7 Aug 2026, 19:00 UTC122 viewsread 8 August 2026 ⏳የልብ ዕድሳት፡ ከመቅደስ እስከ ማኅበራዊ ሚዲያ!!!⏳
✍️ አዘጋጅና ጸሐፊ፦ ዲያቆን ጐሥዓ ቶላ!!!
➜ነሐሴ 01፦ አርብ
➜ርዕስ፦ የጸሎት ይቅርታ፣ የበደለኝንና በጣም የጎዳኝን ሰው ስም ጠርቼ ዛሬ ማታ መጸለይ!!!
🍀በመርዛማና በቆሸሸ ጉድፍ በተሞላ መንበር ላይ ታቦተ ሕጉ ሊቀመጥ እንደማይችል ሁሉ፤ በትላንትናው ቀን ቅሬታ፣ በወንድም ጥላቻ፣ በመኮራረፍ፣ በምቀኝነት፣ በትዕቢትና በበቀል ቂም በተሞላ የሰው ልብ ታቦት ላይም የመንፈስ ቅዱስ ቅድስናና የእመቤታችን የጾመ ፍልሰታ ሰማያዊ በረከት ሊያድር አይችልም። ጾም ማለት ሆድን ከምግብ መከልከል ብቻ ሳይሆን፣ ልብን ከክፉ ሐሳብ፣ አንደበትን ከሐሜትና ነፍስን ከጥላቻ እስራት ነፃ ማውጣት ነው። በዛሬው ዕለት ወደ…
Signed 🕊🕊 ¹² Gosa {Dave} ¹² ¹²፲፪ ፳፩²¹ 🕊🕊
7 Aug 2026, 19:00 UTC136 views2 reactionsread 8 August 2026 🍀ትዕቢትና ምቀኝነት የይቅርታ ትልቁ ጠላቶች ናቸው። ትዕቢተኛ ሰው "እኔ ቅድሚያ ይቅርታ አልጠይቅም" በማለት ልቡን ያደንድናል፤ ምቀኛ ሰው ደግሞ የወንድሙን መባረክ ማየት አይፈልግም። ነገር ግን ክርስቶስ አምላካችን ራሱን ዝቅ አድርጎ የደቀ መዛሙርቱን እግር እንዳጠበ፣ እኛም በትሕትና ራሳችንን ዝቅ አድርገን ይቅር ማለትን ልንማር ይገባል። መጽሐፍ ቅዱስ የትሕትናን ሰማያዊ ዋጋ እንዲህ በማለት ቃል በቃል ያበስረናል፦ "እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል" (1 ጴጥሮስ 5፥5)።
🍀በወጣቶችና በፍቅር ጓደኞች መካከል በሚፈጠር አለመግባባት፣ መጠራጠርና የተስፋ ቃል መታጠፍ ምክንያት የሚፈጠረው የልብ ቁስል ወጣቶችን ወደ ተስፋ መቁረጥ ይ…
❤2
Signed 🕊🕊 ¹² Gosa {Dave} ¹² ¹²፲፪ ፳፩²¹ 🕊🕊
7 Aug 2026, 18:34 UTC122 viewsread 8 August 2026 ⏳የልብ ዕድሳት፡ ከመቅደስ እስከ ማኅበራዊ ሚዲያ!!!⏳
✍️አዘጋጅና ጸሐፊ፦ዲያቆን ጐሥዓ ቶላ!!!
➜ነሐሴ 01፦አርብ
➥በኋላ 4፡ዐዐ ሰዓት ላይ ይቀጥላል..............
Signed 🕊🕊 ¹² Gosa {Dave} ¹² ¹²፲፪ ፳፩²¹ 🕊🕊
7 Aug 2026, 17:14 UTC227 views11 reactionsread 8 August 2026 📜ነሐሴ አንድ ቀን የመጀመሪያ ቀን ሱባኤ!!!📜
ወዳጄ! ዛሬ የመንፈሳዊው ተጋድሎህና የነፍስህ መታደስ የመጀመሪያው ቀን ነው። መርከበኛ ወደ ጥልቅ ባሕር ለመጓዝ የመሬቱን ትስስር በጥሶ እንደሚነሣ፣ አንተም ዛሬ የዓለምን ወከባና የሕይወትን ውጥረት ከኋላህ ጥለህ ወደ እግዚአብሔር ምሕረት ባሕር ለመግባት የመጀመሪያውን እርምጃ ተራምደሃል። ዛሬ አእምሮህ ወደ ቀደሙት የዓለም ሐሳቦች፣ ሥራዎችና ሥጋቶች ሊበተን ይችላል። ይሁን እንጂ " ልጄ ሆይ! ልብህን ስጠኝ" የሚለውን አምላካዊ ጥሪ በማሰብ፣ የቆምክበት ቦታ የጸሎትና የመንፈስ ቅዱስ ቅጽር መሆኑን ለነፍስህ አስረዳት።
ወዳጄ! በመጀመሪያው ቀን ትልቁ ውጊያ የአንደበት ውጊያ ነው። ከሰዎች ጋር ከመነጋገር ይልቅ ከፈ…
❤10🥰1
Signed 🕊🕊 ¹² Gosa {Dave} ¹² ¹²፲፪ ፳፩²¹ 🕊🕊
7 Aug 2026, 13:10 UTC225 views9 reactionsread 8 August 2026 📜ዮሐንስ ግን እንደምን ቢታደል ነው! ከድንግል ጋር የኖረው!!!📜
✍️ ጸሐፊ፦ ዲያቆን ጐሥዓ ቶላ!!!
