ፍልሰታ ... የሁላችን ደስታ። እንኳን ለበረከት እና የጸጋ ግምጃ ቤት ለሆነች ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ ፥ አደረሠን። የእናታችን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅሯ ይደርብን። በልጅነት ጸጋ ለመኖር የምንተጋበት ፣ የምንበቃበት ፤ ኃጢአታችን የሚደመሰስበት ፤ ከቅዱሳን ኅብረት የምናገኝበት ፤ የተወደደ ጾም ያድርግልን። የእመቤታችንን ትንሣኤዋን ፣ ፍልሠቷን ፣ ዕርገቷን ፣ ማሰባችን ፤ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ የሚያፈልሰን ፣ ትንሣኤ ልቡናን ዕርገተ ኅሊናን የሚያድለን እንዲሆልን አምላካችን ይፍቀድልን። አሜን።

Channel
መንፈሳዊ ግጥሞች
@Spritualpoem
On this record: Topic · Growth · Engagement · Posts · Citations · Cite this entry
2,610subscribers
-162 since we began measuring on 7 August 2026
Risers and fallers across the register · movement among entries of 1,000–3,162.
Register entry
| Telegram ID | -1001186123250 |
|---|---|
| Type | Channel |
| Username | @Spritualpoem |
| Created | Between 1 March 2018 and 31 July 2021 — estimated from Telegram’s id allocation, not measured. How this range is calculated. |
| First recorded | 7 August 2026 |
| Last confirmed live | 13 October 2026 |
| Measurements held | 16 |
| Confirmed unchanged | 1 time, most recently 13 October 2026 |
| On Telegram | t.me/Spritualpoem |
Topic
Religion — a classification, not a measurement. An on-box language model (Qwen3.6-35B-A3B-FP8, prompt version 1) read this channel’s own recent posts on 15 September 2026 and assigned it the closest of 31 fixed categories, at 100% confidence. This is a model’s judgement about what the channel is likely to be about, not a fact this register measured the way a subscriber count or a view count is measured — it can be revised on a later pass, and it carries no weight anywhere else on this page. How this classification works, and why it has no browse page of its own yet.
Growth
| Measured (UTC) | Subscribers | Change |
|---|---|---|
| 13 Oct 2026, 15:05 | 2,610 | -14 |
| 7 Oct 2026, 17:16 | 2,624 | -26 |
| 1 Oct 2026, 00:18 | 2,650 | -30 |
| 16 Sept 2026, 03:01 | 2,680 | -3 |
| 12 Sept 2026, 04:39 | 2,683 | -10 |
| 7 Sept 2026, 18:20 | 2,693 | -11 |
| 2 Sept 2026, 20:15 | 2,704 | -11 |
| 30 Aug 2026, 10:24 | 2,715 | -10 |
| 24 Aug 2026, 07:25 | 2,725 | -7 |
| 20 Aug 2026, 10:05 | 2,732 | -2 |
| 17 Aug 2026, 17:48 | 2,734 | -14 |
| 14 Aug 2026, 04:57 | 2,748 | -11 |
| 11 Aug 2026, 03:04 | 2,759 | -11 |
| 7 Aug 2026, 23:07 | 2,770 | -2 |
| 7 Aug 2026, 05:30 | 2,772 | no change |
| 7 Aug 2026, 05:27 | 2,772 | first reading |
Engagement
17 posts held, back to 20 May 2022 — the reader has not yet reached the start of this channel’s public history, so older posts may sit further back, unread. Read across 2 pages of Telegram’s post history, 20 posts per page.
Nothing published in the last 30 days. ERR and ER are rolling 30-day measures, so there is nothing to compute — we hold 17 posts for this entry, the most recent from 6 August 2026. An engagement rate over an empty window would be a number about nothing.
