7 Aug 2026, 09:59 UTC118 views3 reactionsread 7 August 2026 Photo
በጣት እየጠቆሙ ስለ ነገሮች ሕጻናትን ማዋራት
ከ9 ወር አካባቢ ዕድሜያቸው አንሥቶ ሕጻናት በጣታችን የምንጠቁማቸውን ነገር በዓይናቸው ተከትለው ማየት ይችላሉ። አንድን ነገር ጠቁመን እያሳየን ስለዚያ ነገር ስናወራቸው፣ ልጆች ቋንቋ በበለጠ ፍጥነት ሊማሩ እንደሚችሉ ጥናቶች ይጠቁማሉ። ለምሳሌ የመጫወቻ መኪና በጣታችን እየጠቆምን “መኪና” ስንላቸው፣ ያ ነገር ምን እንደሚባል ያውቃሉ፤ ቃሉን ለመድገምም ይበረታታሉ። ሽርሽር ይዘናቸው ወጣ ያልን እንደሆነም እንዲሁ ልዩ ልዩ ነገሮችን
እየጠቆሙ ምን እንደሚባሉ መንገር፣ ስላሳየናቸው ነገሮች ማብራራት ይበጃል።
ገና ዳዴ ማለት ከጀመሩበት ጊዜ አንሥቶ እንዲህ ባለ መልኩ ማጫወት የቋንቋ ክህሎታቸውን ለማዳበር ይመከራል።
…
❤3
6 Aug 2026, 09:59 UTC188 views4 reactionsread 7 August 2026 Photo
በእርግዝና ጊዜ ሆድ ያሳክካል?
በእርግዝና ጊዜ አንዳንዴ የሆድ ማሳከክ “አሁንስ ሊያሳብደኝ ነው” የሚያሰኝ ደረጃ ሊደርስ ይችላል። በተለይ ሆድሽ እየገፋ ሲመጣ ማሳከኩ እየባሰ ይሄዳል።
የዚህ ምክንያቱ ቆዳሽ እየተለጠጠ፣ ተያይዞም እየደረቀ መሄዱ ነው። ማሳከኩ ቢኖርም በተቻለ መጠን ላለማከክ መሞከሩ ይመከራል። ለምን ቢባል ባከክሽው ቁጥር ማሳከኩ ይብስ እንደሆነ እንጂ አይሻልም። ማሳከኩን ለማሻል “ሎሽን” መቀባቱ ጥሩ ሊሆን ይችላል።
#እርግዝና #ማሳከክ #ቆዳ
Telegram፦ t.me/LeLijeInc
Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc
Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc
Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc
…
❤2👌1🙏1
5 Aug 2026, 09:59 UTC244 views7 reactionsread 7 August 2026 Photo
“ሽታ” ከምን ይመጣል?
በእርግዝና ጊዜ የማደርገው ነገር ከልጄ “ሽታ” ጋር ሊያያዝ ይችላል?
“ሽታ” (ቆዳ ላይ ከሌላው የቆዳ ቀለም ለየት ብሎ የሚታይ ምልክት) የተለመደና በብዛት የሚያጋጥም ነው፤ አብዛኛውን ጊዜም ምንም ዓይነት ጉዳት አያስከትልም።
ልጅሽ “ሽታ” እንዳይኖርበት አስቀድሞ መከላከያ ዘዴ የለም፤ በእርግዝና ጊዜ ካደረግሽው/ከምታደርጊው ነገር ጋርም አይያያዝም። በአጭሩ ልጅሽ ላይ ሽታ ለመኖሩ ወይም ላለመኖሩ ልታደርጊ የምትችዪው ነገር የለም።
ሽታ ከዘር ውርስ ወይም መነሻው ሳይታወቅ በራሱ የተከሰተ ሊሆን ይችላል።
ሽታ በሁለት ምክንያት የተከሰተ ሊሆን ይችላል፦
👉🏾 ቆዳን የሚያቀልሙ ንጥረ ነገሮች አንዳንድ የቆዳ አካባቢ መብዛት ወይም ማነስ…
❤4🙏2👌1
16 Jul 2026, 10:04 UTC600 views7 reactionsread 7 August 2026 Photo
“መሰልቸት” ለልጆች ጥሩ ሊሆን ይችላል?
