አቅም በተግባር መንዝረን ፣ የተጏደለውን አሟልተን በሙሉ አቅም የኤሌትሪክ ሀይል ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ግለት ማስጠበቂያ ሚዛን አድርገነዋል" ብለዋል::
"ግድቡ የኢትዮጵያን እና የአፍሪካን እውነታ በዓለም አደባባይ የሰበከ ሀዋርያ ነው" የሚሉት አቶ ዛዲግ "የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሰባሳቢ ትርክት በትውልዶች መካከል ስለ ሀገር የሚከፈል መስዋዕትነት እንንዲቀጥል አድርጎ መፃኢው ጊዜ የእኛ እንደሚሆን ቁልጭ አድርጎ ያ…
👍12👎1
3 Aug 2025, 19:47 UTC≈2,420 views6 reactionsread 7 August 2026 Photo
"ያጋጠሙንን ችግሮች የተሻገርናቸው 'ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ እንሆናለን' የሚለውን ትርክት ተመርኩዘን ነው" ዛዲግ አብርሃ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም (አፍሌክስ):- ሀገራት እና መሪዎች በብሄረ መንግስት ግንባታም ሆነ በብልፅግና መንገዳቸው ችግር ሲያጋጥማቸው የሚሻገሩበት አሰባሳቢ ትርክትን እንደ ምርኩዝ እንደሚጠቀሙ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ተናገሩ::
ፕሬዚደንቱ ለህዳሴ ግድብ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች በሰጡት ስልጠና ላይ እንደገለፁት በህዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት ላይ ያጋጠሙንን የቴክኒክ እና የዲፕሎማሲ ጫናዎች የተሻገርናቸው የአሰባሳቢ ትርክት መሰረት የሆነውን የክ…
👍6
3 Aug 2025, 14:36 UTC≈2,140 views9 reactionsread 7 August 2026 ግድቡ ከውሀ ፖለቲካ አንፃር የተለየ መልክ እንዳለው የሚጠቅሱት አቶ ዛዲግ "ድንበር ተሻጋሪ የሆነ ግድብ ሲገነባ በአወንታዊ እና በአሉታዊ መልኩ የቀጠናውን ፖለቲካ የመዘወር እድሉ ሰፊ ነው:: የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት እኛ የውሀው መነሻ ነን በሚል ውሀ የማይቋጥር ሀሳብ ያነሳሉ:: የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በበኩላቸው ኢትዮጵያ የውሀ መጠናችንን ቀንሳ ብቻዋን ልትበለፅግ ነው በሚል ኢፍትሀዊ አጀንዳቸውን ያራግባሉ" ብለዋል::
የታላቁ ህዳሴ ግድብን ከተለያዩ ሙያዊ መስኮች አንፃር የተነተኑት አቶ ዛዲግ "ግድቡን በፖለቲካ ሳይንስ መነፅር ስንመለከተው የመንግስትን እና የተቋማትን ፕሮጀክት ጀምሮ የመፈፀም አቅም ያመላክታል:: የቀጠናዊ ትብብርን ቅርፅ ይወስናል:: በ…
👍9
3 Aug 2025, 14:36 UTC≈1,800 views5 reactionsread 7 August 2026 Photo
“ይህ ትውልድ በጨለማ ዘመን ተወልዶ ለማያውቀው ብርሀን ታጋይ ሆኖ ህዳሴ ግድብን አዋልዷል” ዛዲግ አብርሃ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም (አፍሌክስ):- ይህ ትውልድ ብርሀን ባልነበረበት ዘመን ተወልዶ ሲናፍቀው ለነበረው ብርሀን ታግሎ ዋስትናውን እያረጋገጠ የሚገኝ ልዩ ትውልድ መሆኑን የአፍሌክስ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ተናገሩ::
"ፅልመትን ተዋግቶ ብርሀንን ነፃ ያወጣ ትውልድ አካል መሆን መታደል ነው" ያሉት አቶ ዛዲግ "ረጅሙን ምናብ ተጠቅሞ ለእሱ ሳይሆን ለትውልድ ተሻጋሪ ተጨባጭ እውነታን ያወረሰ ትውልድ በታሪክ አይረሳም:: የአባይ ምንጭ የነበርነውን ሰዎች ወደ ብርሀን ምንጭነት እንድንሸጋገር ምክንያት በሆነ የትውልድ ዘመን ላይ …
👍5
