8 Apr 2024, 11:08 UTC≈11,000 views28 reactionsread 7 August 2026 ዕለተ ምጽአት
አቤቱ የሚያረጅ የሚጠፋ ይህ የተስፋ ዓለም ለእኛ ለክርስቲያን ወገኖችህ አይደለም የሚመጣውን ተስፋ እናደርጋለን ድጅም እንጸናለን እንጂ። አንተ ሰማይና ምድር ያልፋል ቃሌ ግን አያልፍም ብለሃልና።
በእለተ ምጽዓት አምላክ ሲመጣ ሦስት ጊዜ ታላቅ የሆነ የመለከት መነፋት ይሆናል። ይህ የመለከት ድምጽም ሙታንን ሁሉ የሚያነቃ ነው።
በመጀመሪያው አዋጅ መለከት ሲነፋ በዓለም ዳርቻ ሁሉ የተበተነ የሥጋ ትቢያ ይሰበሰባል። በላይ ያለውና በታች ያለው በባሕር ያለውና በየብስ ያለው በአራዊትም ሆድ ያለው በልዩ ልዩ ሞት ፈጽሞ ያረጀና የጠፋ በምድር ላይ የወደቀ የሥጋ ቅርፍትም ሁሉ ወደ ቀደመ መገናኛው ይሰበሰባል።
በሁለተኛው አዋጅ መለከት ሲነፋ አጥንቶች …
👍28
7 Oct 2023, 03:10 UTC≈18,400 views12 reactionsread 7 August 2026 ይህቺን ዓመት ተወኝ
ከዓመት እስከ ዓመት ፍሬን ሳላፈራ ደረቅ እንደሆንኩኝ
በራድ ወይም ትኩስ ሁለቱንም ሳልሆን እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ ፤
አለሁኝ በቤትህ ለሙን መሬትህን እያጎሳቆልኩኝ ፤
አውቃለሁ አምላኬ ፍሬዬን ለመልቀም እንዳመላለስኩህ ፤
ዛሬም ሳላፈራ እሾህን አብቅየ ደርቄ ጠበኩህ ፤
ያልተደረገልኝ ያላፈሰስክብኝ ያልሰጠኸኝ የለም ፤
ነገር ግን ይህ ሁሉ አላርምህ አለኝ አልለየኝም ከዓለም
የማትሰለቸኝ ሆይ ተነስቼ እስክቆም እባክህ ታገሰኝ ፤
የኔን ክፋት ተወው መልአክህን ሰምተህ ይችን ዓመት ተወኝ ።
አውቃለሁ ታውቃለህ ቀጠሮን ሰጥቼ እንደማላከብር፤
ብዙ ግዜ አቅጄ ብዙ ጊዜ ዝቼ በወሬ እንደምቀር ።
ዘንድሮስ እንዳልኩኝ አምና ይኼን ጊዜ ሰምተኸኝ …
👍12
28 Feb 2022, 18:40 UTC≈25,800 views5 reactionsread 7 August 2026 ✍️ "አሁን እየጾምክ ነው? እስቲ ጾምህን በተግባር አሳየኝ? የቱን ሰራህ? ድሃውን ባየህ ጊዜ ምህረትን አሳየው፤ ጠላትህን ስታየው ታረቀው፤
ስኬታማ የሆነ ወንድምህን ስታየው አትቅናበት በመንገድ የምትሔድ ሴትን ስታይ ዝም በለህ እለፋት፤
በአጠቃላይ አፍህ ብቻ አይጹም ነገር ግን ዓይንህ፣ እግርህ፣ እጅህ ሁሉም አካልህ ይጹም፤ እጅህ ከመስረቅና ከስስት ይጹም፣
እግሮችህ ወደ ኃጢአት ከመጓዝ ይከልከሉ፣ አይኖችህም በሌሎች ሰዎች ውበት ላይ ተተክለው ከመዋል ይጹሙ፤
አሁን ስጋ እየበላህ አይደለም አይደል? በዓይንህም መጥፎ ነገር አትመልከት፤ መስማትንም ጹም፤ የፈውስ ጾም ክፉን አለመስማት የሌሎችንም ስም አለማጥፋት ነው፤