ልጆች ቤት ሲውሉ አንዱ ወላጆችን የሚያሳስብ ጉዳይ ቤት መዋል “ቢሰለቻቸውስ” የሚል ነው። በዕድሜ ከፍ ያሉ ለትምህርት ቤት ዕድሜ የደረሱ ልጆች ትምህርት ተዘግቶ ቤት በሚሆኑበት ጊዜ ይህ ጉዳይ ይበልጥ አሳሳቢ ሊሆን ይችላል፤ ራሳቸውም “ሰለቸን” ብለው ሊማረሩ ይችላሉ።
ቤት ለሚውሉ ልጆች የምናስብና የምናቅደው ነገር ቢያስፈልግም “መሰልቸት” በራሱ ለልጆች በመጠኑ ጥሩ ሊሆን እንደሚችል ጥናቶች ይጠቁማሉ።
1👉🏾 ምናባዊ ሐሳብና የፈጠራ ችሎታን ያዳብራል
ልጆች ካሏቸው መጫወቻዎች ጋር ሲቆዩ ያለማንም እገዛ በራሳቸው ራሳቸውን “ማዝናናት” እንዲሁም ተነሣሽነትን መውሰድ ይማራሉ። ይህም የፈጠራ ችሎታን ለማዳበር ከፍተኛ አስ…
❤4🙏2👌1
15 Jul 2026, 10:04 UTC542 views1 reactionsread 7 August 2026 Photo
"የውሸት" እና "የእውነት" ምጥ ልዩነቶች
የውሸት ምጥ ከእውነተኛ ምጥ በሚከተሉት መስፈርቶች ይለያል።
የውሽት ምጥ፦
👉🏾 የምጥ ቁርጠት ወይም መኮማተሩ
የተዘበራረቀ እንዲሁም ተከታታይነት የሌለው ነው
👉🏾 እረፍት ስታደርጊ፣ ስትንቀሳቀሺ ወይም አቀማመጥ/አተኛኘት ስትቀይሪ ሊቆም ይችላል
👉🏾 ደከም ያለ ነው (ጠንከር ብሎ ቢሰማ እንኳ ብዙም ሳይቆይ ይበርዳል)
👉🏾 የሚሰማሽ በሆድሽ ፊት ለፊት ቦታ ላይ ነው
የእውነት ምጥ፦
👉🏾 የምጥ ቁርጠቱ ወይም መኮማተሩ
ተመሳሳይ በሆነ የጊዜ ልዩነት የሚሰማ፣ እንዲሁም ይበልጥ እየተቀራረበ የሚሄድ ነው (እያንዳንዱ የምጥ ቁርጠት ስሜት ከ30 እስከ 90 ሴኮንድ ይቆያል)
👉🏾 ምንም ብታደርጊ አይቆምም
👉🏾 በቀጣይነ…
❤1
14 Jul 2026, 10:04 UTC438 viewsread 7 August 2026 Photo
“የውሸት" ምጥ
“የእውነት” ምጥ ከመጀመሩ በፊት “የውሸት" ምጥ ሕመም ሊሰማሽ ይችላል። የውሸት ምጥ እንደ የመጨረሻው ምጥ ከማኅጸን መኮማተር የተነሣ የሚኖር ቁርጠት ይኖረዋል፤ ሰውነትሽ ራሱን ለአይቀሬው ምጥ የሚያዘጋጅበት አንድ ዘዴ ነው። (የውሸት ምጥ በእንግሊዝኛ ለመጀመሪያ ጊዜ ትንታኔ በሰጠበት ሐኪም ስም “ብራክስተን ሂክስ” ተብሎ ይጠራል።)
የውሸት ምጥ ሆድ ላይ የሚሰማ ጠንካራ ቁርጠት ዓይነት ስሜት ያለው ሲሆን፣ መጣ ሄደት ይላል። የውሸት ምጥ ስሜት በአብዛኛው አቀማመጥ ወይ አተኛኘት ሲለወጥ የሚመጣ ነው፤ እረፍት ስታደርጊ ጋብ ይላል።
የውሸት ምጥ መቼ ይጀምራል?