2 Aug 2025, 19:43 UTC≈1,690 views10 reactionsread 7 August 2026 ታላቁ የህዳሴ ግድብ የዚህ ዘመን ትውልዶች በደማቸው እና በላባቸው የፃፉት ደብዳቤ እንደሆነ ያስታወሱት አቶ ዛዲግ "የትልልቅ ፕሮጀክቶች እስትንፋስ ትርክት ነው:: ትርክት ፕሮጀክቶችን ያድናልም:: ይገድላልም:: የታላቁን ህዳሴ ክብር የሚመጥንና ትውልድን ተሻግሮ የሚነገር ቋሚ ትርክት መቅረጽ ፣ ማደራጀት እና ማስረፅ ቀጣዩ ቁልፍ ተግባር ነው:: ይህን ሳናደርግ ከቀረን ገንቢ ትርክታችን በጠላት መዳፍ ውስጥ ወድቆ አንድም ይሸረሸራል አሊያም ይጠለፋል" በማለት ቋሚ ትርክት መገንባት ላይ ሰፊ ሀሳብ አቅርበዋል::
የትርክት ሀውልት ሆነው በዓለም መድረክ ምስክርነት ከሚቆሙ ኢትዮጵያዊ ማህተሞች መካከል ታላቁ የህዳሴ ግድብ እንደሆነ ያነሱት አቶ ዛዲግ የትርክት መሰረቶ…
👍10
2 Aug 2025, 19:42 UTC≈1,610 views8 reactionsread 7 August 2026 Photo
“የራስህ ፣ የተቋምህ እና የሀገርህ የትርክት ባለቤት ካልሆንክ የሌሎች የትርክት ጭሰኛ ትሆናለህ” ዛዲግ አብርሃ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም (አፍሌክስ):- ግለሰቦች ፣ ተቋማት እና ሀገራት በአግባቡ ቀርፀው ከትውልድ ወደ ትውልድ ካላሸጋገሩ በተጠለፈ ትርክት ውስጥ እንደሚዳክሩ እና የትርክት ጭሰኛ እንደሚሆኑ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ተናገሩ::
"መርዛማ ትርክትን አፍርሶ ገንቢ ትርክትን መትከል ለሀገር ሉዓላዊነት የሚከፈል መስዋዕትነት ነው" የሚሉት አቶ ዛዲግ "የሀገርን ትርጉም የተረዳ ህዝብ የራሱን አሰባሳቢ ትርክት እየገነባ የጋራ ዕድል-ፈንታውን ይወስናል:: ታላቁ የህዳሴ ግድብ የራሱን ትርክት…
👍8
2 Aug 2025, 08:57 UTC≈1,490 views5 reactionsread 7 August 2026 አቶ ዛዲግ አብርሃ ለህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ምክር ቤት አመራርና ባለሙያዎች ስለ ግድብ ሀይል ስልጠና ሲሰጡ እንደጠቀሱት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የአፍሪካ ሀገራት ኩራት ብቻ ሳይሆን እንደ ትልቅ ሀብት የሚቆጠር በመሆኑ፤ አህጉሪቷ ካላት ተፈጥሮአዊ ጸጋዎች ውስጥ አውራ ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን አስታውሰው “ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለአፍሪካ የሚኖረው ትዕምርታዊ ሀይል በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም። ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካኒዝምን የዕድገት ሞዴል ተከትላ የማንንም ደጅ ሳትጠና በራሷ አቅም መገንባቷ ለቀጠናውና ለአፍሪካ የሚኖረው በጎ መልዕክት ከቃል በላይ ነው። አፍሪካውያን ሲተርኩት የሚኖሩት ከትውልድ ወደ ትውልድ በኩራት የሚያሻግሩት ብሔራዊ ሀብታቸው አድርገው እንደ አይናቸ…
👍5
2 Aug 2025, 08:57 UTC≈2,730 viewsread 7 August 2026 Photo
“የአፍሪካ ስትራቴጂያዊ ገንዘብ ውሀ ነው ከተባለ፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ደግሞ ውሀውን የሚያስተዳድር ብሔራዊ ባንክ ነው” ዛዲግ አብርሃ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም (አፍሌክስ)፡- የአፍሪካ ስትራቴጂያዊ ገንዘብ ውሀ እንደሆነና ታላቁ የህዳሴ ግድብ ደግሞ ውሀውን እንደሚያስተዳድር ብሔራዊ ባንክ ሊቆጠር የሚችልበት አቅም እና ችሎታ እንዳለው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ተናገሩ።
Showing the 12 most recent of 15 posts we hold for @afleexac. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.