8 Aug 2026, 07:03 UTC59 views5 reactionsread 8 August 2026 #የሰይዲና_ኸድር_ቅዳሜ
ወልቂጤ፣ ከአዲስ-አበባ 150 ኪ.ሜ ያህል ትርቃለች። ለተከታታይ ትውልድ ምንጭ ሆኖ ያገለገለውን፣ የቃጥባሬ ማዕከልን አቅፋ ይዛለች። ቃጥባሬ፣ የሼህ ዒሳ ሁላዊ ግምዳይ፣ የልህቀታቸው አደባባይ። እርሳቸው ታላቅ ተምሳሌት፣ ዕውቅ ሙቀረብ፣ ደሚቅ ሊቅ፣ የጀግንነት ምልክት፣ የአያሌ ተዓምራት ቁንጮ፣ የደግነት አምባ፣ የመልካምነት ጉልላት፣ ሊቀ-ሊቃውንት - የቃጥባሬ ታዛ፣ ደማሙ ሼህ ዒሳ ሀምዛ። የትውልዶች መሪ፣ የሊቃውንት አስተማሪ፣ የምዕመናን አስከባሪ፣ የማህበረሳባን አቅኝ፣ በተለይም በዘመናቸው በጉራጌ የገነኑ በርካታውን ጠርበው እያስተካከሉ፣ ከፈሰሱበት እያቃኑ የመሩ፣ ሰበ-አዊ ብርሀን ናቸው። የድንቅ ታሪክ ባለቤት፣ የሀገር አባት፣ የማ…
❤5
Signed አብዱ ኤምሬ
6 Aug 2026, 13:47 UTC112 views3 reactionsread 8 August 2026 #ለይለተል_ጁሙኣ
በሐዲስ እንደተገለጸው፦ "ፀሐይ ከወጣችባቸው ቀናት ሁሉ በላጯ ቀን የጁሙዓ ቀን ናት፤ አደም የተፈጠረው፣ ወደ ጀነት የገበውና ከጀነት የወጣው በዚህች ቀን ነው"። ሊቃውንት የእነዚህን ሁነቶች ምስጢር እንዲህ ይፈታሉ፦
የፍጥረት መፈጸሚያ (አክመሉል-ወጁድ)፦ አላህ ፍጥረታትን በሙሉ አዘጋጅቶ ካጠናቀቀ በኋላ፣ የፍጥረት ሁሉ ዘውድና መገለጫ የሆኑትን አባታችን አደምን በጁሙዓ ቀን ፈጠራቸው። ስለዚህ ጁሙዓ የሰው ልጅ ክብር የተገለጸበት ቀን ናት።
የ"ሩሕ" (የመንፈስ) መነፋት ምስጢር፦ አላህ ከአፈር ለበጀበጀው የአደም አካል መለኮታዊውን መንፈስ (ሩሕ) የነፋበት ቀን በመሆኑ፣ የጁሙዓ ምሽትና ቀን የሰው ልጅ የመንፈስ ሕይወት ያገኘበት ታላቅ ጊዜ…
❤3
1 Aug 2026, 09:10 UTC207 views5 reactionsread 8 August 2026 #የሰይዲና_ኸድር_ቅዳሜ
ታላቁ የሐዲስ ሊቅ ኢማም ኢብኑ ሐጀር አል-ዐስቀላኒ (የ"ፈትሑል ባሪ" ደራሲ) ገና በወጣትነታቸው በዒልም እና በመንፈሳዊ ናፍቆት ውስጥ እያሉ፣ ሰይድና ኸድርን ለማየት እና ከእሳቸው በረከት ለመቀበል ጥልቅ ፍላጎትና ናፍቆት ነበራቸው።
አንድ ቀን በካይሮ መስጂድ ውስጥ ሁልጊዜ የሚቀመጡበት ቦታ ላይ በናፍቆት ተከዝ ብለው ሳሉ፣ አንድ የማያውቁት በእድሜ የገፉ አዛውንት መጥተው ከጎናቸው ተቀመጡ።
አዛውንቱ የኢማም ኢብኑ ሐጀርን የልብ ናፍቆት በማወቅ፦ "እኔን ማየት ትናፍቅ አልነበረም?" ብለው ጠየቋቸው።
ኢማም ኢብኑ ሐጀርም ደንግጠው አዩአቸው። ሰይድና ኸድርም የመንፈሳዊ ዒልምና የበረከት ዱዓ ካደረጉላቸው በኋላ፣ "ፍላጎትህ እና ናፍቆ…
❤5
Signed አብዱ ኤምሬ
30 Jul 2026, 11:48 UTC233 views8 reactionsread 8 August 2026 #ለይለተል_ጁሙኣ
ኢማም ቡሰይሪ በሕይወት ዘመናቸው ሙሉ ልባቸው የሚመታው ለመዲናና ለነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ረውዳ ነበር።
«አሚን ተዘኩሪ ጂራኒን ቢዚ-ሰለሚ...»