Recent posts
♦አዚም ሕይዎት ♦ የነፍስን ጥማት የልብን መሻት ዘንግቶና ረስቶ ከጸጋ ልብስ ተራቁቶ ከድኅነት መንገድ ሸሽቶ ከጽድቅ ጉዞ ዘግይቶ ... ስለ ኃላፊና ከንቱው ነቅቶ/ተግቶ በዓለም ምኞት ተወስዶ/ተገርኝቶ ስለ ዓለም ፥ ሁሉን ትቶ ከሕይዎት ራስ ፥ ተለይቶ የስጋን እንቅብ ፥ በራስ ላይ ደፍቶ... ከክብር ማማ ወርዶ የህሊናን ክስ አፍኖ/ክዶ ከጉስቁልና ተዋድዶ/ተላምዶ... ላመኑበት ሳይታመኑ የጽድቅን ልብስ ሳይሸምኑ ከመታዘዝ ፍሬ ሳይዘግኑ ... መውጣት መግባት መምሸት መንጋት የዘመን መሸኘት የዘመን መተካት አዚም ኑሮ ፥ ከንቱ ሕይዎት በሰም ኖሮ ፥ በወርቅ መሞት 07/08/2013 ዓ.ም ©ዮሴፍ ጌትነት
<<ቅኔ በለስ>> የጽድቅ ሕይዎት መሠረት የአክሊልና የበረከት እናት በለስ ፥ የክብር መክሊት ናት። ለመግባት የሚሻ ፥ ወደ ጌታ ደስታ በጥቂት በለስ ፊት ፥ ይታመን ለጌታ። የቅድስና ሕይዎት ቁልፍ ያለው ፥ መዳን የሚገኘው የበለስን ምስጢር በመረዳት ፥ ርሷን በመውደድ ነው። ©ዮሴፍ ጌትነት 07/08/2014 ዓ.ም
♦ተቃርኖ !♦ ማወቅ እንፈልጋለን ፤ ነገር ግን ለማወቅ የሚያስፈልገንን ሥራ ለመሥራት ታካቾች እንሆናለን፡፡ ብዙ ለማወቅ እንተጋለን ፤ ባወቅነው ግን ራሳችንም ሆነ ሌሎችን ለመጥቀም እንሰንፋለን፡፡ እውቀት ከተግባር ጋር አልተባበረልንም፡፡ ስለዚህም ከመረጃ ኮሮጆነት የዘለለ ድርሻ ሲኖረን አይታይም፡፡ ስለ ብዙ ነገሮች መጽሐፋዊ ትንታኔ/ማስረጃ አለን ፤ የተኖረ - የሕይዎት ማስረጃ ግን ይጎድለናል፡፡ <<የምናምነውን>> ለማወቅ - የምንተጋውን ያክል ፤<<ስለምናምነው>> ያወቅነውን ለመኖር አንተጋም፡፡ በማወቃችን ብቻ የረካን ይመስላል፡፡ ብዙ የዕድሜ ዘመናችን - ከተግባር በተራቆተ ፤ ለማወቅ የሚደረግ ሂደት የተዘለለ/የሚገደፍ/የሚታለፍ ጊዜ ሲሆን ይስተዋላል…
♦"በእኔ የምትኖር"♦ 🌿ማቴ 6 ፥ 9🌿 አባታችን ሆይ የምትኖር በሰማይ ብዬ እንድፀልይ ለኔ ስታስተምር ለኔ ስትናገር ... ደግሞም ፥ ስጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ ፥ በእኔ ይኖራል ብለህ መናገርህ በቅዱስ መጽሐፍ ፥ በዮሐንስ ወንጌል (ዮሐ 6) ቀጠል አድርገህም ... የምትወደኝ ብትሆን ፥ ትዕዛዜን ብትጠብቅ ፥ በቃሌ ብትኖር ከአባቴ ጋር ወደ አንተ እንመጣለን ፥ በአንተ ውስጥ ለመኖር (ዮሐ 14) ብለህ መናገርህ ምን ይሆን ምስጢሩ ? በእኔ እንደምታደር ባንተ መነገሩ ስል እጠይቃለሁ ፥... በሰማይ የምትኖር ፥ ተብለህ መመስገንን የዘወትር ጸሎት ፥ አድርገህ ስትሰጠን እውን በሁሉ የመላህ አንተ ፥ በምድር አትኖርም ? ዓለማተ ዓለም ሥላሴ ፥ በዓለም የለህ…
<<ሰውነቱ ከሰውነታችን ጋር ተዋሐደ። ደሙም ወደ ደም ሥሮቻችን ውስጥ ገባ። ድምፁ ወደ ጆሮዎቻችን ገባ። ብርሃኑም ወደ ዐይኖቻችን! ከፍፁም ፍቅሩ የተነሣ ሁለንተናው ከሁለንተናችን ተዋሐደ። ቤተክርስቲያኑን እጅግ ስለሚያፈቅራትም የብሉይ ኪዳንን መና አልሰጣትም። ትበላው ዘንድ ሕይዎትን የሚያድል ሕብስት እንጅ ። ኅብስት ዘይትና ወይን - እነዚህ ሦስቱ በተምሳሌት አንተን ያገለግላሉ። በሦስት መድኃኒቶች ደዌያችንን ፈወስህ። የሰው ልጅ ደካማና ኀዘንተኛ የጎሰቆለ ኾነ። አንተን ግን በክቡር ሥጋህ ኃይልህን ሰጣሃት ፤ በቅዱስ ደምህ አጽናናሃት ፤ በቅዱስ ዘይትህም ደስ አሰኛሃት>> [ቅ/ኤፍሬም]
