24 Mar 2026, 07:20 UTC490 views2 reactionsread 16 August 2026 Forwarded from @menfesawi_gtmoch
በራስ ውበት ሰጥሞ
ውሳጤዋን ሳታውቅ፣
ዝምታዋን አይተህ፣የፊትዋን ዓይነ ርግብ፣
የቀሚሷን ጥለት የሻሽዋን ክንብንብ፣
ይቺስ መልአክ ናት፣
አምሳያ የሌላት፣
እያልክ በአግራሞት ውበትዋን አታድንቅ!
ሰይጣንም ከሰማይ ሳይወድቅ እንደ መብረቅ፣
ከሉዓሌ ሰማይ ሰውን ለመፈጥፈጥ!
መርዙና ክፋቱ ቢኖርም ልቡ ውስጥ፣
መልአክ ነበረ መልኩ የሚያስደንቅ!
ደርሰህም ተቻኩለህ፣
በፍቅሯ ታውረህ፣
መልአክ መልአክ አትበል፣
በመልክ አትታለል!
ለመልክ መልአክማ ...
ሰይጣንም ይመጣል መልአክን መስሎ!
ጣፋጩን መራራ፣ ለዓይን አስመስሎ!
ስለዚህ ወዳጄ ...
ዓይነ ርግብዋን ሳይሆን ስራውን ተመልከት፣
በዝምታዋ ውስጥ፣
ልብህ አይመሰጥ!
ወደድኩሽ የሚላት እንዲህ እየበዛ፣
ሳታበዛ ስ…
❤2
8 Mar 2026, 11:20 UTC552 views2 reactionsread 16 August 2026 Forwarded from @menfesawi_gtmoch
ኑ በጋራ የተዘጉ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን እናስከፍት 🙏🙏🙏
መጋቢት መድኃኔዓለም ገጃ ሚካኤል ኦርሚያ ክልል ያለ የገጠር ቤተ ክርስቲያንን አስከፍቶ፣ ማኅሌት ቁሞ፣ ቀድሶና ታቦት አስወጥቶ ለመመለስ በካህናትና በዲያቆናት የሚደረግ የአዳር መንፈሳዊ ጉዞ !
🌷 ጉዞውን ለማድረግ የሚያስፈልጉ ወጪዎች :-
✔️ ኹለት መኪና --- 70,000
(አንድ መኪና-35,000)
✔️ለካህናት አስቤዛ---90,000
(ለአንዱ ካህን---7,000)
✔️ በገጠሪቷ ቤ/ክ ያሉ አገልጋዮች :-
ቀሳውስት---5
ዲያቆናት---4
መሪጌታ---1
ዘበኞች---2
ዐቃቢት---1
✔️አጠቃላይ---13 አገልጋይ
✔️ 13 × 7 = 90,000 ብር
✔️ዝክር--- 70,0…
❤2
5 Mar 2026, 06:34 UTC478 views3 reactionsread 16 August 2026 Forwarded from @menfesawi_gtmoch
ክብሬን እጥላለው!
አንተን ተከትዬ፣
ዓለምን ከስሬ፣
ከመጠላት በቀር፣
በሰፈር በአድባር፣
ምን አተረፍኩ እኔ?
ከዓለም ደስታ ይልቅ ለአንተ መወገኔ፣
ይቆጨኝ ጀምሯል!
ዓለም ውሸት እንጂ፣
እውነት መቼ ያውቃል?
ግን ...
ቃልህን በኖርኩኝ፣
ዓለም ለምን ጠላኝ፣
ከደስታ ሐዘኑ ለምን አገለለኝ?
ብዬ ልከስህ ስል ...
ለካስ አስቀድሞ አንተኑ ጠልቶሀል፣
ከወንበዴዎች ጋር እርቃንህን ሰቅሎሀል!
ነጠላ አገልድሜ፣
ቤትህ ብመላለስ፣
በነጠላው ምሥጢር ምጽአትህን ባስታውስ፣
ወንጌልህን በሰበኩ በቀሚስ በልብሴ፣
እንዴታ አወጡልኝ ቅጽል ስም ለራሴ?
ብዬ ላማርህ ስል ...
ለካስ ተብለሀል ...