"(በዚ-ሰለም/በመዲና ያሉትን ጎረቤቶች [ነቢዩን] በማስታወስ ነውን እምባህ ከደም ጋር ተቀላቅሎ የሚፈሰው?)"
የሚለው ስንኛቸው የተጻፈው መዲናንና ረሱልን (ሶ.ዐ.ወ) እጅግ ከመናፈቃቸው የተነሳ እንቅልፍ አጥተውና ከስተው በነበረበት ወቅት እንደነበር ይነገራል። በመጨረሻም አላህ መንገዱን አገራላቸውና ወደ መካ ለሐጅ፣ ከዚያም ወደ መዲና አል-ሙነወራ ለዚያራ ተጓዙ።
መዲና ከተማ አቅራቢያ ሲደርሱና የነቢዩን (ሶ.ዐ.ወ) መስጂድ ጉልላት (ቁበተል ኸድራእ) ከሩቅ ሲመለከቱ፣ ከፈረሳቸው ላይ ወርደው «የነቢ…
❤8
Signed አብዱ ኤምሬ
25 Jul 2026, 08:37 UTC306 views11 reactionsread 8 August 2026 #የሰይዲና_ኸድር_ቅዳሜ
አንድ ታላቅ ዓሊም በባህር ዳርቻ ላይ እየተንሸራሸረ ሳለ፣ በልቡ ውስጥ፦ "እኔ ያልተማርኩትና የማላውቀው የእስልምና ዕውቀት ይኖር ይሆን?" የሚል የኩራት ሀሳብ መጣበት።
በዚያ ቅጽበት፣ አሳ አጥማጅ መስለው በባህሩ ዳርቻ ላይ የተቀመጡት ሰይድና ኸድር ዓሊሙን ሰው ጠርተው፦ "ሸይኻችን ሆይ! እስኪ ወደዚህ ባህር ተመልከት፤ ምን ታያለህ?" አለው።
ዓሊሙም በታበየ ድምፅ፦ "እጅግ በጣም ሰፊና ጥልቅ የሆነ ባህር አያለሁ" ሲል መለሰ። በዚያው ቅጽበት፣ አንዲት ትንሽ ወፍ በርራ መጥታ በባህሩ ዳርቻ ላይ አረፈች። ወፏም አፉን ወደ ባህሩ ውኃ አቅርባ *አንድ ጠብታ ውኃ* በአፏ ቆንጥራ በመያዝ ወደ ሰማይ በረረች።
ሰይድና ኸድርም (ዐ.ሰ) ወ…
❤11
Signed አብዱ ኤምሬ
23 Jul 2026, 13:55 UTC307 views6 reactionsread 8 August 2026 #ለይለተል_ጁሙኣ
ሱልጣኑል አሪፊን አቡ ያዚድ አል-ቡስጣሚ፣ በጁሙኣ ለይል ዚክር ላይ እያሉ ያዩትን ሰፊ የከሽፍ ገለጣ በሰፊው ይተርካሉ።
"በዚህች ሌሊት ልቤ ከዱንያ ግድግዳ ተላቆ ወደ ሰማያውያኑ ዓለም ወጣ። በመጀመሪያው ሰማይ ውስጥ የሚዘክሩ የመላእክት ሀድራ ተገለጠልኝ። መላእክቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰፍ ሠርተው በታላቅ ድምፅ አላህን ያወድሱ ነበር። የዚያን ሀድራ ብርሃን ስመለከት ነፍሴ በመንፈሳዊ ፍቅር (እሽቅ) ተሞላች። መላእክቱ ወደ እኔ ዘወር ብለው 'ያ አቡ ያዚድ! ወደ እኛ ሀድራ ተቀላቀል' አሉኝ። እኔ ግን ወደ አላህ ፍጹም ቅርበት እንጂ ሌላ አልሻምና ወደ ላይኛው ሰማይ ቀጠልኩ። በእያንዳንዱ ሰማይ ውስጥ የተለያዩ የመላእክት ሀድራዎች ነበሩ—አንዳንዶ…
❤6
Signed አብዱ ኤምሬ
18 Jul 2026, 09:02 UTC373 views11 reactionsread 8 August 2026 #የሰይዲና_ኸድር_ቅዳሜ