♦ሰናክሬማዊነት ይቀሰፍ♦ {2 ዜና መዋዕል 32 ፥ 1-22} በእግዚአብሔር ከተማ በእስራኤል ዘነፍስ ማማ በዳግሚት ኢየሩሳሌም የአህዛብ ንጉሥ ፥ ዕቡይ ሰናክሬም ህዝብን ሲሰቀይ በግፍ ሲያምስ የንጹሐንን ደም በከንቱ ሲያፈስስ <<እግዚአብሔር ያድናችኋል እያሉ ፥ ኦርቶዶክሳዊያን አያስቷችሁ ፤ ይሄው ማንም የለም ፥ ከእጄ የሚያድናችሁ።>> እያለ ሲዝት ሲፎክር በትዕቢት ሲታጀር የሰራዊት ጌታን ሲገዳደር በእግዚአብሔር ህዝብ ላይ ፥ መስቃን ሲናገር አቤቱ አሁን አድን ፥ አቤቱ አሁን ተነሥ ሰናክሬምን ደምስስ ፥ የግፉዐንን እንባ አብስ መልአክህን ከሰማይ ስደድ ለቅኖች በእውነት ፍረድ በሰናክሬም ላይ ቁጣህ ትንደድ <<ሰናክሬማዊነትን>> ቅሰፍ ሞት ከእስራኤላ…
♦መካኒቱ ሣራ♦ 🌿ኦሪት ዘፍ 17፥17🌿 መካኒቱ ሣራ ፥ የሁላችን እናት ... ሙቀት ልምላሜ ፥ ከሷ ተለይቷት የመውለድ ተስፋዋ ፥ ተማጥጦ ማኅፀንዋ ደርቆ ፥ የወር አበባዋ ተቋርጦ ስላቅና ስድብ ፥ የበዛበት ሕይዎት እንዲያ ስትገፋ ፥ ሳራ የእኛ እናት... ሥላሴ ወደ ቤቷ ሲገቡ ፥ ወደርሷ ሲመጡላት ታሪክ ተቀየረ ፥ በረከት በዛላት መካን ይቡስ ማኅፀን ፥ በልምላሜ ተጎበኘ የጽድቅ ፍሬ ፥ ይስሐቅ ከሳራ ተገኘ መካኒቷ ሳራ ፥ በሐሴት ተሞላች ፥ በደስታ ዘመረች እንባዋ ታብሶ ፥ ስድብና ስላቅን ፥ ከእርሷ አራቀች። እኔም ምስኪን ልጅህ ምንም ባሳዝንህ ምንም ብበድልህ.. ልምላሜ ሃይማኖት ፥ ከእኔ ዘንድ ባይገኝ መንፈሳዊ ሙቀት ፥ ምንም እንኳን ቢለየኝ አንተን…
♦ጥቂት ሻማ !♦ ጉዞአችን መደነቃቀፍ የበዛበት የድንግዝግዝ ጉዞ ነው። ሁላችንም ተናገሩ ብንባል በምሬት የምንናገርላቸው ብዙ ጉዳዮች በዙርያችን አሉ። ብዙ ሌብነት ፣ ብዙ ግፍ ፣ ብዙ በደል ፣ ብዙ ነውር አለ። ብዙ ስንፍና አልጠግብ ባይነት ፣ ስግብግብነት ፥ እኔ ብቻ የሚል የኑሮ ፍልስፍና ስር ሰድዶ ይታያል። በሌሎች መስዋዕትነት የቅምጥል ሕይዎትን መምራት እንደ ብልጠት ከተቆጠረ ቆይቷል። የሌሎችን ችግርና ስቃይ ፥ የራስን ጥቅም የሚያሳድዱበት መልካም አጋጣሚ አድርጎ መቁጠርም የዘመናችን የሚያስተዛዝብ መቅሰፍት ነው። መብትን መግዛት የተለመደ ነገር ሆኗል። ሰው በሰውነቱ ሊያገኘው የሚገባውን ድጋፍ ፥ በቁስ በኩል እንዲያገኝ በእጅህ ካልሄድክ አይሆንም…
ጊዜ የወራጅ ወንዝ ውሃን ይመስላል። ማንም ያለፈውን ዕድሜውን መልሶ ሊነካ/ሊዳስስ/ሊኖር የሚችል የለም። ስንንኖር ወደ አለመኖር እየቀረብን ነው። (በምድር/በሥጋ) ልደታችን ስናከብር ፥ አዲስ የዕድሜ ቁጥር በዕድሜያችን ላይ ስንደምር ፥ ከምኖረው አጠቃላይ ዕድሜያችን ላይ የቀነስነውን ዕድሜ ማስላታችን ነው። እያረጀን እንጅ ሕፃን እየሆንን አንሄድም። እንዲያ ከሆነ ላይመለስ በተሸኘ የምድር ላይ ቆይታችን ፥ ምን አወንታዊ ተጽዕኖ ፈጥረንበት ፤ ለእኛ እና ለሌሎች የሚጠቅም ምን አይነት ፍሬ አፈራንበት? ማንንም በማያንጽ/ለማንም በማይጠቅም አጀንዳ የገበርነው/የሰዋነው ጊዜ ፤ የሕይዎታችን ስንት ስንተኛ ይዞ/ወስዶ ይሆን?! ያለ ዓላማ የኖርንባቸው ጊዜዎች ፥ …