የቀራጮች ወዳጅ፣
ሰንበት አሪት ሻሪ፣
የአጋንንት አለቃ ጋኔናም ነው ይሄ፣
አድነ…
❤3
3 Mar 2026, 19:33 UTC519 viewsread 16 August 2026 ው ረ ድ እ ን ደ ገ ና!
ለሰማይ ቅርብ መሳይ፣
ምእመን አታላይ፣
ረበናት አሉ፣
ጌታን በአደባባይ፣
በሐሰት የሚሰቅሉ!
የቅዱሳን ወዳጅ፣
የሰይጣን አሳዳጅ፣
የምሥጢር የቅኔው የጥበብ ፈር ቀዳጅ፣
ምእመኑን አራጅ፣
ሊቃውንቱ አሉ!
ጌታን የዘነጉ!
እነርሱ ሳይገቡ ሌላው እንዳይገባ በርን የሚዘጉ!
ወደ ላይም ስናይ፣
ከማዕረጉ ጣርያ፣
በጉን ከፊት አርገው ከኋላ እየነዱ፣
በጎቹን ለተኩላ እሳት ሚማግዱ፣
የበጎቹን ሥጋ በጠጅ የሚያወርዱ፣
መነኰሳት አሉ!
የዓለም ከበርቴ!
የተማሩ ዱላ ቦክስና ካራቴ!
ካህናተ አይሁድ በሐዋርያት ቢተኩ፣
መጽሐፈ ብሉዩን ሕጉን ባልነካኩ፣
ብሉዩ ከወንጌል በዓለም ተኖረ፣
ሰይጣን ድንቅውና በእውነት አፈረ!
ግን ምን ያደርጋል?
ጌታ ካህ…
17 Feb 2026, 03:29 UTC694 views3 reactionsread 16 August 2026 ሁልጊዜ ተመካ!
ወንድም አለኝ እኔ፣
የምለው ደጀኔ፣
የሚቆም ከጎኔ፣
ባርያ አለኝ እኔ፣
ቀኝ እጄ የምለው፣
በጣም የምወደው፣
ነፍሴን የምሰጠው!
ወዳጅ አለኝ እኔ፣
አብሮኝ የሚበላ፣
ማይመኝ ንብረቴን የሔዋኔን ገላ!
እያልክ አትጽናና!
አትሁን ተላላ!
ወንድም አለኝ እኔ ብለህ አትመካ፣
ማያክህን ገላ ደርሰህ አትነካካ!
ጌታችን ተራቁቶ፣
እንደ ጨርቅ ተሰጥቶ፣
ሲሰደብ ሲገረፍ ሲሰቀል እልመክኑ፣
ወንድሜ ሚላቸው ሐዋርያት ላዕካኑ፣
መች ኾኑ ከጎኑ!?
እንደ በግ ሲሸለት፣
አማናዊው መስዋዕት፣
ለድኅነተ ዓለም ስለ ሰው በሙሉ፣
ሲበለት አካሉ፣
የልቡን ትካዜ፣
የሥጋውን ሥቃይ፣
ቢፈስ ማያልቀውን እንደ ፈሳሽ ቀላይ፣
ወንድሜ ሚላቸው ሐዋርያቱ ሁሉ፣
መቼ ተካፈሉ?
ነፍ…
❤3
Signed የማርያም ልጅ
30 Jan 2026, 10:39 UTC752 views8 reactionsread 16 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤8
Signed የማርያም ልጅ
27 Jan 2026, 13:43 UTC780 views5 reactionsread 16 August 2026 Photo
ለሚያምን ሁሉ ይቻላል
ጣፋጩን ቡርቱካን ብለውት መራራ፣
ሔደው ይዘፍቁታል በማያልቅ መከራ፣
ከእንባ አርቀውት በኃላፊው ደስታ፣
ቅዱሱ ሥጋውን አርገው ጋለሞታ፣
ሰላም ይነሱታል ጠዋትና ማታ!
ከትምህርቱ ኋላ ትዳር ነው ችግርህ፣
ከትዳሩ ኋላ ሚስትህ ናት ችግርህ፣
ገዳምኮ ብትሔድ ይመጣል ሰላምህ፣
እያሉ ዘብዝበው፣
ዛሬን አስጠልተው፣
ነገውን አስናፍቀው፣
ከፍቅር አርቀውት ከእምነት ትላንትና፣
ከአፉ ይቀሙታል ተመስገን ምስጋና!
