2 Oct 2023, 12:49 UTC≈5,410 views21 reactionsread 12 August 2026 Photo
በኦሮሚያ እና ሶማሊ የክልል ፀጥታ ኃይሎች መካከል በተደረገ ተኩስ ልውውጥ ስድስት ሰዎች ተገድለዋል ተባለ
መስከረም 21፤ 2015 ዓ.ም.
(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) በኦሮሚያ እና ሶማሊ ክልሎች የፀጥታ አካላት መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ቢያንስ ስድስት ንፁሀን ዜጎች ተገድለዋል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ።
መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በባቢሌ አቅራቢያ በኦሮሚያ እና በሶማሊ ክልል የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተደረገው የተኩስ ልውውጥ የሞቱት ሰዎች በአካባቢው የሚገኝ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የነበሩ ተፈናቃዮች መሆናቸውንም ኮሚሽኑ ገልጿል።
ኢሰመኮ በክስተቱ ላይ ዛሬ ባወጣው መግለጫ “በአሁኑ …
❤13👍7🔥1
Signed ILYAS KIFLE
29 Sept 2023, 18:19 UTC≈3,770 views8 reactionsread 12 August 2026 Photo
የመስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕለታዊ ዋና ዋና ዜናዎች
(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ)
✍ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በተከሰተ ድርቅ 452 ሺህ ዜጎች ሲጎዱ 202 ሺህ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው መንግስት አስታወቀ።
በዞኑ በሚገኙ ጃናሞራ፣ ጠለምት፣ የበየዳ ወረዳዎችን ጨምሮ፣ ምሥራቅና ምዕራብ ጠለምት እና የተወሰኑ የደባርቅ አካባቢዎች ላይ ዝናብ በወቅቱ ባለመዝነቡ ምክንያት፣ ድርቁ በሰዎች ላይ እያደረሰ ካለው ጉዳት ባለፈ ከ19 ሺህ በላይ ሄክታር ሰብል ላይ ጉዳት እንዳደረሰ ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።
✍ የዓለም ጤና ድርጅት እየተባባሰ የመጣውን የኮሌራ ስርጭት ለመከላከል 16 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ መልቀቁን አስታወ…
👍6❤2
Signed Bky
25 Sept 2023, 11:43 UTC≈3,130 views3 reactionsread 12 August 2026 Photo
#ማሳሰቢያ
በአዲስ አበባ ከተማ ከዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ የሞተር ሳይክል እንዲሁም የባጃጅ እንቅስቃሴዎች በሙሉ ይቆማሉ
መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም.
(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከዛሬ ማታ 12 ሰዓት ጀምሮ የሞተር ብስክሌተኞች፣ ባለ አራት እና ባለሶስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪዎች በሙሉ ከእንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
ቢሮው እንዳስታወቀው ከዛሬ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ማክሰኞ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ድረስ ማለትም ለ15 ቀናት ማሽከርከር አይችሉም።
ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን አያካትትም ያለው የአዲስ አበባ ትራንስፖ…
👎2👍1
Signed ILYAS KIFLE
21 Sept 2023, 13:50 UTC≈3,100 views11 reactionsread 12 August 2026 Photo
የመንግሥት ኃይሎች በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚፈጽሙት የጅምላ ግድያና የድሮን ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም ሲሉ አምስት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጠየቁ
መስከረም 10፤ 2016 ዓ.ም.
(አዲስ ዘይቤ፤አዲስ አበባ) አምስት የተፎካካሪ ፓርቲዎች ዛሬ ባወጡት ወቅታዊ መግለጫ በዘመነ ኢሕአዴግ ለተፈጠሩ ስህተቶች ሁሉ ይቅርታ ጠይቆ መንበረ ስልጣኑን የተቆጣጠረው የብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን ሕዝብ እምነትና ተስፋ አምክኗል ሲሉ አስታወቁ።
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ፣ እናት ፓርቲ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በጋራ መግለጫቸው የመንግሥት ኃይሎች በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚፈጽሙት የጅምላ ግድያና የድሮን ጥቃ…
👍6❤3👎2
Signed Bky
21 Sept 2023, 09:28 UTC≈2,350 views6 reactionsread 12 August 2026 Photo
ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም. ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር እንደሚቀጥል ተገለፀ
መስከረም 10፤ 2016 ዓ.ም.