ስሜቱ ከእርግዝና 6 ሳምንት ጊዜ አንሥቶ ሊጀምር ይችላል፤ ሆኖም አብዛኞቹ ነፍሰ …
13 Jul 2026, 10:00 UTC433 views1 reactionsread 7 August 2026 Photo
ልጆች ጥርስ የሚነቅሉበት የጊዜ ሰሌዳ
ልጆች ጥርስ የሚነቅሉበት የጊዜ ሰሌዳ በምስሉ የቀረበውን ይመስላል። ይሁን እንጂ ልክ ሕጻናት ጥርስ ማብቀል የሚጀምሩበት ጊዜ እንደሚለያየው፣ ተያይዞ የሚነቅሉበት ጊዜም ሊለዋወጥ ይችላል።
(ሊንክ፦ "ልጆች ጥርስ የሚያበቅሉበት የጊዜ ሰሌዳ")
(ሊንክ፦ "ሕጻናት ጥርስ ሲያበቅሉ የሚያሳዩት ሁኔታ")
(ሊንክ፦ "ሕጻናት ጥርስ ሲያበቅሉ የድድ ሕመምን ማስታገስ")
#አራስ #ሕጻን #ልጅ #ጥርስ #ጥርስ_መንቀል
Telegram፦ t.me/LeLijeInc
Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc
Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc
Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc
LinkedIn፦ li…
❤1
12 Jul 2026, 10:04 UTC442 viewsread 7 August 2026 Photo
ልጆች ጥርስ የሚያበቅሉበት የጊዜ ሰሌዳ
ልጆች ጥርስ የሚያበቅሉበት የጊዜ ሰሌዳ በምስሉ የቀረበውን ይመስላል። ይሁን እንጂ ሕጻናት ጥርስ ማብቀል የሚጀምሩበት ጊዜ አንዳንዴ ከ3 ወር ሊጀምር ወይም እስከ አንድ ዓመት (12 ወር) ሊዘገይ ይችላል፤ ተያይዞም ቀጥለው ጥርስ የሚያበቅሉበት ጊዜ እንደዛው ሊቀያየር ይችላል። ይህ የሚወሰነው እንደ ቤተሰብ ውርስ ነው።
(ሊንክ፦ "ሕጻናት ጥርስ ሲያበቅሉ የሚያሳዩት ሁኔታ")
(ሊንክ፦ "ሕጻናት ጥርስ ሲያበቅሉ የድድ ሕመምን ማስታገስ")
#አራስ #ሕጻን #ልጅ #ጥርስ #ጥርስ_ማብቀል
Telegram፦ t.me/LeLijeInc
Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc
Instagram፦ instagram.com/LeL…
11 Jul 2026, 10:02 UTC440 viewsread 7 August 2026 Photo
በእርግዝና ጊዜ ለሕመም ማስታገሻ ፓራሲታሞል ብወስድ ችግር አለው?