ገበሬ አንተ ፥ ልትዘራ ስትወጣ ወደ መሬት ልጅህ ፥ ወደ እኔ ስትመጣ ይህንን እይልኝ ይህንን ተረዳልኝ ሁሉም እንደሚያውቀው ፥ እኔ የምገኘው ... በሁሉ ማለፊያ ፥ በዓብይ መንገድ ዳር ነው በዚያውም ላይ ሌላ ምልክት በጭንጫ ፥ የእኔ መሬትነት እሾህ አሜካላ ፥ በብዙው በቅሎበት በምድር መካከል ፥ ታገኘዋለህኝ ፥ የእኔን መሬትነት። ጌታዬ ...! እሾህ አሜካላ ፥ በእኔ ላይ እያለ ፥ በእኔ እየኖረ መሬት ልቦናዬ ፥ በረድኤትህ ቅፅር ደግሞም ካልታጠረ ጭንጫ ልቦናዬ ፥ ካልተስተካከለ መልካም መሬትነት ፥ በእኔ ዘንድ ከሌለ ፍሬን እንደማልሰጥ ፥ ልቤ ስለሚያውቀው ይህንን እላለሁ ... እጠይቅሃለሁ ፥ እለምንሃለሁ ፍሬ ማፍራትን የምትሻ ፥ ይችን ጉስቁል መሬት ከመ…
♦ዘሪ ሊዘራ ወጣ♦ ማቴዎስ 13፥3 ይቀጥላል ...
Showing the 12 most recent of 17 posts we hold for @Spritualpoem. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.
Mentions
Names
Channels on the register whose handles appear in this channel's posts.
A mention is a weaker signal than a forward and is counted separately for that reason — naming a channel is not republishing it, and a handle in a post body is easy to place deliberately. The post counts beside each row below are distinct posts in which the handle appeared, from posts we have read on both sides — the “Named by N registered channels” figure above is a different count, of distinct NAMING CHANNELS rather than posts, and is not the sum of the rows under it.
Cite this entry
A live page changes as we take new readings, so a citation should name the measurement it is based on, not just the URL. The line below cites the subscriber count as measured 13 October 2026 — this entry's latest reading, not the date you are reading this.
“መንፈሳዊ ግጥሞች” (@Spritualpoem), 2,610 subscribers as measured 13 October 2026. Telegram Register, tgregister.com/channel/Spritualpoem.
Full measurement history, CC BY 4.0. Every reading this register holds for this entry, not just the latest one, as a dated, downloadable record: CSV · JSON. Free to use with attribution to tgregister.com. Each file carries its own generation timestamp, which is the figure to cite for exactly when the data was retrieved.