ታላቁ የፋርስ ገጣሚ ሃፊዝ ሺራዚ ገና ወጣት ሳለ በሺራዝ ከተማ ውስጥ በአንድ ዳቦ ቤት ውስጥ ሊጥ አብኪ እና ጋጋሪ ሆኖ ይሰራ ነበር። ከእለታት በአንዱ ቀን በአቅራቢያው ለሚገኝ አንድ ባለጸጋ መኖሪያ ቤት ዳቦ ለማድረስ በሄደበት ወቅት፣ "ሻካ-ነባት" የምትባል እጅግ ውብ የሆነች የባለጸጋውን ልጅ በአጋጣሚ ያያታል። ሃፊዝ በመጀመሪያ እይታ በእሷ ፍቅር እብድ ሆነ። ነገር ግን እሷ የሀብታም ልጅ፣ እሱ ደግሞ ደሃ በመሆኑ እሷን ማግኘት ፍጹም የማይታሰብ ህልም ነበር።
በሺራዝ ከተማ ውስጥ አንድ የታወቀ እምነት ነበር፤ እሱም፡- "አንድ ሰው 'ባባ ኩሂ' በተባለው ተራራ ላይ ለ40 ተከታታይ ቀናትና ሌሊቶች ጸልዮ ካደረ፣ ሰይድና ኸድር ይገለጥ…
❤9🔥2
Signed አብዱ ኤምሬ
16 Jul 2026, 13:10 UTC344 views5 reactionsread 8 August 2026 #ለይለተል_ጁሙኣ
ከመውላና ጀላሉዲን ሩሚ ድንቅ ድንቅ የመስነቪ ታሪኮች መካከል፣
አንድ ጁሙኣ ለይል ነቢዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) በበረሃ ውስጥ ሲጓዙ፣ አንድ ምስኪን እረኛ ብቻውን ቆሞ ወደ አላህ ሲጸልይ ተመለከቱት። እረኛው ልቡ በፈጣሪ ፍቅር ተነክቶ፣ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ ይማጸን ነበር፦
"አምላኬ ሆይ! የት ነህ? ልምጣና ልብስህን ልስፋልህ? ፀጉርህን ላበጥርልህ? ጫማህን ልጠገንልህ?... ጌታዬ ሆይ! ብትታመም እያስታመምኩህ እግርህን ባሸሁልህ... ማታ ማታ የሚጠጣ ወተት አቅርቤልህ ብርድ እንዳይመታህ ብርድ ልብስ ባለበስኩህ... አንተ የኔ ማር፣ የኔ ውድ ጌታ!"
ነቢዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) የእረኛውን ንግግር ሲሰሙ በጣም ደነገጡ። ወደ እረኛው ጠጋ አሉና በቁጣ እ…
⚡4❤1
Signed አብዱ ኤምሬ
15 Jul 2026, 15:18 UTC317 views5 reactionsread 8 August 2026 #የአእዋፋት_ጉባኤ
ፈሪዱዲን አታር በ12ኛው ክፍለ ዘመን የኖረ ታላቅ የፋርስ (ኢራን) ሱፊ ገጣሚ እና ፈላስፋ ነው። የእሱ ድንቅ ስራ የሆነው "የአእዋፋት ጉባኤ" (መናጢቀ ጠያር) በዓለም ስነ-ጽሁፍ ውስጥ እጅግ በጣም ጥልቅ እና ውብ ከሆኑ መንፈሳዊ ምሳሌያዊ ታሪኮች ነው።
"አንድ ቀን በዓለም ላይ ያሉ ወፎች ሁሉ በአንድ ላይ ተሰበሰቡ። ንጉስ የሌለው ህዝብ ሰላምና ስርዓት አይኖረውም በሚል መሪ የሚሆን ንጉስ መፈለግ እንዳለባቸው ተስማሙ። በዚህ ጊዜ ሁድድ ወደ መድረክ ወጣች፤ በጥበቧ የምትታወቅ፣ የንጉስ ሱለይማን መልእክተኛ የነበረች እና የዓለማትን ምስጢር የተረዳች ወፍ ናት። እንዲህ አለች፦
"እኔ ንጉሳችሁን አውቀዋለሁ፤ ስሙም ሲሙርግ ይባላል። የሚኖረው…
🕊4❤1
Signed አብዱ ኤምሬ
11 Jul 2026, 05:56 UTC361 views9 reactionsread 8 August 2026 #የሰይዲና_ኸድር_ቅዳሜ