በእርግዝና ጊዜም ሆነ ጡት በማጥባት ጊዜ የተለመደ ማስታገሻ የሆነውን ፓራሲታሞል (paracetamol) መውሰድ በአጠቃላይ ችግር የለውም። ከሌሎች የሕመም ማስታገሻዎችም በእርግዝና ጊዜ ተመራጭ የሆነው መድሃኒት ይህ ነው።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት በእርግዝናም ሆነ ጡት በማጥባት ጊዜ አስፈላጊ ከሆነ ፓራሲታሞል መድሃኒት ለሕመም ማስታገሻ መውሰድ ምንም ዓይነት ጉዳት ጽንሱ/ሕጻኑ ላይ አያስከትልም።
ያም ሆኖ፣ ሲያስፈልግ ብቻ እና ሳያዘወትሩ መጠቀም ይመከራል። እንዲሁም ሌላ የምትወስጂው መድሃኒት ካለ ፓራሲታሞል መውሰድ ይቻል አይቻል አስቀድመሽ ሐኪም ማማከር ይኖርብሻል።
#እርግዝና #ጤና #ማስታገ…
10 Jul 2026, 10:02 UTC465 viewsread 7 August 2026 Photo
የእርግዝና ጊዜ ቃር / የምግብ አለመፈጨትን መከላከያ ዘዴዎች
የእርግዝና ጊዜ ቃር ወይም የምግብ አለመፈጨትን ገና ሳይመጣ ወይም ሳይብስ መከላከሉ ተመራጭ ነው። እንዲያም ሆኖ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ቢያስቸግርም፣ የሚከተሉትን ማድረጉ ለመከላከል ያግዛል፦
1👉🏾 ለጨጓራ የማይስማሙ ምግብ እና መጠጦችን ማስወገድ
ለስላሳ መጠጦች፣ ቡና፣ ቅባት ወይም ቅመም የበዛባቸው ምግቦች ቃርን ሊያባብሱ ይችላሉ።
2👉🏾 የአንድ ጊዜ ምግብን አነስ አድርጎ መመገብ
በቀን ሦስቴ “ግጥም አድርጎ” ከመብላት፣ ቁጥሩን ጨምሮ አነስ አነስ ያለ ምግብ መመገብ ይመረጣል። ስትመገቢም ረጋ ብለሽ በደንብ አኝከሽ መብላት ቃር የመከሰት እድሉን ይቀንሳል።
3👉🏾 በቂ ውሃ መጠጣት
በአጠቃላይ በእር…
9 Jul 2026, 10:03 UTC465 views1 reactionsread 7 August 2026 Photo
መንከባለል የጀመሩ ሕጻናትን ደኅንነት መጠበቅ
(ሊንክ፦ "ሕጻናት መንከባለል የሚጀምሩት መቼ ነው?")
ሕጻናት አንዴ መንከባለል ከጀመሩ ወዲህ፦
👉🏾 የተኙበት ቦታ ተንከባለው ሊወድቁበት የሚችል እንዳይሆን፣ እንዲሁም
👉🏾 ተንከባለው የሚይዙት አደጋ የሚያመጣ ነገር እንዳይኖር መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
ሕጻናት መንከባለል ከቻሉ በኋላ አንዳንዶቹ ዳዴ ማለት እስኪጀምሩ ዋነኛ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀሻ መንገድ አድርገው ሲጠቀሙት፣ ሌሎች ደግሞ ጭራሽ ርግፍ አድርገው ትተውት ራሳቸውን ችለው ወደ መቀመጥ እና ዳዴ ወደማለት ሊሄዱ ይችላሉ።
#አራስ #አራስ_ልጅ #ሕጻን #መንከባለል #እድገት #1ኛ_ዓመት
Telegram፦ t.me/LeLijeInc
Facebook፦ facebook…
❤1
8 Jul 2026, 10:04 UTC445 views3 reactionsread 7 August 2026 Photo
የእርግዝና ጊዜ ቃር / የምግብ አለመፈጨት
በእርግዝና ጊዜ ቃር ወይም የምግብ አለመፈጨት የተለመደ ክስተት ነው።
የእርግዝና ጊዜ ቃር / የምግብ አለመፈጨት ምክንያቱ ምንድን ነው?
ቃር የሚመጣው፦
👉🏾 እንደ አብዛኞቹ ሌሎች የእርግዝና ጊዜ ለውጦች በሆርሞን መለዋወጥ፣
(ለምሳሌ “ፕሮጄስትሮን” የሚባለው ሆርሞን መጠን መጨመር ማኅጸን እንዲስፋፋ ቢያግዝም፣ ጨጓራን ከጉሮሮ የሚያገናኘው ቱቦ ጡንቻው እንዲላላ በማድረግ ምግብ እንዲመለስ የማድረግ አዝማሚያ አለው)፣ እንዲሁም
👉🏾 ልጅሽ እያደገ ሲመጣ ከሚፈጥረው ጫና ነው።
በተለይ እርግዝና እየገፋ ሲመጣ ቃር እይተባባሰ ይመጣል። እርግዝናው የመጀመሪያሽ ካልሆነ፣ እንዲሁም በፊቱኑም ቃር ወይም የጨጓራ ሕመም ያስ…
❤1👌1🙏1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @LeLijeInc. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.