አንደበትም ከክፉና ከአጸያፊ ንግግር ይ…
🥰5
መንፈሳዊ ግጥሞች እና ብሂሎች pinned «በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ፭፻፺፫ በስ ፸፯ ከካህናት ወገን ማንም ቢሆን በ፵ ጾም በአርብና በረቡዕም ጾም ወይን መጠጣት አይገባውም፡፡ወደ መዋት (ውሽባ ቤት) አይግባ፡፡ ዐቢይ ጾም ወራት ሰው ሚስቱ ጋር አይተኛ፡፡ . . . ፭፻፺፮ ክብርት በምትሆን በ፵ ጾም በመጀመሪያው ሱባዔ ፀሐይ እስኪገባ ድረስ ይጹሙ:- መጀመሪያው ሱባዔ ካለፈ በኋላም እስከ ፲፩ ሰዓት ድረስ ይጹሙ፡፡…»
25 Feb 2021, 09:49 UTC≈29,800 views1 reactionsread 7 August 2026 💦ትንቢተ ዮናስ 💦
ምዕራፍ 4
የተናገረው ቃል ስላልተፈጸመ
ዮናስ ተቆጥቶ እያጉረመረመ
እኔን መጀመሪያ ነነዌ ለመላክ
አስበህ ብታዘኝ ይህንኑ ዐውቄ
ወደ ተርሴስ ልሄድ ጠፋሁ ተደብቄ
ምህረትህ የበዛ መሐሪና ታጋሽ
በደል የምትረሳ ከቁጣ ተመላሽ
የቁጣህን ያህል ምሕረትህ የጠና
መሆንህን ጥንቱንም እኔ አውቄአለሁና
እኔን ግን ግደለኝ ልሙት ልቀበር
ሀሰት ተናግሬ የማይሆን ነገር
አልፈልግምና ቆሜ ለመኖር
ከከተማ ወጥቶ በምስራቅ በኩል
ከወደ ዳር ሆኖ ነነዌን ሊያስተውል
ምን እንደሚያገኛት ለማየት ዮናስ
ተሰርቶ ተቀመጠ አንዲት ትንሽ ዳስ
እግዜር በጥበቡ አንድ ቅል አብቅሎ
ቅሉም አደገና ከፍ ከፍ ብሎ
የዮናስ ራሱ እንዲያገኝ ጥላ
ከፀሐዩ ንዳድ ሆለት ከለላ
በዚህ በ…
🥰1
24 Feb 2021, 00:22 UTC≈23,700 views0 reactionsread 7 August 2026 💦ትንቢተ ዮናስ 💦
ምዕራፍ 2
ዮናስን እንዲውጥ ሕይወቱን ሳይጎዳ
አንድ ትልቅ አሳ እግዜር አሰናዳ
ዮናስም ተውጦ በእግዚአብሔር ፍቃድ
ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት ሲያድር በአሳ ሆድ
ተቀይመህ ኖሮ ከላይ ብተቆጣ
ይህን ያህል መዓት በራሴ ላይ መጣ
የባህሩ ሞገድ እኔን አዋከበኝ
ውሀና ጨለማ ሲኦልም ከበበኝ
አያለ በአሳ ሆድ ዮናስ ሲቀመጥ
አምላኩን ለመነው በመለማመጥ
የታዛዥነትም ጠባይ እያሳየ
አዝኖ ተጸጽቶ ከልቡ ጸለየ
ምን ጊዜመ ቢቆጣ ነው እና መሓሪ
ፊቱን መልሶለት ታረቀው ፈጣሪ
አሳውም ዮናስን ውጦ ሳያስቀረው
ከባህር ተፋና መሬት ወረወረው
ምዕራፍ 3
ይህንን የእኔን ቃል ስማና በቶሎ
ሄደ ለነነዌ እንድትነግራ ብሎ
ደገመና እግዚአብሄር ዮናስን አዘዘ
ነነ…
23 Feb 2021, 00:30 UTC≈27,500 viewsread 7 August 2026 💦ትንቢተ ዮናስ💦
በህዝብዋ መካከል ዓመጽ ስለ ፀና
በጣም ተቆጥቼ አዝኛለሁና