(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ የአስራር ለውጦች እያደረገ ቢሆንም በተያዘው ዓመት የተማሪዎች ቅበላ በምደባ እንደሚሆን አስታወቀ።
የዩኒቨርስቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ የተቋሙን ሽግግር በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሲሰጡ፤ በ2016 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ቅበላን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራት ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር መሰረት እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲው እስከ አንድ ዓመት ተኩል …
👍3😁3
Signed ILYAS KIFLE
19 Sept 2023, 17:53 UTC≈2,110 views0 reactionsread 12 August 2026 Photo
📻 የጦር እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች እንዳይመረመሩ የኢትዮጵያ መንግስት ጫና እያደረገ መሆኑን ተመድ አስታወቀ
✍ የኢትዮጵያ የሽግግር ጊዜ ፍትህ ሂደት በመንግስት ጫና የተጠለፈ እና ተጎጂዎች “ተስፋ የቆረጡበት” መሆኑን የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ያስታወቀ ሲሆን የኮሚሽኑ የስልጣን ዘመን እንዲራዘም ምክረ ሀሳብ ቀርቧል
✍ ከ500 የሚበልጡ የዓይን እማኞች ቃለ መጠይቅ የተደረጉበት ሪፖርት በትላንትናው እለት የቀረበ ሲሆን “የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ ህገ መንግስትም ጭምር ግዴታው የሆነውን የዜጎቹን ደህንነትና ሰብዓዊ መብት መጠበቅ እንደተሳነው” ጠቁሟል።
✍ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ሁኔታዎች ሳቢያ ታኅሣሥ 8 ቀን 2013 ዓ.ም. የተ…
Signed Bky
19 Sept 2023, 14:28 UTC≈1,740 viewsread 12 August 2026 Photo
📢 የመንግስታቱ ድርጅት አባላት ያፀደቁት 'ዘላቂ የልማት ግቦች' ችላ መባላቸው ዋጋ እያስከፈለ ነው ተባለ
✍ ዘላቂ የልማት ግቦች የሚባሉት 17 እቅዶች በቀዳሚነት ድህነትን እና ረሃብን ማጥፋት ሲሆን ጠንካራ የጤና እና ደህንነት አገልግሎት፣ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት፣ የፆታ እኩልነት፣ የንፁህ ውሃና ንፅህና ጥበቃ፣ በዋጋ ተመጣጣኝና አየር የማይበክል ታዳሽ ኃይል አጠቃቀም፣ በቂ የስራ እድል እና የኢኮኖሚ እድገት፣ ኢንዱስትሪ፤ ፈጠራና መሰረተ ልማት፣ ሁለገብ እኩልነት፣ የማያቋርጥ የከተማ እና ማህበረሰብ እድገት፣ ምርቶችን ማምረትና መጠቀም ላይ ኃላፊነት መፍጠር፣ የአየር ንብረት ጥበቃ፣ በውሃ ውስጥ ያሉ ህይወቶችን መጠበቅ፣ የመሬት ሀብትን መጠበቅ፣ ሰላም፤…
Signed Bky
18 Sept 2023, 11:56 UTC≈1,890 views0 reactionsread 12 August 2026 Photo
የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ 11ኛው የኢትዮጵያ ቅርስ ሆኖ ተመዘገበ ፡፡
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ እየተካሄደ ባለው 45ኛው የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ የአለም ቅርስ ጉባኤ ላይ የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በዛሬው ዕለት በአለም ቅርስነት ተመዝግቧል።
የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በኢትዮጵያ ሁለተኛው ታላቅ የተፈጥሮ ቅርስ እንዲሁም ኢትዮጵያ በዓለም ያስመዘገበችው 11ኛው ቅርስ በመሆን መመዝገብ ችሏል።
የባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ ኢትዮጵያ በ45ኛው የአለም የቅርስ ጉባኤ ላይ ከጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር በመቀጠል ያስመዘገበችው ሁለተኛው ዓለም ቅርስ ሆኗል፡፡
ፓርኩን በዩኔስኮ የማስመዝገብ አጠቃ…
Signed ILYAS KIFLE
17 Sept 2023, 17:42 UTC≈1,860 views3 reactionsread 12 August 2026 Photo
🌟 የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ
📢 በሪያድ በመካሄድ ላይ ባለው 45ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል።
ኢትዮጵያ እስካሁን ካስመዘገበቻቸው ዘጠኝ ቅርሶች በተጨማሪ ይሄንኛው አስረኛ ሲሆን ለአፍሪካ ደግሞ 100ኛ ሆኖ ተመዝግቧል።
👍2🔥1
Signed Bky
16 Sept 2023, 13:55 UTC≈1,910 views3 reactionsread 12 August 2026 Photo
የ2016 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ እቅድ ከትምህርት ሚኒስቴር
👍3
Signed ILYAS KIFLE
11 Sept 2023, 19:25 UTC≈2,360 views2 reactionsread 12 August 2026 Photo
💐እንኳን ለ 2016 አዲስ ዓመት
በሰላም አደረሳችሁ! 🌻🌼
🌼መልካም በዓል ይሁንላችሁ🌻
❤1👍1
Signed Bky
11 Sept 2023, 14:25 UTC≈2,170 views3 reactionsread 12 August 2026 Photo
#updates #ተጨማሪ
ጷግሜን 6፤ 2015 ዓ.ም.
(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) ከቀናት በፊት በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ከተደረገው "ኪዳን ለስር ነቀል ለውጥ" ጥምረት ሰላማዊ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ታስረው የነበሩት የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮች
1)ዶ/ር ደጀን መዝገበ
2)ሓያሉ ጎደፋይ
3)ኪዳነ ኣመነ
4)ክብሮም ዘቢብ
5)ዓብለሎም መለስ
6)ዓንዶም ገብረስላሴ መፈታታቸው ታውቋል።
👍2❤1
Signed ILYAS KIFLE
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @AddisZeybe. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.