ወዳጆቼ! ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ከእመቤታችን ጋር የነበረው ኑሮ እንደምን ያለ ድንቅና ታላቅ ምስጢር ነው! "እነኋት እናትህ፤ ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት" (ዮሐ፦19፥27) ተብሎ በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈው፣ ያ የተወደደ ደቀ መዝሙር ከጌታ እናት ጋር ያንን ሁሉ ዓመታት በአንድ ቤት አብሮ ለመኖር እንደምን ያለ ታላቅ ጸጋና ዕድል ተሰጠው! እኔ ኃጢአተኛውና ደካማው ግን የአንቺን የቀሚስሽን ጫፍ ቀርቶ ጥላሽን እንኳን ለመነካት የማልደፍር፣ ቅድስናሽን ፈርቼ በሩቅ የምቆም ምስኪን ነኝ፤ ዮሐንስ ግን እናቴ እያለ እንደ አምላኩ እናት …
❤9
Signed 🕊🕊 ¹² Gosa {Dave} ¹² ¹²፲፪ ፳፩²¹ 🕊🕊
7 Aug 2026, 13:10 UTC255 views10 reactionsread 8 August 2026 ማርያም ሆይ! ዮሐንስ በየቀኑ ዐይኖችሽን ሲመለከት፣ አምላክን በጥቅሻ ያዘዘውን፣ በቤተልሔም በጨርቅ የጠቀለለውን፣ በወይን ጠጅ እጥረት ጊዜ "ያላችሁን አድርጉ" ብሎ ተአምራት እንዲያደርግ ያቀረበውን ያንን ቅዱስ ዐይን ያይ ነበር። "ዓይኖቻችን ያዩትን፣ ጆሮቻችን የሰሙትን... እንሰብካለን" (1ኛ.ዮሐ፦1፥1) ብሎ ሲናገር፣ የአንቺንም እናታዊ ምስክርነት አብሮ የያዘ ምስክር ነበር። ዮሐንስ የጌታን እናት ዐይኖች ማየት የእግዚአብሔርን ክብር እንደ ማየት ይቆጥረው ነበር።
ድንግል ሆይ! ዮሐንስ "ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች" (ሉቃ፦1፥46) ብለሽ ያመሰገንሽበትን ያንን ጣፋጭና የተቀደሰ ድምፅሽን ዘወትር በቤቱ ውስጥ ሲሰማ እንደምን ይፈነድቅ ነበር! የአንቺ ውዳሴ በቤ…
❤8🔥2
Signed 🕊🕊 ¹² Gosa {Dave} ¹² ¹²፲፪ ፳፩²¹ 🕊🕊
7 Aug 2026, 12:59 UTC193 viewsread 8 August 2026 📜ዮሐንስ ግን እንደምን ቢታደል ነው! ከድንግል ጋር የኖረው!!!📜
✍️ጸሐፊ፦ ዲያቆን ጐሥዓ ቶላ!!!
➥ከደቂቃዎች በኋላ ይለቀቃል።
እስከዚያ ቻናሉን ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ።
👇👇👇👇👇
http://t.me/Be_Gosa1224
http://t.me/Be_Gosa1224
http://t.me/Be_Gosa1224
Signed 🕊🕊 ¹² Gosa {Dave} ¹² ¹²፲፪ ፳፩²¹ 🕊🕊
7 Aug 2026, 11:58 UTC230 views6 reactionsread 8 August 2026 Photo
📌ፍቅር፣ ስሜት እና ትውልድ፣ ከኤደን ገነት እስከ ነገው ዘመን!