ይህን ለነነዌ ንገራት በአዋጅ
አለና ለዮናስ ለአሚታይ ልጅ
እግዚአብሔር አዘዘው እንዲሄድ በቶሎ
ዮናስ እምቢተኛው አሰበ ኮብልሎ
ከአምላክ ተደብቆ አምልጦ ሊጠፋ
ወደ ተርሴ ሊጓዝ ፤ ሄደ ወደ ያፋ
ዋጋ ከፈለና በመርከብ ተሳፍሮ
አያጉረመረመ ባህሩን ተሻግሮ
ዮናስ ተደብቆ ሊሄድ በግስገሳ
ከእግዚአብሄር ተልኮ ማዕበል ተነሳ
ታላቅ ሞገድ ሆኖ ባህሩ ተቆጣ
መርከበኞች ፈሩ ትልቅ ሽብር መጣ
መርከቡ እንዲቀለው እናድርግ እያሉ
አንስተው ብዙ እቃ ወደ መርከብ ጣሉ
ባህሩም ባሰበት በጣም ተናወጠ
መርከከቡ መሰለ የተገለበጠ
ሰው ሁሉ ተነሳ ጸሎት ለማድረስ
ይህ ሁሉ ሲሆን ተኝቷል ዮናስ
ወደ ዮናስ ሄዶ የ…
21 Feb 2021, 17:03 UTC≈19,100 views3 reactionsread 7 August 2026 💦 ጾም 💦
"ጾም መድኃኒት ናት፡፡ አወሳሰድዋን በትክክል ላላወቁ ግን ጥቅም የላትም፡፡
ይህችን መድኃኒት የሚወስድ ሰው በየስንት ሰዓቱ እንደምትወሰድ፣ በምን ያህል መጠን (Dosage) እንደምትዋጥ፣ ለምን ዓይነት በሽታ እንደምትጠቅም፣ በየትኛው ወራትና በየትኛው የአየር ሁናቴ እንደምትወሰድ፣ ከእርሷ ጋር የሚሄዱና የማይሄዱ ምግቦችን እንዲሁም ሌሎች ከእርሷ ጋር የማይስማሙ ነገሮችን ለይቶ ማወቅ አለበት፡፡
እነዚህን ግምት ውስጥ አስገብተን የማንወስዳት ከሆነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡
አንድ በሐኪም የታዘዘልንን የደዌ ሥጋ መድኃኒት በትክክል ከወሰድነው ከሕመማችን እንፈወሳለን፤ የነፍሳችንን ደዌ ለመፈወስ ብለን በምንወስደው መድኃኒት ደግሞ ከዚህ …
👍3
7 Jan 2021, 18:53 UTC≈24,700 views5 reactionsread 7 August 2026 💦የተስፋው ቃል💦
በአንዲት ፍሬ ቅጠል ሕይወትን አጥቼ
እርስቴን ተነጠቅኩ የሞት ሞትን ሞቼ
በግዞት ተነዳሁ በድቅድቅ ጨለማ
ወደ ፍዳ መንደር ወደ ሞት ከተማ
የተስፋውን ቃል በልቤ ቋጥሬ
ለዲያብሎስ ግብር ሆንኩት ጋሻ አጃግሬ
የባርነት ቀንበር ፍላፃው በርትቶ
በበርባኖስ መሃል ብርሃኔ ጠፍቶ
የመከራው ዘመን በእኔ ላይ አድርቶ
ዙሪያዬን ተብትቦኝ ሆነብኝ ድሪቶ
እሾህ አሜኬላው ነግሶብኝ ሠልጥኖ
የጽዴቅ ስራዬም የመርገም ጨርቅ ሆኖ
ነፍሴ ብትቃጠል ስጋዬም ቢጠፋኝ ከመሬት ተቀብሮ
5500 ዘመን ድምጼን ከፍ አድርጌ አሰማሁ እሮሮ
ትንቢቱ ተሠብኮ ግዜው ተፈጽሞ
ያ . . . የተስፋው ቃል ነጋሪት ጎስሞ
የምስራች ዜና ድኅነትን አብስሮ
ሕይወትን ለሰጠኝ ሞትን በ…
👍5
2 Jan 2021, 04:10 UTC≈17,700 views2 reactionsread 7 August 2026 Photo
💦የወንጌል ገበሬ💦
እግዚአብሔር...