በአንድ ወቅት ታላቁ ዐሪፍ ቢሽር አል-ሀፊ በባግዳድ ጎዳናዎች ላይ ባዶ እግራቸውን እየተጓዙ ሳለ፣ አንድ የማያውቁትና ፊቱ በኑር (በብርሃን) የተሞላ እንግዳ ሽማግሌ መንገድ ላይ ያገኛሉ። ሽማግሌው ወደ ቢሽር በመምጣት ስማቸውን ጠርቶ ሰላምታ አቀረበ።
ሽማግሌው ሰው ለቢሽር እንዲህ አለ፦ "አንተ ቢሽር ሆይ! አንተ በምድር ላይ ብቻ ሳይሆን በሰማይ መላእክት ዘንድም የምትታወቅ የላቅክ የአላህ ወዳጅ ነህ" አላቸው።
ቢሽርም በንግግሩ ተገርሞ "የአላህ ወዳጅ ሆይ! እባክህ ማንነትህን ንገረኝ?" ሲል ጠየቀ። ሽማግሌውም ፈገግ ብሎ፦ "እኔ ወንድምህ ኸድር ነኝ" አሉ።
ቢሽር ሰይዲና ኸድር መሆናቸውን ሲያውቅ እጅግ ደነገጠ፤ በ…
❤9
Signed አብዱ ኤምሬ
9 Jul 2026, 14:12 UTC379 views7 reactionsread 8 August 2026 #ለይለተል_ጁሙኣ
ታላቁ ሰይድ ዩኑስ ኤምሬ ሸይኻቸውን ታፕዱክ ለ40 አመት ካገለገሉ በኋላ፣ "እኔ ምንም ለውጥ አላመጣሁም፣ መንፈሳዊ ብስለት ላይ አልደረስኩም" በሚል የከንቱነት ስሜት ተጭኖቸው ሀድራውን ጥለው ወጥተው ሲጓዙ መንገድ ላይ ከሰባት የላቁ አውሊያኦች (ደጎች) ጋር ይገናኛሉ። ምሽቱ የጁሙዓ ለይል ነበር፤ እያንዳንዱ ወሊይ በየተራ ዱዓ ሲያደርግ፣ ከተሰወረው ዓለም (ገይብ) እጅግ ጣፋጭ ምግብ ይወርድላቸዋል። ተራው ወደ ዩኑስ ሲደርስ ጨነቃቸው። እጃቸውን ወደ ሰማይ ዘርግተው እንዲህ አሉ፡ "ጌታዬ ሆይ! እኔ ማነኝና ነው የምለምንህ? ነገር ግን እነዚህ ደጋግ ባሮችህ በተማፅኑህና ይህንን ጸጋ በሰጠሃቸው ሰው ስም፣ እኔንም በዚያው ታላቅ ስም ማረኝ፣ አታሳ…
👏4⚡1❤1🤯1
Signed አብዱ ኤምሬ
6 Jul 2026, 20:59 UTC428 views5 reactionsread 8 August 2026 #የግፈኞች_ዘመን
በቴህራን በተካሄደው የአያቶላ አሊ ኻሜኒ (ረ) የስንብት ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢራን መንግሥት የአገራት የዲፕሎማቲክ ልዑካን ቡድኖች ወደ አስከሬኑ ሲጠጉ የተነበበው ቁርኣን አንቀጽ (አያህ)
ቻይና፦ አል-ዒምራን (3:126) — “አላህም (ይህንን እርዳታ) ለእናንተ ብስራት እንድትሆንና ልቦቻችሁም በእርሱ እንዲረኩ እንጂ ለሌላ አላደረገውም። ድልም ከአሸናፊው ጥበበኛው አላህ ዘንድ እንጂ ከሌላ አይደለም።”
ሩሲያ፦ አል-ቀሰስ (28:83) — “ይህች የመጨረሻይቱ ዓለም (ገነት) በምድር ላይ ትዕቢትንና ጥፋትን ለማይፈልጉ ሰዎች እናደርጋታለን፤ መልካም ፍጻሜም ለጠባቂዎቹ (ለጻድቃኑ) ነው።”
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE)፦ አል-ማኢዳህ (5:…
❤5
Signed አብዱ ኤምሬ
Showing the 12 most recent of 21 posts we hold for @abduftsemier. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.