እርሱም ... ትዳር ትዳር ብሎ፣
ለመውለድ ተቻኩሎ፣
ይያዛል በጭንቀት ትካዝ ተጠቅልሎ!
የአምላክ ያለ ብሎ!
ካልኾነም ... ትዳርን አቃሎ፣
በአስኬማ ደንግሎ፣
ይገኛል በዝሙት አልጋ ላይ ተንጋሎ!
በሰይጣን ተጋልቦ!
ዓለምን ተጠምቶ!
ዓለምን …
❤4👏1
Signed የማርያም ልጅ
19 Jan 2026, 16:02 UTC789 views1 reactionsread 16 August 2026 Voice message
ዓለም ለነጻነት!
❤1
Signed የማርያም ልጅ
19 Jan 2026, 15:49 UTC595 viewsread 16 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed የማርያም ልጅ
19 Jan 2026, 15:49 UTC813 views7 reactionsread 16 August 2026 ዓለም ለነጻነት!
መሳቅ አልምደኸኝ ጠዋትና ማታ፣
በኮሜዲ ዳንስህ ልቤ በሳቅ ጠፍታ፣
ከዓለም ተዋድጄ፣
ዓለምን ለምጄ፣
እንባና ጸሎትን አራኩኝ ከደጄ።
እስኪ ልጠይቅህ፣ ነጻነት ወርቅ ነህ፣
እያሳቁ መግደል ማን ነው ያስተማረህ?
ስትኖር አስቀኸኝ፤
ከዓለም አላምደኸኝ፣
በድንገት ስትሞት ለዓለም ገደልከኝ!
በሊቃውንት ስብከት በስግደት ጥብጣቤ፣
ቢሠራ ቢዘከር የማይሰማው ልቤ፣
በጥምቀቱ ጸበል ማይወጣው ሰይጣኔ፣
በዋዛ ፈዛዛ ያለፈ ዘመኔ፣
ምንጣፍ ተሸክሜ፣
እስኪነጥብ ደሜ፣
የምገኝ ከአረቄ፣
ከጌታ እርቄ፣
በሳቅህ ደምቄ፣
እንደ ልጅ ቦርቄ ...
ዛሬ ግን ... ልቤ ብቻ ሳይኾን እራሴው ተሰበርኩ፣
በመሞት ስብከትህ በእንባ ተንበረከኩ፣
ከአእላፋት ዝማሬ ልቡናን አሳዛኝ፣…
😢4❤3
Signed የማርያም ልጅ
5 Jan 2026, 11:30 UTC817 views1 reactionsread 16 August 2026 Voice message
ይሰቀላል አብሮ!
❤🔥1
Signed የማርያም ልጅ
5 Jan 2026, 11:29 UTC634 views1 reactionsread 16 August 2026 Forwarded from @menfesawi_gtmoch
ይሰቀላል አብሮ!
ጸጉርን አጎፍሮ፣
በሱፍ ተንቀባሮ፣
ቮልስን እየነዱ፣
በሬጌ እያበዱ፣
በስሙኒ ሳንቲም ሰንጋ እያረዱ፣
መብላት መጠጣቱ፣ መሳቅ መዝናናቱ፣
ሙዚቃው ፋሽኑ፣
አለፈ ዘመኑ!
ተሻሩ ከመንግሥት ሹምዬው መስፍኑ!
በጃን ሆይ መሸኘት እጅግ እያዘኑ!
ፋሽኑም ሬጌ፣
ተውጦ በመንጌ፣
ለሌላው ተራኛ ለቆ እስኪወጣ!
ኒሻኑን መደርደር፣
መኾን ሀምሳ አለቃ የሀገር ወታደር፣
ፋሽን ኾኖ መጣ፣
ሕዝቤ ከሃይማኖት እግዜር ነጻ ወጣ!
ዘመኑም ዘምኖ፣
በረቂቅ መግነጢስ ዓለም አንድን ኹኖ፣
የምዕራቡ ፋሽን አፍሪካዊ ኾነ፣
ያለ ጅራፍ ዱላ በብር ተለወጠ፣
በባርነት ቀምበር በባህር ተዋጠ፣
ቀስ በቀስ መሰይጠን በሀገር ሰፈነ!
በታቦታቱ ፊት አዝማሪ ከበረ፣
በዘፈን ዝሙቷ ዓለሙ ሰ…
🔥1
Signed የማርያም ልጅ
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Spritual_Fathers_Advices. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.