ሊያድነን ፈልጎ ምሕረትን ሲያበዛ
ምክንያት ሲፈጥርልን ለነፍሳችን ቤዛ
ገና ከማኅጸን ወዶ የመረጠው
ለክብር የታጨ ባርኮ የቀደሰው
አባታችን...
ተክለአብ ተክለወልድ ተክለመንፈስቅዱስ
ኃጢአትን አክስሮ በይቅርታ የሚክስ
ለኛ የተፈጠረ የወንጌል ገበሬ
ተድበስብሶ እንዳይቀር ብስሉ ከጥሬ
በሃይማኖት መንሹ አብጠርጥሮ የለየ
እምነቱ የጸና በተጋድሎ የቆየ
ዛሬም...
ዛሬም ቃልኪዳኑ ተርፎ ዓለምን አጥግቧል
ተክለሃይማኖት ብለን የጎደለው ይሞላል
በጻድቁ አባት ጥላ ሁሉም አልፏል
ቃሉ ለማይሻር አምላክ ምን ይሳናል
💥 💥 💥 💥 💥 💥 💥
✍📚 ስናነብ ካገኘነው፦📚
💥 💥 💥 💥 💥 💥 💥
●🔸 @Behila_Abew 🔸●
●🔸
👍2
10 Dec 2020, 23:50 UTC≈16,100 viewsread 7 August 2026 Photo
የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን፡፡
እርሱ ምስጉን ነው ለዘላለምም ምስጉን ነው፡፡
የተቀደሰ የጌትነቱም ስም ይክበር ይመስገን፡፡
አርሱ ምስጉን ነው በዓለምም ሁሉ ልዑል ነው፡፡
ቅዱስ በሆነ በጌትነትህ መቅደስ አንተ የተመሰገንህ ነህ፡፡
አንተ ምስጉን ነህ ለዘላለምም የከበርህ ነህ፡፡
በኪሩቤል ላይ ሆነህ ጥልቆችን የምታይ አንተ የተመሰገንህ ነህ፡፡
አንተ ምስጉን ነህ ለዘላለምም ልዑል ነህ፡፡
በጌትነትህ ዙፋን ላይ አንተ የተመሰገንህ ነህ፡፡
አንተ ምስጉን ነህ ለዘላለምም ቡሩክ ነህ፡፡
ከሰማዮች በላይ ባለው አንተ የተመሰገንህ ነህ ።
አንተ ምስጉን ነህ፡፡
ለዘላለምም ክቡር ነህ፡፡
💥 💥 💥 💥 💥 💥 💥
🤲(የአናንያ የአዛርያ የ…
14 Nov 2020, 23:14 UTC≈80,400 views7 reactionsread 7 August 2026 አብሬሽ_ልመለስ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን!!!
ከክብር ማረፊያው ከገሊላው ቤትሽ
ሰማሁ መፍለስሽን ወደ ግብጽ ወደ ኩሽ
ፀሐይ ሲያከትራት ያቺን የበረሃ ዖፍ
ጼዋዌን ስትናፍቅ ላንዲት ቅጽበት ሳታርፍ
ሰማሁኝ ስደቷን መጠጊያ ሳታገኝ በልቤ ላይ ስታልፍ
....ፈላሲተ ቁስቋም ወዴት ነው ሀገርዋ
ኀበ ሖረት ላቲ በብካይ እትልዋ
ናዛዚት እም ኃዘን ሁሉ ያላት ለማኝ
የምድረ በዳ ዖፍ ጎጆዋን እስካገኝ
መኃልየ ብካይ ኃዘንዋ እየሆነኝ
..... እፈልጋታለሁ
እፈልጋታለሁ....እፈልጋታለሁ
እንዲያም ያጣኋት ለት..... ፈልጊኝ እላለሁ
አልያማ
ያለ ምዕራፈ ክብር....ያለ ነፍሴ አስኬማ
ያለ ብሔረ ሰላም ....ያለ ጽድቅ ከተማ
ያ…
👍7
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Behila_Abew. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.