➥እነሆ ደረሰ ነገ ይጀምራል።
🌩የዛሬው ዘመን ወጣት ፍቅርን በስክሪን ጀርባ፣ በፊልሞችና በቲክቶክ የውሸት ዓለም እየፈለገው ስንት ልቦች ተሰበሩ?፣ ስንቶቹስ ተስፋ ቆረጡ፣ ስንቶቹስ በራሳቸው ክፉ ነገርን አደረጉ?፣ ስንቶቹስ ከሰው ተገለሉ?፣ ስንቶቻችንስ “ሞክሬው አልሆነም” በሚል ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ነን? ከአንድ በላይ፣ አንዳንዴም ከአምስት በላይ ግንኙነቶችን ፈጥረን ሳይሳካልን ሲቀር እውነተኛ ፍቅር የቱ እንደሆነ ግራ ለገባን በሙሉ... እነሆ ታላቅ የምሥራች! ነገ ማታ ይጀምራልና ተቀላቀሉ። የተቀላቀላችሁ ደግሞ የቻናሉን ሊንክ ለጓደኞቻችሁ በመላክ አስተምሯቸው።
➜"የዲያቆን ጐሥዓ ቶ…
❤6
Signed 🕊🕊 ¹² Gosa {Dave} ¹² ¹²፲፪ ፳፩²¹ 🕊🕊
7 Aug 2026, 09:03 UTC75 viewsread 8 August 2026 Forwarded from @mediazdebreamin
https://youtu.be/wx3QQQnNdXE?si=y_DEx80ng60LPNBx
Signed 🗝ya
7 Aug 2026, 06:58 UTC270 views14 reactionsread 8 August 2026 🛎ነሐሴ 1 ቀን! ዛሬ ምን ይቀደሳል?🛎
የነሐሴ ፩(1) ግጻዌ
➥መልእክታት
1. ፩(1)ኛ ጢሞ ፭(5) ፥ ፩(1) - ፲፩(11)
2. ፩(1)ኛ ዮሐ ፭(5) ፥ ፩(1) - ፮(6)
3. ግብ ሐዋ ፭(5) ፥ ፳፮(26) - ፴፬(34)
➥ምስባክ
መዝ ፻፲፰(118) ፥ ፵፮(46) - ፵፯(47)
"ወእነግር ስምዕከ በቅድመ ነገሥት ወኢይትኀፈር። ወአነብብ ትእዛዘከ ዘአፍቀርኩ ጥቀ። ወአንሥእ ዕደውየ ኀበ ትእዛዘከ ዘአፍቀርኩ።"
"በነገሥታት ፊት ምስክርህን እናገራለሁ፥ አላፍርምም፤ እጅግም በወደድኋቸው በትእዛዛትህ ደስ ይለኛል። እጆቼንም ወደ ወደድኋቸው ወደ ትእዛዛትህ አነሣለሁ፤ ሥርዓትህንም አሰላስላለሁ።"
➥ወንጌል
ዮሐንስ ፲፱(19) ፥ ፴፰(38) - ፍጻሜ
"³⁸ ከዚህም …
❤10👍2🥰2
Signed 🕊🕊 ¹² Gosa {Dave} ¹² ¹²፲፪ ፳፩²¹ 🕊🕊
7 Aug 2026, 05:24 UTC278 viewsread 8 August 2026 በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
📜ጾመ ፍልሰታ (ጾመ ማርያም)/ የነሐሴ ጾም!!!📜
➥#INSTANT_VIEW የሚለውን ተጭነው ያንብቡ።
Signed 🕊🕊 ¹² Gosa {Dave} ¹² ¹²፲፪ ፳፩²¹ 🕊🕊
7 Aug 2026, 05:22 UTC265 views2 reactionsread 8 August 2026 Photo
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
📜ጾመ ፍልሰታ (ጾመ ማርያም)/ የነሐሴ ጾም!!!📜
✍️አዘጋጅና ጸሐፊ፦ ዲያቆን ጐሥዓ ቶላ!!!
1፦ሱባኤ ማለት ምን ማለት ነው?
2፦ሱባኤ መች፣ በማን እና እንዴት ተጀመረ?
3፦ሱባኤ የሚገባ ሰው ምን ማወቅ አለበት?
4፦በሱባኤ ወቅት ማድረግ የሌሉብን ነገሮች ምንድናቸው?
5፦ሱባኤ የሚገባ ሰው ምን ይዞ መግባት አለበት?
6፦ሱባኤ የሚገባ ሰው ምን ይዞ መውጣት አለበት?
7፦የሱባኤ ዓይነቶች ምንድናቸው?
8፦የሱባኤ ጥቅሞችና መንፈሳዊ ፍሬዎች ምንድናቸው?
9፦የጾመ ፍልሰታ ሱባኤ ታሪካዊና መንፈሳዊ አመጣጥ ምንድነው?
10፦ከሱባኤ በኋላ መንፈሳዊ ሕይወታችንን እንዴት መጠበቅ አለብን?
➜ የዲ…
❤2
Signed 🕊🕊 ¹² Gosa {Dave} ¹² ¹²፲፪ ፳፩²¹ 🕊🕊
Showing the 12 most recent of 32 posts we hold for @Be_Gosa1224. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.